Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ምዕራፍ አሥራ አንድ

በመምህር ዕንቈባሕርይ

5500+2009=7509 ዓመተ ዓለም በ532 ዐቢይ ቀመር፣ ሲቀመር 14 ዐቢይ ቀመር ሆኖ 61 ዓመታት ተረፈ ቀመር ይሆናል፡፡

61 ዓመታት በ19 ንዑስ ቀመር ሲቀመር /61.19=3፡4
3 ንዑስ ቀመር ሆኖ 4 ዓመታት ተረፈ ቀመር ይሆናል፡፡ ከ4-1=3 ይሆናል፡፡ ይህ ማለት "አሐዱ አእትት ለዘመን" በሚለው መሠረት ነው፡፡

የ2009 ዓ.ም የዘመኑ መንበር 3 ነው፡፡

አበቅቴ የሚወጣበት መንገድ
መንበር 3x11=33-30=3፤ የ2009 ዓ/ም የዘመኑ ዓበቅቴ 3 ነው፡፡ ይህ ማለት 30 ቀናት አንድ ወር ሆኖ 3 ቀናት የተረፈው የዘመኑ አበቅቴ ነው፡፡

የአበቅቴ ጥቅሙ ወይም /አገልግሎቱ/ ሠርቀ ሌሊትን ለማውጣት ወይም ለማግኘት ነው፡፡

መጥቅዕ የሚወጣበት መንገድ
መንበር 3x19 ጥንተ መጥቅዕ 57-30=27 ቀናት ይህ ማለት 1 ወር ሆኖ ቀሪ 27 ቀናት ነው፡፡ ስለዚህ የ2009 ዓ.ም የዘመኑ መጥቅዕ 27 ቀን በዘመነ ማቴዎስ ወጣ ይባላል፡፡

በዓለ መጥቅዕ

በ2009 ዓ.ም መስከረም 1 ቀን እሑድ ይብታል፡፡

መስከረም በባተ በ27ኛው ቀን ዓርብ በዓለ መጥቅዕ ይውላል፡፡

መባጃ ሐመር
የዓርብ ተውሣክ 2+27=29 ይሆናል፡፡ ይህ የ2009 ዓ.ም መባጃ ሐመር ይባላል፡፡

ጾመ ነነዌ

የመስከረም ሣኒታ ጥር፤ የጥር መባቻ ሰኑይ /ሠኞ/ ይብታል፡፡ ጥር በባተ በ29ኛው ቀን ጾመ ነነዌ ይገባል፡፡ ይህም ሲገለጽ ከሰኑይ - ሰኑይ 8+7= 15+7=22+7=29 ከጥር 29 ቀን በዕለተ ሰኑይ ይገባል ማለት ነው፡፡

ዐቢይ ጾም

የዐቢይ ጾም ተውሣከ 14 ነው፤ 14+29=43-30=13 ቀን ፤ የየካቲት መባቻ ረቡዕ /ሮብ/ ይብታል የካቲት በባተ በ13 ቀን በዕለተ ሰኑይ ዐቢይ ጾም ይገባል፡፡

ደብረ ዘይት
የደብረ ዘይት ተውሣክ 11 ቀን ነው፡፡ 11+29=40 ቀናት ከ40-30 ቀናት 10 ቀናት፤ መጋቢት ዓርብ ይብታል፡፡ መጋቢት በባተ 10 ቀን በዕለተ እሑድ ደብረ ዘይት ይውላል፡፡

ዕለተ ሆሣዕና
የሆሣዕና ተውሳክ 2 ቀን ነው፤፤ 2+29=31-30=1 ቀን፤ ሚያዚያ እሑድ ይብታል፡፡

ሚያዝያ 1 ቀን 2009ዓ.ም በዕለተ እሑድ በዓለ ሆሣዕና ይውላል፡፡

ስቅለተ ክርስቶስ
የስቅለት ተውሣክ 7 ቀን ነው፤ 7+29=36 ቀናት ከ36-30= 6 ቀናት ሚያዝያ 6 ቀን 2009 ዓ.ም በዕለተ ዓርብ በዓለ ሥቅለት ይውላል፡፡

