Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

 

bedokimas betበመ/ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሣሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ መንበረ ፓትርያርክ

የትምህርትና ማሠልጠኛ ዋና ኃላፊ

ምልጃ ዘመናትን ተሻግሮ የመጣውና እውነት የሆነው ደጋግ አባቶች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የጻፉት መጽሐፍ ቅዱስ ከጥንት ጀምሮ የተጀመረ፤ ራሱ ልዑል እግዚአብሔር ያዘዘው እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ለዚህም ሕዝበ እስራኤል ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜና መቅሠፍትና መከራ በሚጸናባቸው ወቅት ወደ መንፈሳውያን መሪዎቻቸው እየቀረቡ ወደ እግዚአብሔር አማልዱን እያሉ ሲማጸኑ፤ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ደግሞ የሕዝባቸውን ጥያቄ ወደ እግዚአብሔር እያቀረቡ ምሕረትንና ቸርነትን እያስገኙ እንደመጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል (ዘፍ. 18.20፡፡ ዘፍ. 20.7-10፡፡ ዘጸ. 32። ዘኁ. 16.41-50፥ 21.7-9፡፡ ኢዮ. 42.7-8፡፡ ኤር. 42.1-11)፡፡

እንዲሁም ሰውን ከሰው ጋር የሚያስታርቁና የሚያ ማልዱ ወገኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ክብር እንዳ ላቸው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ "የሚያስ ታርቁ ብፁዓን ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና"፡፡ በማለት ክብራቸውን ይገልጻል፡፡ (ማቴ. 5.9)፡፡ ስለዚህ ምልጃ እግዚአብሔር ያዘዘውና የሚወደው ቅዱስ ተግባር ነው፡፡

 

በአዲስ ኪዳን የአማላጅነት መሠረት ድንግል ማርያም ናት፡፡

ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አማላጅነት ከማየታችን በፊት በቅድሚያ ስለ መመረጥዋና ቅድስናዋ በመጠኑ እንደሚከተለው በቀረቡት ንዑሳን ክፍሎች ማየት ለተነሣንበት ዋና ርእስ ወሳኝ ነው፡፡

እነዚህም፡-

ሀ. ድንግል ማርያም መሠረተ ድኂን ትሆን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር የተመረጠች ናት፡፡

ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ለመሠረተ ድኂን የተመረጠች ናት፡፡ ለዚህም አዳምና ሔዋን የአምላካቸውን ትእዛዝ አፍርሰው የተሠጣቸውን ጸጋና ግርማ አስነጥቀው ራቁታቸው በገነት ቊጥቋጦ በተደበቁበት ጊዜ "አዳም የት ነህ? ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ቃል ከአዳም ዘር ከምትወለደው ቅድስት ዘር ተወልዶ እንደሚያድነው የተናገረው መለኮታዊ ትንቢት እንደሆነ እንረዳለን (ዘፍ. 3.9። ማቴ. 18.11-13)፡፡ እንዲሁም ልዑል እግዚአብሔር እባቡንና በእባቡ ውስጥ የተሰወ ረውን ዲያብሎስ ሲረግም "ባንተና በሴቲቱ መካ ከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፡፡ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል:: አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅ ጣለህ" (ዘፍ. 3.15) ሲል ለጊዘው በሔዋንና በእባብ መካከል ያለው ጠብ የሚያመለክት ሲሆን መሠረታዊና እውነታዊ ትርጒም ግን ባንተ፥ በዲያብሎስና በድንግል ማርያም ማለት ነው፡፡ 'ከሴቲቱ የሚወለድ ራስህን ይቀጠ ቅጣል' ያለውም ከድንግል ማርያም ስለሚወለደው የእግዚ አብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ወልድ የተናገረው መለኮታዊ ትንቢት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህን እውነት መሠረት አድርጎ "ወአመ በጽሐ ዕድሜሁ ፈነወ እግዚአ ብሔር ወልዶ ወተወልደ እምብእሲት -- የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ" (ገላ. 4.4) በማለት አረጋግጦታል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ አባ ሕርያቆስም "አንቲ ውእቱ ተስ ፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት" አዳም ከገነት በተሰደደ ጊዜ ተስፋው አንቺ ነሽ በማለት ያስረዳል (ቅዳሴ ማር.)፡፡

 

