ቅዱስ ፓትርያርኩ የመቄዶንያ አረጋውያንና ሕሙማን ጎበኙ

ቅዱስ ፓትርያርኩ የመቄዶንያ አረጋውያንና ሕሙማን ጎበኙ በቤተ ክርስቲያኗ ስም መቶ ሺህ ብር ለተረጂዎች ድጋፍ አድርገዋል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ...

ዜና ቤተክርስቲያን መስከረም 2007 ዓ.ም

ዜና ቤተክርስቲያን መስከረም 2007 ዓ.ም

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዲስ ሕንጻ ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ አኖረ የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደ...

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ የኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት በስሙ የመሠረታት ቤተክር...

ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም

ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም የዜና ቤተክርስቲያን  ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ

 • ቅዱስ ፓትርያርኩ የመቄዶንያ አረጋውያንና ሕሙማን ጎበኙ

  Tuesday, 30 September 2014 12:04
 • ዜና ቤተክርስቲያን መስከረም 2007 ዓ.ም

  Monday, 29 September 2014 13:10
 • ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

  Tuesday, 02 September 2014 13:13
 • የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ

  Tuesday, 02 September 2014 13:11
 • ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም

  Wednesday, 20 August 2014 06:47

PostHeaderIcon አዳዲስ አርዕስቶች

PostHeaderIcon በብዛት የታዩ ገጾች

ቅዱስ ፓትርያርኩ የመቄዶንያ አረጋውያንና ሕሙማን ጎበኙ

በቤተ ክርስቲያኗ ስም መቶ ሺህ ብር ለተረጂዎች ድጋፍ አድርገዋል

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መስከረም 17 ቀን 2007 ዓ.ም ከጥዋቱ በሦስት ሰዓት አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ወገኖቻችን ከሚረዱበት በመቄዶንያ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ዘንድ በመገኘት ጉብኝትና በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም ለመረጃ ማእከሉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የመቄዶንያ መርጃ ማዕከል ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ፀጋዬ በርሄ እንደገለፁት መርጃ ማዕከሉ በአንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ /አቶ ቢንያም/ አማካኝነት የተጀመረ መሆኑን ገልጸው አሁን ግን ከስድስት መቶ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን አገልግሎት በማግኘት ላይ እንደሚገኙ በስፋት ገልጸዋል፡፡ የመርጃ መዕከሉ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆነው ወጣት ቢንያም በበኩሉም ይህን መርጃ ማዕከል በጥቂት ሰዎች ጀምሮ አሁን በሦስት ማዕከላት ከስድስት መቶ ተገልጋዮች በላይ መኖራቸውን ገልጸው እነዚህ ወገኖች የሚረዱት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ስለሆነ ሁሉም በጎ አድራጊ ወገኖችን ምስጋና ካቀረቡ በኋላ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግን ለምታደርግላቸው ሁለገብ ድጋፍ ምስጋናቸውን ከፍ ያለ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቦታው ለተገኙ አረጋውያንና ለመረጃ ማዕከሉ ሠራተኞች ሰፊ አባታዊ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል፡፡ በቃለ ምዕዳናቸውም "ተርቤ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፣ ታርዤ አልብሳችኁኛልና" የሚል ቃለ ወንጌል መሠረት አድርገው ለአገልጋዮችና ለተገልጋዮች የማጽናኛና የበረከት ትምህርት ካስተማሩ በኋላ በመርጃ ማዕከሉ ለሚገኙ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ የሚሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም መቶ ሺህ ብር በመስጠት ማዕከሉን አበረታቷል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች በወቅቱ የተደረገውን ጉብኝት በተመለከተ የሚያሳይ ቪድዮ እንድትመለከቱ አቅርበናል፡፡

 

