Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት

ሀልዎተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መኖር)

ካለፈው የቀጠለ (ክፍል 3)

ከሊቃውንት ጉባኤ

ምሉእነት፡- ዓለማትን የፈጠረ እግዚአብሔር በቦታ አይወሰንም፡፡ በየትም ቦታ አለ፣ ምንም እንኳ ስለ ልዕልናው በሰማይ እንደሚኖር ቢናገርም በሰማይ ብቻ አይወሰንም፡፡ በሁሉም ቦታ ይገኛል፣ የእርሱ ያልሆነ እርሱም የሌለበት የለምና "ምድር በመላዋ የእግዚአብሔር ናት ዓለምም በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ" በማለት ነቢዩ ዳዊት እንደተናግረ መዝ 23:1፡፡ በተጨማሪም "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደጥልቁም ብወርድ አንተ በዚያ አለህ፤ እንደንስርም ክንፍን ብወስድ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር በዚያ እጅህ ትመራኛለች፣ ቀኝህም ታኖረኛለች" ብሎ እግዚአብሔር በዓለም ምሉእ እንደሆነ እርሱም የሌለበት ዓለም እንደሌለ ተናግሮአል (መዝ 138: 1-10) ፡፡ ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም "ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለን" ብሏል፡፡ኤፌ 4:6 ፤

ዮሐንስ ወልደ ነጐደጓድም "ኵሉ እምኔከ ወኵሉ ብከ ወኵሉ በእንቲአከ ወአንተ ውስተ ኵሉ ሀሎከ፡- ሁሉ ካንተ ነው፣ ሁሉም ባንተ ነው ሁሉም ስለ አንተ ነው አንተም በሁሉ አለህ ሲል የሆነው ሁሉ በእርሱ እንደሆነና እርሱም በሁሉ እንዳለ መስክሮአል፡፡ ቅዳሴ ወልደ ነጐድጓድ ቁ.6 ፤

በተጨማሪ ያንብቡ…

ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት
ሀልዎተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መኖር)
ካለፈው የቀጠለ
ከሊቃውንት ጉባኤ

 • ቅድስና፡-እግዚአብሔር አምላክ በባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ከክፋት፣ ከርኵሰት፣ ከኃጢአት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ በብሉይ ኪዳን እርሱ ራሱ ስለ ቅድስናው “እኔ ቅዱስ እንደሆንሁ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ”ሲል ለእስራኤል ዘሥጋ ተናግሮአል፡፡ (ዘሌ 19:2)

በሐዲስ ኪዳንም “ነገር ግን የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እንዲሁ እናንተም በአካሄዳችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ የሚል ተጽፎአልና” ብሎ የእግዚአብሔርን የባሕርይ ቅድስና ከመናገሩም ባሻገር ተከታዮቹ ሁሉ ቅዱሳን መሆን እንደሚገባቸው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ለእስራኤል ዘነፍስ ጽሕፏል፡፡ (1ጴጥ 1:15-17)

ምስጋናቸው ዕረፍታቸው ዕረፍታቸውም ምስጋናቸው የሆነ ሠራዊተ መለእክትም ያለዕረፍትና ያለመሰልቸት ከተፈጠሩበት ሰዓት ጀምሮ በባሕርዩ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሕርን ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ እያሉ ያመሰግኑታል፡፡ (ኢሳ 6:3 ራእ 4:8)

በተጨማሪ ያንብቡ…

የመንፈስ ፍሬ /6ኛ በጎነት/

ከመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሳኤ /ዘዲዮስቆሮስ/

በገላትያ ምዕራፍ 5ከተገለጹት የመንፈስ ፍሬዎች መካከል አንዱ በጎነት ነው፡፡ በጎነት ለሰዎች ያለን መልካም አመለካከትና የምናደርገው ማንኛውም መልካም ሥራ ሁሉ ነው፡፡ በጎነት ማንኛውንም መልካምና ጥሩ፣ የበጀ የተወደደ፣ ሥራን ያካትታል አምላካችን እግዚአብሔር በባሕርዩና በሥራው በፈጠረው ፍጥረት መደነቁ ሁሉ የበጎነቱ አይነተኛ ምልክት ነው፡፡ ሁሉንም በየወገኑ በመፈጠሩ ማለቴ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በፍጥረቱ በጎነት ይታወቃል እንዳሉ አበው እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን በጎነት ሲባል ንጽጽራዊ በጎነት ማለት ነው፡፡ ፍፁም በጎነት የእግዚአብሔር ባሕርይ ብቻ ነው፡፡ “የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ” ማቴ. 5፡48 ተብሎ በጌታ ቃል ከተገለጸው ፍጹምነት ጋር ተመሳሳይ ነው ይህም ንጽጽራዊ ፍጹምነት ነው፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት
ሀልዎተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መኖር)

ከሊቃውንት ጉባኤ

እግዚአብሔር ማለት ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የዓለም ፈጣሪ፣ ሠራዒና መጋቢ ይባላል፡፡ የማይታይና የማይመረመር፤ ሁሉን ማድረግ የሚችል፤ ሁሉንም የፈጠረ፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ አምላክ… መኖሩና ራሱን ለሰው ልጆች እንደገለጠ በቅዱሳት መጻሕፍት ተረጋግጧል፡፡ (ዘፀ 3፡6)

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም” (ኢሳ 40፡6)

