Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በኢትዮጵያ ሥልጣኔ የመንፈሳዊ ት/ቤቶች ሚና

ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ
የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
በመምህራን ጉባኤ ወቅት ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ

1. መግቢያ፤

የኢትዮጵያ ሥልጣኔና ታሪክ፣ ነጻነትና ጀግንነት፣ አንድነትና መልካም ሥነ ምግባር ዋና ምንጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፤

በሌሎች ክፍለ ዓለማት እንዲህ ተሟልተው የማይገኙ እነዚህ አኲሪ ዕሴቶች የተፈጠሩትና ተጠብቀው የኖሩት በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን በተስፋፉ ት/ቤቶች ነው፡፡

መቼም ዕውቀትና ሥልጣኔ የሚስፋፋው በትምህርት ቤት ውስጥ በሚሰጠው የመምህራን አስተምህሮ ነው፤ መምህራን ነቅተውና ተግተው ሲያስተምሩ፣ ትውልድም ጠንክሮ ሲማር ጥያቄ ይነሳል፤ ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሲባል ምርምር ውስጥ ይገባል፤

ከምርምር ውስጥ ብዙ የተሻለ ዕውቀት ስለሚገኝ የረቀቀው ጎልቶ፣ የጨለመው በርቶ እንዲታይ ይሆናል፤ አዳዲስ ሐሳቦችም እንዲፈልቁ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፤ በዚህ ሁሉ ዕውቀት ሲዳብር ሥልጣኔ ይመጣል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

"የመንፈሳዊ ትምህርት ቤቶችና የገዳማት የወደፊት ዕጣ"

ከንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ
የመንፈሳዊ ዘርፍ ጉዳዮች ም/ሥራ አስኪያጅ
ከየካቲት 21 እሰከ 22 ቀን 2006 ዓ.ም በመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት
ለተዘጋጀው የምክክር ስበሰባ የተዘጋጀ

መግቢያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያን ሕዝብ በሃይማኖትና በፈሪሃ እግዚአብሔር ከማነጽ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ባህልና ሥነ ጥበብ በመሳሰሉት ጠቃሚ ነገሮች መተኪያ የማይገኝለት ጉልህና ደማቅ ሥራ እንደሠራች ይታወቃል፤

ቤተ ክርስቲያናችን በረጅሙ ታሪካዊ ጉዞዋ በኅበረተ ሰቡ መካከል መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ጥበባዊ ተግባራትን በማሥረጽ እንደዚሁም የተቀደሰ ባህል በመፍጠር ሕዝቡ ጥሩ የሆነ ሰብእና እንዲኖረው አድርጋለች፤

ቤተ ክርስቲያናችን በሀገሪቱ ላይ ከውጭ ኃይሎች የሚሰነዘርባትን ማንኛውንም ጥቃት በመመከት፣ የሀገሪቱ ሉዓላዊነት፣ ነጻነትና አንድነት እንዲከበር ሕዝቡንና መንግሥታቱን በማስተማርና በመምከር፣ አስፈላጊ በሆነ ጊዜም በግንባር ተገኝታ መሥዋዕትነትን በመክፈል የሚጠበቅባትን ሁሉ አድርጋለች፤

በሀገሪቱ ላይ በአሁኑ ጊዜ የሚታወቁ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ እሴቶች ሁሉ ዋና ምንጫቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ገዳማትና በውስጣቸው የሚገኙ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ውጤቶች ናቸው፤

ስለሆነም ዛሬ የሦስት ሺሕ ዓመታት ታሪክና ቅርስ ያላት ሀገር እንድትኖረን፣ በሃይማኖትና በመልካም ሥነ ምግባር የተገነባ ማኅበረ ሰብ እንዲኖረን፣ ያስቻሉን ገዳማትና የመንፈሳዊ ት/ቤቶች መሆናቸው አይካድም