መስቀል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

መ/ር ፀገዬ ኃይሌ

መስቀል በብዙዎች ሰዎች ኀሊና በብዙ ዓይነትና ቅርጽ የተሰራ ተደርጎ የሚታዩ ወይንም የሚተረጎም ቢሆንም እኛ ግን ከዘመነ ብሉይ መጀመሪያ እስከ ዘመነ ሐዲስ እስከ አለንበት ዘመን ስለአለው ስለክርስቶስ ነገረ መስቀል እንናገራለን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አስቀድሞ ከዘመነ አበ ብዙኃን ከአዳም ጊዜ ጀምሮ ብዙ ነቢያት በተለያየ ኅብረ አምሳል ትንቢት የተናገሩለት በዘመነ ሐዲስም እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢአት የወደቀውን የሰውን ልጅ ከራሱ ጋር ያስታረቀበት እስከ አሁንም ድረስ አስቀድሞ የክፋት ምንጭ የሆነው ዲያብሎስ ሰውን ከፈጣሪው እንዲለይና መከራ ውስጥ እንዲወድቅ እንዳደረገው አሁንም ደግሞ ለተመሳሳይ ፈተና እንዳያጋልጠው ሥልጣነ አምላክ በተሰጣቸው ሐዋርያትና ደቀመዛሙርቶቻቸው አማካኝነት በተናገረው ቃሉና በተሰቀለበት ዕፀ መስቀል እራስ እራሱን እየቀጠቀጡበት ለሚያምኑበት ብልሃት ለማያምንኑበት ሞኝነት ሆኖ ሲጠብቀን ይኖራል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 

ዜና ቤተክርስቲያን መስከረም 2007 ዓ.ም

zenab2007

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ ዓውደ ዓመትን (አዲስ ዓመትን) ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ በረከት፤

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤

 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤

 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤

 • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤

 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

የመልካም ስጦታ ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ከ2006 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማርቆስ ወደ 2007 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

 

                                               

aba mathias

  

 

‹‹ ወዓመቲከኒ ዘኢየኃልቅ፤ ዘመንህም አያልቅም (መዝ 101÷27)

ሁሉን ፈጥሮ የሚመግብ እግዚአብሔር አምላክ በባህርዩ ፍጹም ነውና በእርሱ ዘንድ ኅልፈት፤ መለወጥ፤ ማርጀትና የዘመን ፍጻሜ የለም፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 

ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን

የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዲስ ሕንጻ ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ አኖረ

 • የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ከመንግሥት ጋር በመሆን ሕንፃዎችን የማስመለስ ሥራ የሠሩትን አንጋፋ ሰዎች በዕለቱ ሸልሟል

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ካሏት በርካታ ድርጅቶች መካከል ዋነኛውና አንጋፋዉ የልማት ድርጅት የቤቶች እና ሕንፃዎት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመነ ፕትርክና ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቷ የአዲስ አበባ ከተማን ያስዋቡና ለወደፊት የሀገራችን ዕድገት ምሳሌ በመሆን ዱካ የጣሉ ሕንፃዎችን እና ፎቆችን ገንብታለች፡፡

kiray betoch new1ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብትገነባም ከዓመታት በኋላ የደርግ መንግሥት ሀገራችንን ማስተዳደር ሲጀምር ያልለፋበትንና ያልሠራውን መቀማት ልማዱ የሆነው የደርግ መንግሥት የቤተ ክርስቲያንቷን አንጋፋና ምርጥ ሕንፃዎቿን በጉልበት በመቀማት ባዶ እጅ እንድትቀር አድርጓት ነበር፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ

የኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት በስሙ የመሠረታት ቤተክርስቲያን ናት ከተቋቋመችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ውስብስብ ችግር ቢያጋጥማትም ተግባሯ ሳይገታ ዓላማዋም ሳይዛነፍ ከዚህ ደረጃ ላይ ደርሳለች ወልድ ዋሕድ የሚለውን ቃል መሠረት አድርጋ አንድ እግዚአብሔር በሦስት ስም በሦስት ግብር በሦስት አካል አንድ አምላክ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከበረ ብላ ታስተምራለች፡፡ ሆኖም በሃይማኖቷና በነጻነትዋ ጸንታ የምትኖር በመሆንዋ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ የለም፡፡

የኢ.ኦ.ተ. ቤተክርስቲያን እውነተኛና ጥንታዊ ከሚያሰኛት መካከል ሦስቱን ዐበይት ጉባኤያት የኒቂያን፣ የቁስጥንጥንያን እና የኤፌሶንን ጉባኤያት ተቀብላ አክብራ በመያዝዋ ነው፡፡ አራተኛው የኬልቄዶን ጉባኤ ግን አንድ ክርስቶስን ለሁለት የሚከፍል በመሆኑ አልተቀበለችውም፡፡ ይህ መለያየት ቤተክርስቲያንን እየከፋፈለና እየለያየ ከመሄዱም በላይ የዓለም ሥጋዊ መሪዎች የሃይማኖት ነገር በጉዳያችን ውስጥ አይገባም እስከማለት እንደደረሱና ከዚያም አልፎ እግዚአብሔር የለም ወደ ሚለው ስንፍና እንዲያመሩ አድርጓቸዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 

ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም

zenaaugust14

የዜና ቤተክርስቲያን  ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ

 

በዓለ ደብረ ታቦር

በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፤
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ

 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 • ‹‹ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረድአነ፤
 • ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
 • ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ፤
 • መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ፤
 • ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሰርቅ፤
 • በእምርት ዕለት በዐልነ፤
 • እስመ ሥርዓቱ፤ ለእስራኤል ውእቱ››

abune gerimaበረዳታችን፣ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ፤ ዝማሬውን አንሡ፤ ከበሮውንም ስጡ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆው ጋር በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዐላችን ዕለት፣ መለከትን ንፉ፤ የቤተ እስራኤል ሥርዓት ነውና› ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 80፡1-4)

በዚህ መዝሙረ ዳዊት መነሻነት ከዚህ በላይ በተነገረው መዝሙረ ዳዊት መሠረት ይህን በዐለ ደብረ ታቦር በዐላችንን በየገዳማቱና አድባራቱ በየገጠሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን በታላቅ ሥነ ሥርዓት እናከብረዋለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

 

"ፍልሰታ ለማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ"

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA in Philo)

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ "ወአመ በፅሐ ዕድሜሁ እግዚአብሔር ፈነወ ወልዶ ወተወልደ እምብእሲት፡- ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ" /ገላ. 4፡4/ በማለት እንደገለጸልን ፍጠረኝ ሳይለው ከብዝሐ ፍቅሩ የተነሳ የፈጠረው የሰው ልጅ በፈጸመው ስሕተት ወይ በደል ተጸጽቶ፣ በዕንባና በለቅሶ ተሞልቶ፣ ማቅ ለብሶና አመድ ነስንሶ በንስሐ ሕይወት ተሞልቶ ፈጣሪውን ማረኝ ብሎ በመለመኑ ምክንያት ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ርህሩህ አምላክ እጅግ አብዝቶ ራራለት፣ አዘነለት፣ ጸሎቱም ሰማና "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ የምስጢረ ድኅነት የተስፋ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

የሰው ልጆችም ይህንኑ አምላካዊ የድኅነት /የማዳን ቃል ኪዳን/ ተስፋ በማድረግ ምንም ጽድቅ ቢሠሩና ጻድቃን ቢባሉም ቅሉ ከሞተ ሥጋ ከሞተ ነፍስ፣ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ መዳን ስላልቻሉ ወደ ፈጣሪያቸው አብዝተው ይማጸኑ፣ ይለምኑና ይጮኹ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል፡፡

 • "ሁላችንም እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ እንለቃቀሳለን ፍርድን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፤ እርሱም የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል" ኢሳ.59፡11

 • "ሁላችንም እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል ስምህም የሚጠራ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፣ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፤ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል" ኢሳ.64፡6-7

 • "ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ፤ ተራሮችም ምነው ቢናወጡ፤ እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጽ ዘንድ" ኢሳ.64፡1-2

 • "ፈኑ እዴከ እም አርያም፡- እጅህን ከአርያም ላክ" መዝ.144፡7 እንዲል

ዓለምን ፈጥሮ የሚያስተዳድር እግዚአብሔር በንጹሕ ልብ ሆነው የለመኑትን የማይነሳ፣ አስቀድሞ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጽሞ የማይረሳ አምላክ ስለሆነ ወደ ሕዝቡ ልመናና ጸሎት ተመለከተ፡፡ በዚህም በገባው ቃል ኪዳን መሠረት "ተስፋ አዳም" ከሆነችው ከዳግሚት ሔዋን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ዘመን የማይቆጠርለት አምላክ ሲሆን ዘመን የሚቆጠርለት ሰውም ሆኖ በተዋሕዶ ምስጢር ከብሮ መወለድ ግድ ሆነ፡፡ "ለይኩን" ብሎ ለፈጠራት አምላክ "ይኩነኒ" በሚል ቃለ ተአዝዞ ወቃለ አሚን ፈጣሪዋ ሰው ሆኖ እንዲወለድ ምክንያት የሆነች ድንግል በመሆንዋ ምስጢረ ተዋሕዶ የተፈጸመባት፣ የተከወነባት አማናዊት መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ንጽሕተ ንጹሐን ስለሆነች ተቀዳሚ ተከታይ የሌላት የአምላክ እናት ለመሆን በቃች፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ማርያምን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ በረከት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ ሕዝበ ክርስቲያን በአጠቃላይ እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለ2006 ዓ.ም ጾመ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

