Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በዓለ  ጥምቀት

baptism

ከመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሣኤ

ጥምቀት በዓል ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓተ አክብሮት መሠረት በየዓመቱ ከጥር አሥር እስከ አሥራ አንድ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት በካህናት፣ በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አገልግሎት ይከበራል፡፡በዓሉ የሚከበረው ጌታ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ጌታ የተጠመቀው በተወለደ በሠላሳኛው ዓመት ሲሆን ያ ወራት ዮሐንስ መጥምቁ ሕዝቡን እየሰበሰበ የንስሐ ጥምቀት የሚያጠምቅበት ጊዜ ነበር:: ማቴ. 3:1

ጥምቀተ ዮሐንስ

መጥምቁ በብሥራተ መልአክ የተወለደ የካህኑ ዘካርያስና የቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ ነው ሉቃ 1:13 ገና በማሕፀን ሳለ ለጌታ ሰግዷል ሉቃ 1:44 ጌታን በፅንስም በልደትም ስድስት ወር ይበልጣል እናትና አባቱ በልጅነቱ ስላረፉ ያደገው በገዳም ነው አኗኗሩ የብሕትውና ስለሆነ ይህንን ሕይወት የተላበሰውም በሙት ባሕር አካባቢ ኪውምራን በተባለ ቦታ ይኖሩ በነበሩ ኤሴናውያን በተባሉ መናንያን ኗሪዎች መካከል ስለአደገ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ጌታ በተጠመቀበት በዚያ ወራት ዮሐንስ "መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ "ማቴ 3:1 እያለ በይሁዳ ምድር ይሰብክና የንስሐ ጥምቀት ያጠምቅ ጀመረ አለባበሱም አነጋገሩም የባሕታዊ ስለሆነ በሚሰብክበት ጊዜ በከባድ ኃይለ ቃል ሕዝቡን በትምህርቱ እንዲስተካከሉ ይገስጽና ያስተምር ነበር፡፡ከፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ "እናንት የእፉኝት እባብ ልጆች ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ"በልባችሁ አብርሃምን ያህል አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፣ እላችኋለሁ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሳለት እግዚአብሔር ይችላል፡፡አሁንስ ምሳር በዛፎች ላይ ተቃጥቷል፡፡እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል፡፡ እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ ጫማውን እሸከመው ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል እሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል መንሹም በእጁ ነው፡፡ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፡፡ሜቴ 3:7 መጥምቁ ዮሐንስ ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ክርስቶስ ንስሐ ለሚገባና ለሚያምንበት አዳኝ ንስሐ ለማይገባና ለማያምን ግን ፈራጅ አምላክ መሆኑን ለመመስከር ነው፡፡ ሕዝቡ ይህን ተግሳጽና ምክር ሲሰሙ ልባቸው ስለተነካ ወደ ዮሐንስ እየመጡ ኃጢአታቸውን በመናዘዝ የንስሐ ጥምቀት ይጠመቁ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የሄደው በዚህ ወራት ነበር፡፡

የጌታችን ጥምቀት

ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ክብር ምሥጋና ይግባውና ለእኛ ሲል እንደ ተወለደ ለእኛ ሲልም ተጠምቋል፡፡ በመሆኑም ልደቱን በደስታ እነደምናከብር ጥምቀቱንም በደስታ እናከብራለን ለእኛ ሲል መጠመቁንም ማረጋገጥ የምንችለው እሱ ራሱ በተናገረው ቅዱስ ቃል ነው፡፡ጌታችን በዮሐንስ እጅ ለመጠቀም ወደ ዮርዳኖስ በመጣ ጊዜ ዮሐንስ የክርስቶስን አምላክነት ስለሚያውቅ "እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጂ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን" ብሎ አይሆንም አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "አንድ ጊዜ ተው እንግዲህ ጽድንቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል" አለው ማቴ 3:19 የእግዚአብሔር ልጅ ወደዚህ ዓለም የመጣው ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ስለሆነ የተጠመቀው ያን የመጣበትን ጽድቅ ለመፈጸም ነው፡፡ ጽድቅም ይህ ነው፡፡እኛ ልዕልናን ያገኘነው በእሱ ትሕትና ነው፡፡ በኃጢአት ምክንያት ክብራችንን አጥተን ክፉኛ ተዋርደን ከገነት ተባረን ነበር፡፡ እኛ ከወደቅንበት ቦታ በክብር የተነሳነው እሱ ለእኛ ሲል ሰው ሆኖ በጥምቀቱና በሞቱ በፈጸመው ጽድቅ ነው፡፡ በጥምቀቱ ውኃን ባርኮ እኛ እንድንጠመቅበት አድርጓል፡፡በመሆኑም ሁሉም ተመልሶ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆን ዘንድ ሥርዓተ ጥምቀትን መሥርቷል፡፡ የጥምቀት በዓል ዐቢይ በዓል ሆኖ በመላው ኢትዮጵያና በዓለም ሁሉ የሚከበረው በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በዓል መነሻነት ነው፡፡

