Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ከመምህር ዕንቈባሕርይ ተከሥተ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ

በቀጥታ ወደ በዓሉ አከባበር ከመግባቴ በፊት የጾመ ዐርብ አጀማመርና አፈጻጸም የቀናት ልዩነት በጥቂቱ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጾመ ሁዳዴ /ጾመ አርብአ/ የሚጾመው 55 ቀናት ናቸው፡፡
ይኸውም፡-


1. 7 ቀናት የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡
2. 40 ቀናት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጾም ከቅድስት እስከ ተጽዒኖ ያለው ነው፡፡ በውስጡ 6 ሳምንት አሉት፡፡ እነርሱም ቅድስት፣ ምኲራብ፣ መጻጒዕ፣ ደብረ ዘይት፣ ገብርኄር፣ ኒቆዲሞስ ናቸው፡፡
3. 8 ቀናት የሰሙነ ሕማማት ሳምንት ነው፣ ይህም ማለት ከሆሣዕና በፊት ካላቸው ቅዳሜ ቀን ጀምሮ እስከ ከሥቅለት በኋላ ያለችው ቅዳሜ ነው፡፡ ጠቅላላ ድምር 55 ቀናት ናቸው፡፡ በአምሳ ስድስተኛ ቀን በዓለ ትንሣኤ በእለተ እሑድ ይከበራል፡

ከዘወረደ እስከ ኒቆድሞስ

1ኛ. እሑድ ዘወረደ /ቀዳማይ ሳምንት/

የመጀመሪያው ሣምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል ተብሎ የሚታወቀው ከሠኑይ /ሰኞ/ ጀምሮ 7 ቀናት የሚጸመው ነው፡ እንደ ቅዱስ ያሬድ ይትበሐል የዘወረደ ቃለ እግዚአብሔር ከቅበላ ሰንበት ጀምሮ /ዋዜማው/ ይባላል፡፡
ዘወረደ የተባለበት ምክንያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ሰው ሆኖ ለመዳኑ ለመጠየቅ ነው፡፡
የዘወረደ፣ መዝሙር፡- "ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሐት" "እግዚአብሔርን በፍርሐት አገልግሉ" /ልብን ስለማስገዛት፡፡/
የቁመቱ ዓይነት መወድስ ቁመት ሲሆን ድምፀ ከበሮና ድምፀ ጸናጽል አይሰማበትም / ከክብረ በዓል በስተቀር/
የዕለተ ሰንበት ምንባባት፡- ዕብራውያን /3፡7-17/፡፡ ያዕ.ምዕ. 4፡6፡፡ የሐዋሥራ ም. 25፡13 ምስባክ መዝ. 2፡11 የዮሐንስ ወንጌል 3፡10፡፡
ቅዳሴ በግእዝ ዜማ ዕጣነ ሞገርና ዝማሬ በግእዝ ይባላል፡፡
ሳምንቱ ሙሉ በዘወረደ ይታሰባል፡፡

2ኛ. እሑድ ቅድስት /ሁለተኛ ሣምንት/

ከ8ኛ ቀን ጀምሮ /ቅድስት ከሠኑይ /ሰኞ// ጾመ ዓርብአ /ጾመ ኢየሱስ/ ይገባል፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ከ7 ቀን ጀምሮ የቅድስት ቀለም ይባላል፡፡
ቅድስት የተባለበት ምክንያት የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተለየ ጾም ለመሆኑ ለመግለጽ ነው፡፡
የቅድስት መዝሙር፡- "ግነዩ" "ለእግዚአብሔር" ለእግዚአብሔር ተገዙ" የሚለው ነው፡፡ ይኸውም በጾም በጸሎት በስግደት ራስን ማስገዛት ይነገርበታል፡
የዕለተ ቅድስት /ሰንበት/ ምንባባት፡- 1ተሰ. 4፡1-13፣ 1ጴጥ. 1፡13፣ የሐዋሥራ. 10፡17-30 ምስባከ መዝ. 95፡5፡፡ የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 6፡ቁ. 16፡፡
ቅዳሴ በግእዝ ዜማ እጣነ ሞገርና ዝማሬ በግእዝ ይደርሳል፡፡ ሣምንቱ ሙሉ በቅድስት ሰሞን ይታወሳል፡፡

