Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ዐቢይ ጾምና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ

ክፍል አንድ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

በተለያዩ መጻሕፍት እንደተጻፈውና በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን መምህራን ሊቃውንት በየዓውደ ምሕረቱ ዘወትር እንደሚተነተነው ጾም ማለት በታወቀ፣ በተወሰነ፣ በተቀመረ... ጊዜ ከመብል ከመጠጥ መከልከል፣ መቆጠብ፣ መወሰን... ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን "ጾም" ከክርስቲያናዊ ምግባርና ትሩፋት የሚመደብ ኣስተምህሮ ነው፡፡ ጾም የመሠረተውም ሆነ የታዘዘው ከፈጣሬ ሰማያት ወምድር ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ምዕመን ጾምን በመከተል ለሠራዔ ጾም (ጾም ለሠራለት) አምላክ እየተገዛ፣ እያመለከ፣ እያከበረ፣ እየታዘዘ... በበጎ ሕሊና ተሞልቶ ፈቃደ ሥጋውን (ትዕቢት፣ ስስት፣ ዝሙት፣ ቅንዓት...) ለፈቃደ ነፍሱ (የዋህነት፣ በጎነት፣ ርህሩህነት...) በማስገዛት በፈጣሪ መመሪያ፣ ትእዛዝ እና ፈቃድ መኖር ማለት ነው፡፡

ጾም መጋቤ ዓለማት እግዚአብሔር ከብዝሐ ፍቅሩ የተነሳ ምልዓተ ፍቅሩን ለማጋራት ፈልጎ የፈጠረው አዳም የመታዘዙ ምስጢር አድርጎ ከሰጠው ጸጋ የመነጨ የመንፈሳዊ ሕይወት ምርኩዝ ነው፡፡ ይኸውም በመንፈሳውያን ጸጋዎች አንቆጥቁጦ ለፈጠረው አዳም ሁሉም ነገር አሟልቶ ከሰጠው በኋላ የፈጣሪን አዛዥነት፣ የፍጡርን ታዛዥነት የሚገልጽ ሕግ መኖር ስለነበረበት "ከዚህ ከገነት ፍሬ ሁሉ ብላ ነገር ግን ክፉውንና ደጉን ከምታሳውቅ ከዚህች ዕፀ በለስ እንዳትበላ ከበላህ ግን ሞትን ትሞታለህ ብሎ መስጠቱ መሠረተ ጾም እግዚአብሔር መሆኑ ይገልጽልናል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

መስቀል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

መ/ር ፀገዬ ኃይሌ

መስቀል በብዙዎች ሰዎች ኀሊና በብዙ ዓይነትና ቅርጽ የተሰራ ተደርጎ የሚታዩ ወይንም የሚተረጎም ቢሆንም እኛ ግን ከዘመነ ብሉይ መጀመሪያ እስከ ዘመነ ሐዲስ እስከ አለንበት ዘመን ስለአለው ስለክርስቶስ ነገረ መስቀል እንናገራለን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አስቀድሞ ከዘመነ አበ ብዙኃን ከአዳም ጊዜ ጀምሮ ብዙ ነቢያት በተለያየ ኅብረ አምሳል ትንቢት የተናገሩለት በዘመነ ሐዲስም እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢአት የወደቀውን የሰውን ልጅ ከራሱ ጋር ያስታረቀበት እስከ አሁንም ድረስ አስቀድሞ የክፋት ምንጭ የሆነው ዲያብሎስ ሰውን ከፈጣሪው እንዲለይና መከራ ውስጥ እንዲወድቅ እንዳደረገው አሁንም ደግሞ ለተመሳሳይ ፈተና እንዳያጋልጠው ሥልጣነ አምላክ በተሰጣቸው ሐዋርያትና ደቀመዛሙርቶቻቸው አማካኝነት በተናገረው ቃሉና በተሰቀለበት ዕፀ መስቀል እራስ እራሱን እየቀጠቀጡበት ለሚያምኑበት ብልሃት ለማያምንኑበት ሞኝነት ሆኖ ሲጠብቀን ይኖራል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

በዓለ ደብረ ታቦር

በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፤
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ

 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 • ‹‹ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረድአነ፤
 • ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
 • ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ፤
 • መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ፤
 • ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሰርቅ፤
 • በእምርት ዕለት በዐልነ፤
 • እስመ ሥርዓቱ፤ ለእስራኤል ውእቱ››

abune gerimaበረዳታችን፣ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ፤ ዝማሬውን አንሡ፤ ከበሮውንም ስጡ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆው ጋር በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዐላችን ዕለት፣ መለከትን ንፉ፤ የቤተ እስራኤል ሥርዓት ነውና› ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 80፡1-4)

