Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የመንፈስ ፍሬዎች

(2ኛ ደስታ)


                          ከመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሣኤ (ዘዲዮስቆርዮስ)

ደስታ በምናየውና በምንሰማው፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈጸሙ ክስተቶች የሚሰማን የህሊና እርካታ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ የርካታ ስሜት ነው፡፡ ደስታችንም የሚፈጸመው በዓለም ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ በተለየ መልኩ ነው፡፡ የክርስቲያኖች ልዩ ደስታ የሚሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዓምለካዊ ፍቅሩ ዓለምን በማዳኑ በሚሰማን ደስታ ነው፡፡ ይህም መልዐኩ ለእረኞች እንደነገራቸው “ታላቅ ደስታ” ተብሏል፡፡ ሉቃ. 2:፡10

ለጌታችን እናት ለድንግል ማርያምም ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት “ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ”ብሏታል ሉቃ.1፡28እርስዋም የጌታችን እናት ስለ ደስታ ስትናገር “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት /ደስታ/ ታደርጋለች”ብላለች ሉቃ.1፡47የባሕርይ አባቱ አብ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው፣ የመረጥኩት ልጅ ይህ ነው”ብሏል ማቴ 3፡17 ፣ 17፡5፡፡ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስና በፍቅሩ ሥራ ደስ ሊለን ይገባል፡፡

መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን ከሕዝቡ ካገናኘ በኋላ “እንግዲህ ደስታዬ ተፈጸመ” ብሏል ዮሐ. 3፡29፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰውን በደስታ እንዲኖር አድርጐ ነው የፈጠረው ሁሉንም ለሰው ልጅ ምቾት አዘጋጀለት፡፡

 እዚህ ላይ በእርካታና በደስታ መካከል ያለውን ልዩነት ለይተን ማወቅ አለብን እርካታ በአብዛኛው ለሥጋና ለስሜቶች የተገባ ነው፡፡ እውነተኛ ደስታ ግን ለመንፈስ የተገባ ነው፡፡ ሰው በመብላት፣ በመጠጣት ወይም ውብ የሆነ ትዕይንት በማየት ወይም በመስማት እርካታ ሊሰማው ይችላል፡፡ እነዚህም ስሜታዊ እርካታዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊ መዝሙር ወይም መንፈሳዊ ቃላትን በመስማት መንፈስ የራሱን ደርሻ ይወስዳል፡፡