3ኛ. እሑድ ምኲራብ /ሦስተኛ ሳምንት/

3ኛ ሣምንት ምኲራብ ይባላል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ ምኲራብ /ቤተ ጸሎት/ ማስተማሩ፣ በትምህርቱ መደነቁ ይታወስበታል፡፡
የዕለተ ምኲራብ መዝሙር፡- "ቦአ ኢየሱስ ምኲራበ አይሁድ" "ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኲራብ /ቤተ ጸሎት/ ገባ" የሚለው ነው፡፡
የዕለተ ምኲራብ /ሰንበት/ ምንባባት ቈላ. 2 ቂ. 16፣ ያዕ. ምዕ. 2 ቁ. 8 ፍጻሜ የሐዋ.ሥራ. 10 ቁ. 1-9፡፡ ምስባክ መዝ.ዳዊት 68 ቁ. 9፡፡ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 2 ቁ. 12- ፍጻሜ ይነበባል፡፡
ቅዳሴ በግእዝ ዜማ፣ ዕጣነ ሞገር እና ዝማሬ በግእዝ ይደርሳል፡፡
ሣምንቱ ሙሉ በምኲራብ ሰሞን ይታሰባል፡፡ ይሄም ለሊቃውንትና ለመደበኛ አገልጋዮች ግልጽ ነው፡፡

4ኛ እሑድ መጻጒዕ /አራተኛ ሳምንት/

መጻጒዕ ከዘወረደ ጀምሮ አራተኛው ሣምንት ነው፡፡ ይህም ሣምንት ሕሙማነ ሥጋ እና ሕሙማነ መንፈስ የሚታወሱበት ስለሆነ መጻጒዕ ተብሏል፡፡ ማለትም ሽባዎችን፣ በሽተኞችን፣ ማዳኑ ይታወስበታል፡፡ በተለይም በዮሐንስ ምዕ. 5 ቁ. 1-25 ያለውን ይታሰብበታል፡፡
የመጻጒዕ መዝሙር "አምላኩስ ለአዳም ለእረፍት ሰንበተ ሠርዐ" "የአዳም አምላክ ሰንበትን ለዕረፍት ሠራ" የሚለው ነው፡፡
የዕለተ መጻጒዕ ሰንበት፤ ምንባባት፡- ገላትያ ምዕ. 5 ቁ. 1፣ ያዕ.ምዕ. 5 ቁ. 14 እስከ ፍጻሜ የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 3፣ ከቁ. 1-2፡፡ ምስባክ መዝሙር 40 ቁ. 3፡፡ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 5 ቁ. 1-25፡፡ ጸሎተ ቅዳሴ በግእዝ ይቀደሳል፣ ዕጣነ ሞገርና ዝማሬ በግእዝ ይደርሳል፡
ሰሞኑ፡- ሙሉ በመጻጒዕ ይታሰባል፤ ማለትም ከእሑድ እስከ ቅዳሜ

5ኛ እሑድ ደብረ ዘይት (አምስተኛ ሣምንት)

ደብረ ዘይት፡- ከዘወረደ ጀምሮ ሲቀመር አምስተኛ ሳምንት ነው፡፡
ደብረ ዘይት፡- የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ጌታችን የመጣው የሰው ልጅን ለማዳን ነው፡፡ በዚህ አመጣጡ ግን ለፍርድ ይመጣል ማቴ. 25፡25፡፡
የደብረ ዘይት መዝሙር፡- "እንዘይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት" "ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ ሳለ" የሚለው ነው፡፡
የደብረ ዘይት ሰንበት ምንባባት፡- 1ተሰሎንቄ. 4፡13፣ 2ጴጥ. 3፡7-15፤ የሐዋ ሥራ ምዕ. 24፣ 1-22፡ ምስባክ መዝሙረ ዳዊት 49 ቁ. 2፤ የማቴ ወንጌል 24፡1-36፤ ጸሎተ ቅዳሴ በግእዝ ዜማ ይደርሳል፣ ዕጣነ ሞገር እና ዝማሬ በግእዝ ይቃኛል፡
ሰሞኑ ሙሉ /7 ቀናት/ ሰሙነ ደብረ ዘይት ይባላል፡

