Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት

መግቢያ

ከክርስትና በፊትም ሆነ በኋላ በኢትዮጵያና በሌሎች ዓለማት መካከል ሃይማኖት ነክ የሆኑ አያሌ የውጭ ግንኙነቶች ተካሂደዋል፡፡

በሥጋዊውም ሆነ በመንፈሳዊው የዓለም ታሪክ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምን ጊዜም የነበረና የሚኖር ክስተት ነው፡፡የግንኙነቱ ደረጃ የተለያየ ይሁን እንጂ መንፈሳዊውም ሆነ ሥጋዊው ዓለም በየራሱ ዓላማ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት አለው፡፡

የክርስትናው ዓለም በባህል በቋንቋ በአህጉር በተለያዩ ሕዝበ ክርስቲያን አንድነት ላይ የተመሠረቱ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙበት ሰፊ ዓለም ነው፡፡በመሆኑም በዚህ ሰፊ ዓለም ላይ ተራርቀው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የእርስ በርስ ትውውቅና ትብብር ሊኖር የሚችለው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ማድረግ ሲቻል ነው፡፡የውጭ ግንኙነት የሚባለውም ይህ ዓይነቱ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ነው፡፡በአሁኑ ጊዜ የዓለም ሕዝብ በየብስ፣በባህርና በአየር በሚደረገው ጉዞ እርስ በእርሱ እየተገናኘ ስለሆነ በዚያው አንጻር በአብያተ ክርስቲያናት መካከል የሚደረገውም የውጭ ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ ከምንግዜውም በላቀ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው፡፡በዚህም ግንኙነት አማካኝነት የሚደረገው የእርስ በእርስ ተራድኦ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም በዓለም ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት እንደመሆኗ ከራስዋ ውጭ ስለሌላው ማወቅም መስማትም የለብኝም በሚል በብቸኝነት ጠባይ ደጅዋን ዘግታ የተቀመጠች ቤተ ክርስቲያን አይደለችም፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ዛሬም እንደትናንቱ እኅት አብያተ ክርስቲያናት የሚያደርጉት ዓይነት የውጭ ግንኙነት ታደርጋለች፡፡ ከዘመነ ክርስትና በፊትም በሕገ ኦሪት አምልኮተ እግዘኢብሔርን በሚፈጽመው ሕዝበ እግዚአብሔር መካከል በኢየሩሳሌም ማዕከልነት ዓለም አቀፍ ግንኙነት ይካሄድ ነበር፡፡ኢትዮጵያም ከክርስቶስ ልደት በፊት ሕገ ኦሪትን ተቀብሎ አምልኮተ እግዚአብሔርን ለመፈጸም የበቃ ሕዝብ ሀገር ስለሆነች ከኢየሩሳሌም ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበራት የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያንም በሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል በቀጥታ የተሸጋገረ ሕዝብ ቤተ ክርስቲያን ስለሆነች ስለዚህች ቤተ ክርስቲያን ውጭ ግንኙነት ታሪክ ለመጻፍ ከዘመነ ብሉይ መነሳት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

1. የውጭ ግንኙነት ቅድመ ክርስትና

ኢትዮጵያ ከክርስትና በፊት የብሉይ ኪዳንን እምነት በመቀበል አምልኮተ እግዚአብሔርን ስትፈጽም የኖረች አገር በመሆንዋ በዚህ ምክንያት የእምነቱ ማዕከል ከሆነችው ከኢየሩሳሌም ጋር የነበረው ግንኙነት ለረዥም ዘመናት ሳይቋረጥ ኖሮአል፡፡የግንኙነቱ መሠረታዊ ምክንያት ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንድ ሺህ ዓመት አካባቢ የነበረችው የኢትዮጵያ ንግሥት (ንግሥተ ሳባ) የንጉሥ ሰሎሞንን ዝና በመስማት በኢየሩሳሌም ታሪካዊ ጉብኝት ለማድረግ የበቃችው ሴማዊውና ካማዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በህገ ልቦና ይፈጽመው የነበረውን አምልኮተ እግዚአብሔር በሕገ ኦሪት ለመፈጸም ወደሚችልበት የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር ነው፡፡ስለዚህ ኢትዮጵያ የመጻሕፍተ ኦሪት ባለቤትና መንበረ ታቦት ለመሆን የቻለችው በሃይማኖት ምክንያት በተደረገ የውጭ ግንኞነት ውጤት ነው፡፡ ሌዋውያን ካህናት መጻሕፍተ ኦሪትና ታቦተ ሕጉን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ የመጡበትም ሆነ የብሉይ ኪዳን ሕዝብ ናት፡፡ መታወቂያ የሆነው ሥርዓተ ግዝረትና ሥርዓተ ትምህርት (ይህን ብሉ ይህን አትብሉ) ማለት በኢትዮጵያ ሊስፋፋ የቻለው በተለይ ከንግሥተ ሳባ ጉብኝት በኋላ እየተደረገ በመጣው የውጭ ግንኙነት ምክንያት መሆኑ ግልጥ ነው፡፡