                                        ሐሰተኛ ደስታ

-በጠለት ወድቀት ወይም በእርሱ ለይ በደረሰበት ማንኛውም ክፉ ነገር መደሰት የውሸት ደስታ ምሳሌ ነው፡፡ ይህ በራስ ላይ የሚሠራ ኃጢአት ነው ጠቢቡ ሰዘለሞን “ጠለትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ ”ምሳ 24፡17 ሲል ተናግሯል፡፡ ለኃጢአት መጋበዝን የሚያመለክት በኃጢአት የተሞለ ደስታ ነው፡፡ ይህም የፍቅር ተቃራኒ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ“ፍቅር በደልን አይቆጥርም” 1ኛ ቆሮ 13፡6 ብሏል፡፡
-ሌለው በትዕቢት፣ እራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ጋር የተቀላቀለ ደስታም ሐሰተኛ ደስታ ነው፡፡ ለዚህ ትምህርት እጀግ በጣም የምወደውን የወንጌል ክፍል መጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ሉቃ፡10፡17ደቀመዞሙርቱ በደስታ ተሞልተው “ጌታ ሆይ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል”አሉት፣ “ጌታም በዚህ ደስ አይበላችሁ…ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ“ ሲል አስተምሯቸዋል፡፡
-አንዳንዶች በቁሳዊ ነገሮች ይደሰታሉ አንድ ቀን አዲስ አበባ አንድ ትልቅ የገበያ ማዕከል ውስጥ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ገብቼ በጣም ውደ የሆኑ የቤት ዕቃዎችን ማየት ጀመርኩ አንዱ ከእኛ በፊት የገባ ሰው ዓይኑ ላይ የሚገቡትን የዕቃዎች ዋጋ ይጠይቃል፡፡ ዋጋቸው በትንሹ ከ2000በላይ ነው የሚጠሩት እያየ ያደንቃል አንዲት ትንሽ የብር ሳሐን ይዞ ወደ እኔ ጠጋ አለ አየህ እንዴት ያምራል አለኝ እኔም የማላውቀውን ሰው ላለማሳፈር ጥሩ ነው ያምራል አልኩት በሆዴ የማን አቅም ችሎ ይገዛዋል እያልኩ…
-እኔም አንዴ አናግሮኛል ብዬ በቤትህ በጣም የሚያምሩ ነገሮች ቢኖሩህ ደስተኛ ነህ አልኩት ቀበል አድርጐ አወን በጣም ደስ ይለኛል አለኝ፡፡ ግን እቤትህ ታላቁን ደስታ የሚሰጠው መጽሐፍ ቅዱስ አለህ? አልኩት ቀና ብሎ እያየኝ አይ ድሮ ነበረኝ አሁን ግን የለኝም አለ፡፡ ሰዎችን ምን ይህል ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ በቁሳቁስ እንደሚማረኩ ይህ ሰው መልካም ማሳያ ሆኖልኛል፡፡
ለዘለዓለም ወደ ማይሻረው የእግዚአብሔር ሕገ መንግሥት “መጽሐፍ ቅዱስ” ገለጻ ልዉሰዳችሁ፣

መጽሐፍ ቅዱስ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ”ፊል.4፡4፡፡ ሁልጊዜ ሲል በምን በምን ጊዜ ነው? ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ለአንባቢዎቼ አቀርባለሁ፡፡
1.በቀራንዬ አደባባይ ደሙን ለኛ አፍሶ በፍጹም ፍቅሩ የወደደንን አምላክ እምነታችን በተገለጸ ጊዜ ሐዋ.8፡39 ፣ ሐዋ. 16.31
2.ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉን ጊዜ መዝ. 121፡1
3.የክርስቶስ ወንጌል በማንኛውም ጊዜና መንገድ በሙላት ለሰዎች በተሰበከ ጊዜ ፊል. 1፡18
4.እግዚአብሔር በሕይወታችን ታላቅ ነገርን ባደረገልን ጊዜ መዝ. 125፡1
5.ምንም እንኳን እህልና ከብቶች ሌላም ሀብት በማይኖረን ጊዜ ዕንባ. 3፡17
6.በሚወደን በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ስደት፣ መከራና ስቃይ በሚደርስብን ጊዜ ማቴ. 5፡11፣ 2ቆሮ.5፡8 ፣ 2ቆሮ. 7፡4፣ 1ጴጥ. 4፡12

በጌታ ያገኘነውን ደስታ የምንገልጠው እንደዓለም በዘፈንና በስካር ሳይሆን አምላካችንን በመዝሙር በማመስገን ነው ኢሳ. 52፡9፡፡ ይህንንም ቅዱስ ያዕቆብ “ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር”በማለት ገልጾአል፡፡ ያዕ.5፡13፡፡ ከጌታ ጋር ከሆንን የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ ስለምንጥል ሁሉጊዜ ደስታ ይሰማናል፡፡

እርሱም በእኛ እምነትና የክርስትና ሕይወት ይደሰታል፡፡ የወይን ግንድ የሆነው እኛ ቅርንጫፎቹ እንድንሆንና ብዙ ፍሬ እንድናፈራ የነገረን በእኛ ደስ እንዲለው እኛም በእርሱ ደስ እንዲለን ነው ዮሐ. 15፡11፡፡
                  ይቆየን …..

 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የፎንት ልክ መቀየሪያ