Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ምዕራፍ ሁለት

ባሕረ ሐሳብና አገባቡ

ከመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ
       የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ ውድ ተከታታዮቻችን ባለፈው ጽሑፌ ሐሳበ ዘመን ዘኢትዮጵያ በሚለው ርእስ፤

 1. የኢትዮጵያ የዘመን አቈጣጠር
 2. ሐሳበ ዘመን
 3. ባሕረ ሐሳብ
 4. አቡሻክር
 5. የቊጥር ትምህርት
 6. ዘመነ ዓለም

      የኢትዮጵያ የዘመን አቈጣጠር፤ አወቃቀር በሚል ንዑሳን አርእስት ለማስረዳት የጽሑፍ ትንታኔን ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ የዛሬ ትምህርትም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 

 • ባሕረ ሐሳብና አገባቡ

ለጊዜያት፣ ለዘመናት፣ መሥፈሪያ፡ መቈጥርያ እንዳላቸው፣ የአቈጣጠሩም ስልት እንዴት እንደሆነ አስቀድመን በሐተታ መልክ መጥቀሳችን ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ አጠር አጠር እያደረግን መነሻቸውንና አገባባቸውን በሚቀጥለው ብንገልጽ ስለ ሐሳበ ዘመን አትተን ያቀረብነውን ማሰሪያ ያገኛል፡፡
የጊዜያትንና የዘመናትን፣ መሥፈርያ፣ መቊጠርያ የተሰኙ ሰባት (7) መሥፈርታትና ሰባት (7) አዕዋዳት ናቸው፡፡ እነዚህም በቅደም ተከተል ቀርበዋል፡፡
1. ሰባት መሥፈርታት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ሳድሲት
2. ኃምሲት
3. ራብዒት
4. ሣልሲት
5. ካልዒት
6. ኬክሮስ
7. ዕለት ይባላሉ፡፡

2 የሥፍሩ አካሄድ እንደሚከተለው ነው፡፡

ሳድሲት (60) ኃምሲት ነው፡፡
ኃምሲት (60) ራብዒት ነው፡፡
ራብዒት (60) ሣልሲት
ሣልሲት (60) ካልዒት ነው፡፡
ካልዒት (60) ኬክሮስ ነው፡፡
ኬክሮስ (60) ሲሞላ ዕለት ይሆናል፡፡

እነሆም (60) ኬክሮስ አንድ ዕለት ነው፡፡ ዕለትም የመዓልትና የሌሊት /የቀንና፣ የሌሊት/ አስተጋባኢ /ሰብስቦ የያዘ/ ነው፡


3 በሌላ አገላለጽ፡- አንድ ኬክሮስ (60)  ካልዒት ማለት ነው፡፡

አንድ ካልዒት (60) ሣልሲት ማለት ነው፡፡
አንድ ሣልሲት (60)  ራብዒት ማለት ነው፡፡
አንድ ራብዒት (60)  ኃምሲት ማለት ነው፡፡
አንድ ኃምሲት (60)  ሳድሲት ማለት ነው፡፡


4. ኬክሮስና የሰዓት ሥፍር ግንኙነትና ልዩነት እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

60 ኬክሮስ 24 ሰዓት 24 ሰዓትም የቀንና የሌሊት አስተጋብኢ /ስብስብ የያዘ/ ነው፡፡
1 ሰዓት 21/2 ኬክሮስ /2 ኬክሮስ ከ30 ካልዒት/

››  21/2 x60=150 /መቶ ሃምሳ/ ካልዒት
››  21/2 x60 x60 =9,000 /ዘጠኝ ሺህ/ ሣልሲት
››  21/2 x60 x60 x60= 540,000 /አምስት መቶ አርባ ሺህ/ ራብዒት
›› 21/2 x60 x60 x60 x60=32,400,000 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ/ ኃምሲት
›› 21/2 x60 x60 x60 x60 x60= 1,944,000,000 /አንድ ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ሚሊዮን/ ሳድሲት


1. ደቂቃ 21/2 ካልዒት /2 ካልዒት/ ከ30 ሣልሲት

››   21/2 x60=150 /መቶ ሃምሳ ሣልሲት/ ፡፡
››   21/2 x60 x60 =9000 /ዘጠኝ ሺህ/ ራብዒት
››  21/2 x60 x60 x 60=540000 /አምስት መቶ አርባ ሺህ/ ኃምሲት
›› 21/2 x60 x60 x 60 x60= 32400000 /ሠላሳ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ/ ሳድሲት

1. ሰከንድ 21/2 ሳልሲት

››     21/2 x60 = 150 /መቶ ሃምሳ/ ራብዒት
››     21/2 x60 x 60 =9000 /ዘጠኝ ሺህ/ ኃምሲት
››     21/2 x60 x60 x60 = 540000 /አምስት መቶ አርባ ሺህ/ ሳድሲት
››     5.4 x105 =540000 /አምስት መቶ አርባ ሺህ/ ሳድሲት