ዛሬም ቢሆን የኢትዮጵያ ሃይማኖት፣ ታሪክና ማንነት ተጠብቀው የሚገኙት በገዳማት ውስጥ ነው፤ ይህ ታላቅ ሀብት እንዳለ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ገዳማቱ ያላቸው ሚና ከሁሉም የላቀ ነውና እነርሱን በተመለከተ በዚህ ጽሑፍ ለውይይት የሚሆን መንደርደሪያ ሐሳብ ቀርቦአል፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንቀጸ ሕይወት ወፍቅር

"ፍቅር"

አንዲት እናት ናት ነበረች ገና ጡት ያልጣለ ልጇ እንቅልፍ ሲወስደው መደብ ላይ ታስተኛዋለች፡ ፡ ልጇን ከማጥባትና እሽሩሩ በማለት እረፍት ያገኘችው እናት እረፍት የማይሰጠው ሌላውን የቤቷን ሥራ ለመከወን ደፋቀና ማለቱን ተያይዛለች፡፡ እሳት ለኩሳ ማበሳሰሏን ቀጥላለች፡፡ ከመሐል ለምታበስለው ምግብ ማጣፈጫ የምትሻውን ነገር ከቤቷ ባለማግኘቷ አንድ አፍታ ከጎረቤት ተውሳ ለማምጣት ያንቀላፋውን ልጇን ትታ ወደ ጎረቤቷ ቤት አመራች፤ እንዳሰበችው በቶሎ የምትሻውን ሳታገኝ ብትቀርም ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት ፈላልጋ ካገኘች በኋላ ፊቷን በማዞር ተመለሰች፡፡

ከቤቷ አቅራቢያ ልትደርስ ግን ያልጠበቀችው እሳት ቤቷን እንደጧፍ ስያነደውና በአቅራቢያው ያለው ሰው ሁሉ ተሰባስቦ እሳቱን በማጥፋት ሲተራመስ ዐየች፡፡ ሰው ይተራመሳል፣ እኩሌታ ውኃ እኩሌታው ያገኘውን ነገር እያመጣ በቤቱ ላይ ያፍሳል፡፡ ሌላው አፈርና ድንጋይ ይወረውራል፤ የተቀረው ደግሞ በጩኸትና በሁከት ያንን ያዘው ያንን ጣለው ይላል፡፡

ሴቲቱ በሰው ትርምስ መሐል አቋርጣ ወደ እሳቱ ቀረበች፣ እንድትመለስ ከኋላዋ ጩኸትና ሁከታው በረታ፡፡ ነገር ግን እነርሱን በፍርሐት ከራቃቸው እሳት መሐል የእርሷ ልጅ ምንም የማያውቅ እንቦቀቅላ ሕፃን አለና እሳቱ እርሷን ሊያስፈራት የሰዎቹም ሁካታ ሊመልሳት አልቻለም፣ እየሮጠች እሳቱን አልፋ ገባች፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

Ethiopian Orthodox Monasticism and Monasteries

"Homage to the first Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Monastery Overseas after Jerusalem"

Monasticism is a very ancient practice, having existed in the Middle East, ancient Africa and in Asia 20 centuries before it took its form in Christianity. It is found in Judaism [Old Testament], Hinduism, Buddhism, Jainism, Taoism, the Sufi branch of Islam, and Christianity. The English term, Monasticism came from the Greek "monos", meaning "single" or "alone" usually refers to the way of life - communitarian or solitary - adopted by monks and nuns, who have designated to pursue a life of perfection or a higher level of religious experience. In the Old Testament the life of Melketsediq, the Prophet Samuel, Prophets like Elijah, Daniel, Isaiah and John the Baptist, and in the New Testament the Apostles were examples of such a life.

