Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ምዕራፍ አራት 4
ሰባት አዕዋዳት የሚባሉ እነዚህ ናቸው

ከመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

1. ዐውደ ዕለት

5. ዐውደ ዐበቅቴ

2. ዐውደ ወርኀ

6. ዐውደ ማኅተም

3. ዐውደ ዓመት

7. ዐውደ ቀመር ናቸው

4. ዐውደ ፀሐይ

 

እያንዳንዱ ሲተነተን

1. ዐውደ ዕለት፡- ከእሁድ እስከ ቅዳሜ ያሉ ሰባት 7 ዕለታት ናቸው፡፡ እነዚህ አውራኀን /ወሮችን/ ለማስገኘት በዚህ አቋም ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡

2.ዐውደ ወርኅ፡- /ወር/ ዘወትር በፀሐያዊ ቀን ሠላሳ እየሆኑ በጨረቃ ግን አንድ ጊዜ ሠላሳ/30/በሁለተኛ ሃያ ዘጠኝ/29/በመሆን እየተፈራረቁ ዓመታትን ለማስገኘት በዚህ አቋም ሲመላለሱ የሚገኙበት ነው፡፡

3.ዐውደ ዓመት፡-በፀሐያዊ ቀን አቈጣጠር 3ከሩብ፣ በጨረቃ አቈጣጠር ግን 3 የሆኑ የዓመትን ሙሉ ዑደት/ዙር/የሚያስገኝ ነው፡፡ እነዚህ  ከዚህ በላይ1-3ተራ ቊጥር የዘረዘርናቸው ሦስት በዕለት ይቈጠራሉ፡፡ ከዚህ በታች የምንዘረዝራቸው 4ቱን ግን በዓመት ነው የሚቈጠሩ፡፡

4.ዐውደ ፀሐይሃያ ስምንት(28)ዓመታት ነው፡፡ በዚህም ዕለትና ወንጌላዊ  ይገኙበታል፡፡ ዕለቱ ረቡዕ ሆኖ ስለሚገኝ፤ ‹‹ዕለት በትእዛዝህ ይቆማል››ተብሎ የተነገረውን ይገሡበታል፡፡ በፀሐይም ብርሃን ወንጌላዊውን አስመልክተው ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ››የሚለውን በማገናዘብ መምህራን ይናገራሉ፡፡ /መዝ.118/119/91ማቴ.5፡14፡፡ የዐውደ ፀሐይ ቊጥር 28ዓመታት በመሆኑ አራት ጊዜ ሰባት እየሆነ ስለሚገኝ፤ ለዓመተ ወንጌላውያን መሠረታዊ መጠባበቂያ ከመሆኑም በላይ በዐውደ ዓመት ባሉት ዕለታትም በክፍለ ዘመናትና በድቁቅ መሥፈርታትም ቊጥጥር ሰፊ ቦታ የያዘ መሆኑ ይታወቃል፡፡

5. ዐውደ አበቅቴ፡- 19 ዓመት ነው፡፡ በዚህ ፀሐይና ጨረቃ ጐዳናቸውን እየፈጸሙ በቀዳሚ ጥንተ ኆኅት ተራክቦ /መገናኘት/ የሚያደርጉበት መሆኑን  የኀሳበ ዘመን መምህራን ይገልጻሉ፡፡

6. ውደ ማኅተም፡-76 ዓመታት ነው፡፡ በዚህም ዐበቅቴና ወንጌላዊ ይገኙበታል፡፡ ዐበቅቴው 18 ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ማኅተም መባሉ ዐበቅቴው ለዐበቅቴው፣ ወንጌላዊው ለወንጌላዊው ፍጻሜ ናቸውና፡፡ በዚህ መሠረት ነው፡፡

7.ዐውደ ቀመር፡-ዐውደ ቀመር ዐቢይ ቀመር 53 ዓመታት ነው፡፡ በዚህም ዕለትና ወንጌላዊ ዐበቅቴም ይገኙታል፡፡ ዐበቅቴው 18 ነው፡፡ ወንጌላዊውም ዮሐንስ ነው፡፡ ዕለቱም ሰኞ ሲሆን ወደፊት ማክሰኞ የሚል ነው፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ ሲሆን ወደፊት ማቴዎስ የሚል መሆኑን አይዘነጋም፡፡ዐውደ ቀመር በቤተ ክርስቲያን የኀሳበ ዘመን ሊቃውንት ዘንድ በ53ዓመታት ውስጥ በሕርግራግ/በሰንጠረዥ አቀማመጥ/የሚገኙ ልዩ ልዩ ምድቦች አጽዋማትና በዓላት፤ ወይም ሠረቀ ሌሊት ቢሆን የጨረቃ አወጣጥ፤ የሰንበተት ክፍሎች ቢሆኑ፤ ሱባዔያት ወይም ዐውደ ፀሐይ ቢሆን ዐውደ ማኅተም ሁሉ ተጠቃልሎበት ይገኛል፡፡

ስለዚህ በአንድ ዐቢይ ቀመር ያለ ጓዝ ሁሉ በሌላው ተከታይ ዐቢይ ቀመር ያለመለወጥ ይገኛል፡፡ የኀሳብን ሥርዓት ለማወቅ የአንዱን ዐቢይ ቀመር ይዞታን አጠናቆ የዘመን ቊጥር ወደተጀመረበት መነሻ ቢሄዱ ወይም ወደፊት በሚገኘው የዘመን ቊጥር ቢራመዱ መሪ ይሆናል፡፡በቤተ ክርስቲያን የኃሳበ ዘመን ሊቃውንት ዘንድ ስለዐውደ ቀመር /ዐቢይ ቀመር/አቋም እንደዚህ ባለው አቋም የሚነገር ሲሆን በፋሌካውያን የኃሳበ ዘመን አቈጣጠር ደግሞ የሕግ ተፈጥሮ ለውጥንም የሚያሳይ ምልክት እንደሚሰጥ ይታሰብበታል፡፡እነሆም የሰባቱ መሥፈርታትና የሰባቱ አዕዋዳት ምንነት በአጠቃላይ ተመልክተናል ነገር ግን በዝርዝር መግለጹ እሥራ ላይ የሚውልበትን ሁኔታማስረዳቱ የሚከፋ አይደለምና እንቀጥልበታለን፡፡ ለዛሬው ግን ከዚህ ይብቃን፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