Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

"ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ፡- የዓለም ቤዛ ዛሬ ተወለደ" ቅዱስ ያሬድ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

በባሕርዩ ፍቅር የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር ከብዝሐ ፍቅሩ የተነሳ የምናያቸውንም ሆነ የማናያቸው ፍጥረታትን ካለ መኖር አምጥቶ ይኸው አምላካዊ ፍቅሩን ተጋርተው እንዲኖሩ በመለኮታዊ ጥበቡ ህልዋንና ሕያዋን አድርጎ አስቀምጦአቸዋል፡፡ ይኸው የአምላካችን ጸጋ ከበዛላቸው መካከልና ከፍጡራን ሁሉ ለየት ባለ ጥበብ ማለትም በፈጣሪ ቃለ ትእዛዝ "ለይኩን" ይሁን በማለት ብቻ ሳይሆን አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ "እንደመልካችንና እንደምሳሌያችን እንፍጠር" (ዘፍ.1፡26)ብለው የፈጠሩት ደግሞ ሰው መይም አዳም አባታችን ነው፡፡

birthofchrist

አዳም አባታች በንጽሐ ጠባይዕ የተፈጠረ፣ በአምላካውያን ጸጋዎች የከበረ፣ በሰማያውያን በረከቶች የተሞላ ከመሆኑም በተጨማሪ የምድራውያን ፍጡራን ሁሉ የበላይ አስተዳዳሪ (ንጉሥ) ሆኖ የተሾመ ባለ ሙሉ ሥልጣንም ነበረ (ዘፍ.1፡26)፡፡

በዚህ መንፈሳዊ ጸጋ ምክንያትም እንስሳት ሁሉ ይገዙለት፤ እርሱም "በዚህ ውጡ በዚህ ደግሞ ግቡ" እያለ ይመራቸውና ያስተዳድራቸው እንደነበረ እስትንፋሰ እግዚአብሔር የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡

እግዚአብሔር ለአዳም አስቀድሞም ሆነ ከተፈጠረ በኋላ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ ከሰጠው በኋላ ፍጡርነቱን እንዲጠብቅና እንዳይዘነጋ አንዲት ትእዛዝ ወይም ሕግ ሰጠው፡፡ ይህችም ሕግ የአዳም አማኝነትና ታማኝነት የሚገለጽባት ስለሆነች እንዳትሽራት ማለትም ከዕፀ በለስ እንዳትበላ በማለት አጥብቆ አስጠነቀቀው፡፡ ማስጠንቀቅም ብቻ ሳይሆን ይህችን ሕግ ከሻረ ወይም ዕፀ በለስ ከበላ ከፈጣሪ ዘንድ ያልሆኑትን እርሱም በፊት የማያውቃቸውን መቀሰፍታት ሞትን ጨምሮ ገንዘብ እንደሚያደርግ ጭምር መከረው፣ አስተማረው፡፡

ይሁን እንጂ አዳም ይኸው የተሰጠው የመሬት ንግሥና አልበቃ ብሎት "ንጉሠ ሰማያት ወምድር" ለመሆን በመሻት በሰይጣን አነሳሽነት በእባብ አማካኝነት ወይም ፈረስነት የመጣለትን የስሕተት አማራጭ ተቀብሎ የፈጣሪውን ትእዛዝ ትቶ አምላክነትን ፍለጋ ጉዞውን ወደ ዕፀ በለስ አደረገ፡፡

በመሆኑም አዳም በፈጣሪ የተሰጠውን ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ማንም ሳያስገድደው ራሱ ወዶና ፈቅዶ አጥር ጣሰ፣ ቅጠል በጠሰ ቀጥሎም አትብላ የተባለው ዕፅ በመብላት የአምላኩን ሕግ አፈረሰ፡፡ ይህንን ስሕተታዊ ድርግት ተከትሎም ከመቅጽበት በጸጋ ከፈጣሪ የተሰጡት ጸጋዎች ሁሉም ተወሰዱ፤ ልጅነቱ ተወሰደ፣ ጸጋው ተገፈፈ፣ ዕርቃኑ ቀረ፣ ከገነትም ተባረረ እንዳይመለስም በሱራፊ እንድትጠበቅ አደረገ፡፡ ሰማያውያኑ በእንዲህ ሁኔታ ሲርቁት ያከብሩትና ይፈሩት እንዲሁም ይገዙለት የነበሩ ምድራውያን ፍጡራንም ደፈሩት፣ ሸሹት፣ ተተናኮሉት፣ ናቁት፣ ተጣሉት፡፡

