Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ዐቢይ ጾምና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA in philo)

"ቀድሱ ጾመ … ቀድሱ ጾመ …"

"ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ …"

"ጾመ እግዚእነ

ጾመ በእንቲአነ

አርአያሁ ከመ የሀበነ"

"ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ

ወንትፋቀር በበይናቲነ "

"ዓይን ይጹም እምርእየ ሕሱም

ዕዝን ይጹም እምሰሚዓ ሕሱም

ልሳንኒ ይጹም እምተናግሮ ሕሱም "

                                ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ

በተለያዩ መጻሕፍት እንደተጻፈውና በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን መምህራን ሊቃውንት በየዓውደ ምሕረቱ እንደሚተነተነው ጾም ማለት በታወቀ፣ በተወሰነ፣ በተቀመረ…ጊዜ ከመብል ከመጠጥ መከልከል፣ መቆጠብ፣ መወሰን…ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ጾም”ከክርስቲያናዊ ምግባርና ትሩፋት የሚመደብ ኣስተምህሮ ነው፡፡ ጾም የመሠረተውም ሆነ የታዘዘው ከፈጣሬ ሰማያት ወምድር ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ምዕመን ጾምን በመከተል ለሠራዔ ጾም (ጾም ለሠራለት)አምላክ እየተገዛ፣ እያመለከ፣ እያከበረ፣ እየታዘዘ…በበጎ ሕሊና ተሞልቶ ፈቃደ ሥጋውን (ትዕቢት፣ ስስት፣ ዝሙት፣ ቅንዓት…) ለፈቃደ ነፍሱ (የዋህነት፣ በጎነት፣ ርህሩህነት…) በማስገዛት በፈጣሪ መመሪያ፣ ትእዛዝ መኖር ማለት ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን

በመ/ር ዕንቈባሕርይ ተከስተ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/መ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ

"ወይቤሎ መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ ሑር ወትልዎ ለዝንቱ ሠረገላ ወሮጸ ፊልጶስ ወበጽሐ ወስምዖ ያነብብ መጽሐፈ ኢሳይያስ ነቢይ ወይቤሎ ፊልጶስ ተአምርኑ እንከ ዘታነብብ፡፡ ወይቤሎ ኀፅው በአይቴ አአምር ለእመአልቦ ዘመሀረኒ"፡፡

"መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን ይህን ሠረገላ ሂድና ተከተለው አለው፡፡ ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማውና በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን አለው ጀንደረባውም የሚያስተምረኝ ሳይኖር ይህ እንዴት አውቀዋለሁ አለው፡፡" (የሐዋ.ሥራ ም.8፥29-32)

እኛም ሆነ ሌላው የክርስትና ዓለም እንደሚያውቀው ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ የታወቀች ሀገር እንደሆነች ብዙ ነቢያት በትንቢታቸው አንስተዋታል፡፡ በጽሑፋቸውም በብዕራቸው ደጋግመው ቀልመዉታል፡፡

ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ45 ጊዜ በላይ ስምዋ የተጠቀሰ ሲሆን ከክርስትና እምነት በፊት ማለትም በብሉይ ኪዳን ዘመን በአንድ አምላክ ታምን እንደ ነበረ በብዙ ቦታ ተጠቅሳለች፡፡ በተለይ ከ1013 - 982 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረችው የኢትዮጵያ ንግሥት ማክዳ /ንግስተ ሳባ/ የሰሎሞንን ጥበብና ዜና ለማየት በዘመኑ የነበረው የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለማስተዋወቅ የብሉይ ኪዳንንም እምነትና ሥርዓትን ትምህርቱን ከመሠረቱ ለመረዳት ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መሄድዋን በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕ.10 ቁ.1-12፡፡ በዜና መዋዕል ካልእ.ምዕ.9 ቁ.1‐12 ተመዝግቦ ስለሚገኝ የታሪክ እውነትነቱን ያረጋግጧል፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም ለኢትዮጵያ ንግሥት ማክዳ የወደደችውን ሁሉ እንደሰጣት መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ምሥጢረ ሥጋዌ፤