ዓለማትን የፈጠረ ዘለዓለማዊ አምላክ መኖሩን ከሚያስረዱን የአእምሮ ማስረጃዎች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሥነ-ፍጥረት፡-ይህ ዓለም በራሱ የተገኘና በራሱም የሚኖር ወይም ያለአስገኝ፣ ያለሠራዒና መጋቢ በራሱ የሚንቀሳቀስ ሥነ ፍጥረት አይደለም፣ ለተፈጥሮ አስገኝ ለኑሮው ሠራዒ፣ መጋቢ፣ ጠባቂ፣ ለጉዞውም መነሻና መድረሻ አለው፡፡
ይህ ዓለም ሠራዒና መጋቢ ተንከባካቢም ባይኖረው ብርሃናት እየተመላለሱ፣ ነፋሳት እየነፈሱ፣ ማያትና አፍላጋት እየፈሰሱ፣ መዓልትና ሌሊት በጋና ክረምት ጊዜያቸውንና ሰዓታቸውን ጠብቀው እየተፈራረቁ የሰው ልጅ ሲገለገልባቸውና ሲጠቀምባቸው የሚኖር ባልሆነም ነበር፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

5ኛ ቸርነት

ከመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሳኤ /ዘዲዮስቆሮስ/

 • መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ከመንፈስ ፍሬ መካከል አንዱ የሆነው ቸርነት ነው፡፡
 • ቸርነት ማለት በደግነት፣ በለጋስነት ካለን ነገር ለሌላው መስጠት መቻል ማለት ነው፡፡
 • በቈላ.3፡12 ላይ ከተዘረዘሩት መንፈሳዊ ልብሶች መካከል አንዱ ቸርነት ነው፡፡ ክርስቲያን በሚቻለው መጠን ለሰዎች ሁሉ ቸርነት ማድረግ አለበት፡፡

ቸርነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው

ሐዋርያው ስለጌታ ሲናገር “ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግስቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?”ሮሜ.2÷4ይላል፡፡ ይህም የሚያስረዳን እኛን ለሚታገስ የእግዚአብሔር ትዕግስት እና ወደ ንስሐ ስለሚመራን መልካምነቱ ነው፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

4ኛ ትዕግሥት

ከመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሳኤ /ዘዲዮስቆሮስ/

የቃሉ ትርጉም መተው፣ መቻል፣ ማለፍ፣ አይተው፣ ሰምተው፣ ደርሰው…

 • ትዕግስት የሚከተለውን ሐሳብ ያካትታል፡-

 • ትዕግስት አንድ ሰው የሚደርስበትን ተቃራኒ ነገሮች መቻልና እስኪያልፍ ድረስ ንቆ መተውን ያመለክታል 1ቆሮ፥4፡11

 • የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ለረጅም ጊዜ በተስፋ መጠባበቅም ትዕግስት ይባላል ሮሜ.8፡25

 • ሕግና ሥርዓትን የሚተላለፉ ሰዎችን እስኪመለሱ ድረስ በይቅርታ ማለፍ 2ጴጥ.3፥9

 • እግዚአብሔር በባሕርይው ታጋሽ አምላክ ነው፡፡ መዓቱ የራቀ ቁጣው የዘገየ መሆኑ ትዕግሥቱን ያመለክታል፡፡ ሰዎች ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ እንዳይጠፉ ይታገሳል ሮሜ.2፡4 ፤ ሮሜ.15፡5 1ጴጥ.3፡20

በተጨማሪ ያንብቡ…

 3ኛ. ሰላም

 በመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሳኤ

- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከገለጸው የመንፈስ ፍሬ ፍቅርን፣ ደስታንና ሰላምን አስቀድመን ተመልክተናል፡፡ አሁን ዳግም ወደ ሰላም እንሸጋገራለን፡፡
በቅድሚያ በቅዱስ መጽሐፍ በጸሎት እና በሕይወታችን ሰላም ያለውን አስፈላጊነት እና ጥቅም በመግለጽ እንጀምር፡፡ ሰላም በአጭሩ ለሰዎች ሕይወት በጣም አስፈላጊና የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡

 በመቀጠልም ስለሰላም ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን እንመልከት፡-

1. ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም እና ከእግዚአብሔር የሚገኝ ሰላም
2. ሰላም ከሰዎች ጋር
3. ከራስ ጋር የሚረግ በልብ ያለ ውስጣዊ ሰላም

በተጨማሪ ያንብቡ…

የመንፈስ ፍሬዎች

(2ኛ ደስታ)


                          ከመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሣኤ (ዘዲዮስቆርዮስ)

ደስታ በምናየውና በምንሰማው፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈጸሙ ክስተቶች የሚሰማን የህሊና እርካታ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ የርካታ ስሜት ነው፡፡ ደስታችንም የሚፈጸመው በዓለም ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ በተለየ መልኩ ነው፡፡ የክርስቲያኖች ልዩ ደስታ የሚሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዓምለካዊ ፍቅሩ ዓለምን በማዳኑ በሚሰማን ደስታ ነው፡፡ ይህም መልዐኩ ለእረኞች እንደነገራቸው “ታላቅ ደስታ” ተብሏል፡፡ ሉቃ. 2:፡10

ለጌታችን እናት ለድንግል ማርያምም ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት “ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ”ብሏታል ሉቃ.1፡28እርስዋም የጌታችን እናት ስለ ደስታ ስትናገር “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት /ደስታ/ ታደርጋለች”ብላለች ሉቃ.1፡47የባሕርይ አባቱ አብ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው፣ የመረጥኩት ልጅ ይህ ነው”ብሏል ማቴ 3፡17 ፣ 17፡5፡፡ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስና በፍቅሩ ሥራ ደስ ሊለን ይገባል፡፡

መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን ከሕዝቡ ካገናኘ በኋላ “እንግዲህ ደስታዬ ተፈጸመ” ብሏል ዮሐ. 3፡29፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰውን በደስታ እንዲኖር አድርጐ ነው የፈጠረው ሁሉንም ለሰው ልጅ ምቾት አዘጋጀለት፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