Jesus said (Matt 16:24), "If any man will come after me, let him deny himself and take up his cross and follow me". That is to say self-interest, self-protection, self-regard of all kinds is absolutely a part of man's nature and to master such instincts and govern the passions demand a supernatural strength self denial. Again the Lord said "If you want to be perfect, go and sell what you have, and give to the poor and you shall have treasure in heaven: and come and follow me" Matt 19:21. Therefore, monastic life is a life towards perfection, experience of the heavenly life on earth. Formally speaking, Christian monasticism began in the deserts of Egypt and Syria in the 4th century AD. Saint Anthony the Great was connected with the first Egyptian hermits; Saint Pachomius (d. 346), form the first communities of cenobites in Egypt. Saint Basil bishop of Caesarea (d 379), placed monasticism in an urban social context by introducing charitable service as a work discipline. As Ethiopia has been in contact with the original monastic evolvement the earliest monastic tradition has played a strong role in the development of Ethiopian monasticism. Although monasteries are places of asceticism, spiritual practice and theological learning their services to the society and country was always indispensable. They have for a long time been serving as sources of literally education, social welfare, community leadership, artistic formulation, church music and the study of the Holy Scriptures. Concerning the number of monasteries existing in Ethiopia, out of the nearly 50 thousand churches more than one thousand five hundred are monasteries.

nine saints

The Nine Saints, their names are listed below

Read more...

ገዳማትና ገዳማውያን

መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ፈለቀ

የቅርስ ጥበቃና ምዝገባ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ኃላፊ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በማንኛውም የሰው ልጅ የሥልጣኔ ታሪክ በእምነትም ሆነ በሥነ ጥበብ በየትኛዉ ዘመን በዐለም ላይ ገነው ከወጡ ታሪኮች ጋር አብራ የምትጠራ ጥንታዊት ሀገር ናት፡፡ የተጻፈ ሕግና የተደራጀ የእምነት ተቋም ባልነበረበት ዘመን በሕግ ልቡና ከዚያም በሕገ ኦሪት አንድ አምላክን በይፋ ስታመልክ የነበረች ለመሆንዋም ብዙ ምስክሮች አሉ፡፡ በሐዲስ ኪዳንም የክርስቶስን መንግሥት የምስራች /ወንጌል/ ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ በመስማት ቀዳሚ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ በሐዲስ ኪዳን ከተፈጸሙት አበይት ክንዋኔዎች በሐዋርያት የኑሮ ዘይቤ ላይ የተመሠረተው ሥርዓተ ብሕትውና አርዓያ የወጠነው ሥርዓተ ምንኵስና አንዱ ነው፡፡ በአፍሪካ በረሃ ውስጥ በአባ እንጦንስ የተጀመረው ሥርዐተ ብሕትውና ሐዋርያዊ ትውፊቱን ሳይለቅ የመንፈሳዊ ቅድስና ትውልድ ሐረጉ ሳይበጠስ ፀንቶ የቆየው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

“ገዳማቶቻችን ይጠኑ! መዝገበ ምስጢር ናቸውና”

“ገዳማቶቻችን ይጠበቁ! መሠረተ ስልጣኔአችን ናቸውና”

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA IN PHILO)

የደብረ ምሕረት ጨለቖት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን
ታሪክ፣ ቅርስና መንፈሳዊ አገልግሎት

የጨለቖት ሥላሴን ታሪክ በተለያዩ ሙሁራን በተለያዩ መጻሕፍቶቻቸው በተለያየ ርእሰ ጉዳይ እየተነሱ የተቻላቸውን ያህል አትተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ መምህር ያሬድ ፈንታ አንድ ናቸው፡፡ መምህር ያሬድ ፈንታ ቤተክርስቲያናችን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላሳተመችው “Ethiopian Church Treasures and Faith: 2009”የተሰኘ መጽሐፍ ስለ ጨለቖት ሥላሴ ያቀረቡት ግሩም የሆነ ጽሑፍ በውል ከተገነዘብኩት በኋላ ወደ አማርኛ ተመልሶ ሁሉንም ለአንባቢ ቢቀርብ የተሻለ መልካም ነው በሚል እሳቤ ሙሉ ጽሑፉን እነሆ እላለሁ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ግን እኔም እንደ ታናሽነቴ መጠን ከገዳሙ ዘንድ ተገኝቼ የታዘብኳቸውን እውነታዎች ከሊቁ ከመምህር ያሬድ ፈንታ የጎደለ ታሪክ ለመጨመርና ለማስተካከል ሳይሆን ልናተኩርባቸው ስለሚገቡን ነገሮች ብቻ በስተመጨረሻ ትንሽ ማለቴ አይቀርም፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የቅድስና ትውልድ ሐረግ እንዳይበጠስ
የገዳማት ድምጽ በ፴፻

