Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የመንፈስ ፍሬዎች

ከመ/ሐ መኰንን ወ/ትንሳኤ /ዘዲዮስቆሮስ/

የዚህ ትምህርት ዓላማ

በዚህ ትምህርት ለአንባብያን ለማቅረብ የፈለኩት ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ሊታይባቸው የሚገባውን መንፈሳዊ ገጽታ ለማሳየት ካለኝ ፍላጐት በመነሳት ነው፡፡

የመንፈስ ፍሬዎች ሲባል መልካም፣ ሸጋ የሆነ የነፍስ ስራዎች ማለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቅዱስ መንፈስና ርኩስ መንፈስ እንዳሉ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል፡፡

ርኩስ መንፈስ ክፉ መንፈስ ተብሏል፡፡ ቅዱስ ዳዊት በበገናው የሳኦልን ክፉ መንፈስ እንደአራቀለት አይተናል፡፡ 1ኛሳሙ.16፥22፡፡

የመንፈስ ፍሬዎች ስንል ግን በክፉው መንፈስ ግፊት የሚሰሩትን መጥፎ ሥራዎች አይመለከትም፡፡ ነፍስ ራስዋ በባሕርይዋ እስትንፋስ ስለሆነች ቅዱስ የሆነች መሠረት ናት፡፡ ዘፍ. 2፥7 ፤ ዕብ. 12፥23፡፡

ስለዚህ አንድ ሰው በፈቃደ ነፍሱ መሠረት የሚሰራቸው የጽድቅ ሥራዎች የመንፈስ ፍሬዎች ተብለዋል፡፡ የመንፈስ ፍሬዎች በእውነተኛ ክርስቲያን ላይ የሚታዩ በጽድቅ ሥራ ምክንያት የሚገኙ የክርሲያናዊ ህይወት የብስለት ውጤቶች ናቸው፡፡

 የመንፈስ ፍሬዎች የሚባሉትን በሁለት ዓይነት መንገድ እንመልከት፡-

1. በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት፣ ረዳትነት መሠረት የሚፈጸሙና የሚገኙ ናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ራሱ መንፈስ ይባላልና፡፡ ሮሜ . 8፥9፡፡
2. በእግዚአብሔር ቃል መሰረት የሚፈጸሙና የሚገኙ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል መንፈስ እንደሆነ ተገልጧልና፤ ዮሐ. 6፥63 ፡፡

የመንፈስ ፍሬዎች የተባሉበት ምክንያት

1. አንድ ተክል ከተተከለ ወይንም ዘር ከተዘራ በኋላ ሲያድግ ከእርሱ የሚጠብቀው ዋና ፍሬው እንደሆነ ሁሉ በመንፈሳዊ ቅዱስ ሳንበረታና በእግዚአብሔር ቃል እውቀትና በክርስቲያናዊ ሥራ ስናድግ ከእኛ የሚጠበቀው መንፈሳዊ ሥራ ስለሆነ ፍሬ ተብሏል፡፡ 1ቆሮ. 3 ፥6 ፣ ዮሐ. 15 ፥1
2. ከአንድ ተክል /ዘር/ ለምግብነት የሚሆነው ፍሬው እንደሆነ መንፈሳቸው ለተራበ ሰዎችም ከእኛ የሚገኘው ምግብ መንፈሳዊ ሥራ ስለሆነ ፍሬ ተብሏል፡፡ ማቴ. 21፥18
3. አንድ ተክል /ዘር/ የሚራባው ፍሬው ተዘርቶ እንደሆነ ሁሉ በክርስትና ብዙ ነፍሳትን መመለስ የሚቻለው መንፈሳዊ ሥራችንን በሌሎች ህይወት በመዝራት ስለሆነ ፍሬ ተብሏል፡፡ ዮሐ. 12፥24
እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ እኛ ክርስቲያኖችም እግዚአብሔርን በመንፈስ ልናመልከው በመንፈስ ልንሰግድለት እንደሚገባ ተናግሮናል፡፡ ዮሐ. 4፥24

ስለዚህ የስጋ ፍላጎታችንን አስወግደን ከስጋ ሥራ ተለይተን በመንፈስ መኖርና በመንፈስ መመላለስ ይኖርብናል፡፡ ገላ. 5፥16፡፡ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነው፡፡ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው፡፡ ሮሜ. 8፥6፡፡ይሁንና መንፈስን ሁሉ ግን ማመን አይገባም፡፡ መንፈስን ሁሉ መመርመር ከኛ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው 1ኛዮሐ. 4፥1፡፡ አንድን የመንፈስ ፍሬ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ መግቦት አኳያ ልንመዝነው ያስፈልጋል፡፡ እርሱ ለእኛ አርአያ ሆኖአልና፡፡ ሲያስተምርም ፍሬ የምናየው /የምናፈራው/ በእርሱ ሆነን እንደሆነ ገልጾልናል፡፡ ዮሐ.25፥1፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ ሲያስተምር እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ብሏል፡፡ ማቴ. 3፥8፡፡ የመንፈስ ፍሬዎች በክርስቲያናዊ ሕይወት ካደግን በኋላ በእኛ የሚታየውን መልካም ሥራ ብቻ ሳይሆን ከሐጢአት ወደ ጽድቅ መመለሳችን ራሱ የመንፈስ ፍሬ እንደሆነ ከዚህ እንረዳለን፡፡

በመሆኑም በመንፈስ የተነገረውን ቃለ ወንጌል ሰምተን /ተመግበን/ መለምለም ብቻ ሳይሆን ፍሬ ማፍራት ይገባናል፡፡ ካልሆነ ግን ጌታ እንደረገማት “በለስ” እንደርቃለን አለዚያም በምሳር ተቆርጦ ወደ እሳት እንደሚጣል ደረቅ ዛፍ ከጻድቃን ተለይተን ወደ ዘለዓለም እሳት እንጣላለን፡፡ ከዚህ ለመዳን ፍሬ ልናፈራ ፍሬአችንም ሊታይ ይገባል፡፡

በመንፈስ ቅዱስ እገዛና በቃለ እግዚአብሔር መሠረት በህይወታችን የሚታዩ የመንፈስ ፍሬዎች ብዙ ቢሆኑም በዚህ ትምህርት ግን የምናያቸው “በገላ. 5፥22” ላይ የተዘረዘሩትን ዘጠኙን የመንፈስ ፍሬዎች በማየት ነው፡፡ መልካም ንባብ ከመልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ ለዛሬው “ይቆየን” ይቀጥላል…

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