1.1 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት በዘመነ ክርስትና

እሥራኤላዊና የእሥራኤልን እምነት የተቀበለ ወንድ ልጅ ሁሉ በዓመት 3 ጊዜ የሚያከብራቸው እጅግ የተከበሩ በዐላት 3 ናቸው፡፡እነዚህም የቂጣ በዐል (በዐለ ናዕት) ከሰባት ሱባኤ በኋላ የሚከበረው በዐለ (በዐለ ሰዊት) የዳስ በዐል (በዐለ መጸለት) ናቸው እነዚህን በዐላት እሥራኤላዊ ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በመረጠው ቦታ ማለትም በእግዚአብሔር ቤት እየተገኘ ማክበር ግዴታው መሆኑን ህገ ኦሪቱ ያዛል ዘዳ 16.16 ይህን ሃይማኖታዊ ሕግ መሠረት በማድረግ ሕገ ኦሪትን የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እግዚአብሔር ወደመረጠው ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ በዐል ያከበሩ ነበር፡፡ይህ ዓይነቱ የውጭ ግንኙነት የዘመነ ብሉይ ኢትዮጵያን ብሉይ ኪዳንን በመቀበል ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አቻ አገር ለመሆን እንደአበቃት ሁሉ የዘመነ ሐዲስ ኢትዮጵያንም ሐዲስ ኪዳንን በመቀበል ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ የምትጠቀስ የክርስትና ሀገር ለመሆን አስችሎአታል፡፡

በንግሥት ማክዳ (ንግሥተ ኢትዮጵያ) የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ጉብኝት ውጤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍተ ብሉያት ባለቤትና መንበረ ታቦትም ለመሆን እንደቻለች ሁሉ የብሉይ ኪዳን እምነት ተከታይ በሆነችው በንግሥት ሕንደኬ (ንግሥተ ኢትዮጵያ) ከፍተኛ ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ጉብኝትም ኢትዮጵያ ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ የክርስትና እምነት ተቀባይ ሀገር ለመሆን በቅታለች፡፡

ይህ የታሪክ ቅድምና ሊገኝ የቻለው በመጽሀፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8.25 ላይ እንደሚነበበው ንግሥቲቱ ጃንደረባ ባከስ የኦሪቱን የፋሲካ በዓል እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ሲመለስ በመንፈስ ቅዱስ ቀስቃሽነት በወንጌላዊው ፊሊጶስ ስብከት የክርስትና እምነትን ተቀብሎና ተጠምቆ ወደ ሀገሩ የተመለሰው ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ገና ከኢየሩሳሌም ሳይወጡ በመሆኑ ነው፡፡የታወቀው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ጀሮም ስለዚህ ታሪክ ዕውንነት በየጽሑፋቸው ግልጽ ምስክርነት የሰጡበት ስለሆነ ይህ ታሪክ በመላው የክርስትና ዓለም የታወቀ ነው፡፡

1.2 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና ለመመሥረት የተደረገ የውጭ ግንኙነት