ኢትዮጵያ በማንኛውም የሰው ልጅ የሥልጣኔ ታሪክ መዝገብ ቀዳሚ ወይም ቀድመው ከሚጠቀሱ ሀገሮች እንዷ ናት በእምነትም ሆነ በሥነ ጥበብ በየትኛው ዘመን በዓለም ላይ ገነው ከወጡ አጋጣሚዎች ሁሉ የሀገራችን ስም አብሮ አለ፡፡ የተጻፈ ሕግና የተደራጀ ተቋም ባልነበረበት ዘመን በሕገ ልቡና ከዚያም በሕገ ኦሪት አንድ አምላክን በይፋ ስታመልክ የነበረች ለመሆንዋም ብዙ ምስክሮች አሉ፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ከተፈጥሮ ሀብቷና ሉዐላዊ ታሪኳ ጋር ከመጀመሪያው መጽሐፍ ሁለተኛ ምዕራፍ ጀምሮ ተጠቅሳለች፡፡ በሐዲስ ኪዳንም የክርስቶስን መንግሥት የምስራች /ወንጌል/ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ በመስማት ቀዳሚ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ በሐዲስ ኪዳን ከተፈጸሙት ዓበይት ክንዋኔዎች በሐዋርያት የኑሮ ዘይቤ ላይ የተመሠረተው ሥርዓተ ብሕትውና አርአያ የወጠነው ሥርዓተ ምንኩስና አንዱ ነው፡፡ በአፍሪካ በረሃ ውስጥ በአባ እንጦንስ የተጀመረው ሥርዓተ ብሕትውና ሐዋርያዊ ትውፊቱን ሳይለቅ የመንፈሳዊ ቅድስና ትውልድ ሐረጉ ሳይበጠስ ፀንቶ የቆየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡

በሀገራችን የምንኩስና አመጣጥ ከአባ ፍሬምናጣስ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የሚጀምር ቢሆንም በቀደምት ታሪኩ አባ ሙሴ ኢትዮጵያዊ /ጸሊም/አባ መጣዕ /ዘሊባኖስ/አብረው ይጠቀሳሉ፡፡ እነርሱም የጉባዔ ጻድቃን መሥራች የማኀበረ በኩር መሪዎች ነበሩ፡፡ ፍጹም መስፋፋትና ጠንካራ መሠረት የቆመው ከምዕራባዊ ሜዲትራንያን ከመጡ ከ፱ቱ ቅዱሳን በኋላ ነው፡፡ ፍፁም ኢትዮጵያዊ የሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ ሊቃውንት ተጋድሎ ነው፡፡ ከ5ኛዉ ክፍለ ዘመን ማብቂያና ከ6ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ገዳማት ጥንታዊ ሥልጣኔ እንዳይጠፋ የሐዋርያት መሠረት ላይ የቆመችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ክርስትና እንዳትዳከም፤ በአሕዛብ መካከል የክርስትና ደሴትን አጽንቶ በማቆየት ፈተና መከራን አልፈው አሁን ድረስ ዘልቀዋል፡፡ በአሳለፉአቸዋው ዘመንም የአራዊትን ድምጽ ታግሰው፣ የሌሊት ቁርን የቀን ሐሩርን ተቋቁመው፣ ዋሻ ሞሰው ጤዛ ለብሰው ዳዋ ተንተርሰው፣ የባዕድ ወራሪን የወገን ሰርሳሪን፣ መክተው ታላላቅ ማዕከላት አቋቁመዋል፣ ብራና ፍቀው ቀለም በጥብጠው ብዕር ቀርጸው ታሪክንና ዕውቀትን በጽሑፍ በሥዕል በዜማ አቆይተዋል፣ ሰው በተፈጥሮው ተጋብቶ ትዳር መሥርቶ ወንድም እህት ልጅ አፍርቶ ከሚኖረው ኑሮ ተለይተው ሳይተዋወቁ ተዋደው ከአንድ እናት ሳይወለዱ ወንድማማች እህትማማች፤ እህትና ወንድም ሆነው አባትና ልጅ ተባብለው ጠንካራ ማኀበራዊ ሥርዓትን መሥርተዋል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ የዓለምን ቀደምት ሥልጣኔ አንገት የምታስደፋበትን ታሪክ አቆይተዋል፡፡

