Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

"ኪዳነ ተካ የድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ" መዝሙር 88፡3

ይህ ቃል እግዚአብሔር ከቅዱሳን ሰዎችና መላእክት እንዴት ቃል ኪዳን እንደሚገባ በነቢዩ በቅዱስ ዳዊት አንደበት አድሮ የተነገረው የቃል ኪዳን ዕብነ ማዕዘንት መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡ ቃል ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካከል የሚፈጸምና ሁለቱም ወገኖች ሊጠብቁት የሚገባ ውል ወይም ስምምነት የመሐላ መተማመኛ ማለት ነው፡

ከሁለቱ አንዱ ውሉን ቢያፈርስ ሌላው ወገን ቃል ኪዳኑን ለመጠበቅ አይገደድም፣ ቃል ኪዳን አፍራሹን ክፍል ሊቀጣ ይችላል፡

ቃል ኪዳን ብዙ ጊዜ በሰዎችና በሰዎች ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከልም እንደተደረገ ቅዱስ መጽሕፍ ያወሳናል፡

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ከኃጢአቱ ብዛት የተነሳ በጥፋት ውሃ በኮነነ ጊዜ ለኖህ በሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት እሱንና ቤተሰዎቹን ከጥፋት ውሃ ጠበቀ፣ በጠቅላላው በመርከቧ ውስጥ የነበሩትን ነፍሳት ሁሉ አተረፈ፣ የጥፋቱም ውሃ /ማየ አይኅ/ ከደረቀ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ኖህን ባረከው የቃል ኪዳንም አደረገለት፤ የምሕረቱም ቃል፣ ኪዳን ምልክት ቀስተ ደመናን በሰማይ አደረገ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

"መነ ይብልዎ ሰብእ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው፣ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" (ማቴ. 16፥13)

በሀገራችን በኢትዮጵያና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ሆናችሁ ይህን የቅዱስ ወንጌል ቃል በመስማት ላይ የምትገኙ ውሉደ እግዚአብሔር ሁሉ፣ እግዚአብሔር አምላካችን በረከቱን፣ ጸጋውንና መልካም ስጦታውን ሁሉ እንዲያበዛላችሁ እየጸለይን፣ እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ እንላለን ፡፡

የደብረ ታቦር በዓል ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ባህርዩንና ምሥጢረ መንግሥቱን የገለፀበት ቀን በመሆኑ፣ በክርስትናው ዓለም ዓቢይ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ነው ፡፡

የታቦር ተራራ ቀደም ሲል ከክርስቶስ ልደት በፊት ዲቦራ የተባለች ነቢይት በዚህ ተራራ ላይ ቆማ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይና የጦር አመራርን በመስጠት፣ ሕዝበ እሥራኤልን ለመውጋትና ለመውረር በእብሪት ተነሣሥቶ የመጣውን ሲሣራን፣ በባርቅ አዝማችነት ድል ያደረገችበት የድል ተራራ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎአል፤ (መሳ. 4፡4-24)፡፡

ይህ ድል በዘመነ ሥጋዌ የሚነሡትን የኑፋቄ ትምህርቶች ሁሉ በደብረ ታቦር በሚገለፀው መለኮታዊ ትምህርት ድል የሚደረጉ መሆናቸውን የሚያመለክት ነበር ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ክቡራን ክቡራት እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እግዚአብሔርን የምትወዱ ሁላችሁ፤ ሁላችንንም በዚህ ቅዱስ ቦታ ሰብስቦ ስሙን በመጥራት ስሙን በመቀደስ፤ ቃሉን በመስማት ይህን የቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያውያት ታላቅ ዓመታዊ መንፈሳዊ በዐል የሆነውን በዐለ ደብረ ታቦርን በአንድነት ሁነን በቅዳሴ፣ በውዳሴ፣ በዝማሬ፣ ለማክበር ላበቃን እግዚአብሔር አምላካችን "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት፣ ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት" በማለት ምስጋናችንን ለእግዚአብሔር አምላካችን እናቀርባለን፡፡

"ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረድአነ፤

 • ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
 • ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ፤
 • መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ፤
 • ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሰርቅ፤
 • በእምርት ዕለት በዐልነ፤
 • እስመ ሥርዓቱ፤ ለእስራኤል ውእቱ"

"በረዳታችን፣ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ፤ ዝማሬውን አንሡ፤ ከበሮውንም ስጡ፣ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆው ጋር በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዐላችን ዕለት፣ መለከትን ንፉ፤ የቤተ እስራኤል ሥርዓት ነውና" ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 80፡1-4)

ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በዐላትን በከበሮና በጸናጽል ማክበሩ የቤተ እስራኤላውያን ሥርዓት መሆኑን ይናገራል፡፡

ይሁንና በዐላትን በከበሮና በጸናጽል ማክበሩ የእስራኤላውያን ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የኢትጵያውያንም ሥርዓት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡

በዚህ መዝሙረ ዳዊት መነሻነት ከዚህ በላይ በተነገረው መዝሙረ ዳዊት መሠረት ይህን በዐለ ደብረ ታቦር በዐላችንን በየገዳማቱና አድባራቱ በየገጠሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን በታላቅ ሥነ ሥርዓት እናከብረዋለን፡፡

አሁንም የ2008 ዓ.ም. በዐለ ደብረ ታቦር በዐላችንን በማክበር ላይ እንገኛለን ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

በዛሬ ዝግጅታችን ትምህርተ ሃይማኖት የሚል ነው፡፡ ይህም ሰሙነ ሕማማት ማለት ምን ማለት ነው? ሆሣዕና ማለት ምን ማለት ነው? ዕለቱን በየዓመቱ እናከብረዋለን፣ ምን የተደረገበት ነው? የሰሙነ ሕማማት ምሥጢር ምንድን ነው?

እሑድ፣ሠኑይ፣ ሰሉስ፣ ረቡዕ ኀሙስ፣ ዓርብ፣ ቅዳሜ፣ እሑድ እያንዳንዱ ዕለት ምን የተከናወነበት ነው?

በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸመው ሥርዓትስ፤ የዕለተ ዓርብ ታምራት፣ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ስለሚባለው፤ ጌታ በመቃብር ስለቆየበት የሰዓት አቈጣጠር፣ እንዲሁም ጌታ "ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ" ያለበት ምክንያት ምንድነው?

ቅዳሜ ሥዑር የተባለበት ምክንያትስ ዋና ትርጉሙ ምን ይመስላል? ትንሣኤ ክርስቶስና ትንቢቱ፣ የሚሉና የመሳሰሉ ነጥቦችን ነው፡፡

በዚህም መሠረት ከእኛ የሚጠበቀው የቤተ ክርስቲያንዋን ትምህርተ ሃይማኖት በጥንቃቄ ማቅረብ ሲሆን ከአንባቢው የሚጠበቀው ደግሞ ጽሑፉን በጥንቃቄ አንብቦ ማወቅና መረዳት ነው፡፡

19.1፣ሰሙነ ሕማማት

ከትንሣኤ /ፋሲካ/ በፊት ያለው ሳምንት በማንኛውም ቤተ ክርስቲያን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሕማማቱ መታሰቢያ ሳምንት ነው፡፡ በየአብያተ ክርስቲያናት የተለያየ አጠራር አለው፣ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፣ የመከራ ሣምንት ማለት ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ከመምህር ዕንቈባሕርይ ተከሥተ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ

በቀጥታ ወደ በዓሉ አከባበር ከመግባቴ በፊት የጾመ ዐርብ አጀማመርና አፈጻጸም የቀናት ልዩነት በጥቂቱ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጾመ ሁዳዴ /ጾመ አርብአ/ የሚጾመው 55 ቀናት ናቸው፡፡
ይኸውም፡-


