Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ዝክረ ጋዛ በሲና በረሀ


በመ/ር አባ በኩረ ጽዮን መ/ጊዮርጊስ
የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ም/ኃላፊ

በመለኮተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ አሐዱ ሰለስቱ ወእንዘ ሰለስቱ አሐዱ ብለን ጽሑፋችን እንጀምራለን፡፡

በግዕዙ የተጻፉ መጻሕፍተ ብሉያት የተገኙበትን ምንጭ ከዚህ ቀጥሎ እንጽፋለን፡፡

ዓለም ከተፈጠረ በሺህ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት /ዘመን መጽሐፈ ሄኖክ ተጻፈ/፡፡ ይህም መጽሐፈ ሄኖክ ከአዋልድ መጽሐፍተ የሚቆጠር አይደለም ቀዳሚ ለምዕመናን ምሥጢር ለመናፍቃን ከባድ የመልስ መጽሐፍ ነው እንጂ፡፡
ሐዋርያው ይሁዳ ም. 6 ቁ. 14 ከአዳም ሰባተኛው ሄኖክ ለነዚያ ትንቢት ተናግሮባቸዋል፡፡ እንዲህ ሲል እንሆ እግዚአብሔር ከአእላፍ ቅዱሳን ጋራ ይመጣል አለ ብሎ መናፍቃንን ረትቶበታል፡፡ ይህንም ሐዋርያት ምስክር አድርገው ይቈጥሩታል፡፡ መጽሐፉ እንደ መንቀፍ ይመስላል ከዚህ ቀጥለው እስራኤል በግብጽ ሳሉ በፈርዖን ዘመን እንዲሁ መጽሐፈ ኢዮብ ተጽፈዋል፡፡

በ3843 ዓመተ ዓለም እስራኤል ከግብጽ ወጡ በዚህ ጊዜ ኦሪት ተጻፈች በ4407 ዓመተ ዓለም ሳኦል ነገሠ በዚህ ጊዜ መጽሐፈ ነገሥት ተጀመረ፡፡ በ4447 ዓመተ ዓለም ሳኦል ሙቶ ዳዊት ነገሠ በዚህ ጊዜ የዳዊት መዝሙር ተጻፈ፡፡ በ4481 ዓመተ ዓለም ዳዊት ሙቶ ሰሎሞን በገሠ በ4 ዓመቱ 1 ነገ. 10፡1 እንደተጻፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ንግሥት ቡዥሮንድ ብላ የሰየመችው የሰሎሞን ጥበብ አይቶ ለመረዳት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ተብሎ የተነገረውን ትንቢት ተጀመረልን፡፡ መዝ. 67 ምክንያቱም አምልኮተ እግዚአበሔር ስትፈልግ እንደ ሄደች ጌታ በወንጌል ቅዱስ 12፡32 ንግሥቲ አዜብ ከዚህ ትውልድ ጋር በፍርድ ቀን ትነሣለች፣ ትፋረዳቸዋለች፡፡ ከምድር ዳር መጥታለችና ብሎ ጌታ በወንጌለ መንግሥቱ አስተምሮናልና፡፡ ሰሎሞንም የፈለገችውን ሁሉ ነግሯታል፡፡ 1ነገ. 10፡13 መመልከት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሥርዓተ መንግሥት አድርሶ ልጅዋን ምንሊክን አንግሦ ከመጽሐፈ ሄኖክ ጋር እርሱ ራሱ ከጻፋቸው መጻሕፍት ጋር ሰብስቦ ምሥጢሩ ከሚገልጹ መምህራንና መተርጉማን 318 ሌዋውያን ጨምሮ ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ ልኳልና፡፡ ይህንን ነገር ለማወቅ ከተፈለገ ታሪከ ነገሥቶቻችንን መመልከት ያስፈልጋል፡፡