በመጀመሪያው ሺህ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገዳማት በሰፊው የተዋቀሩበት በመላው የአክሱም ግዛት የተመሠረቱበት የተገነቡበት ዘመን ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የነበሩት ገዳማት ትልቁ ተግባራቸው አንደኛ የኦሪቱን አምልኮተ እግዚአብሔር ወደ ሐዲስ ሥርዐት በመለወጥ ክርስትና ያለ ደም መፍሰስ በሰላም እንድትሰበክ ማድረግ ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል የተሳካ ሽግግር ማድረግ፤ መስዋዕተ ኦሪትን በአማናዊው መስዋዕተ ሐዲስ መለወጥ፡፡ እንግዳ በመቀበል ዐሠረ ምንኩስና በመከተል ገዳማትን መመሥረት የክርስትና መጻሕፍትን ወደ ግእዝ ቋንቋቸው በጥንቃቄ በመተርጎም ሀገራቸው የክርስቶስን ትምህርት በራሷ ቋንቋ እንድትሰማ ማድረግ፤ ነባሩን የሥነ ሕንፃ፣ ሥዕል፣ ሥነ ጽሕፈት፣ ሥነ ዜማ በመከተል አቢያተ ክርስቲያናትን፣ ድንቅ ሥዕላትን የዜማና የሥርዐት መጻሕፍትን በማዘጋጀት ጽኑ መሠረትን ጥለዋል፡፡ የእነዚያን ገዳማት ተጽዕኖ ለማየትና ለመረዳትም በሀገራችን ከጥፋት የተረፉት የ፱ቱ ቅዱሳንን ገዳማት በማየትና የቅዱስ ያሬድ የዜማ ሥራ፣ የአፄ ካሌብ ከየመን ድል በኋላ ወደ ገዳም መግባት የደብረ ዳሞን ጥንታዊ ትምህርት ቤት አበይት ምስክሮች ናቸው፡፡

የዚህ ሺህ ዘመን ፍፃሜ የዐረባዊው የባህል ሃይማኖት እስልምና መስፋፋትና የባህር በሮቻችን መዘጋትና የዮዲት ጉዲት የ40ዓመት ከፍተኛ ጥፋት ተፈጸመ፡፡ ከኢትዮጵያ ሥልጣኔ ወድቀት ጋር በርካታ ገዳማትና ሀብቶቻቸው አብረው ወደሙ፡፡ ሆኖም ግን ጥንካሬው መሬትና ራስን አሳልፎ በመስጠት የሚመራው ገዳማዊ ሕይወት የሀገርን ማዕከላዊ ሉዓላዊነትና የቤተ ክርስቲያንን ህላዌ ይዞ ወደ ሁለተኛው ሺህ ዘመን ተሻገረ፡፡