ምሥጢረ ሥጋዌ የሚባለው ትምህርተ ሃይማኖት፤ ቃል ሥጋ ኾነ ብለን የምናምነው እምነት፤ ቃል ሥጋ ኾነ ብለን የምንማረው ትምህርት ነው፡፡ በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት እናምናለን በአብ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ ባንድ አምላክ በማለት እምነታችንን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
በምሥጢረ ሥጋዌ እምነታችንንም እንደሚቀጥለው /በሚቀጥለው/ እንማራለን፡፡ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ለአድኅኖተ አዳም /ለአድኅኖተ ዓለም/ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም በግብረ- መንፈስ ቅዱስ ነፍስንና ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ኾነ፣ ሰው እንደኾነ እናምናለን፡፡ (ዮሐ. 1፡14፤ ዕብ. 2፡14-15፣ 1ጢሞ. 2፡6)

 • "ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ-መድኃኒትነ ወረዶ እምሰማያት ተሰብአ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም /እማርያም/ እም-ቅድስት ድንግል" በማለት አብራርተዋል፡፡ (ሠለስቱ ምእትም ጸሎተ-ሃይማኖት)፡፡ ሰው የኾነበትም ዕለት መጋቢተ 29 እሑድ ዕለት ነው፡፡

ማስገንዘቢያ፡-

ሰው ሆነ ያልነው ወልድ፣ ዮሐንስ ወንጌላዊ "ቃል ሥጋ ኮነ" ያለው አካላዊ ቃል ነው፡፡ አካላዊ ቃል ወልድ ሰው ሲሆን ሳለ መለኮቱ እና ትስብእቱ /ሰውነቱ/ አንድ አካል አንድ ባህርይ ሁኗል፡፡ ሁለት አካል፣ ሁለት ባሕርይ አይባልም ወይም አንድ አካል ሁለት ባህርይ አይባልም፡፡ ምንታዌ የለበትም፣ በተዋሕዶ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ሁኗል ወልደ አብ ወልደ ማርያም ነው፡፡
አካላዊ ቃል ወልድ ሰው ሆኖ መዋዕለ ፅንስ ዘጠኝ ወር ካምሥት ቀን በማህጸነ ማርያም ኖረና ታሕሣሥ ሃያ ዘጠኝ ዕለት ሌሊት ለሃያ ዘጠኝ ቀን አጥቢያ ተወለደ፣ የተወለደበት ቦታ በምድረ እስራኤል የዳዊት ከተማ ቤተልሔም ይባላል፡፡ (ሉቃ. 2፡4-7 ፤ ማቴ.2፡1)

 • አካላዊ ቃል ወልድ በሥጋ ሲወለድ በተወለደበት ቦታ በቤተልሔም ላይ ከሰማይ ብርሃን ወርዷል፡፡

 • የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከብት ሲጠብቁ ላደሩ እረኞች መድኅን ክርስቶስ እንደተወለደ አብሥሯቸዋል፡፡

 • ብዙ መላእክትም ከሰማይ ወርደው "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ" እያሉ በዜማ ለእግዚአብሔር ክብር አቅርበዋል፡፡

 • በልደተ ክርስቶስ የሰው ምኞት የነበረ ሰላም መሆኑን /መፈጸሙን/ አብሥረዋል /ሉቃ.2፡8-14/፡፡

 • ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ሰብአ-ሰገል ከምሥራቅ አገር መጥተው ሰግደውለታል፤ ለክብሩ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ አቅርበውለታል፡፡ /ማቴ. 2፡1-2 ፤ ቁጥር 11/

 