1. 7 ቀናት የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡
2. 40 ቀናት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጾም ከቅድስት እስከ ተጽዒኖ ያለው ነው፡፡ በውስጡ 6 ሳምንት አሉት፡፡ እነርሱም ቅድስት፣ ምኲራብ፣ መጻጒዕ፣ ደብረ ዘይት፣ ገብርኄር፣ ኒቆዲሞስ ናቸው፡፡
3. 8 ቀናት የሰሙነ ሕማማት ሳምንት ነው፣ ይህም ማለት ከሆሣዕና በፊት ካላቸው ቅዳሜ ቀን ጀምሮ እስከ ከሥቅለት በኋላ ያለችው ቅዳሜ ነው፡፡ ጠቅላላ ድምር 55 ቀናት ናቸው፡፡ በአምሳ ስድስተኛ ቀን በዓለ ትንሣኤ በእለተ እሑድ ይከበራል፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

 

bedokimas betበመ/ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሣሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ መንበረ ፓትርያርክ

የትምህርትና ማሠልጠኛ ዋና ኃላፊ

ምልጃ ዘመናትን ተሻግሮ የመጣውና እውነት የሆነው ደጋግ አባቶች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የጻፉት መጽሐፍ ቅዱስ ከጥንት ጀምሮ የተጀመረ፤ ራሱ ልዑል እግዚአብሔር ያዘዘው እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ለዚህም ሕዝበ እስራኤል ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜና መቅሠፍትና መከራ በሚጸናባቸው ወቅት ወደ መንፈሳውያን መሪዎቻቸው እየቀረቡ ወደ እግዚአብሔር አማልዱን እያሉ ሲማጸኑ፤ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ደግሞ የሕዝባቸውን ጥያቄ ወደ እግዚአብሔር እያቀረቡ ምሕረትንና ቸርነትን እያስገኙ እንደመጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል (ዘፍ. 18.20፡፡ ዘፍ. 20.7-10፡፡ ዘጸ. 32። ዘኁ. 16.41-50፥ 21.7-9፡፡ ኢዮ. 42.7-8፡፡ ኤር. 42.1-11)፡፡

እንዲሁም ሰውን ከሰው ጋር የሚያስታርቁና የሚያ ማልዱ ወገኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ክብር እንዳ ላቸው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ "የሚያስ ታርቁ ብፁዓን ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና"፡፡ በማለት ክብራቸውን ይገልጻል፡፡ (ማቴ. 5.9)፡፡ ስለዚህ ምልጃ እግዚአብሔር ያዘዘውና የሚወደው ቅዱስ ተግባር ነው፡፡

 

በአዲስ ኪዳን የአማላጅነት መሠረት ድንግል ማርያም ናት፡፡

ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አማላጅነት ከማየታችን በፊት በቅድሚያ ስለ መመረጥዋና ቅድስናዋ በመጠኑ እንደሚከተለው በቀረቡት ንዑሳን ክፍሎች ማየት ለተነሣንበት ዋና ርእስ ወሳኝ ነው፡፡

እነዚህም፡-

 በተጨማሪ ያንብቡ…

እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮም በሐዲስ ተፈጥሮም ከእርሱ ጋር አስተካክለን
ጥንተ ተፈጥሮ አዳም በመጀመሪያ ከፍጥረታት ሁሉ ጋር የተገኘበት ተፈጥሮ ነው፡፡ ሐዲስ ተፈጥሮ ጌታችን በዕለተ ዓርብ በመሠረታት ጥምቀት ዳግመኛ ከእግዚአብሔር የምንወለደው የልጅነት ተፈጥሮ ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ሲፈጥረው በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ካለ በኋላ በዚህ ቀን ይህን ፈጠረ በዚህ ቀን ይህን ፈጠረ ዘፍ. 1:1-25 እያለ ሂዶ "እግዚአብሔርም አለ ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር... ሁሉን ይግዛ ብሎ እግዚአብሔር ሰውን በእግዚአብሔር አምሳል ፈጠረ" ዘፍ. 1:26-27 ይላል፡፡