የሁለኛው ሺህ ዘመን ገዳማት

ሁለተኛው ሺህ ዘመን የተጀመረው በዛግዌ ኢትዮጵያ ሥርዐት አክሱም የነበረውን ማዕከል ወደ ደብረ ሮሃ በማዛወር ነው፡፡ በዚያም በተገኘው ነፃነት አሁንም ገዳማውያን ሥራቸውን እንደገና ጀመሩ በተለይ አራቱ የመጨረሻ የዛግዌ ነገሥታት ሕይወታቸው ሙሉ ለሙሉ የክርስቶስ አገልግሎት የተሠጠ በመሆኑ ዛሬ ዓለም የሚደነቅባቸውን የሥነ ሕንፃና ጥበብ ባለቤት ሆኑ የመሠረቱአቸው ገዳማትም የከፍተኛ እውቀትና እምነት ማዕከላት ነበሩ፡፡ የሁለተኛው ሺህ አጠቃላይ የገዳማትን ገጽታ ወደ ልዩ ምዕራፍ የለወጡት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ናቸው፡፡ ከጥንታዊው የአቡነ አረጋዊ ትምህርት ቤት የሥርዐተ ምንኩስና መምህር አባ ዮሐኒ ሥር ተምረው በደብረ ሐይቅ በመምጣት ትልቁን ትምህርት ቤት መሠረቱ በዚህም አእላፍ መነኮሳትንና ሊቃውንትን በመንፈስ ወለዱ፡፡ በመላው ኢትዮጵያ የወንጌል ሐዋርያትን ላኩ፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ድንቅ የሆነውን ገዳም የትምህርት ማዕከል በማድረግ በጊዜው በሰሜን ተወስኖ የነበረውን ሥርዐተ ምንኩስና ወደ ደቡብና መካከለኛ ኢትዮጵየ አመጡት እንደ ክዋክብት የሚያበሩ ቅዱሳንን በማፍራት ደብረ ሊባኖስ፣ ደጋ፣ ጋሥጫ፣ ደብረ አሮን . . . እጅግ ብዙ ገዳማት የዚሁ ትምህርት ቤት ውጤት ሆኑ፡፡ ገዳማት አበቡ ጠነከሩ ኢትዮጵያም አደገች የድንበር ወሰኗ ሰፋ በትምህርት አደገች በሥነ ጽሑፉ በሥነ ጥበብ ከበረች ገዳማቱ የትምህርት ማእከል ብቻ ሳይሆን የአስተዳደር የፍትሕ የማኀበራው ዋስትና፣ የሥነ ምግባር የብሔራዊ ደኅንነት፣ የባህልና የኢኮኖሚ መሠረትም ሆኑ፡፡ ከዚያ ሁሉ አልፎ ገዳማቱ እንደ ዐቃቤ ሰዓት /የደብረ ሐይቅ ማዕረማ/የመሰለ ከፍተኛ የመንግሥት /የቤተ መንግስት/ሥልጣን ባለቤት ሆኑ፡፡ አበው መነኮሳት ዐለምን ንቀው በበረሃና በዱር ውስጥ ተቀምጠው ከሰው መደበኛ ሕይወት ርቀው ለዓለምና ለሰው ልጅ የሚጠቅምን ሥራ ሠሩ፡፡ ይኸ ሁሉ ሲሆን ግን ያለመከራ አልነበረም በፈቀዳቸው ከገቡበት የተጋድሎ ሕይወት የውጭ ወራሪ እየመጣ ብዙ መከራን ደርሶባቸዋል፡፡ ከእነዚህም በሁለተኛው ሺ ከደረሱ ጥፋቶች የ15 ዓመቱ የቱርክ መንግሥትና የአህመድ ግራኝ ወራሪ የካቶሊካውያን ተንኮልና የጥፋት ተልዕኮ እንግሊዝ የቱርክ የዐረቦች፣ የግብጽ፣ የጣሊያን ወራሪና ድብደባ መጠን እንደእነሱ ቢሆን ዛሬ በኢትዮጵያ አንድም ገዳም ባልተገኘ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ገዳማትና ገዳማውያን ግን ይህን ሁሉ ተቁቁመው በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም እንኳን ያሏትን ገዳማት ሳይቀር ጠብቀው የ፳፻ መድረሻ ዘልቀዋል፣ የኢትዮጵያ ገዳማት የእምነትና ሥርዓተ አምልኮ መተግበሪያ መካናት ብቻ አይደሉም የኢትዮጵያዊያን የማንነት መዛግብት የሥልጣኔአቸው ማኀደራት የማኀበራዊ እሴቶቻቸው ሁሉ ማምረቻ መርሆዎች፣ የሉዓላዊነትና የክብር ጉልላቶች የዕውቀት ባህር የጥበብ ሙዳይ የፍቅርና የርህራሄ ምንጭ የበረከት መፍለቂያ የመንግሥተ ሰማያት መሻገርይ መሰላል ትክል ናቸው፡፡