ትንሣኤ ክርስቶስ
የትንሣኤ ተውሣክ 9 ቀን ነው፡፡ 9+29=38 ቀናት 38-30=8 ቀናት ሚያዝያ 8 ቀን 2009 ዓ.ም በዕለተ እሑድ ትንሣኤ ይሆናል፡፡

ርክበ ካህናት
የርክበ ካህናት ተውሣክ 3 ቀን ነው፤ 3+29=32 ቀናት ከ32-30=2 ቀን ይሆናል፡፡ የግንቦት መባቻ ማክሰኞ ይውላል፡፡ ግንቦት 2 ቀን 2009 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ ርክበ ካህናት ይውላል፡፡

ዕርገተ ክርስቶስ
የዕርገት ተውሣክ 18 ቀን ነው፤ 18+29=47 ቀናት ከ47 ቀናት -30=17 ቀናት ይሆናል፡፡ ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በዕለተ ኅሙስ ዕርገተ ክርስቶስ ይሆናል፡፡

በዓለ ጰራቅሊጦስ
የበዓለ ጰራቅሊጦስ ተውሣክ 28 ቀን ነው፤ 28-29=57 ቀናት ከ57-30=27 ቀን ይሆናል፡፡ ግንቦት 27 ቀን 2009 ዓ.ም በዓለ ጰራቅሊጦስ በዕለተ እሑድ ይውላል፡፡

ጾመ ሐዋርያት
የጾመ ሐዋርያት ተውሣክ 29 ቀን ነው፤ 29+29=58 ቀናት ከ58-30=28 ቀናት፤ ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም በዕለተ ሠኑይ /ሠኞ/ ጾመ ሐዋርያት ይውላል፡፡

ጾመ ድኅነት
የጾመ ድኅነት ተውሣክ 1 ቀን ነው፤ 1+29=30 ቀናት ይሆናል፡፡ ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ /ሮብ/ ጾመ ድኅነት ይውላል፡፡

ማሳሰቢያ ጾመ ፍልሰታ ለማርያም በባሕረ ሐሳብ ቀመር ባይካተትም ሁል ጊዜ ከነሐሴ 1-15 ቀን የሚጾም ሲሆን በ2009 ዓ.ም የሚገባው መባቻ በዋለበት በዕለተ ሰኑይ /ሠኞ/ ይሆናል፡፡

አሥርቆት /ጸሎት/
በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ "ናሁ በዘንዜከር ሐሳባተ ሕጉ ወትእዛዛቲሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወሐሳባተ አዝማነ ዓለም፣ ወሠርቀ አውራኅ ዘሌሊት ወዘመዓልት፣ እንዘ ሀሎነ በዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቡሩክ፤ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ አሜን፡፡" በሠርቀ ፀሐይ 7509 ዓመተ ዓለም፣ ወእምኔሁ 5500 ኮነ ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኲነኔ፤ 2009 ዓመተ ሥጋዌ፡፡ ዮም ሠርቀ ለነ ወርኃ መስከረም ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኃ ጥቅምት ሰላመ እግዚአብሔር አሜን፡፡

ኅሙሱ ሠርቀ ሌሊት /5/ ነው፤
ተሥዑ ሠርቀ ወርኅ /9/ ነው፤
አሚሩ ሠርቀ መዓልት /1/ ነው
አሚሩ ጥንተ ዕለት /1/ ነው
ኃምሱ ጥንተ ዮን /5/ ነው
ኮነ በዛቲ ዕለት፡፡

መምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ
ነሐሴ 19 ቀን 2008ዓ.ም

የፎንት ልክ መቀየሪያ