ክፍል ሁለት

አእማደ ምስጢር

በብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ሊቀ ጳጳስ
"ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን" ከሚል ለሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ማስተማርያ እንዲሆን አዘጋጅተው ለሰ/ት/ማደራጃ መምሪያ ከሰጡት መጽሐፍ በከፊል የተወሰደ ትምህርት

 • ምሥጢረ ሥላሴ በአማርኛ የሦስትነት ምሥጢር

የቃሉ ሐሳብ አገላለጽ ምሥጢረ ሥላሴ ስንል ሦስትነት የሚነገርበት ምሥጢር ማለታችን ነው፡፡ ይኸውም በሦስቱም ሰው "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ" ያለ ሁኔታ ነው፡፡ ሥላሴ የሚለው ቃል ሦስትነትን እንጂ አንድነትን አይጠቁምም ጥሬ ቃሉ ቢሆንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሦስትነት ያለአንድነት /አንድነት አልባ/ አንድነት ያለሦስትነት /ሦስትነት አልባ/ የለም፡፡ ጥቅስ "ሥላሴ በተዋህዶ ወተዋህዶ በሥላሴ" እንዳለ ሃይማኖተ አበው፡ እመልእክተ ሲኖዲቆን ዘአባ ፈላታኦስ ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ኀበ አትናቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት ዘአንጾኪያ፡ ክፍል 2፡ በእትሙ መጽሐፍለ፡ ገጽ. 472/ ስለዚህ ምሥጢረ ሥላሴ ሲባል አንድነትና ሦስትነት የሚነገርበት ምሥጢር ለማለት ነው ሐሳቡ፡፡
ምሥጢር መባሉ በአእምሮ ብቻ ይታያል /ይታወቃል/ እንጂ እንደ ቀለም በዓይነ ሥጋ አይታይምና ነው፡፡ ምሥጢርም ማለት የማይታይ ረቂቅ፣ ኅቡእ ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ሥላሴ በሚለው ርእሰ ነገር ፈንታ ነገረ ትሥልስት ወተዋሕዶ የሚል አርእስትም ይገኛል፡፡ ሐሳቡ አንድ ነው ባማርኛ የሦስትነትና የአንድነት ነገር ማለት ነው፡፡
ሁለተኛ ትርጓሜ ሥላሴ የሚለው ጥሬ ቃል ከመሆኑ ሌላ ማለት ሦስትነት ከመባሉ ሌላ ሦስቱን አካላት አብን ወልድን መንፈስ ቅዱስን ይጠቁማል፡፡ የሦስቱ አካላት ስም ሆኖ ይነገራል፡፡ ጥቅስ

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ክፍል አንድ
ትምህርተ ሃይማኖት
በብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ሊቀ ጳጳስ

"ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን" ከሚል ለሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ማስተማርያ እንዲሆን አዘጋጅተው ለሰ/ት/ማደራጃ መምሪያ ከሰጡት መጽሐፍ በከፊል የተወሰደ ትምህርት

ሃይማኖት፡-

 • ለዓለም ፈጣሪ አለው ብሎ የሚያምኑት እምነት ነው

 • ለዓለም ፈጣሪ አለው ብሎ የሚመሰክሩት ቃል ነው

 • መሠረተ ነገሩ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፤ "እግዚአብሔር በመልካችንና በምሳሌአችን ሰውን እንፍጠር አለ፡- እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረ" የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው፡፡ /ዘፍ.፩፡፩ እና ፳፮‐፳፯/

