ኪነ -ጥበባት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ "በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዝክረ ቅዱስ ያሬድ" በሚል ጥር 5 ቀን 2005 ዓ.ም በተካሄደ ታሪካዊ ጉባኤ
በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ
ከዚህ ተነሥተን የዜማን አመጣጥ ስናስተውል እግዚአብሔር አምላክ በዜማ መመስገን ፈቃዱ ስለሆነ ፍጡራን በተፈጥሮአቸው ዜማን እንዲወዱ አድርጎ እንደፈጠራቸው እንገነዘባለን፡፡ የሃይማኖት ዜማ የራሱ የሆነ የእንቅስቃሴ ስልት፣ የኃይለ ቃል ምጥቀት፣ የሥነ ቃልና የምሥጢር ቅንብር ስላለው ከሌሎቹ ሳይደባልቁ ራሱን አስችሎ ማስኬድ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ከራሱ ጠባይ ወጥቶ ከዘፈኑም ከቀርርቶውም ከተደባለቀ ሕዝቡ የሃይማኖትን ዜማ ከዘፈን ለመለየት ይቸገራል፤ ዜማው ከዘፈን ጋር ሲመሳሰል ክብርና ልዕልና ያጣል፣ ማንም ዘፋኝ እንደሚቀባጥረው ተራ ነገር መስሎ እንዲታይ ይሆናል፤ ተመስጦ አይሰጥም፣ ተወዳጅነትና ተቀባይነትም ያጣል፣ ስለሆነም የሃይማኖት መዝሙር ይህንን ሁሉ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በጥንቃቄ ሊዘጋጅና ሊዘመር የሚገባ ነው፡፡ እንግዲህ ስለዜማ አመጣጥና አጠቃቀም በአጭሩ ይህንን ካልን ዜማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ከዚህ ቀጥሎ እናያለን፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መምህራን ወንጌልን እንዴት ማስተማር አለባቸው?በመምህር ሙሴ ኃይሉ
|
"የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን"በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA IN PHILO) "በገና"፡- እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደ መሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡ እነርሱም፡- 1. ሰዋስዋዊ ትርጉምና 2. ሥነ ቃላዊ ትርጉም.............. ይባላሉ፡፡ 1. የበገና ሰዋስዋዊ ትርጉም
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ "መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ" በሚል መጽሐፋቸው በሁለት መልኩ ማለት "ሲጠቅብና ሲላላ" ብለው በማመሳጠር እንዲህ ብለው ተርጉመውታል፡፡ በገና፡- በዕብራይስጥ ናጌን ይባላል ካሉ በኋላ ሲተረጉሙት ፡- ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ ማለት ነው፡፡ ሲጠብቅ ግን ፡- ነደደ፣ ተቆጣ... ያሰኛል ብሏል፡፡ በገና፡- በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ፡ መጽሐፈ ስዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)
"የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን"በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA IN PHILO)
እነርሱም፡- 1. ሰዋስዋዊ ትርጉምና 2. ሥነ ቃላዊ ትርጉም.............. ይባላሉ፡፡
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፡፡ሚልክ 3፡ 10ዐሥራት በኩራት በቤተ ክርስቲያንበመምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በምንኖርበት ዓለም እግዚአብሔር ከሠራ ውጭ ያለ ምንም ነገር የለም፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔር ሥራና የርሱ ስጦታ ነው፡፡ የሁሉ ፈጣሪና አስገኝ የሁሉ ምክንያት የሆነ አምላ ሰውን በራሱ መልከና አርዓያ ሲፈጥር የፍጥረቱ ሁሉ ማእከልና የፍጥረቱ ጠባቂ የፍጥረቱ አዛዥ እንዲሆን አድርጎ ፈጥሮታል፡፡ እግዚአብሔርም አለ ሰውን በምልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር፣ የባሕር ዓሣዎችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁሉ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዙ (ዘፍ 1፡ 26) በዚህ ዓላማ የፈጠረውን ሰውም ከፈጠረው በኋላ ይኽንኑ ዓላማ እንዲፈጽም ከቡራኬ ጋር አዞታል፡፡ (ዘፍ 1፡ 28)፡፡ ዐሥራት በኩራት ማለት የሰው ልጅ እግዚአብሔር ከሰጠው ነገር ሠርቶ፣ ወይም አምርቶ፣ ወይም አትርፎ ለራሱ ከሚያደርገው፣ ከወረቱ ከሚተርፈው ዐሥር እጅ በቃል ሳይሆን በተግባር አምላኩን የሚያመሰግንበት የዕሴት ስጦታው ነው፡፡ የዐሥራት በኩራን ትርጉምና አገልግሎት ለይተን ካላወቅን በትክክል ልንረዳው አንችልም፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ቢሆንም የሰውም ልጅ አምላኩ ከሰጠው ውጭ ምንም የራሱ የሆነ ነገር የለውም፡፡ የሰው ልጅ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ይዞት የመጣው ነገር፣ ከዚህ ዓለም ተለይቶ ወደ ሌላው ዓለም ሲሻገርም ይዞት የሚሔደው ነገር የለውም፡፡ ሁሉንም ነገር የሚያገኘው እዚሁ ዓለም ነው፡፡ በግብርና እርሱ አንዲት ቅንጣት ዘር ሲዘራ በዝናብ አርጥቦ በቀደመ የሥነ ፍጥረት ትእዛዙ አንዷ ስንዴ በርክታ የምትወጣው በአምላክ ርዳታ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሚሠራው ሥራ ሁሉ የእግዚአብሔር መግቦትና በረከት ሳይኖርበት የሚያገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ አማኝ ያለሆነው በመግቦቱ የሚያምነው ደግሞ በመግቦቱም በበረከቱም ይሆራል፡፡
SAINT ABBA GIORGIES OF GASSICHA THE ETHIOPIAN THEOLOGIANDaniel SeifeMichael Feleke (Memihir) Head of the Department for Heritage preservation and Library-Museum of the Patriarchate
His blessing be with us all SAINT YARED THE ETHIOPIAN HYMNOLOGISTDaniel SeifeMichael Feleke (Memihir) Head of the Department for Heritage preservation and Library-Museum of the Patriarchate