6ኛ እሑድ ገብርኄር /ስድስተኛ ሣምንት/

ገብርኄር፤ ከዘወረደ ጀምሮ በስድስተኛ ሳምንት የሚገኝ ነው፡፡ ገብርኄር /መልካም አገልጋይ/ /የሚያገለግል/ ዋጋ አለው፡፡ /ካህናት አገልጋዮች/ መታሰቢያ ነው፡፡
የገብርኄር ሰንበት መዝሙር፡- "መኑ ውእቱ ገብርኄር ወምዕመን" "ታማኙ፣ ደጉ አገልጋይ ማን ነው?" የሚለው ነው፡፡
የገብርኄር ሰንበት፡- ምንባባት፣ 2ጢሞ. 2፡1-16፡ 1ጴጥ. 5 ቁ. 1-12፡፡ የሐዋ.ሥራ. 1፡6-9፡፡ ምስባክ መዝ 39 ቁ. 8፡፡ ወንጌል የማቴ. ወን. ምዕ. 25፡14-31፡
ጸሎተ ቅዳሴ በግእዝ ዜማ ይደርሳል፣ ዕጣነ ሞገርና ዝማሬ በግእዝ ዜማ ይቃኛል፡፡
ሰሞኑ /7 ቀናት/ የገብርኄር ሳምንት መሆኑን ይታሰባል፡

7ኛ እሑድ ኒቆዲሞስ /ሰባተኛ ሣምንት/

ኒቆዲሞስ ከረበናተ አይሁድ /ፈሪሳውያን/ አንዱ የነበረ ፣ሕገ ኦሮትን፣ ሥርዓተ ኦሪትን ጠንቅቆ የተማረ፣ በጌታችን ትምህርት ወደ ክርስትና የተመለሰ ሰው ነው፡፡
ይህ ሰባተኛ ሣምንት በኒቆዲሞስ እንዲሰየም ሊቃውንት ተስማምተውበታል፡
ሰሙነ ኒቆዲሞስ ከዘወረደ በሰባተኛ ሰሞን የሚገኝ ነው፡፡ በሰሙነ ኒቆዲሞስ የነፍስን ግዴታ ቅን ፍላጎት፣ ዳግም ልደት፣ ከመንፈስ ቅዱስ መወለድን ይታሰብበታል፡፡
የኒቆዲሞስ መዝሙር "ሖረ ኀቤሁ ዘሰሙ ኒቆዲሞስ" "ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለ ወደእሱ ሄደ" የሚለው ነው፡፡
የዕለተ ኒቆዲሞስ ሰንበት፡- ምንባባት፡- ሮሜ. 7፡1-13፡፡ 1ዮሐ. 4፡18 ፍጻሜ የሐዋ.ሥራ. 5፡34 እስከ ፍጻሜ፤ ምስባክ መዝ. 16፡3፤ ወንጌል ዮሐንስ ምዕ. 3 ቁ. 1-12፡፡
ጸሎተ ቅዳሴ በግእዝ ዜማ ይደርሳል፤ ዕጣነ ሞገርና ዝማሬ በግእዝ ዜማ ይቃኛል፡፡

8ኛ. ተፅዒኖ ዲበ እዋል፤

የጌታችን የአርባ ጾም መጀመሪያ የሁለተኛ ሰሞኑ የመጀመሪያ ቀን /ሠኑይ/ /ሠኞ/ ሲሆን የጾመ አርባአ /40/ ቀናት የፍጻሜ ጾም በሰሙነ ኒቀዲሞስ በዕለተ ዓርብ ነው፡፡ ይህም ማለት የዘወረደ /ጾመ ሕርቃል/ 7 ቀን፤ የሰሙነ ሕማማት 8 ቀናት በድምሩ 15 ቀናት ሳይጨመሩ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው በሰሙነ ሕማማት የሚታሰብ ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለ ትንሣኤ የሚከበረው እንደ ኒቅያ ጉባኤ ውሳኔና አቈጣጠር ነው፡፡

9ኛ. በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት

ማለት በእነ ሩሲያ በእነ ግሪክ ቡልጋሪያ የመሳሰሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚጾሙት 48 ቀናት ናቸው፡፡
ይህም 1. 40 ቀናት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጾም፤
2. 8 ቀናት የሰሙነ ሕማማት ናቸው በድምሩ 48 ቀናት ይጾማሉ፡፡
ልዩነቱ የዘወረደ ጾም /ጾመ ሕርቃል/ አይጾሙም፡፡
በዓለ ትንሣኤ ግን እንደ ኢትዮጵያ አቈጣጠር ባይሆንም ከእኛ ጋር አብረው በዓሉን ያከብራሉ /ይፈስካሉ/፡፡

10. የምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት

የምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት በመባል የሚታወቁት የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡
የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት የሚጾሙት 40 ቀናት ብቻ ናቸው ይህም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጾም ብቻ ነው፡፡
የዘወረደ /ጾመ ሕርቃል/ እና የሰሙነ ሕማማት አጽዋማት 15 ቀናትን አይጾሙም፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