ዳግመኛ ይህን በዝርዝር የተናገረውን ሥነ ፍጥረት በመጽሐፈ ኩፋሌ ጠቅለል አድርጎ

"ሁሉም ሃያ ሁለት ዓይነት ፍጥረት ሆነ በስድስተኛዪቱም ቀን በሰማይና በምድር በባሕሩና በጥልቁ ውስጥ በብርሃንና በጨለማ መካከል በሁሉም ላይ ያለውን ፍጥረት ሁሉ ፈጥሮ ፈጸመ ኩፋ. 3:2 ብሎአል፡፡ ሃያ ሁለተኛው አዳም ነው፡፡

ሃያ ሁለት ዓይነት ፍጥረት ሆነ ሲባል ግን እያንዳንዱ በዝርዝር ተቈጥሮ አይደለም ብዙውን አንድ እያሉ በጥቅል ሲቈጠር ነው ለምሳሌ ከዋክብት ስፍር ቁጥር የላቸውም ልበ አምላክ ዳዊት

"ከዋክብትን በመላው የሚቈጥራቸው በየስማቸውም የሚጠራቸው እግዚአብሔር ታላቅ ነው ለጥበቡም ቁጥር የለውም" መዝ. 146:4-5

እንዳለው ከፈጠራቸው ከእግዚአብሔር በስተቀር ሊቈጥራቸው የሚችል የለም፡፡

መላእክትም ምንም እንኳ እንደ ከዋክብት ተደርድረው ባይታዩም ቁጥራቸው ከከዋክብት ሊበልጥ እንደሚችል ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ ታዲያ እነዚህና እንደ እነዚህ ብዛት ያላቸው ሁሉ በጅምላ አንድ እየተባሉ ተቈጥረው ነው ሃያ ሁለት ዓይነት ፍጥረት ሆነ የተባለው፡፡ ይሁን እንጂ ከእነዚህ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ፍጥረታት ሁሉ በእግዚአብሔር ምሳሌና መልክ የተፈጠረ የሰው ልጅ ብቻ ነው ዘፍ. 1:26-27 ዳግመኛ እንደ እግዚአብሔር ሁሉን እንዲገዛ የከበረ ዕድል የተሰጠው ለሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡
ሦስተኛ በአፍንጫው እፍ ብሎ አርአያ እግዚአብሔርን ያደለው ሰውን ብቻ ነው፡፡

"እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ" ዘፍ. 2:7፡፡

ይህች የሕይወት እስትንፋስ የተባለች ሕያውነት ለባዊነትና ነባቢነት ያላት ፍጹምነት አርአያ እግዚአብሔር ወይም እግዚአብሔርን መምሰል ያላት ልጅነት ናት፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በዚህ መልኩ ራሱን አስመስሎ በመፍጠር አክብሮና አልቆ አስቀምጦት ነበር "ወረስዮ ርኡሰ ወስሉጠ" አማርኛ ገዥና አለቃ አደረገው" መቅድመ ወንጌል፡፡ ነገር ግን ሰው የተሰጠውን ጸጋ ጠብቆ ሊኖር አልቻለም የጠላት ምክር ሰምቶ አምላክነት ሽቶ አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በመብላት ከፈጣሪው ተጣልቶ ከክብሩ ተዋረደ ከገነት ተባረረ ዘፍ. 3:1-24
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት

"ሰው ግን ክቡር ሲሆን አላወቀም ልብ እንደሌላቸው እንስሶችም ሆነ መሰላቸው" መዝ. 48:12-20

እንዳለ በዚህ ጊዜ አዳምና ሔዋን እግዚአብሔርን ያዩበት የነበረ መልካሙ ዐይነ ልቡናቸው ታውሮ ከፉውን ነገር ሁሉ የሚያዩበት ዐይነ ሥጋቸው ተገለጠ ዕራቁታቸውን እንደሆኑ ዐወቁ" ዘፍ. 3:1-7 ልጅነታቸው ተገፈፈ ጸጋ እግዚአብሔር፣ ረድኤተ እግዚአብሔር ራቀቸው በአንጻሩ ፍራት፣ መንቀጥቀጥ፣ ድንጋጤ፣ ሽብር፣ እፍረት ያዛቸው ከዚህም የተነሣ የበለስን ቅጠል ሰፍተው ዕርቃናቸውን ሰወሩ ያም አልበቃ ብሎ በገነት ዛፎች ውስጥ ተሸሽጉ፡፡ ዘፍ. 3:8
ከዚያች ሰዓት ጀምሮ አዳም ከገነት መውጣቱ ሳያንስ በተጨማሪ ከእግዚአብሔር ጋር ከመኖር ከሰይጣን ጋር ወደ መኖር ከእረፍት ወደ ድካም ከደስታ ወደ ኀዘን ከሕይወት ወደ ሞት ተሸጋገረ "በዚህ ምክንያት ሞት በሰው ልጅ ላይ ሠለጠነ ስለዚህ ነው

"እግዚአብሔርስ ሞትን አልፈጠረም ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረትን ፈጠሮአልና የሰዎች ጥፋት ደስ አያሰኘውምና ለመቃብርም በዚህ ዓለም ግዛት አልነበረውምና እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎች ግን በቃል ጠሩት ባልንጀራም አደረጉት በዚህም ጠፉ" ጥበ.1:13-15:16

ከዚህም ጋር የሰው ልጅ የሰይጣን ተገዥ ሆነ፡፡
አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አክብሮ ሥርዓቱን ጠብቆ ሲኖር የሁሉ ገዢ አደርጐታልና ሁሉ ያከበረው ሁሉ ይፈራው ነበረ ለአብነት ዛሬ ብዙ ቱሪስቶች ጊዜያቸውን ሠውተው ብዙ ገንዘብ አውጥተው አገር ለአገር ጫካ ለጫካ እየኳተኑ በአድናቆት የሚጐበኙአቸውን የዱር እንስሳትና አራዊት ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስም እንዲያወጣላቸው ዘወተር ወደ እርሱ እየሄዱ ከማዝናናታቸውም በላይ አልበህ ጠጣን አርደህ ብላን እያሉ ለእርሱ ያላቸውን አክብሮት ይገልጹ ነበር ዘፍ. 3:19-20 ሰይጣንም አይቀርበውም ነበር፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ከመምህር ዕንቈ ባሕርይ ተከስተ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ

 

1. ስለ መሲሑ የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድና የበዓሉ አከባበር፤


birthofchrist

ዝርዝር ሐተታ ከመሄዳችን በፊት ገና ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙ እነሆ፡፡ ገና ማለት ከጽርዕ /ግሪክ/ ቋንቋ የተወረሰ ነው፡፡ ትርጉሙም ልደት ማለት ነው፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ አዳም አባታችን ወዶ በሠራው ኃጢአት ምክንያት የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት ጊዜ ድረስ ዓለም በጨለማ ጒዞ ይጓዝ ነበር፡፡ /ኢሳ. 9፡2/

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ ግን በጨለማ ጥላ ሥር ይንከራተትና ፍዳውን ይቈጥር ይኖር የነበረ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ ተስፋ ያልነበረው ሕዝብ የተስፋ ባለቤት ሆነ፣ የጨለማና የኀዘን የሥቃይ፣ የፍዳ፣ የገፊና የተገፊ መናኸሪያ የነበረው አሮጌው ዓለም በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ዓለም ሆኗል፡፡ /ኢሳ. 9፡2፣ ሮሜ.13፡12/

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