በጥምቀት የተገለጠ ሰማያዊ ምሥጢር

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ከውኃው እንደወጣ ወዲያው ሰማያት ተከፈቱ መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በርሱ ላይ ሲቀመጥበት ዮሐንስ አየ እነሆ ድምጽ ከሰማይ ወጥቶ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡" ማቴ 3:16 "ሰማይ ተከፈተ ሲባል" በሰማይ መከፈትና መዘጋት ያለ ሆኖ አይደለም ደጅ ሲከፈት በቤት ያለው ነገር ሁሉ እንደሚታይ ከጥምቀቱ በፊት ያልተገለጠ ሰማያዊ ምሥጢር በጥምቀቱ ጌዜ ተገለጠ ማለት ነው፡፡ የተገለጠውም ምሥጢረ ሥላሴ ነው፡፡ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ የሥለሴ አንድነትና ሦስትነት ምሥጢር ተገልጿል፡፡ ይህውም፣ አንደኛ "የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ"የሚል ከአብ ድምጽ ከሰማይ መሰማቱ ነው ሁለተኛ "መንፈስ ቅዱስ በአምሳ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ መቀመጡ"ነው ሦስተኛ አብ ይህ የምወደው ልጄ ነው ያለውና መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ የተቀመጠበት ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ መታየቱ"ነው፡፡በዓለ ጥምቀት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት እንዲከበር ካደረጉትም፡ ምክንያቶች አንዱ ዕለተ ጥምቀት ይህ የሦስትነት ምሥጢር የተገለጠበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡

ምሥጢረ ጥምቀት

1. የሰው ልጅ ዳግመኛ ተወልዶ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚገባበት ምሥጢር ነው፡፡
2. የው ልጆች የሚጠመቁት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛምርት አድርጓቸው እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ሲል ባዘዘው ቃል መሠረት ነው፡፡ ማቴ 28:20 በጥምቀት ኃጢአት ይሠረያል በተጠማቂውም ላይ መንፈስ ቅዱስ ያድራል፡፡ ይህንንም ከሚከተለው የወንጌል ቃል ማረጋገጥ ይቻላል ሐዋ.2:38 1ኛ ጴጥ. 3:21፣ ቲቶ 3:5 በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናት በ40 እና 80 ቀን አዋቂ ደግሞ አምኖ በቀረበ ጊዜ ሁሉ የክርስትና እምነትን ሲቀበል መጠመቅ ይችላል ጌታችን ጥምቀትን በመባረክ እኛ እንድንጠመቅ ሥርዓተ ጥምቀትን በመሥራቱ ስለሆነ በክርስቶስ አምኖ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቀ ሁሉ በዓለ ጥምቀትን ያከብራል፡፡

የአከባበር ሥነ-ሥርዓት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጥምቀትን በዓል የምታከብረው ከሌሎች በዓላት በተለየ ሥነ-ሥርዓት ነው የተለየ የሚያደርገው ከገዳማት በቀር በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ወንዝ ወርደው ለማረፊያ በተዘጋጀላቸው ቦታ ያድራሉ፡፡ የየአጥቢያው ሕዝብም በነቂስ ወጥተው ታቦታቱን በማጀብ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመሄድ ያገለግላሉ በዕለቱ እዚያው ያድራሉ፡፡ ካህናት ሌሊቱን በማኀሌት ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ቆይተው የቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት በመንፈቀ ሌሊት ተጀምሮ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል፡፡ ጥር 11 ቀን ጠዋት በባሕረ ጥምቀቱ ላይ ጸሎት ይደረግና ውኃው ይባረካል፡፡ ሕዝቡም በተባረከው ውኃ ይረጫል፡፡ከዚህ የሚቀጥለው ታቦታቱን የተሸከሙ ካህናት ከድንኳን ወጥተው ለዝማሬ ማኀሌት በተዘጋጀው አውደ ምሕረት ላይ ይቆማሉ፡፡ መዘምራኑ በዓሉን በተመለከተ ቃለ ማኀሌት በመቃኘት ያሸበሽባሉ፡፡ ከዚያ በወጣት መዘምራን ዝማሬ ጉዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሆናል፡፡ በዋዜማው እንደተደረገው ሕዝቡ ሁሉ በቋንቋው፣በባህሉ መሠረት እያሸበሸበ በእልልታና በሆታ በማጀብ ይጓዛል፡፡ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደተባለው ሁሉም አዲስ ልብስ በመልበስ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ያከብራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን ወደ ሐዲስ ኪዳን በቀጥታ የተሸጋገረ ሕዝበ ክርስቲያን ያላት በመሆኑ የእግዚአብሔር ማደሪያ ለሆነው ታቦት አሁንም በዚሁ መልክ ልዩ ክብር በመስጠት ሲያከብሩ ይኖራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