Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የትንቢት ቀጠሮ

ከመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ም/ኃላፊ

birthofchrist1. ስለ መሲሑ የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድና የበዓሉ አከባበር፤

ዝርዝር ሐተታ ከመሄዳችን በፊት ገና ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙ እነሆ፡፡ ገና ማለት ከጽርዕ /ግሪክ/ ቋንቋ የተወረሰ ነው፡፡ ትርጉሙም ልደት ማለት ነው፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ አዳም አባታችን ወዶ በሠራው ኃጢአት ምክንያት የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት ጊዜ ድረስ ዓለም በጨለማ ጒዞ ይጓዝ ነበር፡፡ /ኢሳ. 9፡2/

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ ግን በጨለማ ጥላ ሥር ይንከራተትና ፍዳውን ይቈጥር ይኖር የነበረ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ ተስፋ ያልነበረው ሕዝብ የተስፋ ባለቤት ሆነ፣ የጨለማና የኀዘን የሥቃይ፣ የፍዳ፣ የገፊና የተገፊ መናኸሪያ የነበረው አሮጌው ዓለም በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ዓለም ሆኗል፡፡ /ኢሳ. 9፡2፣ ሮሜ.13፡12/

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ታህሳስ 3 ቀን በዓታ ለማርያም ድንግል

"ሰአሉ ወይትወሀበክሙ ለምኑ ይሰጣችሁማል ማቴ 7፡7"

አባ ሳሙኤል ወ/ሐዋርያት

ኢያቄም እና ሐና አንድ ወንድ አንድ ሴት በሚለው በተከበረው ጋብቻ የጸኑ በሀገራቸው የተከበሩ፤ በመልካም ሥነ ምግባር የታወቁ ሰዎች ነበሩ በእግዚአብሔር ፊትም እውነተኞች ነበሩ ትእዛዙም ሁሉ ይፈጽሙ ነበር ይሁን እንጂ በዚህ በተከበረ ጋብቻ ጸንተውና ተወስነው እያሉ ነገር ግን እንደሌሎች ሰዎች ወልደው የሚሰሙት አይቶው የሚደሰቱበት ልጅ ባለማግኘታቸው እጅግ ያዝኑና ይተክዙ ነበር፡፡ በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርንም ይጠይቁ ነበር፡፡ ስዕለትም ይሳሉ ነበር ስዕለታቸውም ወንድ ልጅ ብንወልድ እርሱ ወጥቶ ወርዶ ያበላናል አንልም ያንተ ቤት ቤተ እግዚአብሔር ያገለግላል እንጂ ሴትም ብትሆን ጋግራ ታብላን ፊትላ ታልብሰን አንልም ሀርና ወርቅ እየፈተለች መሶበ ወርቅ እየሰፋች ቤተክርሲያን ታገለግላለች እንጂ ብለው ተሳሉ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ልጄን ከግብጽ ጠራሁት (ካለፈው የቀጠለ...)

ጉዞ ወደ ምድረ ግብፅ

በመ/ር ንዋይ ካሳሁን

የማደራጃ መምሪያው ትምህርት ክፍል

(BTH,BscN

እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ምድረ ግብፅ ሲጓዙ ሦስት ቀን ጫካ ውስጥ ሰነበቱ፡፡ በጣም ተራቡ፣ ተጠሙ፡፡ በበረሃ በረሃብና በውሃ ጥም እንዳይሞቱ እመቤታችን ጸለየች፡፡ ወዲያው የተሠራ ማዕድ /የተዘጋጀ መግብ/ መጣላቸው በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢንፍሎን ወደተባለ አገር ሄዱና ርግባዳ ከተባለ ሰው ቤት ተቀመጡ፡፡ ብዙ ሰዎች ዕውቀት ፈልገው ወደ እመቤታችን ይመጡ ነበር፡፡ እመቤታችን ከጥበበኞች ከእስራኤል አገር ስለመጣች ብዙ ጥያቄዎችን ይጠይቋት ነበር፡፡ እመቤታችን ብዙ ምሳሌ እየመሰለች ጥያቄዎቻቸውን ስትመልስላቸው እያደነቁ ይሄዱ ነበር፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ልጄን ከግብጽ ጠራሁት (ት.ሆሴዕ 11፡1)

ካለፈው የቀጠለ...

