Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ትምህርተ ተዋሕዶ

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቀደምትነት ከታወቁ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አንዷ እንደሆነች ግልጽ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ የተቋቋመችበትን ዘመን ከእውነተኛ የታሪክ ገጽታ ስናስተያየው፣ ምንም እንኳን በነገሥታተ አኲስም በአብርሃ ወአጽብሐ ዘመነ መንግሥት ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ያስፋፋች መሆኑ ቢታወቅም፣ የተመሠረተችው ግን በ34 ዓ.ም ነው፡፡ የሐ.ሥ 8፡26 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጃንደረባው ሐዋርያነት በአኲስም ከተማ ከተቋቋመች ጀምሮ እስከ አብርሃ ወአጽብሐ ዘመን ድረስ ግልጽ የሆነ መለያ አላስቀመጠችም ነበር፡፡

በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ዘመነ ጵጵስና እና በአብርሐ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ግን ሕዝባውያኑና ካህናቱ ሊቃውንቱና መኳንንቱ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖችና ነገሥታቱ የሚያምኑት እምነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተብሎ እንዲጠራ ሆነ፡፡

ይህ ስያሜ በመላ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች የእምነታቸው መለያና የክርስትናቸው መጠሪያ ሆኖ እስከ አሁን ድረስም ያገለግላል፡፡ "ኦርቶዶክስ" የሚለው ቃል የጽርዕ ቃል ሲሆን ትርጉሙ የቀና፣ ርቱዕ እምነት የሚል ትርጉም ይኑረው እንጂ ቤተ ክርሰቲያኒቱ ከሌሎች የተለየችበትን አቋም ለይቶ አያሳይም፡፡

"ተዋሕዶ" የሚለው ቃል ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ የተመሠረተችበትን እምነት ወይም ሃይማኖት ስምን ከምግባር አስተባብሮ ይዞ በመገኘቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ መለያ አድርጋ ትጠራበት አለች፡፡ይህ ስያሜ እንደ አጋጣሚ የተገኘ ነገር አልነበረም፡፡ ነገር ግን ንጽሕናን ከቅድስና ሊቅነትን ከመንፈሳዊነት ጋር አሟልተው በያዙ ሙሉ ሕይወታቸውን ለእግዚአበሔር በሰጡ በእምነትና በትምህርት በበሰሉ በሀገር ሊቃውንት ድካምና ጥረት የተገኘ ነው እንጂ፡፡

10.1. ትምህርተ ተዋሕዶ /አንቀጸ ተዋሕዶ/

የተዋሕዶ ትምህርት "አንቀጸ ተዋሕዶ" ይባላል፡፡ ምሥጢረ ተዋሕዶ ሊገኝ የቻለው "ተወሐደ" አንድ ሆነ ካለው አንቀጽ የወጣ የመለኮትና የትስብእት ተዋሕዶን የሚያስረዳ ስለሆነ ነው፡፡ ሃይማኖተ አበው ፊልክስዩስ ሰማዕት ክፍል 2 ተመልከት፡፡
ይህም የልደታቱን መነሻ ሲያዩ ጥቅስ "ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት፤ ወአብ በዲበ ምድር"፣ በሰማይ ያለእናት ከአብ መወለዱን፣ በምድርም ያለ አባት ከድንግል ማርያም መወለዱን እናምናለን፡፡ ተብሎ መግለጫ የተሰጠበት ወይም ባሕርያተ ልደታትን በመገንዘብ "ነአምን ክልኤተ ልደታተ" ተብሎ እንዲታመንበት ያስቻለ ምሥጢር መሆኑ ይታወሳል፡፡