ለ. የድንግል ማርያም ንጽሕናና ቅድስና ከመላእክት ንጽሕናና ቅድስና በላይ ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት ደማዊና ሥጋዊ ባሕርይ የሌላቸው ረቂቃንና እሳታውያን እንደሆኑ ይታወቃል (መዝ. 103÷4 (104) ማቴ. 22÷30)፡፡ ይሁን እንጂ "ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ ድንጋሌ ኅሊና እስመ አበሱ በፍትወት ወወረዱ ምድረ በመዋዕል ዘቀዳሚ -- ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ለመላእክትስ እንኳን አልተቻላቸውም፤ በቀደመው ዘመን ያልተሰጣቸውን ሽተው በድለው ከሰማይ ወደ ምድር ወርደዋልና" (መቅ.ተአ.ማ.) ተብሎ እንደተጻፈው ከማኅበረ መላእክት መካከል ኃጢአትን ሠርተው ከማዐርጋቸው ወድቀዋል (2ጴጥ. 4÷4 ይሁዳ. 1÷6 ራእ. 12÷7-9)፡፡ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ግን ምድራዊት የአዳምና የሔዋን ዘር ብትሆንም ከጥንት ጀምሮ ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት፤ ከኅሊዮ፥ ከነቢ ብና ከገቢር የተለየች፤ ርኵሰተ ሥጋና ርኵሰተ ሕሊና የሌላት፥ አደፍ፥ ጒድፍ የማታውቅ፥ ንጽሕት ፍጥረት ናት፡፡

ድንግል ማርያም ከወደቁት መላእከት ብቻ ሳይሆን ከቅዱሳን መላእክትም በእጅጉ ትበልጣለች፡፡ ምክንያቱም ኪሩቤልና ሱራፌል የማይነኩት፤ የማይቀርቡት፤ ብሎም በዓይኖቻቸው መመልከት የማይችሉትና በፊቱ የሚበረክ ኩለትን አምላክ ወልዳለችና (2ሳሙ. 22÷11 ኢሳ. 6÷ 1-3 ኢሳ. 37÷16። ራእይ 5÷8-11 7÷12)፡፡

ከላይ ከተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በተጨማሪ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን "የዐቢ ክብራ ለማርያም እምኵ ሉሙ ቅዱሳን እስመ ድልወ ኮነት ለተወክፎ ቃለ አብ -- ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፡፡ የአብ ቃል ለመቀበል ተገብታ ተገኝታለችና (ውዳሴ ማር. ዘረቡዕ)፤ ማርያም ሆይ! መላእክት ያገኑሻል፥ ሱራፌልም ያመስግ ኑሻል፤ በኪሩቤል በሱራፌል ላይ አድሮ የሚሮር ጌታ መጥቶ በማኅፀንሽ አድረዋልና (ውዳሴ ማር. ዘዓርብ) በማለት ይመሰክሩላታል፡፡ በመሆኑም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናና ቅድስና ከሁሉም መላእክት ንጽሕናና ቅድስና በላይ ነው፡፡

 

ሐ. እመቤታችን ከፍጥረተ አዳምም በቅድስናና በንጽሕና የሚስተካከላት የለም፡፡

አዳምና ሔዋን ሕገ እግዚአብሔርን ከመተላለፋቸው በፊት ንጽሐ ጠባይእ ያላደፈባቸው ንጹሐን፥ ቅዱሳን እንደነበሩና ኋላ ግን በኀልዮ፥ በነቢብና በገቢር ኃጢአት ሠርተዋል፡፡ ሕገ እግዚአብሔርን ከመተላለፋቸው የተነሣም ሞተ ሥጋና ሞት ነፍስ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ከእነርሱ የተገኘች ድንግል ማርያም ግን እንከን ያለተገኘባት ንጽሕትና ቅድስት ናት፡፡ ከዚህም የተነሣ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት፡- "ወኢረኲሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ -- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን ከድንግልናዋ አልተለወጠችምና (ርኵሰተ ሥጋና ርኵሰተ ኅሊና አልተገኘባትም) ሃይ. አበ. ቴዎዶስዮስ ምዕ. 53÷22 ሕቅ. 44÷1-3)፡፡

የኪስኪስ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስ እመቤታችንን ለመጠብቅ ስለተመረጠ ቅዱስ ዮሴፍ በተናገርበት አንቀጹ "ከንጹሕ ዘር የተፈጠረች ድንግል የእግዚአብሔር ማደሪያ እንድትሆን አላወቀም፡፡ ዘለዓለም መለወጥ የሌለበት ዳግማይ አዳም ክርስቶስ ድንግልና ካላት ገነት እመቤታችን እንዲገኝ አላወቀም" (ሃይ.አበ. ኤራቅሊስ ምዕ. 48፥ ቁ. 31። መኃ. 4.12)፡፡ "ማርያምሰ ታሐቱ እምትካት ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ ማርያም -- ከጥንት ጀምሮ በአዳም ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቊ ታበራ ነበር" (ሕዳር ጽዮን አራራይ)።

"ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐተ ከመ አንስት እለ እምቅድሜኪ ወእምድኅሬኪ አላ በቅድስና ወበንጽሕ ስርጉት አንቲ -- ድንግል ሆይ፥ ከአንቺ አስቀድመውና ከአንቺ በኋላ እንደ ነበሩና እንዳሉት ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም፤ በቅድስናና በንጽሕና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ" (ቅዳ. ማር.) በማለት ይመሰክሩላታል፡፡

 

መ. ድንግል ማርያም በብዙ ኅብረ መልክ ተመስላለች።

በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስለ ሰው ልጅ ተስፋ ድኅነትን ለማብሠር በየጊዜው የተነሡ ነቢያትም ድንግል ማርያምን በብዙ ምሳሌ እየመሰሉ ተናግረውላታል፡፡ በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል፦ የወይራ ቅጠል በመያዝ የጥፋት ውኃ መድረቊን ያበሠረች የኖኅ ርግብ (ዘፍ. 8.11)፤ ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥል፥ ሐመልማልም ነበልባሉን ሳያጠፋ በተዋሕዶ ስትምቦገቦግ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ (ዘጸ. 3÷1)፤ ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች፥ ያበበችና ያፈራች የአሮን በትር፤ የኃያላን ኃያል ሳይከፍት ግብቶ ሳይከፍት እንደተዘጋች የወጣባት የሕዝቅኤል በር (ሕዝ. 44÷2-5) ምሳሌዎችዋ ናቸው፡፡

ምሳሌ የሆኑበትም ምክንያት ዘመነ ፍዳና ዘመነ ኵነኔ አልፎ የሰላም፥ የፍቅር፥ የነጻነትና ድኅነትና የምሕረት ዘመን እንደደረሰ ያበሰረች ድንግል ማርያም በመሆንዋ በኖኅ ርግብ ትመሰላለች፡፡ እንዲሁም ነበልባለ እሳት የተሰኘው መለኮት ሲሆን፥ ሐመልማል የተሰኘችውም ድንግል ማርያም ናት፡፡ ስለሆነም እሳተ መለኮትን ተሸክማለችና የሲና ዕፅ ትባላለች፡፡ ድንግል ማርያም ያለዘርዐ ብእሲ በኅቱም ድንግልና ፀንሳ፥ በኅቱም ድንግልና ፍሬ ሕይወት ጌታችንን በመውለዷም በአሮን በትር ተመሰላለች፡፡ እንዲ ህም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልስ ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙም ኢየሱስ ትይዋለሽ ብሎ ያበሠራት "የእግዚአ በሔር አገልጋይ እነሆ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ "ስትለው በድምፅ አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍስዋ ነፍስን ነሥቶ፥ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ፥ በኅቱም ድንግልና በመውለዱ ነቢዩ ሕዝቅኤል ባያት በር ትመሰላለች (ሉቃ. 1÷38) ፡፡

 

ሠ. ድንግል ማርያም ጌታን ከመውለዷ በፊት፥ በወለ ደች ጊዜና ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡

አስቀድሞ በትንቢተ ኢሳይያስ "ድንግል ትፀንሳለች ወንድልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች" ተብሎ እንደተጻፈ፤ ድንግል ማርያም ከመውለዷም በፊት፤ በወለደች ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት፤ ተፈት ሖም የላትም (ኢሳ. 7.14)። ኦርቶዶክሳውያን ሊቃ ውን ትም "እናንት አላዋቂዎች የድንግል ማርያም ጌታን መፅነ ሷን መውለዷን እንደሌሎች ሴቶች አታስመስሉ፤ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ይህ ሊነገርባት አይገባም፤ የእግዚ አብሔርን ቃል ያለ ዘርዐ ብእሲ ፀንሳ ምጥ ሳይሰማት ወለደችው እንጂ (ሃይ.አበ. ጎርጎርዮስ ምዕ. 60.19-20)።

