Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ዓቢይ ጾም ለምን 55 ቀናት ሆነ?
ክፍል ሁለት

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

በክፍል አንድ ጽሑፌ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ዓቢይ ጾም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በደማቅ መንፈሳዊ አገልግሎት በጸሎት፣ በስግደት፣ በምግባር፣ በትሩፋት... በአጠቃላይ በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በሱባዔ የሚከበር ትልቅ የበረከት ጾም ነው፡፡ በዚህ የጾም ወራት ምዕመናን የረሃብን ችግር፣ የረሃብን አስከፊነት... ይበልጥ ተገንዝበው ለተራበ ወገናቸው በርህራሄ፣ በፍቅር፣ በልግስና ... እንዲያስቡና አስተዋይ ልቡና እንዲያዳብሩ የሚረዳቸው የመንፈሳዊ በረከት መገኛ፣ የንጽሕና መገኛ... የሆነ የቅድስና ጾም ነው፡፡

በዚህ ጾም ምዕመናን በየአብያተ ክርስቲያናቱ እየተገኙ በፍጹም መንፈሳዊ ጥንካሬ ሌሊት በሰዓታት፣ በኪዳን ... ቀን በቅዳሴ በውዳሴ /በጸሎት/ በሱባዔ የሚጸኑበት የነፍስ ትጋትና የሥጋ ድካም የሚያገኙበት፣ መልካም የሆነውን የአፋቸው ፍሬ /ምስጋናና ልመና/ ለፈጣሪ የሚያቀርቡበት፣ ኃጢአታቸው ተናዝዘው የሚፈቱበት፣ የምግባር የትሩፋ ዕሴት የሚያበለጽጉበት... የሱባዔ ጾም ነው፡፡ በመሆኑም አበው ይህን ጾም ሲተረጉሙ ለጸሎት እናቷ፣ ለዕንባ መፍለቂያዋ፣ ለበጎ ሥራ ሁሉ መሠረቷ በማለት በጣዕመ ስብከታቸው እንደጸጋቸው መጠን ይተነትኑታል፡፡

ወደ መነሻ ርእሳችን እንመለስና ጌታችን የጾመው 40 ቀናት ሲሆን ለምን እኛ 15 ቀን እንጨምራለን ለሚለው ጥያቄም የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት በሁለት መልኩ ያመስጥሩታል፣ ታሪካዊ ዳራውንም ያስቀምጡታል፡፡
1. በመጀመሪያ በዚህ ጾም ወቅት የሚመላለሱ ቅዳሜና እሁድ (15 ቀናት) በጾም ወቅት ከተከለከሉ ጥሉላት (የእንስሳት ተዋጽኦ) ውጭ ከእህልና ከውኃ ስለማይጾምባቸው እነዚህ ታስቦ ቢወጡ ጾሙ 40 ቀን ይሆናል የሚል ትውፊታዊ አስተምህሮ ነው፡፡

2. በስፋት የሚታወቀው ግን ጾሙ 40 ቀን ሆኖ ሳለ ከፊትና ከኋላ ሁለት ሳምንታት በመጨመራቸው ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሳምንታትም መንፈሳዊ ምክንያት የተላበሱ፣ ዕሴተ ነፍስን የሚያድሱ በመሆናቸው እንጂ እንዲሁ የተጨመሩ አይደሉም፡፡
የመጀመሪያው ሳምንት ለዋናው ጾም መለማመጃና የዝግጅት ጊዜ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ምስጢሩ ግን ከቢዛንታይን ንጉሥ ከህርቃል ምግባር ትሩፋት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የመጀመሪያ ሳምንት ጾም "ጾመ ህርቃል" ተብሎ ይጠራል፡፡ ታሪኩም ሊቃውንት እንደሚከተለው አስፍረውታል፡፡

አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ "መጽሔተ አሚን" በተሰኘ መጽሐፋቸው የጾመ ሕርቃልን ታሪክ ከዚህ እንደሚከተለው አስቀምጠውታል፡-