በዚህ መዝሙረ ዳዊት መነሻነት ከዚህ በላይ በተነገረው መዝሙረ ዳዊት መሠረት ይህን በዐለ ደብረ ታቦር በዐላችንን በየገዳማቱና አድባራቱ በየገጠሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን በታላቅ ሥነ ሥርዓት እናከብረዋለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የፕሮቴስታንት እይታ
ወጌሻ የሌለው የምላስ ወለምታ

ውድ አንባቢዎቻችን ከላይ ያስነበብኳችሁ ርዕስ በጥንቃቄ ካያችሁት ቀጥሎ ያለው ንባብ በትክክል ይገለጥላችኋል፡፡ ይህን ርዕስ የሰጠሁበትም ምክንያት ፕሮቴስታንት ወገኖቻችንን ለመንቀፍ ሳይሆን አመለካከታቸውን ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመልሱ ለማለት አስተያየት ለመስጠት ያህል ነው፡፡ መልካም ንባብ፤

የክርስቲያን ህብረት የሚባሉትን ሃይማኖተኞች ባጠቃላይ ወይም ክርስቶስን የሚያመልኩ ሃይማኖተኞችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው በጋራ የሚጠቀሙት መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሃይማኖተኞች መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጉሙት በተመቻቸውና አንዳንዴም በአኗኗራቸው በሚስማማ መልኩ ነው ይህ ደግሞ ስህተት ከመሆኑም በላይ ሰዎች ወንጌልን ወንጀል እንዲያደርጉ መንገድ ይከፍታል፡፡

ለዛሬ የዮሐንስ ወንጌል ምዕ 2፡1-6 ያለውን ንባብ እንመልከት በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ፡፡ የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው፡፡ ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት እናቱም ለአገልጋዮቹ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው ዮሐ ፡-፤

እንግዲህ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ካነበብን በኋላ እንደየአቅማችን እንረዳለን፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ኦርቶዶክሳዊያን አፈታት ካየን በኋላ ወደ ፕሮቴስታንት አፈታት አንሄዳለን፡፡

ኦርቶዶክስ

የጌታ እናት ማርያም በታሪኩ ውስጥ እንደምንረዳው ወደ ሰርጉ ከታደሙት እንግዶች መካከል አንዷ ናት፡፡ በዚያ ስፍራ በርካታ የተከበሩ ባለሥልጣናት እና የቤተ መቅደስ አገልጋዮች እንዲሁም ባለፀጎች እና በልዩ ልዩ ሙያ የተካኑ ሰዎች እንደሚኖሩ መገመት አያዳግትም፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

"የምንሞት ስንመስል እነሆ እያዋን ነን" 2ኛ ቆሮ. 6፡9

በመምህር ጸገየ ኃይሌ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
የደብረ ኃይል ቅዱስ ተራጉኤል ቤተ ክርስቲያን
ስብከተ ወንጌል ኃላፊ

ትንሣኤ የሚለው ቃል ተንሥአ ተነሳ ከሚል የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ስም ነው፡፡ ትንሣኤ አንድ ነገር ከነበረበት (ከተቀመጡበት) ቦታ ተነስቶ መቆምን መሔድን ከእንቅልፍ ነቅቶ መነሳትን ወዘተ ያመለክታል፡፡ እኛ ግን ከዚህ ዓይነቱ ትንሣኤ ፍጹም ልዩ ስለሆነው ከሞት ወደ ሕይወት ከሐሣር ወደ ክብር መሸጋገርን ስለሚሰብከው ስለ መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እንናገራለን፡፡

የክርስቶስ ትንሣኤ

የክርስቶስ ትንሣኤ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ በእኔ የሚያምን ቢሞትም እንኳን በሕይወት ይኖራል፤ በሕይወት የሚኖር በእኔም የሚያምን ሁሉ ከቶ አይሞትም" /ዮሐ.11፡25/ በማለት በተናገረው አምላካዊ ቃሉ መሠረት ማንም ሰው ሳይቀሰቅሰው ለአነሳሱ አጋዥ /ረዳት/ ሳያስፈልገው ሞትን ድል ነስቶ መግነዝን ፈቶ መቃብርን ከፍቶ በመነሳት አምላካዊ ኃይሉን የገለጸበት ምሥጢር ነው፡፡