በዘመነ ብሉይ ከተነሱ ነቢያት አንዱ ሶፎንያስ ምዕ. 3፡10 ከኢትዮጵያ ወንዝ ማዶ የሚሰግዱልን የተበተኑት ልጆቼ መባኤን ይዘው ይመጣሉ ብሎ እንደተናገረ ይህም ነገር በኢትዮጵያ አምልኮተ እግዚአብሔር እንደነበር ያስረዳናል፡፡

ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ሰዎች በኦሪት ሕግ አምነው ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግዱ ይወጡ እንደነበረና ከክርስቶስ መወለድም በፊት መጻሕፍተ ነቢያት ወደ ግዕዝ ተተርጉመው በኢትዮጵያ ተሰብስበው እንደነበሩ በሐዋርያት ሥራ ተጽፎ እናገኘዋለን የሐ.ሥራ. 8፡26-40፡፡

ወይቤሎ መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ ሑር ትልዎ ለዝ ሠረገላ ባለው መሠረት ከጌታችን ዕርገት በኋላ የኢተዮጵያ ንግሥት ጃንደረባ የሚሆን አንድ የኢትዮጵያ ሰው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ የሥግደቱን ሥርዓት ፈጽሞ ሲመለስ በሠረገላ ተጠምቆ መጽሐፈ ኢሳይያስን ይመለከት ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ ሐዋርያው ፊልጶስ ጃንደረባውን ተከተለው፡፡ አንተ ሰው የምትመለከተውን መጽሐፍ ምሥጢሩ ታውቀዋለህ ወይ ብሎ ሐዋርያው ሕጹውን ጠየቀው የሐ.ሥራ 8፡32፡፡ ጃንደረባው ሲያነበው የነበረው ኃይለ ቃልም መጽአ ይጠባሕ ከመ በግዕ ወከመ በግዕ በቅድመ ዘይቀርጾ ከማሁ ኢከሰተ አፉሁ በሕማሙ ወተንሥአ እምኩነኔ ወእሞቅህ ወመኑ ይነግር ልደቶ እስመ ተአተተ እምድር ሕይወቱ ኢሳ. 53፡7 የሚለውን ቃለ ነቢይ ያነብ ነበር፡፡ ያም የኢትዮጵያ ሰው መጻሕፍተ ነቢያትን ጠንቅቆ ተምሯልና፡፡ የተማረውን ደገመ እንጂ ትንቢቱ እንደደረሰ ምሳሌውም እንደተፈጸመ አላወቀም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ንግሥት ጃንደረባ መጽሐፈ ኢሳይሳይ እንደምን ያውቃል ቢሉ ጊዜው ስላልደረሰ ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ያስተምረናል፡፡ ወባሕቱ እፎ ይጸውዕዎ እንዘኢያአምኑ ቦቱ ወእፎ ያአምኑ በዘኢሰምዑ ወእፎ ይሰምዑ ዘኢሰበኩ ለሙ ወእፎ ይሰብኩ ሎሙ ዘኢይተፈነወ ሐዋርያው ኀቢሆሙ እንዳለ ሮሜ. 10፡11፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እኮ ጥንታዊት ታሪካዊት ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ ሁሉ በዓለም ከምትታወቅባቸው ዐበይት መገለጫዎች ውስጥ በዋቢነት በሚጠቀሰው በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ በነበሩ ብሔራዊያን ሊቃውንት ሲወርድ ሲዋረድ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተጠብቆ የቆየው ትውፊት ቃለ መምህራን አጽንታ ብሂለ አበው እያስታወሰች የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ናት በማለት የውጭ ሰዎች ስያወድሷት ይኖራሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ብለው የታሪክ ሰዎች የጻፏቸው መጻሕፍት ንግሥት አዜብ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን በሄደች ጊዜ ጋዛ ላይ ሰፍራ ነበርና ወደ ሀገርዋ ስትመለስ ጉልት ይሁንሽ ብሎ ስለሰጣት አንዳንድ ጠባቂ ሹም ይቀመጥበት ነበር፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ንግሥት