Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ምዕራፍ 3

ውድ የዚህ ዓምድ አንባቢያን ወንድሞቸ እንደምን ሰንብታችኋል? እኔ በበኩሌ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ፡፡
በምዕራፍ ሁለት ትምህርታችን፤

 1. ባሕረ ሐሳብና አገባቡ
 2. ሰባት መሥፈርታት
 3. የሥፍሩ አካሄድ
 4. የኬክሮስና የሰዓት ሥፍር ግንኙነትና ልዩነት
 5. ደቂቃ
 6. ሰኮንድ
 7. ኢትዮጵያዊ የሰዓት አመዳደብ እና የምዕራባዊ የሰዓት አመዳደብ በሚሉ ነጥቦች መጻፌን አስታውሳለሁ፡፡

በዚህም ቀጣይ የትምህርት ምዕራፍ ደግሞ እንደሚከተለው አቀርብላቸኃለሁ፡፡
ከሁሉም በላይ ግን ልዑል እግዚአብሔር ልቦናችሁን ከፍቶ፣ ዓይነ ሕሊናችሁን አብርቶ፣ እውቀቱን እንዲገልጽላችሁ አምላኬ እግዚአብሔርን በጸሎት እጠይቃለሁ፡፡

 

1. ዐውደ ዕለታት

ዐውደ ዕለታት ከእሑድ እሰከ ቅዳሜ ያሉት ሰባት ዕለታት ያሉበት ሲሆን፣ እነዚህ ሰባት ዕለታት ለአውራኅና /ለወሮች/፣ ለዓመታት መሠረት መሆናቸውን ከዚህ አስቀድመን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
ዐውደ ዕለታት ከጥንት ከሥነ ፍጥረት ታሪክ ጀምሮ በሰባት ዕለታት ስምና መደብ ቀመር ሆኖ እናገኘዋለን ዘፍ.2፡2-3 ዘፀአ.20፡11

 2. ሰባቱ ዕለታት

ሰባቱ ዕለታት የሚከተሉት ናቸው የአጠራራቸው መነሻ ከግዕዝ በመሆኑ በግዕዝ፣ በትግርኛና በአማርኛ ተጽፈዋል፡፡

ግዕዝ

ትግርኛ

አማርኛ

1.እሑድ

ሰንበት

እሑድ

2.ሰኑይ

ሰኑይ

ሰኞ

3.ሠሉስ

ሠሉስ

ማክሰኞ

4.ረቡዕ

ረቡዕ

ረቡዕ

5.ሐሙስ

ሓሙስ

ሐሙስ

6.ዓርብ

ዓርብ

ዓርብ

7. ቀዳም

ቀዳም

ቅዳሜ ናቸው

እነሆም እነዚህ በዚሁ መደባቸው እየተመላለሱ ወራትንና ክፍለ ዘመናትን ዐውደ ዓመትን ያስገኛሉ፡፡

3. አውራኅ /ወራት/

ወራቱ በፀሐያማ ዕለት ተቀምረው በ30በ30እየሆኑ አሥራ ሁለት ወራት ሲሆኑ አምስት ቀን ከሩብ ደግሞ ጳጉሜን ተብላ ትጠራለች፡፡ ይህ አቀማመር በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ የምትጠቀምበት ሲሆን ዓመተ ኖኅ በሚል ዘይቤ ሲነገርለት የቈየ የኢትዮጵያና የምስር ጥንታዊ ባህል መሆኑን ከዚህ በፊት አትተን ገልጸናል፡፡ ዘፍ.7፡24 ም.8፡3 አቡሻ -/1/

4. የአሥራ ሁለት ወራት ስም ዝርዝር

1 መስከረም

30

5 ጥር

30

9 ግንቦት

30

2 ጥቅምት

30

6 የካቲት

30

10 ሰኔ

30

3 ኅዳር

30

7 መጋቢት

30

11 ሐምሌ

30

4 ታኅሣሥ

30

8 ሚያዝያ

30

12 ነሐሴ

30

ጳጉሜን /ተረፍ/ 5 ቀን ¼

ይህም የወራት አቈጣጠር ከምዕራባውያን አቈጣጠር የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ አቈጣጠር 12ቱ በ30 በ30 ቀን ተመድበው ትርፍ አንድ ላይ ሆኖ ጳጉሜን ስለሚባል ነው
የኢትዮጵያና የምዕራባውያን ወራት ልዩነታቸው ለመረዳት በኢትዮጵያ አቈጣጠር 2003ዓ.ም የዘመነ ሉቃስ ወንጌላዊን ከኤሮፓውያን 2010/2011ዓ.ም አነጻጽረን አቅርበናል፡፡