በ፳፻ መዳረሻ ዘመን ወታደራዊው የቁሳዊ ፍልስፍና ተከታይ ኮሞኒስት መንግሥት እጅግ በከፋ ጭካኔ ንብረታቸውን ወረሰ ክብራቸውን ገፎ ያለመተዳደሪያ ያስቀራቸው የኢትዮጵያ ገዳማት ልጃቸው መነኮሳት የቀደመ አገልግለታቸው እንዳይታጎል ወደ ከተማ በመምጣት ከምእመናን ርስት ቢሰበስቡ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም አንዳንዶቹ በገቡበት ከተማ መረብ ሥር ወድቀው በዚያው ይቀራሉ የሚመስላትም ልባቸው እየተከፈለ ገባ ወጣ በማለት ይታያሉ፡፡ ዛሬ ገዳማት ለብዙ ዘመናት ያከማቿቸውን የእምነት፣ የታሪክ፣ የዕውቀትና የጥበብ ቅርሶች /ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱት/የሚጠብቃቸው እንዳይታጣ ሽማግሌዎቹ አበው እጃቸውን ያዛል ኃላፊነትን ወገባቸውን ያጎበጠ አደራንና ትከሻቸውን ያቆሰለ ግዳጅን ተሸክመው በአምላክ ቸርነት ቆመዋል፣ ኢትዮጵያዊያን የተዋሕዶ ልጆች የአባቶቻቸውን አጽም በረከት፣ የገዳማት የፈውስ እጣን መዓዛ ስቧቸው በረድኤት ይመጡ ይሆናል በማለት በርበር ያያሉ፣

