Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንቀጸ ሕይወት ወፍቅር

"ፍቅር"

አንዲት እናት ናት ነበረች ገና ጡት ያልጣለ ልጇ እንቅልፍ ሲወስደው መደብ ላይ ታስተኛዋለች፡ ፡ ልጇን ከማጥባትና እሽሩሩ በማለት እረፍት ያገኘችው እናት እረፍት የማይሰጠው ሌላውን የቤቷን ሥራ ለመከወን ደፋቀና ማለቱን ተያይዛለች፡፡ እሳት ለኩሳ ማበሳሰሏን ቀጥላለች፡፡ ከመሐል ለምታበስለው ምግብ ማጣፈጫ የምትሻውን ነገር ከቤቷ ባለማግኘቷ አንድ አፍታ ከጎረቤት ተውሳ ለማምጣት ያንቀላፋውን ልጇን ትታ ወደ ጎረቤቷ ቤት አመራች፤ እንዳሰበችው በቶሎ የምትሻውን ሳታገኝ ብትቀርም ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት ፈላልጋ ካገኘች በኋላ ፊቷን በማዞር ተመለሰች፡፡

ከቤቷ አቅራቢያ ልትደርስ ግን ያልጠበቀችው እሳት ቤቷን እንደጧፍ ስያነደውና በአቅራቢያው ያለው ሰው ሁሉ ተሰባስቦ እሳቱን በማጥፋት ሲተራመስ ዐየች፡፡ ሰው ይተራመሳል፣ እኩሌታ ውኃ እኩሌታው ያገኘውን ነገር እያመጣ በቤቱ ላይ ያፍሳል፡፡ ሌላው አፈርና ድንጋይ ይወረውራል፤ የተቀረው ደግሞ በጩኸትና በሁከት ያንን ያዘው ያንን ጣለው ይላል፡፡

ሴቲቱ በሰው ትርምስ መሐል አቋርጣ ወደ እሳቱ ቀረበች፣ እንድትመለስ ከኋላዋ ጩኸትና ሁከታው በረታ፡፡ ነገር ግን እነርሱን በፍርሐት ከራቃቸው እሳት መሐል የእርሷ ልጅ ምንም የማያውቅ እንቦቀቅላ ሕፃን አለና እሳቱ እርሷን ሊያስፈራት የሰዎቹም ሁካታ ሊመልሳት አልቻለም፣ እየሮጠች እሳቱን አልፋ ገባች፡፡

የቤቱን ዙሪያ ያጠረው እሳት በፈጠረለት ሙቀት ያለ ሐሳብ እንቅልፉን የሚሰጠውን የአብራኳን ክፋይ ተንደርድራ ከተኛበት መደብ አነሳችው፤ የፍቅሯን በእቅፏ ይዛ ደጋግማ ሳመችው በኋላም የልጇን የእርሷንም ሕይወት ለማትረፍ ፈጥና ለመውጣት የተሻለ መንገድ ታማርጥ ጀመር፡፡ ነገር ግን ስትገባ አነስተኛ ቁመት የነበረው ነበልባል የጎጆዋን ዙሪያ በልቶ ወደ ሳሩ በመድረሱ ረዝምአል፡፡ መውጫዋን ሁሉ አጥሮባት እንዳትወጣ ከለከላት፤ ከዚህ ባለፈ ደግሞ የእሳት ጉራጆች እየወደቁ እሷን ሊያቃጥሏት ልጇንም ሊነጥቁባት መሆኑን ስታይ የመዳን ተስፋቸው መጨለሙ ጭንቀትና ፍርሃት በረታባር፡፡ ቢሆንም ፍርሃት በርሷ ዘንድ ቦታ እንዳይኖረው ያደረጋት የደረሰውን ሁሉ ባለማስተዋል በፍቅር ዓይን የሚያዩዋት የልጇ ዓይኖች ነበሩ፡ ፡ እናም ተበራታች ሞታቸው እንኳን የማይቀር ቢሆን እርሷም ልጇም በአንድነት መጥፋት የለባቸውም፡፡