አዳም መበደሉ አምኖና ተጸጽቶ ከልብ የመነጨ የንስሐ እንባ በእግዚአብሔር ፊት አነባ፡፡ ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ አምላካችን እግዚአብሔርም ንስሐውን ተቀብሎ የድኅነተ ዓለም ተስፋ፡- "እትወለድ እምወለት ወለትከ ወእድህክ ውስተ መርኅብከ እትቤዘወከ በሞትየ ወበመስቀልየ" ከልጅ ልጅህ ተወልጄ እንደህፃናት በየጥቂቱ በደጅህ አድጌ ጸዋትወ መከራን ተቀብዬ በመስቀል ተሰቅዬ ሞቼና ተነስቼ በአጠቃላይ ነፍሴን ለብዙዎች ድኅነት ቤዛ አድርጌ በመስጠት አድንሃለሁ ብሎ የሚድንበት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡

ይኸው አምላካዊ ቃል ኪዳን እስኪፈጸም ድረስም ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት ያህል መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ፣ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ በዓለም ላይ ሰልጥኖ ሁሉንም አንድ አድርጎ ሲያሰቃይ ኖረ፡፡ የብሉይ ኪዳን ጻድቃን ቅዱሳን ሁሉ ይህንን የዓለም ኃጢአት ማስወገድ የሚቻለው በፈጣሪ ቸርነት ብቻ መሆኑን አምነው ምንም ጽድቅ ቢሠሩ፣ ጸሎት ቢጸልዩ፣ መሥዋዕት ቢያቀርቡ ከሞተ ነፍስ ግን መዳን ስላልቻሉ እግዚአብሔር ወርዶ እንዲያድናቸው ይጸልዩና ይማጸኑ ነበር፡፡

 • "ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ!፤ እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ። ... እነሆ፥ እነተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን ስለዚህም ተሳሳትን። ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፥ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል" ኢሳ.64፡1-7

 • "አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም። መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም። እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም" መዝ.144፡5-7

 • "ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ" ሮሜ.5፡14 እንዲል፡፡

መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንን ምስጢረ ድኅነት ብዙዎች የብሉይ ኪዳን ጻድቃንና ነቢያት ሊያዩት ይመኙና ይጸልዩ እንደነበር ከሐዋርያት ዕድል ፈንታ ጋር አነጻጽሮ በወርቃማ አንደበቱ አስተምሮአል፡፡

 • "የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም" ማቴ. 13፡17 እንዲል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ "ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን" (ዕብ.1፡1) በማለት እንዳስተማረን እግዚአብሔር በአባቶቻችን አድሮ ያስቆጠረውን ሱባኤ ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ተወግዶ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚነግሥበት ዘመን በደረሰ ጊዜ አስቀድሞ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም መጋቢት 29 ቀን ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድንግል ማርያም በመላክ የድኅነተ ዓለም የምስራች ተሰማ፡፡

ድንግል ማርያም ለአምላክ እናትነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችበት ዋና ምክንያት ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና፤ ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ለመላእክት እንኳ ያልተቻላቸውን ድንጋሌ ህሊና ገንዘብ አድርጋ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ስታገለግል ለማኅደረ መለኮትነት አኅላ፣ በቅታ፣ ሆና ስለተገኘች ብቻ ነው፡፡

ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም በቅድስና በንጽሕና የሚመስላ የሚያኅላት ስላልነበረ ለአድኅኖ ዓለም፣ ለቤዝዎ ዓለም የሚወለድ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ካንቺ ይወለዳል ብሎ ባበሰራት ጊዜ በትሕትና ትሩፋት "ይህ እንዴት ይሆናል" ብላ በተከራከረች ጊዜ መልአኩ መልሶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ሲላት ከልብ ተቀብላ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ" እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደቃልህ ይሁንልኝ በማለት ታዘዘች፡፡ በቀዳሚት ሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ያጣነውን ክብር በዳግሚት ሔዋን መታዘዝ እንደገና ተመለሰልን፡፡ በዚህ ቃለ ተአዝዞ ወቃለ ትሕትና መሠረትም አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በማኅጸንዋ አደረ፡፡

በረቂቅ ምስጢረ ተዋሕዶም አምላክ ሰው፣ ሰው ደግሞ አምላክ ሆነ፤ ጥንት ፍጻሜ የሌለው መለኮት ዘመን ከሚቆጠርለት ሥጋ ጋር፣ የማይታይ የማይዳሰስ ረቂቅ መለኮት ከሚታይ ከሚዳሰስ ግዙፍ ሥጋ ጋር፣ ሕመም ሕልፈት የሌለበት ወይም የማይስማማው መለኮት ሕመም ሞት ከሚስማማው ሥጋ ጋር፣ የማይራብ የማይጠማ መለኮት ከሚራብ ከሚጠማ ሥጋ ጋር በተዋሕዶ ምስጢር አንድ ሆነ፡፡ መለኮት የሥጋ ባሕርይን ሳያጠፋ፣ ሳይለውጥና ሳይውጥ፤ ሥጋ የመለኮት ባሕርይን ሳያጠፋ፣ ሳይለውጥና ሳይውጥ በፍጹም ተዋሕዶ ሁለትነትን የሌለበት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ፡፡