St. Yared lived in the 6th century. He was born in Axum, Ethiopia's ancient capital city, from the family of orthodox priesthood. Yared received educational and moral guidance from his uncle Gaidiwon who was chief scholar of the church. He was highly promoted by the then Emperor Gebre Meskel. Abune Aregawi was also one of the Nine Saints who gave him information about the church. Saint Yared, the king and Abune Aregawi were close friends who jointly expanded church services and established sacramental institutions in Ethiopia. St. Yared composed his music in his five major hymnological books (called Daggawa, TsomeDaggawa, Zamare, mawas‛at and ma‛araf), with three types of melodies or modes: Geez, Ezle, and Araray. Each tune is distinct that do not mix, or overlap with one another. They have their own exclusive symbolic meanings and applications. Along with these there are three distinct musical instruments namely Kebero (drum), Tinasil (Cestrum) and Mequamia (prayer staff). The kebero is always played with the bare hands on its two faces. The Ethiopian cestrum is the oldest and best known idiophone instrument. The prayer staff is made of wood or iron and has a handle in the shape of horn at one end. It is moved by the singers in different directions; where each movement has symbolic meaning. The books Daggawa, Tsome Daggawa, Zamare, mawas‛at and ma‛araf are written by selecting appropriate readings for prayer and chanting from the Old Testament, New Testament and books of Scholars. He composed songs for four seasons of a year - Matsew (spring), Hagay (summer), Tsedey (harvest Season) and Kiremt (the rainy season). All songs follow the canonical liturgical calendar of the church. St. Yared is considered as the founder and organizer of Ethiopian Church liturgical songs, throughout the history of Ethiopian Church different schools and hymnological scholarship has been developed all based on his original works. His blessing be with us all |

"በገና"፡- እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደ መሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡
Saint Abba Georges of Gashicha the Ethiopian theologian was of the most prominent Theologians of the EOTC, and an important figure in monastic, literary, liturgical and doctrinal history. He was born in Amhara region South Wollo Zone, in 1357 AD. He prolifically wrote a number of influential theological, philosophical, poetic and liturgical works. He had a strong impact on monastic leaders of his time and inspired and advised monks to work harder and to deepen their spirituality. Saint Abba Giorgis was both a churchman and a well known personality in his own right at the royal court of emperor Dawit. He was the tutor of King Dawit II's eight children most of whom became kings successively. He was also a leader of one monastic community in Wollo Kelela. He played a significant part in theological debates, shaming his opponent's by his erudition and gaining great prestige as defender of Orthodox Tewahedo faith. He developed profound theology in his book of Mystery, which expressed the depth of Ethiopian spirituality and responded to the burning issues of his day. His very practical personalities, made tangible contributions to the development of monastic life, inspire both intellectual and laity to a biblical and spiritual orientated life. Saint Abba Giorgis of Gasicha's presence and charisma was such that generations of monks have been motivated to emulate him and to be enthusiastic, diligent and self- sacrificing in their commitment. His intellectual legacy is enormous, among his more than 40 authentic compositions 'payer of the hours' and Eucharistic anaphora, the book of mystery, Arganon, Hohite Brehan, Selamta, are still widely used. His other works have in many ways provided a frame of reference for the standard Orthodox faith, to the extent that he has been given the epithet, the St, Cyril and the St, Johan Chrysostom of Ethiopia. His works encourage modern Ethiopians to have a conscious faith which is nourished by a wealth of profound erudition, and a deep Marian devoutness.