"ወዘሰ እንተ አንቀጽ ይበውእ ኖላዊ ዓባግዕ ውእቱ"
በበሩ የሚገባ የበጎች እረኛ ነው /ዮሐ.10፡2/

 

                                                                         
          
Picture 280

በብሉይ ኪዳን የበጎች እውነተኛ እረኛ እንደሆነ በብዙ ስፍራ የተነገረለት መሢሕ አንድ ቀን በዓለም እንደሚገለጽና በጎቹን በትክክል እንደሚጠብቅ በሕዝበ እግዚአብሔር ዘንድ የታወቀና የታመነ ነበረ /ሕዝ. 34፡1-24/

እግዚአብሔር ያስቀመጠው ቀመረ ዘመን ሲደርስ እውነተኛው እረኛ ክርስቶስ በተነገረለት በር በኩል ወደዚህ ዓለም መጣ፤

ይኸ በር የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ማኅፀን ነበረ /ሕዝ. 44፡2-3/

በኦርቶዶክሱ ዓለምና በሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የምንገኝ ክርስቲያኖች ቅድስት ድንግል ማርያምን ከእግዚአብሔር በታች፣ ከፍጡራን በላይ፣ ከፍ አድርገን የምናከብርበት ዋና ምክንያት ድንግል ማርያም የዓለም መድኅን የክርስቶስ መግቢያ በርና ለሰው ልጅ የድኅነት ምክንያት ስለሆነች ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 

የፕሮቴስታንት እይታ
ወጌሻ የሌለው የምላስ ወለምታ

ውድ አንባቢዎቻችን ከላይ ያስነበብኳችሁ ርዕስ በጥንቃቄ ካያችሁት ቀጥሎ ያለው ንባብ በትክክል ይገለጥላችኋል፡፡ ይህን ርዕስ የሰጠሁበትም ምክንያት ፕሮቴስታንት ወገኖቻችንን ለመንቀፍ ሳይሆን አመለካከታቸውን ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመልሱ ለማለት አስተያየት ለመስጠት ያህል ነው፡፡ መልካም ንባብ፤

የክርስቲያን ህብረት የሚባሉትን ሃይማኖተኞች ባጠቃላይ ወይም ክርስቶስን የሚያመልኩ ሃይማኖተኞችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው በጋራ የሚጠቀሙት መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሃይማኖተኞች መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጉሙት በተመቻቸውና አንዳንዴም በአኗኗራቸው በሚስማማ መልኩ ነው ይህ ደግሞ ስህተት ከመሆኑም በላይ ሰዎች ወንጌልን ወንጀል እንዲያደርጉ መንገድ ይከፍታል፡፡

ለዛሬ የዮሐንስ ወንጌል ምዕ 2፡1-6 ያለውን ንባብ እንመልከት በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ፡፡ የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው፡፡ ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት እናቱም ለአገልጋዮቹ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው ዮሐ ፡-፤

እንግዲህ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ካነበብን በኋላ እንደየአቅማችን እንረዳለን፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ኦርቶዶክሳዊያን አፈታት ካየን በኋላ ወደ ፕሮቴስታንት አፈታት አንሄዳለን፡፡

ኦርቶዶክስ

የጌታ እናት ማርያም በታሪኩ ውስጥ እንደምንረዳው ወደ ሰርጉ ከታደሙት እንግዶች መካከል አንዷ ናት፡፡ በዚያ ስፍራ በርካታ የተከበሩ ባለሥልጣናት እና የቤተ መቅደስ አገልጋዮች እንዲሁም ባለፀጎች እና በልዩ ልዩ ሙያ የተካኑ ሰዎች እንደሚኖሩ መገመት አያዳግትም፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

 
የፎንት ልክ መቀየሪያ
Download Fonts

Having problem reading in

Amharic? Click here to Download

Nyla font. Open the file, click 

install button at the top.

መግቢያ