Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

"ኪዳነ ተካ የድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ" መዝሙር 88፡3

ይህ ቃል እግዚአብሔር ከቅዱሳን ሰዎችና መላእክት እንዴት ቃል ኪዳን እንደሚገባ በነቢዩ በቅዱስ ዳዊት አንደበት አድሮ የተነገረው የቃል ኪዳን ዕብነ ማዕዘንት መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡ ቃል ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካከል የሚፈጸምና ሁለቱም ወገኖች ሊጠብቁት የሚገባ ውል ወይም ስምምነት የመሐላ መተማመኛ ማለት ነው፡

ከሁለቱ አንዱ ውሉን ቢያፈርስ ሌላው ወገን ቃል ኪዳኑን ለመጠበቅ አይገደድም፣ ቃል ኪዳን አፍራሹን ክፍል ሊቀጣ ይችላል፡

ቃል ኪዳን ብዙ ጊዜ በሰዎችና በሰዎች ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከልም እንደተደረገ ቅዱስ መጽሕፍ ያወሳናል፡

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ከኃጢአቱ ብዛት የተነሳ በጥፋት ውሃ በኮነነ ጊዜ ለኖህ በሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት እሱንና ቤተሰዎቹን ከጥፋት ውሃ ጠበቀ፣ በጠቅላላው በመርከቧ ውስጥ የነበሩትን ነፍሳት ሁሉ አተረፈ፣ የጥፋቱም ውሃ /ማየ አይኅ/ ከደረቀ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ኖህን ባረከው የቃል ኪዳንም አደረገለት፤ የምሕረቱም ቃል፣ ኪዳን ምልክት ቀስተ ደመናን በሰማይ አደረገ፡፡

ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ከእናንተ ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ለዘለዓለም የማደርገው የቃል ኪዳን የምሕረት ምልክት ነው ሲል ነግሮታል፡: ዘፍ. 9፡12-13
ይህ የምሕረት፣ ቃል ኪዳን ለኖህ ብቻ የተሰጠ ሳይሆን በየጊዜው የምሕረት የቃል ኪዳን የተሰጣቸው አበው ነበሩ፡

ከእነዚህም በአብርሃምና በእግዚአብሔር መካከል የተደረገው ሌላ ቃል ኪዳን አለ፡፡ እርሱም እግዚአብሔር አብርሃምን እንደሚባርከው፣ ዘሩን እንደሰማይ ኮከብና እንደ ባሕር አሸዋ እንደሚያበዛለት፤ አብርሃምና ልጆቹ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጸንተው እንዲኖሩ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ ነበር፡ የቃል ኪዳኑ ምልክትም ግዝረት ነበረ ዘፍ. 17፡9-12፡፡

ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር ለሕዝበ እስራኤል ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ የምሕረቱ የቃል ኪዳኑ ምልክት ጽላተ ሕጉ ነበር፡፡ ዘዳ. 34"10-29፣ ኢያ. 4፡9 በዚህ መሠረት እግዚአብሔር ከብዙዎች ቅዱሳን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ "ነቢይን በነቢይ ስም የተቀበለ የነቢዩን ዋጋ ይቀበላል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የተቀበለ የጻድቅን ዋጋ ያገኛል ማንም ከእነዚህ ከታናናሽ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋዕ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም" /ማቴ. 10.40/ በሐዲስ ኪዳን ውስጥ ለቅዱሳን ለተሰጠው አማላጅነት ቃል ኪዳን መሠረት ይህ አሁን የተጠቀሰው ዓረፍተ ነገር ነው፡፡ በሰዎችና በሰዎች የሚፈጸመው ቃል ኪዳንም አለ፡፡

ለምሳሌ፡- ኢያሱ ከእስራኤላውያን ጋር ያደረገው የቃል ኪዳን ውል ነው፡፡ ይህም እስራኤላውያን ጣዖት ማምለክ ትተው እግዚአብሔርን ለማምለክ እርግጠኞች መሆናቸውን የሚያስታውስ የድንጋይ ሐውልት ነበር፡፡ ኢያሱ. 4፡6-7 ዛሬም ቢሆን ባለንት ዓለም በምድራውያን መንግሥታት መካከል፣ በባልና በሚስት፣ በአሠሪዎችና በሠራተኞች መካከል በጠቅላላው በሁለት ወገኖች ዘንድ የቃል ኪዳን ምልክት /መሐላ/ የውል ስምምነት ሲፈፀም ይታያል፡

ይህም በሁለቱ መካከል ከተፈጸመ በኋላ በአንደኛው በኲል ሲፈርስ ለአፈረሰው ወገን ጉዳት የሚያስከትል ጥቅም የሚያሳጣ እየሆነ አንዳንድ ጊዜ ስለሚገኝ እግዚአብሔር ከሰጠው የምሕረት፣ ቃል ኪዳን ጋር አይመሳሰልም፡፡ ሰብአዊ ቃል ኪዳን ጥቅሙ ሲጎድል ይፈርሳልና፡፡