ለዚህም ቅዱስ ባስልዮስ በሰፊው አብራርቶታል፡፡

"ይደልወነ ንእመን ከመ ቦቱ ለወልደ እግዚአብሔር ክልኤቱ ልደታት ቀዳማዊ ልደቱ፣ እም እግዚአብሔር አብ፣ እምቅድመ ኲሉ መዋዕል፡፡ ወዳግማዊ ልደቱ፣ እም እግዚእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ በደኃሪ መዋዕል"፡፡
ለወልደ እግዚአብሔር ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምን ዘንድ ይገባናል፡፡ አንዱ "ከዘመን ሁሉ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው፡፡ ሁለተኛውም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በኋላ ዘመን የተወለደው ልደት ነው"፡፡ መዝ. 2፡7፡፡ 108/109 ቁጥር 3፡፡ ማቴ. 19፡28፣ ዮሐ. 16፡26 እና 28፡፡ ገላ. 4፡4፡፡ ሃይማኖተ አበው ምዕ. 34 ቁጥር 6 ክፍል 5 ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ምዕ. 35 ክፍል 2 ቁጥር 17፡18፡፡

የተዋሕዶ ይዞታ ከሁለት ባሕርያተ ልደታት ምንጭነት አንዱን የአማኑኤልን ህላዌ ቅውም አድርጎ ሲያስገነዝብ ቄርሎስ "ኢትፍልጥ ሊተ እምድኅረ ትድምርት እስመ ዘፈለጠ እንተ ባሕቲቶ ብእሴ፤ ወእንተ ባሕቲቶ አምላከ፤ ቃለ ክልኤተ ይረስዮ ለአማኑኤል" ከተዋሕዶ በኋላ አትለይብኝ፡፡ ከተዋሕዶ በኋላ ብቻውን ሰው፣ ብቻውን አምላክ፣ ቃል የሚል ሰው ቢኖር አማኑኤልን ሁለት ያደርገዋል ብሎአል፡፡

ባስልዮስ ዘአንጾኪያም፡- "ኢይትከፈል ኅበ ክልዔቱ ህላዌያት እምድኅረ ተዋሕዶ እስመ ለምንታዌ አእተታ ተዋሕዶ፣ ወተዋሕዶኒ ያግኅሥ ኲነኔሁ ለምንታዌ፣ እስመ ውእቱ ተዋሕዶ አካላዊ ዘኢትከፈል" ከተዋሕዶ በኋላ ወደ ሁለት ባሕርይ አይከፈልም "ተዋሕዶ ሁለትነትን አስወግዶአልና" የሁለትነትንም ፍርድ አርቆአል፡፡ እርሱ የማይከፈል አካላዊ ተዋሕዶ ሆኖአል፡፡ ብሎአል ሃይማኖተ አበው ዘባስልዮስ ምዕ 96 ቁጥር 17 ክፍል 1፡፡

ቅዱስ አትናቴዎስም "አኮ ዘንብል እስመዝንቱ ወልድ ክልኤ ህላዌ ለአሐዱ ዘንሰግድ፣ ወለካልኡ ዘኢንሰግድ፣ አላ አሐዱ ህላዌ ውእቱ ዘእግዚአብሔር ቃል ዘተሰገወ፡፡ ንሰግድ ሎቱ ምስለ ሥጋሁ አሐተ ስግደተ"፡፡
ይህ ወልድ ለአንዱ የምንሰግድለት ለአንዱ የማንሰግድለት ሁለት ባሕርይ ነው የምንል አይደለም፡፡ ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ባሕርይ አንድ ነው እንጂ፣ ከሥጋው ጋር አንዲት ስግደትን እንሰግድለታለን እንጂ፣ ብሎአል፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ምዕ. 27 ቁ. 15 ክፍል 13፡፡