ጃንደረባ /ባኮስ/ በዚያ ልማድ ተሹሞ በጋዛ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ነበረ የሚሉ ታሪክ ጸሐፊዎች አሉ፡፡ ሰሎሞንም ሲሰጥ ጋዛ ጉልት ይሁንሽ ብሎ እንደሰጣት ጠባቂውም እንድታደርግበት እንደፈቀደላት ይናገራሉ 1ነገ. 10፡3 ግን ይህ ሕፅው በጋዛ ተሹሞ የሚኖር መሆኑን በሐዋርያት ሥራ 8፡36 የተፃፈው የሐዋርያት ትምህርት አያስረዳም፡፡ በኢየሩሳሌም ሊሰግድ ከኢትዮጵያ የሄደ መሆኑ ብቻ እንጂ በጋዛ ተሹሞ ይኖር እንደነበር ለማወቅ ለጊዜው ያልተጻፈ ታሪክ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ምዕመናን ሆይ ሀገራችን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር እንደመረጣት እንደባረካት የሚታወቀው ወይቤሎ መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ ሑር ትልዎ ለዝሠረገላ ብሎ በትእዛዘ መንፈስ ቅዱስ የተጠመቀው በባኮስ ምክንያት ወንጌለ መንሥተ ሰማያት በፈቃደኝነት የተቀበለች ቅድስት ሀገር እንደሆነች በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ስሟና ታሪኳ የገነነ ሀገረ እግዚአብብሔር ሁና የምትገኝ ሀገር ነች፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ወቅትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገዳመ ቆሮንጦስ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ለሊት የጾመበት ወራት ተስፋ ነፍስ ተስፋ ሥጋ የሚያሰጠን ጾማችን ነው፡፡ ጌታችን መዋዕለ ጾሙ ሲፈጽም ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን ጌታችንን በሦስት ነገሮች ሊፈታተነው መጣ፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡ በትዕቢት፣ በፍቅረ ንዋይ፣ በሦስት ናቸው፡፡ በዕቢት ቢመጣበት በትሕትና በሦስት ቢመጣበት በትዕግስት በፍቅረ ንዋይ ቢመጣበት በጸሊአ ነዋይ ድል ነስቶታል ማቴ. 4፡1፡፡ ዐበይት አርዕስተ ኃጣውዕ የሚባሉትን እነዚህ ናቸው፡፡ ሌሎችም ለድኀነተ ዓለም የሚበጁትን ዝግጅቶች ከአስተካከለ በኋላ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር የተባለውን ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ኢይደልዎ ለነቢይ መዊት በአፍአ ዘእንበለ በኢየሩሳሌም እንዲል መዝ. 74፡12፣ ሉቃ. 13፡33 በኢየሩሳሌም ተሰቅሎ በሞቱ ዓለምን አድኖዋል ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊትም በከርሠ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሥቷልና፡፡ በሰኑይ ዕለት ይቀስፈነ ወበሰሉስ መዋዕል ይሤርየነ ወያሐይወነ ወአመሳሣልስት ዕለት ንትነሣኦ ሲል ነቢዩ ሆሴ ቀደም ሲል ትንቢት ተናግሮ ነበርና፡፡ ሆሴ. 6፡2 ዮሐንስ አፈወርቅን ወአመሣልስት ዕለት ሦጣ ለነፍሱ ውስተ ሥጋሁ እንዳለ፡፡

በአሁኑ ዘመን ያለነው ትውልድም ወፈድፋደ ጸንዑ እምቀደምተሙ ይላልና በሃይማኖት በታሪክ ጸንተን እንድንኖር ቤተ ክርስቲያናትን ታዘናለች፡፡ እስመ ኩሉነ ውሉደ ብርሃን ተብለን በሐዋርያው ቃል ተጠርተናልና ይህንን ቃል ይዘን 1ቆሮ. 5፡5 ፈጣሪያችንን እያመሰገን እንድንኖር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን ፡፡
ይቀጥላል ............

የፎንት ልክ መቀየሪያ