አስቀድሞ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው በመጀመሪያ ምእት ዓመት በ34 ዓ.ም ማለት በዘመነ ሐዋርያት ጥንተ ስብከት ሲሆን እምነቱ በኤጲስ ቆጶስ መሪነት የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ለመሆን የበቃውና የእምነቱንም ሥርዓት ምልዓት ያለው ለማድረግ የተቻለው በአራተኛው ምእት ዓመት (በ330) ላይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያኒቱ ኤጲስ ቆጶስ በትውልዱ ግሪካዊ በነዋሪነቱና በዜግነቱ ኢትዮጵያዊው የሆነው ፍሬምናጦስ በኋላ ከሣቴ ብርሃን ሰላማ የተባለው አባት ሲሆን ፍሬምናጦስ ለዚህ ጵጵስና የበቃውም በዘመኑ ለአከባቢው የክርስትና ማዕከል በነበረችው በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስት ቅዱስ አትናቴዎስ ነው፡፡ ፍሬምናጦስ ወደ እስክንድርያ የሄደው ቀደም ብሎ የክርስትናው እምነት ዜና በተሰበከላቸው ኢትዮጵያውያን ምእመናን ውሳኔ ነበር፡፡አባ ሰላማ ወደ እስክንድርያ ሄዶ ከዘመኑ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አትናቴዎስ ጋር እንደተገናኙና ስለ ክርስትናው እምነት መስፋፋትም እንዲነጋገር በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ መላኩ የሚያመላክተው ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ የዳበረ የውጭ ግንኙነት ልምድ የነበራት መሆኑን ነው፡፡

የተሰዐቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት

ዘጠኙ ቅዱሳን በመባል የሚታወቁት ቅዱሳን በጊዜው በነበረው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስለ ኢትዮጵያ መልካም ዜና በመስማት በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡የመጡትም ከቂሣርያ ከታናሿ ኢስያ፣ ከቂስጥንጥንያ፣ ከቂልቅያ፣ ከቆስያ፣ ከአንጾኪያ ነው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡበትንም ምክንያት የተወገዘውን የኬልቂዶኑን ጉባኤና ውሳኔውን አንቀበልም በማለታቸው በቢዘንታይን ነገሥታት ሥቃይ ስለጸናባቸው ነው የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝበ ክርስቲያንም የቅዱሳኑ እምነት በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ እምነት ጋር አንድ ሆኖ ስለተገኙት በፍቅር ተቀበሏቸው እነሱም በዓት አጽንተው እስከዛሬ ድረስ በስማቸው የሚጠሩትን ገዳማት አቅንተው ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን፣ሥርዓተ ገዳምና ምንኩስናን እያስተማሩ ኑረዋል፡፡የውጭ ግንኙነቱም መጠናከር ችሏል፡፡

በ15ኛው ክፍለ ዘመን ፍሎሬንስ ላይ በተደረገው ሃይማኖታዊ ጉባኤ በኢየሩሳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ተገኝቶ ነበር ጉባኤው የሌላውን ቤተ ክርስቲያን የበላይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አላማ የነበረው መሆኑ ስለታወቀ መልእክተኛውን በጉባኤው ላይ ድምጽ ሳይሰጥ በተመልካችነት ብቻ ተሳትፎ ተመልሶአል፡፡

በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በክርስትያን ኢትዮጵያና በክርስቲያን ፖርቱጋል መካከል በክርስቲያናዊ ተራድኦ ላይ ያተኮረ ግንኙነት ተደርጎ ነበር፡፡ሆኖም ግንኙነቱ የሌላውን እምነት ለማስፋፋት የታቀደ አላማ እንዳለው ስለተረጋገጠ እስከደም መፍሰስ በመድረስ ግንኙነቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

1.3 የ21ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ

በመጀመሪያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አዳኝ መሆኑን ማመንና በዚያም እምነት አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ የሚገባውን የክብርና የምሥጋና አቅርቦት ተልዕኮ በኅብረት መፈጸም መልካም ፈቃዳቸው የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ማህበር ነው፡፡ ድርጅቱ የተመሠረተው እ.አ በ1948 ዓ.ም በአምስተዳርም ነው፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሥራችና ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ አባል የሆነች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡

ዓላማው፡

ሀ. በአባል አብያተ ክርስቲያናት መካከል ሊኖር የሚገባውን የእርስ በርስ ተራድኦ ማጠናከር እንዲሁም ከመሰል አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለውን አንድነት ለመግለጽና ለማጠናከር የሥራ አፈጻጸም ልምድን ለመለዋወጥና ከሌላው የክርስትና ዓለም ጋር ሊኖር ስለሚገባው የግንኙነት ዓይነት ለመምከር

ለ. የራስዋን ማንነት ጥንታዊነትና ታሪካዊነት ለሌላው የክርስትና ዓለም ለማሳወቅ ስለሌላውም ምንነት በትክክል ለማወቅና ለመረዳት

ሐ በክርስትናው ዓለም ውስጥ አንዱን የሌላውን መንጋ ለመቀሰጥ የሚደረገውን ጥረት በጉባኤ በማቅረብ ይህን ኢ-ክርስቲያናዊ ድርጊት ለማስቆም ነው፡፡ሌሎችም የተወሰኑ መሠረታዊ ውሳኔዎች አሉ፡፡

በሕጉ መሠረት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ዓላማውን ተግባራዊ የሚያደርገው በጠቅላላ ስብሰባ፣በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ፣በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባና በሌላም እንደ አስፈላጊነቱ ሊመደብ በሚችል የሰው ኀይል ነው፡፡

ሕጉ ለአባል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ብዛት ከፍተኛ ግምት ስለሚሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞቿ ብዛት በ7 ዓመት አንድ ጊዜ በሚካሄደው ጠቅላላ ስብሰባ ደግሞ ሁለት መቀመጫዎች በመያዝ በምታደርገው ተሳትፎ የበኩላን አስተዋጽኦ ታደርጋለች፡፡

ዘንድሮ ለአስረኛ ጊዜ የተደረገው የአለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ "God of life, lead us to justice and peace" በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 20-ህዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም ደቡብ ኮሪያ በምትገኘው ወደባዊ ከተማ ቡሳን (Busan) ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ልዑካን መርተው የተጓዙት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑተልዕኮአችንን የተሳካ እንዲሆን ልዑካን በሚገባ መርተዋል፡፡ ረዳት በመሆን አባ ኃይለማርያም መለሠ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ከሌሎች 10 አባላት ጋር በመሆን ስብሰባውን ተሳትፈናል፡፡ ከሰባት ዓመት አንድ ጊዜ የሚደረገው አጠቀላይ ስብሰባ አንድ ዋና Moderators (የውይይት መሪ) እና ሁለት ምክትል Vice moderator (ምክትል የውይይት መሪዎችን) የማዕከላዊ ኮሚቴና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎችን ይመርጣል ቢዘህ መሠረት ቤተ ክርስቲያች በአመት አንድ ጊዜ በስብሰባ እየተገኙ የሚሰበሰቡ ሁለት ሰዎች በማዕከላዊ ኮሚቴ ተመርጠዋል፡፡

1. ዶር አባ ኃይለማርያም መለሰ

2. አቶ ይልቃል.....ሲሆኑ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴነት (Excutive) ቤተ ክርስቲያኗ ማህበሩ ከተቋቋመችበት ጀምሮ እድሉ ገጥሟት አያውቅም ነበር፤አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ተወካይ ሊኖራት ችሎአል የተመረጡትም ዶ/ር አባ ኃይለማርያም መለሰ ናቸው፡፡

ስለዚህ በደቡብ ኮርያ የተካሄደው 10ኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የውጭ ግንኙነት አጀማመርና አሁን ያለበት ሁኔታ ከላይ በመጠኑ ያብራራ ነውና የተመለከተው ሲሆን የውጭ ግንኙነቱ በትምህርት ሰጭነቱ በአርአያነቱና በምሳሌነቱ በቤተ ክርስቲያናችን መድረክ መዘክርነት ሲወሳ እንደሚኖር መግለጽ ከማስፈለጉ በቀር ሪፖርቱ የጉባኤውን ጥቂት መረጃዎችን ወደናንተ ለማድረስ እንጂ ታሪካዊና የተሟላ ገጽታ አጠቃሎ የያዘ ጽሑፍ አለመሆኑን ጭምር በዚህ አጋጣሚ እየገለጽን መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡

አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር)
በኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

የፎንት ልክ መቀየሪያ