ቅዱስ አቡሊድስም፡- "ወኢንከፍሎ ለሰማያዊ እምነ ምድራዊ፤ ወኢለ-ምድራዊ እምሰማያዊ፤ እስመ ክፍላትሰ ዐመጻ ውእቱ ወኢነሀቦሙ ለእለ ይብሉ ክልኤ ህላዌ ምክንያተ ለፍልጠት" ሰማያዊ መለኮትን፣ ከምድራዊ ሥጋ፣ ምድራዊ ሥጋንም ከሰማያዊ መለኮት አንለየውም፡፡ መክፈል ክሕደት ነውና፤ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ፣ ለሚሉ ሰዎች ለመለየት ምክንያት አንስጣቸው፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘአቡሊድስ ምዕ. 39 ቁ. 20፡፡

እኛ ግን መለየት፣ ሕፀት፣ መቀላቀል፣ ሳይኖርበት አንድ ሆነ እንላለን፡፡ ከተዋሕዶ በኋላም ወደ ሁለትነት አይከፈልም እንላለን፡፡ ዮሐ. 3፡18፡፡ 1ቆሮ. 8፡7 ሃይማኖተ አበው ዘቴዎዶጦስ ምዕ. 53 ቁ. 31 ክፍል 3፡፡

በምሥጢረ ሥጋዌ በተዋሕዶ ትምህርት ከትስብእትና ከተዋሕዶ በፊት ስለ ነበረው አቋም በአንቀጸ ተከፍሎ ሊነገር ሲገባ ከትስብእትና ከተዋሕዶ ወዲህ ስላለው ምሥጢር ግን በአንቀጸ ተዋሕዶ መነገር እንዳለበት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ሁሉም የሚስማሙበት ነው፡፡

ስለዚህም ዮሐንስ አፈወርቅ "ወአሠረ ክልዔቱ ህላዌያት በበይና-ቲሆሙ" "በተዋሕዶ ሁለቱን እየራስ የሆኑትን ህላዌያት በተዋሕዶ አንድ አደረገ" ይላል፡፡ ሃ.አ.ገጽ. 249 ክፍል 22 ቁ. 22፡
ሳዊሮስ ዘአንጾኪያም "ኢይት ከሐል ይፍልስ ሥጋ ዘይትዌለጥ ኀበ ዘኢትዌለጥ ወበከመ ግብር ዘይከውን እምክልዔቱ ህላዌያት ሶበ የኀብሩ በበይናቲሆሙ ይከውኑ አሐደ፣ እንዘ አሐዱ አሐዱ እምኔሆሙ እምኅላዌሁ እንዘ ቀዳሚ ክልዔቱ፡፡

ትርጉም፤ "የሚለወጥ ሥጋ የማይለወጥ ባሕርይ ወደ መሆን ይለወጥ ዘንድ አይቻልም፣ ከሁለት ባሕርያት እንደሚገኝ ሥራ፣ ጥንቱን ሁለት ሲሆኑ አንዱም አንዱ ከባሕርዩ ሳይለወጥ እርስ በእርሳቸው በተዋሕዶ ጊዜ አንድ ይሆናሉ" ብሏል፡፡
ሃይ.አበው ገጽ 378 ክፍል 8 ቁ. 30፡፡

10.2. ተዐቅቦ ማለት ፡- ተዐቅቦ ማለት "ዐቀበ" ጠበቀ ካለው ግሥ የወጣ ሲሆን ተዐቅቦ ማለት ጥበቃ፣ አለ መለወጥ፣

አለመቀላቀል፣ አለመጣፋት፣ አለመደባለቅ ነው፡፡ ከትንሣኤሙታን በኋላ እንደ ነፍስና ሥጋ ተዋሕዶ ነው፡፡

ቅዱስ አትናቴዎስም ስለ ምሥጢረ ተዋሕዶ በተናገረበት አንቀጹ እንደሚከተለው ይገልጻል፡፡

"ወኪያሁ ለቢሶ ቃለ እግዚአብሔር ሥጋ ኮነ፣ እንዘ ኢይትዌለጥ እምህላዌ መለኮቱ፣ ወለውእቱሂ ሥጋ ዘለብሶ ረሰዮ ዕሩየ ምስሌሁ፣ በአሐዱ ህላዌ እንዘ ኢይትዌለጥ እምህላዌ ሰብእናሁ"፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ከባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ እርሱን ተዋሕዶ ሰው ሆነ፣ የተዋሐደውን ያንን ሥጋም ከሰውነቱ ባሕርይ ሳይለወጥ አንድ አካል፣ አንድ ባሕርይ፣ በመሆን፣ ከእርሱ ጋር አንድ አደረገው፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ምዕ. 30 ቁ. 7፡፡

ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት ዘእንዚናዙም፤

"ወኢፈለሰ ህላዌ መለኮቱ ኅበ ህላዌ ትስብእቱ፣ ወኢህላዌ ትስብእቱ ኀበ ህላዌ መለኮቱ፣ አላ በአሐዱ አካል ወለደቶ እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወበአሐዱ ህላዌ ሰገዱ ሎቱ ሰብአ ሰገል"፡፡
ትርጉም፡- የመለኮቱ ባሕርይ ወደ ሰውነቱ ባሕርይ አልተለወጠም፡፡ የሰውነቱ ባሕርይም ወደ መለኮቱ ባሕርይ አልተለወጠም፡፡ ድንግል ማርያም አንድ አካል ሆኖ ወለደችው እንጂ፣ ሰብአ ሰገልም አንዱ ባሕርይ ሆኖ ሰገዱለት እንጂ፣ ማቴ. 1፡18-25 ምዕ. 2፡1-12፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ምዕ. 60 ቁ. 12 ክፍል 1፡፡

10.3. "የኮነንና" "የኀደረን" አብነት ትርጉም

"ቃል ሥጋ ኮነ" "ቃል ሥጋሆነ" "ወኀደረ ላዕሌነ" "በእኛም አደረ" በሚል በቅዱስ መጽሐፍ አባባል የተዋሕዶ ምሥጢር መመሥረቱ ይታወቃል፡፡ ዮሐ. 1፡14፡፡ "ኮነና ኀደረ" ሆነ፣ አደረ፣ እነዚህ ሁለቱ የተዋሕዶውን አንቀጽና የተዐቅቦን ምሥጢር በመያዝ እንደ አለቃና እንደ ጠበቃ ሆነው ይጠባበቃሉ፡፡ "በኮነ" የተነሱት መናፍቃን በኀደረ "በኀደረ" የተነሡት መናፍቃን "በኮነ" ይረታሉ "ኮነ" "ኃደረ" እንደ አለቃና እንደ ጠበቃ ይጠባበቃሉ እንጂ አንዱ ከሁለተኛው ተነጥሎ ተለይቶ "ኮነ" ለብቻው "ኀደረ" ለብቻው በመነጣጠል የተዋሕዶን ምሥጢር ጠንቅቆ ለመጠበቅ አያስችሉም፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ሊቃውንት የብሂላዊ ትርጓሜ አብነታዊ አዋጅ ነው፡፡

10.4. የእነዚህም ትንትና ለመርዳት የሚከተለውን ይመለከቷል፡፡

ለምሳሌ ንስጥሮስ "ኮነ"ን የ"ኀደረ"ን ንባብ ይዞ ምሥጢሩን ሳይመረመር "በአንድ ክርስቶስ ሁለት ህላዌያት አሉ" ብሎ በመተርጐም ውስጣዊ መለያየትን፣ መፈራረቅን፣ ቡዓዴንና ፍልጠትን፣ በምሥጢረ ተዋሕዶ አመጣ፡፡ ለዚህም የ"ኮነ"ን እውነተኛ ትርጉም ወይም ፍቺ የያዘ ከ"ኀደረ" ጋር የሚያገናኝ የሚያስማማ ተዐቅቦ እንዲኖር አስፈለገ፡፡ "እነሆም ዘእንበለ ቡዓዴ፣ ዘእንበለ ፍልጠት፣ በኢተላፅቆ፣ ያለ መለየት፣ ያለ መከፈል፣ ያለመነባበር፣ /አነባብሮ/ የሚሉ ቃላት የ"ኮነ"ን ምሥጢር ይዘው "ኀደረ" ያለውን አንቀጽ እንዲጠብቁ ተደርጎ የሥግው ቃል በተዋሕዶ ተጠናቀቀ፡፡