"ሥጋ የሌለው እርሱ ሥጋዋን ተዋሕዶ እንደ ሰው ሁሉ ዘጠኝ ወር በእናቱ በጌትነቱ ሳለ በማኅፀኗ ተፀነሰ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀንም ከተፈጸመ በኋላ የሚወለ ድበት ቀን ሲደርስ በማይመረመር ግብር በኅቱም ድን ግልና ተወለደ ማኅተመ ድንግልናዋም አልተለወጠም፤ ማኅ ተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ተወለደ እንጂ" (ቅ.ጎርጎርዮስ ነባቤ. ሃይ. አበ. ምዕ. 60.12። ቅ.አትናቴዎስ ሃይ.አበ. ምዕ. 27.37። ሕዝ. 44.1-3)።

 

ረ. ድንግል ማርያም የሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ እናት ናት፡፡

እመቤታቸን ቅድስት ድንግል ማርያም የሕዝበ ክርስ ቲያን ሁሉ እናት እንደሆነች ልበ አምላክ ዳዊት "በአባቶ ችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፡፡ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፡ ፡ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ" (መዝ 44.16 /45/) በማለት ይመሰክራል፡፡ ድንግል ማርያምም እግዚአብሔርን ባመሰገነችበት ጸሎትዋ ላይ "እነሆም ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና" ስትል ታረጋግጣለች (ሉቃ. 1÷48)።

ስለሆነም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ እናቱን፦ "አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ"፤ ደቀ መዝሙሩን፦ "እናትህ እነኋት" ባለው መሠረት፤ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አስተ ምህሮና እምነት ለምንኖር ሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን እመቤታችን የቃል ኪዳን እናታችን ናት (ዮሐ. 19÷26)፡፡

 

የእመቤታችን አማላጅነት በዶኪማስ ቤት

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ " በልዑል ዙፋን ላይ ተቀ ምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ፤ ሥጋ ሳይሆን የነበረ፥ የማይ ዳሰስ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ፤ ኃጢ አትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ (ሃይ.አበ. ምዕ. 66÷19። ሉቃ. 2÷6-19) እንዳለው፤ እግዚአብሔር በራሱ የተናገረው መለኮታዊ ትንቢትና በነቢያት አድሮ ያናገረው ትንቢት እውን ሆኖ የማይታይና የማይመረመር አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ሥጋን ተዋሕዶ በተገለጠ ጊዜ የመጀመሪያውን አምላካዊ ተአምር በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት እንዳደረገ፤ ቅድስት ድንግል ማርያም፥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ደቀ መዛሙርቱ በሰርጉ ቤት እንደ ነበሩ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ያስረዳል (ዮሐ. 2.1-11)፡፡

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ "ማርያምሰ ተንከተመ እግዚአብሔር ኮነት ለነ (የጥር ፯ እስመ ለዓለም) -- ማርያምስ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ድልድይ ሆነችልን" እንዳለው፤ ለሰርግ ዕድምተኞች የተዘጋጀ የወይን ጠጅ ማለቁን የተረዳች ርኅርኅተ ልቡና ድንግል ማርያም እውነተኛውን መፍትሔ መስጠት ወደሚችለው ልጇና አምላኳ ጌታችን መድኃኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ "የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም" ብላ ባቀረበችው ጥያቄ "አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ፤ ጊዜየ ገና አልደረሰም"፤ የሚለውን ጥልቅ ምሥጢር ያዘለ ቃል ከተናገረ በኋላ በቀጥታ ጥያቄዋን ተቀብሎ ውኃውን ወደ ወይን ቀይሮአል፡፡ በዚህም የአስተና ጋጆቹን ድንጋጤና የሰርጉ ባለቤትን ኀፍረት አስወግዷል፡፡ የመጀመርያ ተአምርንም አድርጎአል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጅዋና በዶኪማስ መካከል ድልድይ ሆና በሰርጉ ቤት ላይ አንጃቦ የነበረውን ጭንቅና ኀዘን በአማላጅነቷ እንዳስወገደች እናያለን፡፡

በዚሁ ላይ ጌታችን "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም" ያለው ኃይለ ቃለም ጥልቅ የሆነ ሃይማኖታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሥጢር ያለው ከመሆኑም በላይ አባባሉም የቊጣ ወይም የእምቢተኝነት ቃል ሳይሆን የእሺታና የአክብሮት አገላለጽ እንደሆነ በሚገባ መረዳት ተገቢ ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድንግል እናቱን "ሴትዮ" ብሎ በመጥራቱ አላከበራትም የሚል የተሳሳት አስተሳሰብ ያለው ሰው ካለም ቢያንስ ቀጥለው የተጠቀሱትን በማስተዋል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም፦