የኢትዮጵያ ዓመተ ምሕረት 2003ዓ.ም

የኢት፡ወር

የምዕራባውያን 2010/2011 ወራት
2010/2011    

ወንጌላዊ ሉቃስ መስከረም

1

2010    Sebtember

11

ጥቅምት

1

2010    octeber 

11

ኅዳር

1

2010    Nobember

10

ታኅሣሥ

1

2010     December  

10

ጥር

1

2011     Junuary  

9

የካቲት

1

2011     Febriuary

8

መጋቢት

1

2011     March  

10

ሚያዝያ

1

2011     April  

9

ግንቦት

1

2011     May  

9

ሰኔ

1

2011    June  

8

ሐምሌ

1

2011     Jully  

8

ነሐሴ

1

2011     Auguest    

7

ጳጉሜን

1

2011     Sebtember  

6

5. ዐውደ ዓመት

ዐውደ ዓመት /የዓመት ሙሉ ዙር/ በዐውደ ዕለታትና በሱባዔ ዐውደ ዕለታት በክፍለ ዘመናት አቋም ላይ ተመሥርቶአል፡፡

6.ሱባዔ ዕለታት

የዓመቱ ዐውደ ዕለታት አምሳ ሁለት ናቸው፡፡ይህም የሚያሳየው መጀመሪያ የሳምንት ዕለታት ሰባት እንደመሆናቸው መጠን በአንድ ዓመት ውስጥ 52 ጊዜ እየተመላለሱ ስለሚገኙ 52 ሱባኤ ዕለታት ይባላሉና ነው፡፡ 52 ሱባኤ ዕለታት ከሱባዔነት አቋም ወደ ዕለታት ዝርዝር ሲተነተኑ 52 ሱባዔ ዕለታትን በሰባት ማባዛት ነው፡፡ /52x7=364/ አምሳ ሁለት ሱባዔ ዕለታት በሰባት ሲባዛ 364 ቀን ይሆናል፡፡
እነሆም እዚህ ላይ የዕለታት ሱባዔ ስፍራ ይዞ መገኘቱን በማየት የኢትዮጵያ ጠቅላላ ባሕረ ኀሳብ ከአይሁድ እንደመጣና የ52ሱባኤ ዕለታት ቊጥርም ያለ ሠግር ፍጹም ዐውደ ዓመት እንደተሟላ አድርገው የሚያስቡ መኖራቸው ከዚህ በፊት እንደገለጽን የሚታወስ ነው፡፡

 7.ክፍለ ዘመናት

ከሃምሳ ሁለት ሱባዔ ዕለታት ተባዝቶ የተገኘ 364 ቀን ወደ አራት ቢከፈል አራት ክፍለ ዘመናትን ያስገኘ መሆኑ ይታያል፡፡
ይኸውም ሲከፈል /364፡4=91/ ዘጠና አንድ፣ ዘጠና አንድ ሆኖ ለአራት ክፍለ ዘመናት 91፣91 ቀን ደርሶአቸው ይገኛል፡፡


ክፍለ ዘመናቱ የሚከተሉት ናቸው

 1. ከመስከረም 26 እስከ ታኅሣሥ 25 ዘመነ መፀው /ጥቢ/ ሆኖ 91 ቀን ይይዛል፡፡
 2. ከታኅሣሥ 26 እስከ መጋቢት 25 ዘመነ ሀጋይ /በጋ/ ሆኖ 91 ቀን ይይዛል፡፡
 3. ከመጋቢት 26 እስከ ሰኔ 25 ዘመነ ፀደይ /በልግ/ ሆኖ 91 ቀን ይይዛል፡፡
 4. ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ዘመነ ክረምት ሆኖ 91 ቀን ይይዛል፡፡