ገዳማት ስፍር ቁጥር ከሌለው የበረከትና የጸጋ ስጦታ ይዘው ወደ ሦስተኛው ሺህ ተሻግረዋል፣ ያወቀባቸው አስከአሁን ተጠቅሟል፡፡ በመንፈስ መንግስተ ሰማያትን ወርሷል በሥጋ ተከብሮ ኑሮባቸዋል፣ የአውሮፓ ሊቃውንት ሳይቀሩ ከነርሱ በተገኘ ሀብት ፕሮፌሰር፣ ዶክተር፣ ተብለውባቸዋል ኤክፖርት ተጠያቂ እየተባሉ ተሹመውባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ትውልድስ ምን አስቧል፡፡ በርግጥ ቅርሶቻቸውን በመዝረፍ እንደ ሸቀጥ እቃ የአባቶቻቸውን የሕይወትና የጥበብ ማኀተም የሚሸጡ ብዙ አሉ፣ በርግጥ በአውሮፓ የኑፋቄ ዘንግ ህሊናቸው ተማስሎ የአባቶቻቸውን እውነት ዘወር ብለው እንዳያዩ የሉተር ጋሬጣ ተሰክቶባቸው የአምላክን አካል እናድሳለን በማለት በነፋቄ ጥፋት ገዳማትንና መነኮሳትን የሚሳደቡ አሉ፣ በርግጥ የዐረብ ባህልና ፖለቲካን ሃይማኖት አድርገው እሳት የሚጭሩም አሉ፣ ስዕል ወጥረው፣ ወይም ጥላ ዘቅዝቀው፣ ካርኒና ትራክት አዘጋጅተው፣ የፕሮጀክት እቅድ ነድፈው፣ በልዩ ልዩ በየደረጃው በገዳማት ስም እየለመኑ ለራሳቸው ዝናንና ገንዘብን የሚያካብቱም አሉ፣ እውነተኛ የተዋሕዶ ልጆች፣ የቅዱሳን ጉባዔ መንጎችስ ምን ይላሉ?ይህ የሺህ የዓዳም ድምር መልስ የሚፈለግባቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ዛሬ ገዳማት በያሉበት ቦታ ለአካባቢው እና ሩቅ ላለው ትውልድ ሁሉ እንዳጥንቱ የልማት፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የሥነ ጥበብ፣ የታሪክና የቅርስ ማዕከል ለመሆን የሚከለክላቸው ምንም ነገር የለም፡፡ ትብብርና የጋራ ጥረትን ግን ይጠይቃሉ፡፡ የንጽሕናና የቅድስና ሕይወት መመሪያ የያዙ በህብረተሰብ አገልግሎት ላይ ያተኮሩ የማንነታችን መገለጫ የሆኑ ገዳማት ለአዲሱ የ፫ተኛ ሺህ ትውልድ ያስፈልጉታል፡፡ የዐለም ሰላምና የሰው ልጅ ደህንነት የሚረጋገጠው መንፈስ ጠንካራነትና የሰለጠነ ትውልድ የበላይነት ሀገር የተረጋጋ ዜጋ፣ ማፍራት የሚችለው ሰጥቶ መቀበልን ወይም ንግድን፣ ወይም ቅጥረኛነትን መሠረት ባደረገ ማኀበራዊ አደረጃጀት ሳይሆን ራሳቸውን ለእግዚአብጠር አገልግሎት፤ እውቀትና ችሎታቸውን ለእግዚአብጠር ሥነ ፍጥረት ደኀንነት መስዋዕት ባደረጉ ገዳማውያንና ገዳማት ነው፡፡ ስለዚህ የገዳማት የወደፊት ራዕይ በትውልዱ ቅን የአስተሳሰብ እኅት ላይ የወደቀ ነውና የገዳማትን ድምጽ እንስማ፡፡ ሰምተንም በበጎ እንመልስ፡፡ እንዳልሰማን አንሁን፡፡ እኛ እንድንሰማ ምዕራገ ፀሎት የሚሆኑን በመላው ዓለም ደግም ክፉ ብለን እንድንታይ የሚያደርጉን ግርማ ሞገሠቻችን ናቸው፡፡ የገዳማትን ቅርሶች አብረን እንጠብቅ በልማት እናግዛቸው አባቶች በየጊዜው ዕጣን ጧፍ እያሉ ከሚመጡ እዚያው በልማት ብንደግፋቸው ምርታቸውን ያበረክቱልናል፣ በቅዱስና እንጎበኛቸው እንደ ዐይን ብሌን እንጠብቃቸው የአባቶቻችን የተጋድሎ ላሕብ፣ የመስዋዕትነት ደም ያረፈባቸው የስባረ አጽማቸው መካናት ሕያው አሻራ ናቸውና እንዳይጠፉ እንንከባከባቸው፡፡ የቅድስና የትውልድ ሐረግ እንዳይቆም ፈጽሞም እንዳይበጠስ ገዳማውያንና ገዳማትን እናበረታታ፡፡

የሰለም አባት እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል

የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዋና ሥራ አስኪያጅ

የፎንት ልክ መቀየሪያ