በፍጥነት የቤቷን ወለል ምሳ ልጇን ከስር ከልለው ተኛች፡፡ እሳቱ ግን አሁንም አላቆመም እጅግ ተባብሶ ቤቷን እስኪያስከስል ድረስ ነደደ፡፡ ሊያጠፉት የተሯሯጡት በዙሪያው የቆሙ ሰዎች ሁሉ ማጥፋቱ እንዳልተሳካላቸው ሲያውቁ ... የእሳቱን ነዶ መጨረስና ማቆም ከጠበቀ በኋላ እናትና ልጅ ገላ ለመቅበር ወደ ከሰለው ቤት ቀረቡ፤ የሕፃን ለቅሶ እንደሚሰሙ ግን አልጠበቁም ነበር፡፡ እናት ልጇን አድና እርሷ ነዳ አልቃለች፡፡

ከዚህ ሁሉ የበለጠ ነገር ምን አለ? ራስን መስዋዕት አድርጎ ሌላው እንዲኖር ከማስቻል የሚበልጥ ፍቅር ከወዴት ይኖር ይሆን? ፍቅር እውነተኛነቱ ተፈትኖ የሚታወቀው እንዲህ በችግርና በስቃይ ውስጥ አልፎ መስዋዕትነትን ሲከፍል ነው፡፡ መሥዋዕትነትን ሊከፍል ያልወደደ እሱ ፍቅር የለውም ፍቅር ያለው ሰው ሁሉን ስለፍቅር ይተዋልና፡፡

የሁሉ አባት የሆነ አብርሃም ለአምላኩ እግዚአብሔር ስለነበረው ፍቅር ሕዝብንና የአባቱን ቤት ትቶ ተሰደደ፣ በዚህ ብቻ አላበቃም በስተርጅናው ያገኘውን ዘር አንድ ልጁን አሳልፎ ለመስጠት ወደ ሞርያም ተራራ ወጣ፣ እንጨትና እሳን አዘጋጀ ሰይፍ የያዘውን እጁን ለመስዋዕት በልጁ ላይ አነሳ ዘፍ.22፡ 1-10 ዳንኤልም አምላኩን በወደደ ጊዜ እስከ አንበሶች ጉድጓድ ድረስ ራሱን አሳልፎ ሰጠ ትዳ.6፡10-18 ሦስቱ ሕፃናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤልም እንዲሁ ፍቅራቸውን ያረጋገጡት በእሳት እስከመጣል ነበር፡፡ ትዳ.3፡14

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ የነበረውን ፍቅር ሲገልጥ ቢሆንልኝ በሞት እንድመስለው እመኛለሁ ፊሊ. 3ፏ.10-11 በማለት ጽፏል፡ ፡ ጻድቃን ሰማዕታትም ለአምላካቸው ስለነበራቸው ፍቅር ደማቸውን አፍስሰዋል፣ ሕይወታቸውንና ተድላ ደስታቸውን ትተዋል፡፡ ለእርሱም በነበራቸው ፍቅር የተነሳ መከራውን ሳይሳቀቁ ፍርሃትን ከልባቸው አውጥተው ጥለዋል፡፡

ፍፁም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላልና፡፡ ፍቅር መስዋዕትን የሚጠይቅ መሆኑን ካነሳን ታዲያ የሰው ልጅ ዛሬ ባለንበት ዘመን አንዲህ እንደቀደሙት ሁሉ ስለ ፍቅር መስዋዕትነትን እንዳይከፍል ምን አገደው?

ራስን መስዋዕት አድርጎ ሌላው እንዲኖር

ከማስቻል የሚበልጥ ፍቅር ከወዴት ይኖር ይሆን?

የፎንት ልክ መቀየሪያ