ለሃይማኖት አመሠራረት ታሪክ አንፈልግለትም ማለትም ሃይማኖትን ማን ጀመረው? እንዴት እንዴት ተጀመረ? በምን ምክንያት ተጀመረ? መቼስ ተጀመረ? ብለን አንጠይቅም ለጥያቄውም በአንጻሩ ማለት በትይይው በተመሳሳዩ መልስ አንፈልግም፤ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር ፍጥረታቱን ሲፈጥር ለፍጥረቱ ራሱን ገልጿልና፣ በፍጥረቱም ታውቋልና፡፡ /ዘፍ.፩፡፳፯‐፴/ ዘፍ.፪፡፲፭‐፲፯፤ዘፍ.፫፡፱‐፲፫፣ መዝ.፲፱፡፩‐፪፣ የሐዋ.፲፬፡፲፯፤ም.፲፯፡፳፮‐፳፰፣ ሮሜ.፩፡፳‐፳፩፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም የመድኃኔዓለም በዓለ ንግሥን በማስመልከት ብፁዕ አቡነ ገሪማ ያስተማሩት ትምህርት:

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በብፁዕ አቡነ ገሪማ ዶክተር

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትየውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትፕሬዝዳንት ቢሮ ዋና ጸሐፊና

የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

"እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም፡ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር"

እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ በማዕከለ ምድር ቀራንዮ ኢየሩሳሌም ተሰቅሎ ባፈሰሰው ደሙ መድኃኒትን አደረገ ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት /መዝ. 73፡12/

ይህ በመጋቢትና በጥቅምት 27 ቀን በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት የምናከብረው በዐላችን ዓመተ ፍዳው፤ ዓመተ ኲነኔው አክትሞ የሰው ዘር የሆነው ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከኃጢአት ወደ ስርየት፣ ከሲኦል ወደገነት፣ የተመለሰበትና የተሸጋገረበት ዕለት መሆኑን ለማዘከር ነው፡፡

አዳም በሥላሴ አርአያና አምሳል ተፈጥሮ ጸጋ እግዚአብሔርን ተጎናጽፎ ነጻ የኅሊና ፈቃድ ያለው ሰው ሁሉ ገነትን ያህል ቦታ ይዞ ሥዩመ እግዚአብሔር፡ ነቢየ እግዚአብሔር፣ ካህነ እግዚአብሔር ሁኖ ለሰባት ዓመታት በስነ ሥርዓት በገነት ይኖር ነበር፣ ይሁንና እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም እጅግ መልካም ሆነ /ዘፍ. 1፡31/ ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደምንረዳው እግዚአብሔር አምላካችን በስድስቱ ቀናት የፈጠረው ሁሉ መልካም ሲሆን በተለይም በሥላሴ አርአያና አምሳል ለተፈጠረው ሰው የሕይወት እስትንፋስን ሰጥቶ በገነት በሕያውነት እንዲኖር ያስቀመጠው የከበረ ክቡር ፍጡር ነበር፡፡

 • "ሰብእሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ ወኮነ ከመ እንስሳ ዘአልቦ ልብ ወተመሰሎሙ ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት፡፡

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ የስሙ ቀዳሽ የክብሩ ወራሽ አድርጎ ቢፈጥረውና የጸጋ ገዥ ቢያደርገው ያልተሰጠውን የባህርይ አምላክነትን በመፈለጉ የገዥና የተገዥ፣ የፈጣሪና የፍጡር መለያ የሆነውን ትእዛዘ እግዚአብሔርን በመጣሱ በዚህ ምክንያት ሞተ ሥጋ፣ ሞተ ነፍስ ተፈረደበት፡፡ ከክብሩ ተዋርዶ ከገነት እንዲወጣ ተደረገ፡፡ ተመልሶ ወደገነት ገብቶ ተጨማሪ ኃጢአትን እንዳይሠራም ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍ ሜሎስን በእጃቸው የያዙ ኪሩቤልን በኤደን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ ይላል የሙሴ መጽሐፍ፡፡ /ዘፍ. 3፡22-24/

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ወርሐ ጽጌ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

የእመቤታችን ስደትና የደብረ ቁስቋም አጭር ታሪክ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA IN PHILO)

saintmary"ጽጌ አስተርአየ ሰሪፆ እምአጽሙ

ለዘአምሀኪ ጽጌ ለገብርኤል በይነ ሰላሙ

ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሀወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ

ለተአምርኪ አሀሊ እሙ

ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ"

ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ክርስቲያናዊ ትውፊታዋን ጠብቃ፣ መንፈሳዊ አገልግሎቷን በሚገባ አራቅቃ፣ ዘመንን በክፍል በክፍል ቀምራ፤ ከመስከረም ጀምሮ እስከ ጳጉሜን ድረስ ያሉት ሰንበታት የራሳቸው የሆነ ከምሥጢረ ድህነት ጋር የተያያዘ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስያሜ ሰጥታ የሰው ልጆችን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ለማዳን የተደረገው (የተፈጸመው) አምላካዊ የድኅነት ጉዞ እያዘከረች፣ እያስተማረች... ለዘመናት ቆይታለች፣ አሁንም በማስተማር ላይ ናት፤ ለወደፊትም እግዚአብሔር እስከ ፈቀደላት ጊዜ ድረስ ስትመሰክር ትኖራለች፡፡ በምሥጢረ ድኅነት ውስጥ ወላዲተ አምለክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትልቅ ድርሻ ያለት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ይኸውም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ተወልዶ በግርግም ከተኛበት ጊዜ አንስቶ በዮሴፍና በኒቆዲሞስ አማካኝነት ከመስቀል ወርዶ ወደ መቃብር እስኪወርድ ድረስ ከዚያም አልፎ ከትንሣኤው እስከ ዕርገቱ ድረስ ከጌታ እግር ሥር ሳትለይ በነገረ ድኀነት ውስጥ የማይናቅ ሱታፌ በማድረጓ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን በተለየ ፍቅር ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች (መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን) በሆነ ክብር በማክበር እመቤታችንን ታመሰግናለች፣ ታከብራለች፣ ትወድሳለች፣ ትቀድሳለች፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም

መ/ር ንዋይ ካሣሁን

የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ

የትምህርት ክፍል ኃላፊ (BTH,BSN)

ልዑል እግዚአብሔር ሰውንና መላእክትን የስሙ ቀዳሾች የክብሩ ወራሾች እንዲሆኑ ለዘለአለም ክብር ቢፈጥራቸውም ከመላእክት ወገን ዲያብሎስና ሠራዊቱ በክህደታቸውና በትዕቢታቸው ያልተሰጣቸውን ክብር በመሻታቸው ከክብራቸው ተዋርደው ወዳሲኦል ወረዱ፡፡ ለክብሩ የተፈጠረውም ሰው የምድር ንጉሥ መሆኑ አልበቃ ብሎት አምላክነትን ሲሻ በዕፅ ምክንያት ከክብሩ ተዋረደ፡፡ የመጀመርያዎቹ ሰዎች አዳምና ሔዋን እንደ አጋንንት በስሕተታቸውና በትዕቢታቸው ስላልጸኑ በደረሰባቸው ቅጣት ደንግጠው ንሥሐ ቢገቡ የምህረት ቃል ኪዳን ተስፋ አገኙ፡፡ ዘፍ. 3፡22

እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ድህነተ ዓለምን ለነቢያት እየገለጸ ትንቢት እያናገረ ሱባዔ እያስቆጠረ ምሳሌ እያስመሰለ ካስረዳ በኋላ ጊዜው ሲደርስ የተጠበቀው መድኅን በቤተልሔም ከድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ገላ. 4፡4 ከዚህም ጀምሮ ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔ አብቅቶ ዓመተ ምህረት ዘመነ ሰላም ተጀመረ፡፡ ጨለማው ተገፎ የጽድቅ ፀሐይ ወጣ በድንቁርና በቀቢስ ተስፋ የነበረው ሕዝብ ተስፋው ለመለመ የመዳኛው ቀን ቀረበ፡፡ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ሰውን ለማዳን ሰው ሆኗልና መላእክትና እረኞች በአንድነት ዘመሩ፡፡ ሉቃ. 2፡15

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