1ኛ) "ሴትዮ" የሚለው ቃል በእኛና አሁን ባለው መረዳት አሉታዊነት ያለው መስሎ ቢሰማንም በዕብራውያንና አዲስ ኪዳን በተተረጐመበት የግሪክ ቋንቋ ግን የአክ ብሮት መገለጫ ነው፡፡ በዚያውም ላይ "አባትህንና እናትህን አክብር" ብሎ ሕግ የደነገገ እግዚአብሔር፥ ቃል ኋላም እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፥ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም (ዘጸ. 20.12። ዘዳ. 5.16። ማቴ. 5.17) ብሎ ያጸናው ጌታ፤ ከሁሉም በላይ አብልጦ ለእናትነት የመረጣትን እናቱን አላከበረም ብሎ ማሰብ ፍጹም ድፍረት እንደሆነ ሊረዳና ሊገነዘብ ይገባል፡፡


2ኛ) ጌታችን ድንግል ማርያምን "ሴትዮ" ብሎ የጠራበት ዋና ምክንያት ጥልቅ የሆነ ቲኦሎጂካል (Theological) ትንታኔ (ትርጒም) አለው፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲ ያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ "እንዘ ሥዉር እምኔነ ይእ ዜሰ ክሡተ ኮነ ማየ ረሰየ ወይነ ምልጣን (አንገርጋሪ) ዘቃና -- ከእኛ ተሰውሮ የነበረ፥ ማለትም በዓይነ ትንቢትና በዓይነ ሃይማኖት እንዲሁም በቃለ መጻ ሕፍት ብቻ እየተመራን እናመልከው የነበረ አምላክ አሁን ግልጽ ሆኖ ታየ፡፡ ውኃውንም የወይን ጠጅ አደረገ" እንዳለው፤ አስቀድሞ "ባንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርዋና በዘርህ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፡፡ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንትም ተረከ ዙን ትቀጠቅጣለህ" ብሎ የተናገረው መለኮታዊ ትንቢቱ እንደተፈጸመ ለማመልከት ነው፡፡ ምክንያቱም አስቅደሞ በኦሪቱ በውስጥ ታዋቂነት ሴት ብሎ የጠራት ድንግል ማርያም ስትሆን፥ የሴቲቱ ዘር የተባለ ደግሞ ራሱ በኅቱም ድንግልናዋ ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወለደና ሥጋችን ተዋሕዶ የተገለጠ፥ ውኃውን ወደ ወይን የቀየረ፥ የዲያብሎስን ራስ በዕለተ ዐርብ የቀጠቀጠ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፡፡ በመ ሆኑም "ሴትዮ" ያለው ከዚህ ምሥጢርም በማያያዝ ነው (ዘፍ. 3.15። ገላ. 4.4)፡፡

"ካንቺ ጋር ምን አለኝ?" ስላለውም፥ ሊቃውንት አባቶቻችን፦ "ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለ? የምትዪውን አደርገዋለሁ፡፡ የምትዪኝን ላለማድረግ ምን ምክንያት አለኝ? አደርገዋለሁ" የሚለውን ፍቺና ትንታኔ በመስጠት ተርጒመውታል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ከዚህ ጋር ተመሳ ሳይነት አባባል ያላቸው በርካታ መረጃዎች ተጠቅሰው ይገኛሉ (1ነገ. 17.18። ማር. 1.24)፡፡

መሠረታዊ ትርጒሙም ይህ ስለሆነ ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን የተናገረውን ቃል በሚገባ ስለተረዳች፥ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ እንደሚቀይር ስላወቀችና ስለአመነች ደግማ ልጇን አልጠየቀችውም፡፡

"ጊዜዬ ገና አልደረሰም" ያለበት ዋና ምክንያትም፦ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደእኛ የመጣው ዋና ምክንያት ራሱን በዕለተ ዐርብ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሠውቶ በሚከፍለው መሥዋዕትነትና በሚያ ፈሰው ደሙ በሰው ሊወገድ ያልተቻለው በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው የጥል መጋረጃና የኃጢአት ግድግዳን በማፍረስ ዓለምን (የሰው ልጅን) ለማዳን ነው (ኤፌ. 2.13-15። ቈላ. 2.14-15)፡፡ ይህ ደግሞ የሚፈጸመው ገና በዕለተ ዐርብ በመሆኑ ይህንን ለማመልከት ጊዜዬ ገና አልደረሰም አለ፡፡ ስለዚህ እውነት በትክክል ለመረዳትም ቀጥለው የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሚገባ እንዲህ ሲሉ ያረጋግጣሉ፡፡