በመ/ር ንዋይ ካሳሁን

የማደራጃ መምሪያው ትምህርት ክፍል

(BTH,BscN)

ከዚህ በፊት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደት በማስመልከት ምክንያት ስደቷንና ተያያዥ ርዕሶችን ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጽሁፌ ደግሞ እመቤታችን በስደቷ ወቅት ብዙ ውጣ ውረድ ያሳለፈች ሲሆን ከብዙው በጥቂቱ ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ክስተቶች እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መደረጃዎችን ከነ ሙሉ ክስተታቶች ለማስነበብ እሞክራለሁ፡፡

የሄሮድስ ቁጣና የሕፃናት ሞት

ሄሮድስ ሰብአሰገል እንደተሳለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአሰገል እንደተረዳው ዘመን በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ፡፡ ማቴ. 2፡16-18 ሰብአሰገል ወደ እርሱ ባለመመለሳቸው የተበሳጨው ሄሮድስ የራሱን እርምጃ ለመውሰድ ወሰነ፡፡ ምንጊዜም ሄሮድስ የሚፈልገው በቤተልሔም የተወለደ ውን የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ሕፃን ክርስቶስን አግኝቶ መግደል ነው፡፡ ከሰብአሰገል መረጃን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ ስለሆነም ሕፃኑ ክርስቶስ ያለበትን ቦታ የሚጠቁም ሰው አላገኘም፡፡ ትክክለኛውን መረጃ ባያገኝም ከሰብአሰገል አንደበት የሰማውን ለእንቅስቃሴው መነሻ አድርጎ ተነሣ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ልጄን ከግብፅ ጠራሁት

ት.ሆሴዕ 11፡1

መምህር ንዋይ ካሳሁን (BTH, BSEN)

የማደራጃ መምሪያው ትምህርት ክፍል ኃላፊ

የብኤሪ ልጅ ነቢዩ ሆሴዕ ይህንን የትንቢት ቃል የተናገረው ከክርሰቶስ ልደት በፊት በስምንተኛው ምእተ ዓመት አጋማሽ ገደማ ሲሆን ሆሴዕ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪኳ ከተዘረዘሩላት ሀገሮች መካከል ግብጽ አንዷ ስትሆን ግብጽ የብዙኀን አባት አብርሃም በረሃብ ምክንያት የተሰደደባት፣ ዮሴፍ በባርነት የተሸጠባት፣ ወገኖቹ እስራኤላውያን ለሁለት መቶ አስራ አምስት ዓመታት ያህል በባርነት የተገዙባት በኋላም የአለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ድንግል ማርያም ጋር የተሰደደባት ሀገር ስትሆን መሪዎቿም አህዛብ አማልዕክቷም ጣኦታት ነበሩ፡፡ ነቢዩ ሆሴዕ የጌታችንን ሥደት ቀድሞ በትንቢት ከተናገሩት ውስጥ ሲሆን ልጄን ከግብፅ ጠራሁት በማለት የስደቱን ማብቃት ተናግሯል፡፡ በዚህ ትንቢት መሰረት መሰደዱን አልተነበየም፡፡ ነገር ግን ከስደት መመለሱን መናገሩ ካልተሰደደ መመለስ የለም በመመለሱ መሰደዱን ተናገረ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን እና የልጇን ስደት በማሰብ ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር 6 ያለውን ግዜ ወርኃ ጽጌ በማለት ታከብረዋለች፡፡ ጽጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ምድሪቱ በአበባ የምትሞላበት ጊዜ ከመሆኑም በላይ አበው ሊቃውንት እመቤታችንን በብዙ ኅብር መስለዋታል፡፡ በአበባ /ጽጌ/፣ በወይን ሐረግ፣መልካሙን የወይን ፍሬ አስገኝታለችና አበባ ፍሬን እንዲያስገኝ ድንግል ማርያምም ለሰው ያልተቻለውንና የማይቻለውን አንዴ ብቻ የሆነውን መለኮትን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት በማህፀንዋ ተወሰነ፡፡ አዳምና ልጆቹ እንዳይበላ በተከለከለችዋ ፍሬ ምክንያት ገነትን ከሚመስል ቦታ እግዚአብሔርን ከሚያክል ጌታ ተለዩ የሰዎች ድቀት ተጀመረ ሁሉን አጣ የመጀመሪያ በደል /ጥንተ አብሶ/ ማለት ይህ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የመለየትን ረጅም ግዜ ገፋ ገዥ የነበረው የሰው ልጅ ተፈጥሮ ሰለጠነበት፣ ጠላት በዛበት፣ ምድሪቱን ከፋችበት አዳምም ባለቀሰው መሪር እንባ ተስፋ ተሰጠው የህይወት ፍሬንም ዳግም እንዳይበላ በሱራፊ ታጠረችበት፡፡ ይህም የሚያመላክተው ሞትን የምታመጣ ዕፀ በለስን የበላ አዳም ደግሞ ዕፀ ህይወት ቢበላ ኖሮ ካሳ የማያስፈልገው ኢመዋቲ (immortal sinner) እንዳይሆን የእግዚአብሔር ቸርነት ከለከለችው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የመንፈስ ፍሬዎች 9ኛ (ራስን መግዛት)

በመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሣኤ

በመንፈስ የሚኖር ሁሉ የመንፈሳዊ ሕይወት ፍሬ የሆነው ራስን መግዛት ይኖረዋል፡፡ ታዲያ ራስን መግዛት ምንድን ነው? ከውስጣችን ሊወጣ የሚታገለንን ማናቸውንም የስጋ ፍላጎትና ምኞትን መቆጣጠርና መግዛት ራስን መግዛት ይባላል፡፡ ለቁጣ፣ ለቂም ለበቀል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለስካር ወዘተ... በውስጣችን የሚሰማንን ግፊት በእግዚአብሔር ቃልና በመንፈስ ቅዱስ ሆነን ልንቆጣጠር ያስፈልገናል፡፡

ራሳችንን ለመግዛት የምንችለው እንዴት ነው?

1. ለበጎ እንኳን ዝም እስከማለት ድረስ የሌላውን ቁጣ በትዕግስት በማሳለፍ ያዕ.1፡19 ፤ 2ሳሙ. 16፡5 ፤ መዝ. 38፡1

2. በጾምና በጸሎት ስጋችንን በመስገዛት መዝ. 108፡24 ፤ ሉቃ. 2፡37 ፤ 2ቆሮ. 6፡6

3. በአርምሞና ራስን ለተወሰነ ጊዜ ከሰዎች በመሰወር ሉቃ. 1፣25 ፤ ገላ. 1፡15

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጴላጦስና በሄሮድስ ፊት ተከሶ በቀረበ ጊዜ ያ ሁሉ የሐሰት ክስና ስድብ ሲደርስበት በዝምታ ማየቱ ራስን መግዛት እንዴት እንደሆነ ለማስረዳትና ለማስተማር ነው፡፡ ሉቃ. 23፡1

ቅዱስ ጳውሎስ በፊልክስ ፊት ተከሶ በቀረበ ጊዜ ራስን ስለመግዛት ተናግሮአል፡፡ ሐዋ. 24፡25 . . .

 በተጨማሪ ያንብቡ…

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

በመምህር ንዋይ ካሣሁን

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ

ትምህርት ክፍል ኃላፊ

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለዓለምም ሆነ ለሀገራችን ፈርጀ ብዙ በሆነ መንፈሳዊ እንዲሁም ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው የስልጣኔ በር ከፋች የሆኑ አባቶች የነበሯትና አሁንም ያሏት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ከነዚህ ታላላቅ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሥነፅሑፍ እድገት ሲሆን ብዙ ጉልህ ድርሻ ካበረከቱት አባቶችም አንዱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የዜማ ሊቅ ከሆነው ታላቁ ቅዱስ ያሬድ ካበረከተው የዜማ ሥርዓት ባልተናነሰ መልኩ በሥነ ጽሑፍ ረገድ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቀዳሚ ከሆኑት ውስጥ ይጠቀሳል፡፡ በዚህም ቤተክርስቲያንን በስነ ጽሑፍ ከመጀመርያዎቹ ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል፡፡