ይሁን እንጂ በአራቱ የዓመቱ ክፍለ ዘመናት 91፣91እየሆነ የተገኘው 364ቀን በሚገባ መቈጣጠሪያ ሲታይ የዓመቱ ዙር አያስተባቃም፡፡ ማለት የቀኑ ፀሐያዊ ብርሃን የሌሊቱ ጨለማ በምጣኔ ተስተካክለው እኩል በእኩል ሆነው እስከሚገኙበት የዓመቱ ዙር መነሻ ነጥብ ለመድረስ አያበቃቸውም ማለት ነው፡፡መቼውንም ትውፊታዊ ታሪኩን ስንከታተል መጥተን በመሠረቱ የምንናገረው ስለ ጊዜ መለኪያ እንጂ በሜትር ገመድ ስለሚለካው ስለ ቦታ ርቀት እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡

ይሁን እንጂ የቀን ፀሐያዊ ብርሃንና የሌሊት ጨለማ ተስተካክለው የሚገኙበትን ኆኅታዊ ነጥብ አሥምረን በዘመኑ አነጋገር የምድር ዑደት ከዙሩ ኆኅታዊ ነጥብ መነሻ እስከ ዙሩ መድረሻ በ364ቀን ሊፈጸም አይችልም ብለን ብንናገር አቀራረባችን ግልጽ ይሆን ይሆናል፡፡

ይህም ማለት የዓመቱን ዑደት በሚጠተ ብርሃነ ፀሐይ ማለት በብርሃን መመላለስ ብናደርገው ወይም በምድር ዑደት ከነጥብ እስከ ነጥብ በሚፈፀም ጉዞ ብናደርገው ከ364ቀን ጋር ገና መጨመር ያለበት የ30 ሰዓት ወይም የአንድ ዕለት ከአሥራ አምስት ኬክሮስ፤ በሌላም አገላለጽ የአንድ ዕለት ከሩብ ጒዞ መጨመር አስፈላጊ መሆኑ መቼም መች ይታያል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ አስፈላጊነቱ ታውቆ በፋሌካውያን፤ በጥንታውያን ሠራዕያነ ሕግ ይልቁንም በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ምርምር ጸድቆ በግብር እንደመዋሉ መጠን በመጽሐፈ አቡሻክር ሆነ ኢትዮጵያውያን ከጻፉዋቸው ቀደምት ድርሰቶች ተገልጾ የታወቀ ነው፡፡

እነሆም 91፣91 እየሆኑ በአራት ክፍለ ዘመናት ከተመደቡ ቀኖች እያንዳንዳቸው የሰባት ሰዓት ተኩል ጊዜን ያስገኛሉና፡፡

ማለት 7x4=28 ሰዓታት፤ 30x4=120 ደቂቃ ሆኖ  120÷60 ደቂቃ= 2 ሰዓት፡፡ 28+2=30 ሰዓት
ይህ ተውጣጥቶ ሲደመር አንድ ቀን ተኩል ስለሚሆን ከ364 ቀኖች ጋር ተደምሮ 365 ቀን ከስድስት ሰዓት ይሆንና ፍፁም ዐውደ ዓመትን ያስገኛል፡፡
የየዓመቱ ስድስት ሰዓት /የዕለት ሩብ/ደግሞ በአራት ዓመት 24ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ስለሚሆን በአራተኛው ዓመት 366ቀን እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህም በመሆኑ በአራቱ ክፍለ ዘመናት የመጸውና የሐጋይ የጸደይና የክረምት ወቅታውያን የአየር ጠባዮች ከተመደቡባቸው ወራት እንዳይፋለሱ ይጠበቃሉ፡፡ ከዚህም በላይ ለዓመተ ወንጌላውያን መነሻ መሠረት ነው፡፡ ሌላው መንገድ እንዳለው አይዘነጋም ለታሪካዊ ገለጻችን ግን ይህ ይበቃናል፡፡
ይቀጥላል….

ከመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

የፎንት ልክ መቀየሪያ