እንግዲህ በእግዚአብሔርና በቅዱሳን መካከል ያለውን የምሕረት የቃል ኪዳን በሰዎችና በሰዎች መካከል የሚደረገውን የሰዎች ሥጋዊ ውልን በመጠኑ ከተረዳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን ለምን እንደተሰጣትና ኪዳነ ምሕረት የሚለውንም ስም እንዴት እንዳገኘች በመጠኑ እገልጻለሁ፡፡

"በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋም መካከል፣ ጠላትነትን አደርጋለሁ፣ እርሱ፣ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኲናውን ትቀጠቅጣለህ" ዘፍ. 3፡15 ሲል ለመጀመሪያው ሰው ለአባታችን አዳም በሰጠው ተስፋ መሠረት የዘመነኑ ፍጻሜ ሲደርስ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው "የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን በሕግም በታች የተወለደውን ልጁ ላከ" ገላ. 4፡4 ብሎ የመሰከረለት በመስቀሉ የእባቡን /ሰይጣን/ እራስ የቀጠቀጠው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

ቅዱስ ያሬድ "ብኪ ድኅነ ዓለም ወበወልድኪ ኮነ ሰላም" "በአንቺ ምክንያት ዓለም ዳነ፤ በልጅሽ በኢየሱስ ክርስቶስም ሰላም" ሆነ ብሎ የዘመረላት አባ ሕርያቆስም እንደገለጸው ለአዳም ተስፋ ሆና የተገኘች፣ የኖህ መርከብ ምሳሌ፣ የምሕረት፤ ቃል ኪዳን ምልክት፣ የታቦተ ጽዮን አማናዊት ምሳሌ ከሆነችው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለተወለደ ኪዳነ ምሕረት የተባለችው በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ይህንንም እውነት ያደረገው ክርስቶስ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ምልክት የሰጠው ተስፋ እርግጠኛነት የፍቅሩ ብዛት፣ የርኅራሄው መግለጫ፣ የምሕረቱ ማወጃ ሆና ዓለምን ለማዳን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ ተወልዷል፡፡ ይህም ሁሉ የምሕረት ቃል ኪዳን በእሷ ስለተገለጸ ኪዳነ ምሕረት የሚለው ስም አገኘች፡፡

ይህም የቃል ኪዳን ኪዳነ ምሕረት መታሰቢያ ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክረስቲያን ሥርዓተ ቀኖና መሠረት የካቲት 16 ቀን በየዓመቱ ይከበራል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ ነው ብለን ለምናምነው ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ስለሆነች፣ በቃል ኪዳንዋ ለተማፀኑ ሁሉ ምሕረትን ከልጅዋ ዘንድ ትለምንላቸዋለች፡፡ በእምነት ሆነው መልካም ሥራ እየሰሩ የእርስዋን የአምላክ እናትነት ለሚያምኑ በፀጋ ላይ ፀጋን ትሰጣቸዋለች፡፡

ነገር ግን ማንም ሰው ከእርስዋ በተወለደው በክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነት ሳያምን ለእምነቱ መግለጫ የሚሆነው መልካም ምግባር ሳያሳይ ድንግል ማርያምን በመጥራትና በስዋ ስም በመሰየም ብቻ አይድንም፡፡ ምክንያቱም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በንሥሐ ለሚመለሱ የሐጥአን ተስፋ፣ የጻድቃን ሞገስ፣ የቅዱሳን መመኪያ፣ የሰማዕት እናት እንጂ የአመፀኞች እና የኢአማንያን ተስፋ አይደለችምና፡፡

የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነትና አዳኝነት አምነን ስንቀበል፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የድኅነት መገኛ መሆንዋን እናምናለን፡፡ እግዚአብሔር ለዓለም የሰጠው ቃል ኪዳን ያናገረው የተስፋ ትንቢት በእርስዋ ተፈጽሞአልና፡

"ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል" የአበው ተስፋ ትንቢት በማርያም ድንግል ተፈጸመ ተብሎ እንዲነገር ያስቻለ የኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ነውና፡

ስለዚህ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት አምላክ ለፈጸመው የድኅነት ሥራ ሁሉ ምክንያት እንደሆነች እንመሰክራለን፡ ከዚህም ጋር በእምነትና በምግባር ደካማ ለሆኑ ምሕረትን የምትለምን ርኅርኅት ሕሊና እንደሆነች አምነን እንመሰክራለን እናስተምራለን፡፡

ወረብ፡- ይቤላ ለእሙ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ይቤላ ለእሙ /2/ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመአድኅን ዘተአመነኪ ኪዳነ ምሕረት /2/
መዝሙር፡-ማርያም ንጽሕት ድንግል ማዕምንት ወላዲተ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ለውልደ ሰብእ /2/
ሰዓሊ ለነ ኅበ ክርስቶስ ወልድኪ ይሥረይ ኃጢአተነ ሰዓሊለነ ቅድስት፤

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