እነሆም ከዚህ በላይ የተገለጸው እጅግ በጣም ድቁቅ የሆነ ጊዜን ነው፡፡
እንግዲህ ከዚህ ከመጨረሻዪቱ ድቁቅ ተነሥቶ ነው 60ው ኬክሮስ አንድ ዕለት ሊሆን የቻለ፡፡ 60ው ኬክሮስ 24ሰዓት ለመሆኑ እላይ ተገልጿል፡፡ 30ው ኬክሮስ ወይም 12ሰዓት የቀን 30ው ኬክሮስ ወይም 12ሰዓት የሌሊት ጊዜን ይመግባል፡፡ በድምሩ 24ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያውያንና በብግፆች፣ በሕዝበ እስራኤል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ቀን የፀሐይ ብርሃን ያለበት ክፍል ሆኖ፣ ሌሊት የሚባለው ደግሞ የፀሐይ ብርሃን የሌለበት ክፍል ነው፡፡ ዘፍጥ.ምዕ.1፡15፡፡ የተጠቀሱት ሕዝቦችና ተመሳሳዮቻቸው የቀንና የሌሊት ምግብና በተባለው የሥፍረ ሰዓት ሕጋቸው ይህን ሲከተሉ ኖረዋል፡፡ጌታም በወንጌል፡-“ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን?በቀን የሚመላለስ የዚህ ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ግን በእርሱ ብርሃን ስለሌለ፤ ይሰናከላል”በማለቱ ይታወቃል፡፡ /ዮሐ.12፡9-10 ማቴ.ምዕ.22፡12 ምዕ.27፡1፡45፡57

እንዲሁም የዕለት መነሻ ጊዜን፣ ማታ ያደርጋሉ፡፡ ይህም “ከማታ እስከ ማታ ድረስ” ተብሎ በኦሪት ሕግ መታወጁ የሚታወስ ነው፡፡
/ዘሌዋ. 23፡32/ /ዘፀአ. 12..6-18፡29/ ዘኁል. ምዕ. 10፡15፡16 ኤር. 31፡35 መዝ. 103(104)23 /ይህ እንግዲህ አሁንም ኢትዮጵያ የምትመራበት የመሥፈሪያ አካሄድ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከዓለም ህዝቦች ጥንታውያን አባቶቻቸው ወይም የአሳብ ዘመን ሊቃውንቶቻቸው የተመሩበት ልዩ ልዩ ነጥብ ስለነበረ በዚያ ተመርተው የዕለት መነሻ ጊዜን በነግህ ጸሐይ በምትወጣበት ጊዜ የሚጀምሩ፤ ገሚሶቹም፣ እኩለ ሌሊት፣ የዕለት መነሻ የሚያደርጉት መኖራቸው በታሪክ የተመዘገበ ነው፡፡

ይልቁም ከክርስትና ዘመን በፊት የመገብተ ከዋክብትን አጓጓዝ ወይም አካሄድ የተመረኰዘ ፍልስፍናን ይዘው የተነሡ ክፍሎች ዕለቱን ከቀትር ማለት በኢትዮጵያ የሰዓት አቈጣጠር በስድስት ሰዓት ይጀምራሉ፡፡
ይህም ሊቁ አቡሻክር እንደገለጸው “እስመ ኀሳበ ከዋክብት ይትሜጠን በመንፈቀ መዓልት”ከዋክብትን የመቆጣጠር አሳብ በቀትር /የቀን አጋማሽ/ይመሠረታልና የዕለቱን መነሻ ይህን እልባ ወይም ነጥብ በማድረጋቸው መሆኑ ይታያል፡፡

ምሳሌ በሥፍረ ሰዓት ይዞታና በዕለት አጀማመር ባለው ልዩነት የሌሎችን ክፍሎች አቈይተን በኢትዮጵያ በምዕራባውያን መካከል ያለው ልዩነት  ቀጥሎ በሚገኝ ሠንጠረዥ ቀርቧልና መመልከቱ ይጠቀም ይሆናል፡፡

 

ኢትዮጵያዊ የሰዓት አመዳደብ

የምዕራባዊ የሰዓትና የዕለት አመዳደብ

የኢትዮጵያዊ የሰዓት አመዳደብ

የምዕራባዊ የሰዓት አመዳደብ

 

ሠርክ ማታ ምሽት

1  ሰዓት

7

1 ሰዓት ጧት

7 ሰዓት

2 ሰዓት

8

2ሰዓት ጧት

8 ሰዓት

3 ሰዓት

9

3ሰዓት ጧት

9 ሰዓት

4 ሰዓት

10

4ሰዓት ጧት

10 ሰዓት

5 ሰዓት

11

5ሰዓት ጧት

11 ሰዓት

 

መንፈቀ ሌሊት /ውድቅት/

6 ሰዓት

12

6 ቀትር

12 ሰዓት

7 ሰዓት

1

7 ቀትር

1 ሰዓት

8 ሰዓት

2

8 ቀትር

2 ሰዓት

9 ሰዓት

3

9 ቀትር

3 ሰዓት

10 ሰዓት

4

10 ቀትር

4 ሰዓት

11 ሰዓት

5

11 ቀትር

5 ሰዓት

ጎህ ከፈተ ነግህ ጧት

12 ሰዓት

6

12 ምሽት

6 ሰዓት

/ነጋ ጥዋት ሆነ/

/ሰርክ ማታ/

 

 

ሰባቱ መሥፈርታት ስለተባሉት ከዚህ በላይ በቀረበው ገለጻ ተመልክተናል፡፡ አሁን ሰባቱ (7) አዕዋዳት ስለተባሉት እንደሚከተለው ይገለጻል፡፡
አዕዋዳት ማለት እንደቀለበት ዙሪያ ገጠም እየሆነ የሚታዩ የጊዜያት ድንጋጌዎች ናቸው፡፡
…. ይቀጥላል

የፎንት ልክ መቀየሪያ