በዚህ መልክ የተጀመረው ምስጢር አምላክ ነኝና በአንድ ቀን ልደግ ሳይል እንደሰው ሁሉ በየጥቂቱ በማደግ ታሕሳስ 29 ቀን በእንስሳት ግርግም ላይ ተወለደ፡፡ እንስሳት ይጠብቁ ለነበሩት እረኞችም መልአከ እግዚአብሔር ተገልጾ የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን አበሰራቸው፡፡ እረኞችም ይህንን የተነገራቸው የምስራች እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ግርግሙ ሲሄዱ ህፃኑና እናቱ እንዲሁም ዮሴፍ አብረው አገኟቸው፡፡ እናቱም ጨርቅ ስላልነበራት በቅጠል ጠቀለለችው፡፡ እረኞቹም ይህንን ድንቅ ምስጢር ባዩ ጊዜ ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመሆን "ለእግዚአብሔር ምስጋና በሰማያት ይሁን ሰላም ደግሞ በምድር ላይ ለሰው ልጆች ይሁን" እያሉ እጅግ አድርገው አመሰገኑ፤ ይህንን የምስራችም በአካባቢው ለነበረው ሕዝብ ሁሉ እየዞሩ መሰከሩ፡፡

በዚህ የቅዱሳን መላእክትና የእረኞች የጋራ ምስጋና ምክንያትም የቤዛነትና የእርቀ ሰላሙ ሂደት ተጀመረ፡፡ ተጣልተውና ተለያይተው የነበሩ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች አብረው በአንድ ላይ በዝማሬ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ጀመሩ፡፡

በነቢያትና በሐዋርያት መሠረትነት የተመሠረተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህንን የቅዱሳን መላእክት ምስጋና መሠረት በማድረግ ይኸው በዓላችን "ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ፡- የዓለም ሁሉ ቤዛ ዛሬ ተወለደ" በማለት ዕለቱን በማኅሌት፣ በዝማሬ በቅዳሴ በልዩ መንፈሳዊ ትሩፋት በየዓመቱ ታከብዋለች፡፡ በዚህ ቀንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀዳሚ ተከታይ በማይገኝለት መልኩ አንድ ጊዜ ለዘላለም የዓለም ቤዛ ሆኖ ለዓለም ነፃነት ሊሰጥ የከፈለው የቤዛነት ምስጢር በማሰብ እጅግ አድርገን የምናመሰግንበት የምስጋና ቀን ነው፡፡

"ቤዛ" ማለት ያለ ምንም ውለታ፣ ያለ ምንም የዋጋ ተመን በነፃ ከምልዓተ ፍቅሩ የተነሳ የበደሉትን በደል ይቅር ብሎ በበደሉት ፈንታ እርሱ እንደበደለ ሆኖ፣ ዕዳበደላቸውንም ተሸክሞ፣ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት ካሳ ከፍሎ በኃጢአታቸው ምክንያት በሞት ቀንበር ተይዘው የነበሩትን ነፍሳት ሰላም፣ ነፃነት፣ ሕይወት፣ አርነት... መስጠትን የሚያመለክት ኃይለ ቃል ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የፈጸመውም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አማናዊ (በባሕርዩ) ቤዛ ነው በማለት ታምናለች ትታመናለች እንዲሁም ትመሰክራለች፡፡

 • "እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም" ማቴ.20፡28

 • "ነገር ግን። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው"1ኛ ቆሮ.1፡30-31

 • "በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን" ኤፌ.1፡7-8

 • "ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ" 1ኛ ጢሞ.2፡6 እንዲል፡፡

ከላይ የተገለጹ እውነታዎች የሚያስገነዝቡን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት የቤዛነታቸን ምስጢር እያስታወስን፣ ለቤዛነታችን የተከፈለውን መሥዋዕትነት (ነገረ መስቀሉን) ዘወትር በፊታችንና በሕሊናችን እየሳልን ይበልጥ የምናመሰግንበት የምስጋና ቀን ከመሆኑም በተጨማሪ በዓለ ልደት አባቶቻችን ባቆዩልን መጽሐፋዊ ትውፊት መሠረት በምስጋና፣ በውዳሴ፣ በቅዳሴ፣ በማኅሌት ማክበርና ባሰብ እንጂ አሁን ዘመን እንደወለደው ትውልዱ እንደፈቀደው አለልክ በመብላትና በመጠጣት፣ በዘፈንና በዳንስ በአጠቃላይ በአሕዛባዊነት ግብር ማክበር ኦርቶዶክሳዊነት አይደለም እላለሁ፡፡

መልካም የልደት በዓል ያድርግልን
ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ፡- እንድናመልከው ለፈጠረን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው፡
አሜን!

የፎንት ልክ መቀየሪያ