አውጣኪ በአንዱ ሥግው ቃል /ክርስቶስ/ ቱስሕት /መደባለቅ/ ውላጤ /የሰውነት/ መለወጥ ሚጠት /መለዋወጥ/ እንዳለበት፣ ሰውነቱ ወደ አምላክነቱ እንደ ተለወጠ ተናገረ፡፡

አውጣኪ "ኀደረ"ን በመተው የ"ኮነ"ን ፍቺ በተሳሳተ አተረጓጎም "ኮነ"ን ተለወጠ በሚል ቃል ተርጒሞ ተሰናከለበት፣ እንደ እሱ ሐሳብ ወይም አተረጓጐም ቢሆን ኖሮ ምሥጢረ ተዋሕዶን ደመሰሰበት፡፡

ለዚህም ጠንቀኛ ትርጒም መጠበቂያ /ልጓም/ አስፈለገ፡፡ እነሆም ዘእንበለ ቱስሕት፣ ዘእንበለ ውላጤ፣ ዘእንበለ ሚጠት፣ ያለመደበላለቅ፣ ያለመለወጥ ያለመለዋወጥ፣ ያለመመላለስ፣ የሚሉ ቃላት የ"ኀደረ"ን ምሥጢር ይዘው የ"ኮነ"ን ፍቺ ወደሌላ እንዳይሄድ ይኸውም በመለወጥ እንዳይተረጐም ይጠብቁ ዘንድ ተደረገ፡፡

10.5. ስለአንቀጸ ተአቅቦ መጻሕፍት ጠንቅቀው ያስረዳሉ ለዚህም፤

አቡሊድስ እንደ ገለጸው "ወዓዲንብል አልቦቱ ቱሳሔ ወኢካልዕ ነገር ዘከመዝ ወኢይተልዎ ንባበ ቱሳሔ በእንተ ነገረ ተዋሕዶ ወልድ ወልደ እግዚአብሔር ተሰነአወ ወኮነ ሰብአ ወበእንተ ዝንቱሂ ነገር ኢይበው ዕቱሳሔ ውስቴቱ ዘከመ የአምኑ እልክቱ ወኢተወለጠ ህላዌ ቃል ኀበ ህላዌ ትስብአት፣ ወህላዌ ትስብእት ኀበ ህላዌ ቃል፣ ዳዕሙ ይሄልው ክልኤቱ ህላዌያት በበህላዌሆሙ እንበለ ውላጤ፡፡

ዳግመኛም መቀላቀል ይህንንም የመሰለ ሌላ ነገር የለበትም እንላለን፣ ተዋሕዶው እውነተኛ ስለሆነ ተቀላቀለ ማለት አይስማማውምና፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ ዋሕድ ነፍስን ሥጋን ነስቶ ሰው ሆነ ባልን ጊዜም ስለዚህም ነገር ቢሆን እነዚያ እንደሚያምኑ መቀላቀል የለበትም፣ የቃል ባሕርይ የሥጋን ባሕርይ ወደመሆን፣ የሥጋ ባሕርይም የቃልን ባሕርይ ወደመሆን፣ አልተለወጠም፣ ሁለቱ ባሕርያት ያለ መለዋወጥ፣ ባለመቀላቀል፣ ጸንተው ይኖራሉ እንጂ፡፡ ዮሐ. 1፡ቁ .1-18፤ 3፡18 1ቆሮ. 8፡6፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘአቡሊድስ ምዕ. 43 ቁ. 5-6 ክፍል 1፡፡