 • "ሕርቃልም በ628ዓ.ም ወደ ፋርስ ዘምቶ ኮስሮዬን ድል አድርጐ የጌታችንን መስቀል አግኝቶ ሲመለስ መስቀሉን እርሱ ራሱ ተሸክሞ ከፋርስ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ አለጨማ በእግሩ እየሄደ አምጥቶ ለኢየሩሳሌም ምዕመናን አስረከበ፡፡ ሕርቃልም መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ በደረሰ ጊዜ የከተማው ሕዝብ ሁሉ ከደስታ ብዛት የተነሳ በዕልልታ መብራት፣ ችቦና ጡዋፍ እያበራ ንጉሡንና መስቀሉን አበባ ይዞ ተቀበለ፡፡ ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱም በጣም ደስ ስለአላቸው ስለ እርሱ ብለው ሰባት ቀን ሙሉ በጾምና በጸሎት የያዙትን ሱባኤ ከጌታችን ጾም ጋራ ሆኖ በየዓመቱ ሰባት ቀን እንዲጾም አዘዙ፡፡ ሄራቅልዮስም 729ዓ.ም የመስቀልን በዓልን በየዓመቱ እንዲከበር አዘዘ፡፡ ስለዚህ ስለ ጌታችን መስቀል ምክንያት ከምርኮ ስለመመለሱ መታሰቢያ ሆኖ የሚኖር ሁለት ምክንያት አለ፡፡

1. መጀመሪያ ንጉሡ ሕርቃል ዘመቻው ድል እንዲቀናው ሲል ሰባት ቀን በጾምና በጸሎት ሱባዔ ያዙልኝ ብሎ ስለነበር በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከጾመ 40 በፊት ያለውን የአንድ ሳምንት ጾም /ዘወረደን/ ስንጾም እንኖራለን፡፡
2. በኢየሩሳሌም ያሉ ምዕመናን ክርስቲያን ሁሉ መስቀሉ ከምርኮ ሲመለስ በዕልልታና በደስታ አበባ እየያዙ በመብራት እንደተቀበሉት፤ በሀገራችን በኢትዮጵያም መስከረም 16 ቀንና 17 ቀን መብራት እያበራን አበባ ይዘን በዕልልታና በሆታ በየዓመቱ በዓሉን እናከብራለን፡፡ ይህም በ629ዓ.ም የተጀመረው በዓል በኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ድረስ ጸንቶ ይኖራል፡፡ (አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ፡ መጽሔተ አሚን፡ ሚያዝያ 30 ቀን 1946ዓ.ም፡ ገጽ ከ 55-56)

የመጨረሻው ሳምንት ደግሞ ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ይኸውም የጌታችን ሕማም፣ ስቃይ፣ ስቅለትና ሞት የሚታሰብበት ስለሆነ አብሮ በመጾም ይከበራል፡፡ ሐዋርያትም ሕማሙንና ሞቱን ለማሰብ የጾሙት በመሆኑ አብሮ ይጾማል፡፡ የሁለቱም ሳምንት መጨመር ባጭሩ በዚህ መንፈሳዊ ታሪክ ምክንያት ነው፡፡

ዐቢይ ጾምንና የሕርቃል እንዲሁም የሰሙነ ሕማማት በተመለከተ ቤተክርስቲያን ባስተመችው መጽሐፍ ባጭሩ እንደሚከተለው ተጽፎ እናገኛለን፡-

 • "ዐቢይ ጾም ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የዓርባ ቀን ነው (ማቴ.4፡1)፡፡ ቤተክርስቲያንም ጌታ ያደረገው ምሳሌ ተከትላ ትጾማለች፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት ወይም 55 ቀኖች አሉት፡፡ የመጀመሪያ ሳምንት ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ሕርቃል /አራቅሊዮስ/ የቤዛንታይን ንጉሥ ነበረ /614ዓ.ም/፡፡ ይህ ሳምንት በስሙ የተጠራበትም ምክንያት እንደሚከተለው ነው፡፡ በዘመኑ ፋርሶች ኢየሩሳሌምን ወርረው የጌታን መሰቀል ማርከው ወስደው ነበር፡፡ እሱ ወደ ፋርስ ዘምቶ እነርሱን ድል አድርጐ መስቀሉን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶአል፡፡ በዚህ ምክንያት ክርስቲያኖች ተደስተው ለስሙ መታሰቢያ ይህን የጾም ሳምንት በቀኖና ውስጥ አስገብተውታል፡፡ ቤተክርስቲያናችንም በቀኖናዋ አስገብታ ተቀብላዋለች፡፡ ከዐቢይ ጾምም ጋር አንድ ሆኖ ተቆጥሮአል (ፍት.ነገ. 15)፡፡ የመጨረሻ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ነው፡፡ ሐዋርያት የጌታችንን ነገር መሰቀል እያሰቡ የጾሙት ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ሁሉም ከዐቢይ ጾም ጋር አንድ ሆነው ተቆጥሮአል፡፡ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት አዲስ አበባ 1988ዓ.ም ገጽ 70)

ይቆየን

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ፣
/እንድናመልከው እኛን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን/
የካቲት 2007 ዓ.ም

የፎንት ልክ መቀየሪያ