የቀደሙት ሊቃውንት በስራዎቻቸውና በጽሑፎቻቸው ልንከፍላቸው ብንሞክር የቃል ሊቃውንት እና የጽሑፍ ሊቃውንት በማለት እንከፍላቸዋለን፡፡ በዘመናቸው የክርስትና ትምህርትን ተቃውመው የተነሱትን አጽራረ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ጽፈው፣ በአንደበት ተናግረው የረቱ ሊቃውንትን የጽሑፍ ሊቃውንት ሲባሉ መጽሐፍቶቻቸው ትናንትናን አልፈው ዛሬም ይገስጻሉ ያስተምራሉ፡፡

የወርቃማው ዘመን አባት ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የህይወት ታሪኩንና የሥነ ጽሑፍ ስራውን እጅግ ባጠረ መልኩ ለማስነበብ እንወዳለን፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

"በዓለ ደብረ ታቦር በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን"

በመምህር ሙሴ ኃይሉ /B.TH, MA in Philo/

 • "ታቦር ወኤርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ"

መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት

 • "እግዚኦ እግዚእ ሠናይ ለነ ሀልዎ ዝየ፡-ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው"

ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ

"ደብረ ታቦር" የሁለት ቃላት ጥምር ገጸ ንባብ ስለሆነ የቋንቋ ሊቃውንቱ ለእያንዳንዱ ቃል የሚሰጡትን ትንታኔ በማስቀደም እንመልከት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደብርን ሲተረጉሙ፡-

ደብር፡- ተራራ፣ ጋራ ገምገም፣ የምድር ዕንብርት ጉብር፣ ታላቅ ረዥም ከወግር የሚበልጥ፣ ደብረ ዘይት፣ ደብረ ሲና፣ ደብረ ታቦር፡፡ አድባረ እስራኤል /ሕዝ. 6፡2/

 • የተራራ ተራራ፣ ከተራራ ሁሉ የሚበልጥ በረዶ የሚፈላበት ሰው የማይደርስበት እንደ ዳሽን፣ እንደ ሄርሞን ያለ የሰማይ ጎረቤት፡፡ አድባረ አራራት፤ አድባረ ነዋኋት ዘመትሕተ ሰማይ /ኩፋ. 8፤ ዘፍ. 7፡19 ፤ 8፡4/
 • ወሰን ድንበር መዲና ከተማ ታላቅ ሀገረ፡- ወኮነ አድባሪሆሙ ለከነዓን እምነ ሲዶን እስከ ጌራራ፣ ደብረ አህጉር ዲበ ኩሉ አድባሪከ፡፡ አድባረ ግብጽ /ዘፍ.10፡19፤ ኢያ. 14፡15 ፤ ዘፀ. 10፡4 ፤ ኢሳ. 1፡26/
 • ገዳም ቤተክርስቲያን፣ ታላቁም ታናሹም ደብረ ሊባኖስ፤ ደብረ ዐስቦ፤ አድባራት ወገዳማት አባ መቃርስ ዘደብረ አስቄጥስ ወዳልወ አልባብ ተሰምየት እስከ ዮም ደብሩ.../ገድለ ተክለሃይማኖት፤ ስንክሳር ዘመጋቢት 27/
 • ደብር ማለት በተራራ ላይ የሚሠራ ተራራ የሚያህል ታላቅ ማለት ነው፡፡ ... በማለት መጽሐፋዊ ማረጋገጫዎችን አስደግፈው ሐተታ ጨምር ትርጉም ሰጥተውታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ /አለቃ/፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡ 1948ዓ.ም፡ አዲስ አበባ፡ ገጽ. ከ336-337 ይመልከቱ)

በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