በዚህም ተዐቅቦ የሥግው ቃል ተዋሕዶ ተጠነቀቀ፣ ታወቀ፣ ይህ ተዐቅቦ ባይኖር የአውጣኪን ግንጥል ሐሳብ ለተከተለ ሰው የተዋሕዶ እምነቱንና በቅዱሳት መጻሕፍት ያለው የአተረጓጐሙን መንገድ ያቃውስበት ነበር፡፡
መናፍቃን "ኮነ" ያለውን ይዘው "በትረ ሙሴ ኮነት ዓርዌ ምድር" "የሙሴ ብትር ዓርዌ ምድር እባብ ሆነች" ዘዳ. 4 ቁ. 3፡፡

"ብእሲተ ሎጥ ኮነት ሐወልተ ጼው" ማለት "የሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት ሆነች" ዘፍ. ም. 19 ቁ. 26፡፡ የሚለውን ገጸ ንባብ ይዘው ምሥጢሩን ሳይመረምሩ መለኮቱ ተለውጦ ሥጋ ሆነ ብለው ለተነሱ መልሱ "ኀደረ" አለባችሁ "ኀደረ" ብለው ለተነሱ መናፍቃን ደግሞ "ኮነ" አለባችሁ፣ በማለት በ"ኀደረ" የተነሱ መናፍቃን በ"ኮነ"፣ በ"ኮነ" የተነሱ መናፍቃን በ"ኀደረ" ይረታሉ፡፡

ማስጠንቀቂያ "ወበከመ ኀደርኩ ምስለ ሙሴ ከማሁ ኀደርኩ ምስሌከ" ማለት "ከሙሴ ጋር እንደሆንኩ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን እንዳለው" አይደለም፡፡ ኢያሱ ም. 3 ቁ. 7፡፡
እግዚአብሔር በነቢያት፣ በሐዋርያት፣ በሊቃውንት፣ በቅዱሳን፣ እንደሚያድር በሥጋ ማርያም አደረ አይባልም፡፡

"ወኢኀደረ ውስቴቱ ዘከመ ኲሉ ሰብእ አላ ለሊሁ ነሥአ ሥጋ ሎቱ ለባሕቲቱ ወአስተዓመሮ በተዋሕዶ፡፡ አኮ ከመ ኲሎሙ ነቢያት ዘሰፍሐ ቦሙ ወተናገረ ውስቴቶሙ አላ ኮነ ሰብአ ፍጹመ ቃል ሥጋ ኮነ ወኢተወለጠ ኢያፍለሰ መለኮቶ ኀበ ከዊነ ትስብእት፣ ወረሰየ ፍጻሜሁ ቅድስተ በብርሃን ምስለ መለኮት"፡፡

በሰው ሁሉ እንደሚያድርም አላደረበትም፣ እርሱ ሥጋን ነሥቶ ለእርሱ ለብቻው ገንዘብ አደረገው እንጂ፡፡ አድሮ እንደ ተናገረባቸው እንደ ነቢያት ሁሉ አይደለም፡፡ ፍፁም ሰው ሆነ እንጂ፣ ቃል ሥጋ ሆነ አልተለወጠም፡፡ መለኮቱ ሰው ወደ መሆን አልለወጠውም፡፡ ከመለኮት ጋር ጽኑዕ አንድነቱን በተዋሕዶ አደረገ እንጂ፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ ምዕ.57 ቁ. 26-28፡፡

በዚህም "ቃል ሥጋ ኮነ" "ቃልም ሥጋ ኾነ" አለ እንጂ "ኀደረ በሥጋ" አላለም፡፡ የመለኮትና የትስብእትን ተዋሕዶ የሚያስረዳ የነፍስ የሥጋ ተዋሕዶ ባይኖር ኖሮ በየጊዜው እንደ አሸን የሚፈሉ መናፍቃን ሰውን ሁሉ እያሳቱ በክህደት ማዕበል ባናወጡ ነበር፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