"ሊይዙት ፈልገው ነበር ነገር ግን ጊዜው ገና ስላል ደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም" (ዮሐ. 7.30)። እንዲ ሁም "ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ተናገረ ጊዜው አልደረሰምና ማንም አልያ ዘውም" (ዮሐ. 8.20) በማለት ያስረዳሉ፡፡

መከራ የሚቀበልበትና በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን የሚታረቅበትና የሚያስታርቅበት ሰዓት እንደ ደረሰ ሲያስ ረዳም፡- "እንግዲህ ተኙ፥ ዕረፉም፤ እነሆ ሰዓቲቱ ደርሳ ለች፤ የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል፡፡ ተነሡ እንሂድ! እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል (ማቴ. 26.45)። "የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል" (ዮሐ. 12.23)። "ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፡- አባት ሆይ ሰዓቱ ደርሶአል (ዮሐ. 17.1) ይላል፡፡ ስለዚህ ጌታችን ጊዜዬ ገና አልደረሰም ያለው ስለዚህ እንደ ሆነ በትክክል እንረዳለን፡፡

አማላጅዋ ርኅርኅት ድንግል ማርያምም ልጅዋ የመለ ሰላት መልስ የእሺታና አደርገዋለሁ የሚል እንደመሆኑ መጠን ለአገልጋዮቹ ጌታችን በሚላቸውና በሚያዛቸው ሁሉ ፈጽመው እንዳይጠራጠሩና ያላቸውን ሁሉ ያለም ንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያደርጉ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" ብላ ማዘዝዋ በግልጽ የምናየው እውነት ነው፡፡ ስለሆነም ድንግል ማርያም ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃዋን ተቀብሎ በፊት ይጠጣ ከነበረ የወይን ጠጅ ይልቅ ወደሚጣፍጥ የወይን ጠጅ ቀይሮታል፡፡

ለዚህም አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፡- "ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፡፡ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን። አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ አቆይ ተሃል" ብሎ በአድናቆት ሲናገር እናነባለን፡፡ ስለዚህ በእመቤታችን አሳሳቢነት የተቀየረ የወይን ጠጅ በዛው ለነበሩት እንግዶች የሚያስደስትና የሚጣፍጥ እንደሆ ነላቸው ሁሉ ከቅድስት ድንግል የተወለደው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜው ሲደርስ በቀራንዮ መስቀል የቈረሰው ሥጋውና ያፈሰሰው ደሙ ግን ከዚያ በበለጠ አምኖ ለሚቀበለው ሁሉ ሕይወት፥ መድኃኒትና ስርዬተ ኃጢአት የሚሰጥ ነው (ዮሐ. 2.9 ማቴ. 26÷26 ዮሐ. 6÷51-56)።


እመቤታችን ድንግል ማርያም የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን አማላጅና የአማላጅነት መሠረት ናት ያልነውም ከዚህ እውነት በመነሣት ነው፡፡ በቤተ ዶኪማስ የተፈጸመ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትም እስከ ምጽአት የሚቀጥል በመሆኑም በቃል ኪዳንዋ አምነን "ሰአሊ ለነ ቅድስት -- ቅድስት ሆይ ለምኝልን" ለምንላት ሁሉ ከአምላካችን በረከትንና ምሕረትን እናገኛለን፡፡
ማጠቃለያ
በመሆኑም ሁላችን ድንግል ማርያም "ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" እንዳለችው፤ እንዲሁም ቅዱስ ገብርኤል፦ "ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ" ብሎ እንዳመሰገናት፤ ቅድስት ኤልሣቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝታ፦ "አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፡፡ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?" ብላ እንዳመሰገነቻት፤ እኛም፦ በቅድስናዋና በንጽሕናዋ ብሎም በአማላጅነቷ አምነን የሚገባትን የጸጋና የእናትነት ክብርና ምስጋና ልናቀ ርብላት ይገባል፡፡ ከዚህ እውነተኛ አስተምህሮና በጽኑ ዐለት ላይ ከተመሠረተች ቤተ ክርስቲያናችን ሳንናወጥ ስለ ሃይማኖታችን ጠንቅቀን ልናውቀና ባወቅነውም እውነት ልንኖር ይገባናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የፎንት ልክ መቀየሪያ