መሞቱም ወደ መቃብር መውረዱም ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱም በራሱ በፈቃዱ የተናገረውና ያደረገው ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ይህንን የጌታ አስተምህሮቱን በጽሑፍ ሲገልጽ "ነፍሴን ደግሞ አነሳት ዘንድ አኖራለሁና፣ ስለዚህ አብ ይወደኛል እኔ በፈቃዴ አኖራለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ለኖራት ደግሞም ላነሳት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልኩ" (ዮሐ. 10፡17-21) በማለት ይገልጻል፡፡

ስለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ከዚህ አምላካዊ ጥበብ እምንመለከተው እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅር የከፈለንን ዋጋ እንዲሁም ደግሞ ዳግም ሞት እንዳያገኘን ትንሣኤ እንዳለን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳ አምላክ ከእኛ ጋር እንዳለና እኛም ከእርሱ ጋር እስከወዲያኛው እንደምንኖር ያሥረዳል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

እንግዲህስ ለንስሐ የሚያበቃችሁን በጎ ሥራ ሥሩ (ማቴ. 3፡8)

በመጋቤ ብሉይ ዕዝራ ለገሠ
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን
የሊቃውንት ጉባኤ አባል

1. መግቢያ

ንስሐ የሚለው ቃል "ነስሐ" ንስሐ ገባ፣ ዐዘነ፣ ተጠጠተ፣ ተመለሰ፣ ክፉ ዐመሉን ተወ፣ ክፉ ጠባዩን ለወጠ፣ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ንስሐ ማለት "ንስሐ" መግባት፣ ማዘን መጠጠት መመለስ፣ ክፉ ዐመልን መተው፣ ክፉ ጠባይን መለወጥ ማለት ነው፡፡ ደግሞም ንስሐ ማለት ሐዘን፣ ጸጸት፣ ቊጭት፣ምላሽ፣ መቀጮ፣ ቅጣት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሳ፣ ራስን በራስ ወይም በካህን ፊት መውቀስ፣ መክሰስ በደልን በቄስ ፊት ማፍሰስ ማለት ነው፡፡ ንስሐ የብሉይ ኪዳን መድረሻ የሐዲስ ኪዳን መነሻ ነው፡፡ ፍጻሜ ትምህርተ ነቢያት የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ ነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት ሲል (ማቴ. 3፡2) እግዚአ ነቢያት ክርስቶስም ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት በማለት ትምህርተ ወንጌልን ጀምሯል ማቴ. (4፡17፣ ማር 1፡14)

ንስሐ ከጥፋት መመለሻ መንገድ፣ ከውድቀት መነሻ ምርኩዝ፣ ከዝቅጠት መውጫ መሰላል ነው፡፡ ያለንስሐ ፍጹም የሆነውን የክርስትና ሕይወት ልንኖርና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ ሕይወት ሊኖረን አይችልም፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

"አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እም ገነት፡- ከገነት በተባረረ ጊዜ የአዳም ተስፋ አንቺ ነሽ" ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ዘሀገረ ብሕንሳ

 • "ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፤ ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ" መዝ. 89፡3

 • ኪዳነ ምሕረት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
የሰንበት ትምህርት በቶች ማደራጃ
መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊ


አምላካዊ ሕግ ወደ ጎን ትቶ በሰይጣን ምክንያት የቀረበለት ፍጹም የሐሰት ሽንገላና ሥጋዊ ፍላጉቱን ተከትሎ አትብላ የተባለውን በልቶ፤ አታድርግ የተባለውን ያደረገው አዳም አባታችን ከፈጣሪ የተሰጡትን አምላካውያን በረከቶች አንድ በአንድ ከላዩ ላይ እየተገፋፉ ርቀው ዕርቃኑን በቀረ ጊዜ የፈጸመው ድርጊት ሥጋዊና ሰይጣናዊ እንዲሁም ፈቃደ እግዚአብሔርን ያልተከተለ መሆኑ ተገንዝቦ በሰውነቱ ላይ ቅጠላ ቅጠልን አገልድሞ ከልቡ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ፊቱንም በንስሐ እንባ ታጠበ፡፡

ከክብር ይልቅ ውርደትን፣ ከሕይወት ይልቅ ሞትን፣ ከደስታ ይልቅ ሐዘንን መርጦ በራሱ ፈቃድ በጸጋ ከፈጣሪ የተሰጡት ጸጋዎች መገፈፋቸው ካወቀ በኋላ የፈጣሪው ርህሩህነትና መሐሪነት አብዝቶ ተረድቶ ስለነበረ ሳይውል ሳያድር ንስሐ ገብቶ "አጥፊቻለሁ ይቅር በለኝ" ብሎ ከልቡ ተጸጽቶ የንስሐ ጸሎት አቀረበ፡፡

ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔርም የንስሐ ጸሎቱን ተቀብሎ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በሞቴና በመስቀሌ ቤዛ ሆኜ አድንሃለሁ በማለት የድኅነት ተስፋ /የድኅነት ቃል ኪዳን/ ሰጠው፡፡

ይህች አማናዊት የደኅነተ ዓለም ተስፋ /ቃል ኪዳን/ ማለትም አስቀድሞ ለአዳም ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ በማለት የሰጠው ተስፋ፣ እግዚአብሔርም ለአዳም የገባለትን የምሕረት፣ የይቅርታ ቃል ኪዳን እውን የሚሆንባት፣ ዘመን የማይቆጠርለት ረቂቁ መለኮት በተዋሕዶ ምስጢር ሥጋ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ ሆኖ የሚያድርባት አማናዊት ቅድስተ ቅዱሳን፣ አካላዊ ቃል፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅጸንዋን ዓለም አድርጎ በቅዱሳን መላእክት የሚመሰገንባት እውነተኛ የድኅነት ምልክት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም መሆንዋ እውነት ሆነ፡፡ ነቢያት ድንግል ማርያም ትክክለኛ የድኅነታችን ምልክት መሆንዋ አስቀድመው ትንቢት ተናግረዋል፡፡

 • "ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፡፡ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች" ኢሳ.7፡14 ይህንን አማናዊ ትምህርት አምልቶና አስፍቶ፣ በምስጢርም አገናኝቶ ካስተማሩን አበው አንዱ ብርሀን ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ ይኸውም በጥንተ ፍጥረት አዳም በተሳሳተ ጊዜ እግዚአብሔር ሲረግማቸው ለእባብ እንዲህ አለው፡-

 • "ከምድር አራዊት ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፡፡ በሆድህም ትሄዳለህ፤ አፈርም በሕይወትህ ሁሉ ትበላለህ፡፡ በአንተና በሴቲቱ መካከል በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እራሱ ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ሰኰናውን ትነክሳለህ" /ዘፍ. 3፡14-15/፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

"ሌላ ሸክም አልጥልባችሁም ያላችሁን የሰጠኋችሁን ጠብቁ" ራዕ 2፡25


በመ/ር ጸገየ ኃይሌ ገብረስላሴ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን
ስብከተ ወንጌል ኃላፊ

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ አስቀድሞ አዳም በበደል ምክንያት ከእግዚአብሔር መንግስት በጠፉ ጊዜ የጠፋውን አዳምን ፈልጎ ከልጅ ልጁ ተወልዶ ያጣውን ልጅነቱን እንደሚሰጠው ሞቱን በሞቱ ሽሮ ወደቀደመ ክብሩ እንደሚመልሰው ቃል ገብቶለታል፤ በቃሉም መሠረት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ለሰው ልጅ ከሰጠው ውለታ አንዱ ጥምቀት ነው፡፡

ፈጣሪ ወመጋቤ ዓለማት እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ነቢያት እያስነሳ መወለዱን በትንቢት ሲያናግር አዳምና የአዳም ልጆች ተስፋ እንዳይቆርጡ ሲያስተምር ቆይቶ በመወለድ ግብሩ ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር የሚወለደውን አንድያ ልጁ እግዚአብሔር ወልድን ወደዚህ ዓለም ላከው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊተ ዓለም ከሆነችው ከድንግል ማርያም ተወልዶ እንደማንኛችንም የሰው ልጆች በጥቂት በጥቂት ከአደገ በኋላ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ከማስተማሩ በፊት እንደቀደሙት ነቢያት ነቢይ እንደ ሐዋርያት ካህን በመሆን ነቢይነትን ከክህነት ጋር የተሰጠው መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ነቢያት መንገድ ጠራጊነቱን እርሱ በውኃ እያጠመቀ ከእርሱ የሚበልጥ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቅ የሚመጣ መሆኑን ትንቢት ተናግሯል (የማቴዎስ ወንጌል 3፡1-12)፡፡ እንደ ካህናቱም በማየ ዮርዳኖስ ኢየሱስ ክርስቶስ እጁን ዘርግቶ በአየር ላይ ባርኮ አጥምቆታል፡፡ ማቴዎስ. 3፡13-17፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