Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፡፡

ሚልክ 3፡ 10

ዐሥራት በኩራት በቤተ ክርስቲያን

በመምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል

በምንኖርበት ዓለም እግዚአብሔር ከሠራ ውጭ ያለ ምንም ነገር የለም፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔር ሥራና የርሱ ስጦታ ነው፡፡ የሁሉ ፈጣሪና አስገኝ የሁሉ ምክንያት የሆነ አምላ ሰውን በራሱ መልከና አርዓያ ሲፈጥር የፍጥረቱ ሁሉ ማእከልና የፍጥረቱ ጠባቂ የፍጥረቱ አዛዥ እንዲሆን አድርጎ ፈጥሮታል፡፡ እግዚአብሔርም አለ ሰውን በምልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር፣ የባሕር ዓሣዎችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁሉ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዙ (ዘፍ 1፡ 26) በዚህ ዓላማ የፈጠረውን ሰውም ከፈጠረው በኋላ ይኽንኑ ዓላማ እንዲፈጽም ከቡራኬ ጋር አዞታል፡፡ (ዘፍ 1፡ 28)፡፡ ዐሥራት በኩራት ማለት የሰው ልጅ እግዚአብሔር ከሰጠው ነገር ሠርቶ፣ ወይም አምርቶ፣ ወይም አትርፎ ለራሱ ከሚያደርገው፣ ከወረቱ ከሚተርፈው ዐሥር እጅ በቃል ሳይሆን በተግባር አምላኩን የሚያመሰግንበት የዕሴት ስጦታው ነው፡፡ የዐሥራት በኩራን ትርጉምና አገልግሎት ለይተን ካላወቅን በትክክል ልንረዳው አንችልም፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ቢሆንም የሰውም ልጅ አምላኩ ከሰጠው ውጭ ምንም የራሱ የሆነ ነገር የለውም፡፡ የሰው ልጅ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ይዞት የመጣው ነገር፣ ከዚህ ዓለም ተለይቶ ወደ ሌላው ዓለም ሲሻገርም ይዞት የሚሔደው ነገር የለውም፡፡ ሁሉንም ነገር የሚያገኘው እዚሁ ዓለም ነው፡፡ በግብርና እርሱ አንዲት ቅንጣት ዘር ሲዘራ በዝናብ አርጥቦ በቀደመ የሥነ ፍጥረት ትእዛዙ አንዷ ስንዴ በርክታ የምትወጣው በአምላክ ርዳታ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሚሠራው ሥራ ሁሉ የእግዚአብሔር መግቦትና በረከት ሳይኖርበት የሚያገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ አማኝ ያለሆነው በመግቦቱ የሚያምነው ደግሞ በመግቦቱም በበረከቱም ይሆራል፡፡

ስለዚህ ዐሥራት በኩራ ማለት ለሰጭው ሲተረጎም እግዚአብሔር ከሰጠው፣ ነገር ሁሉ አንድ ዐሥረኛውንና (ዐሥራት) የመጀመሪያውን (በኩራት) ለቤተ እግዚአብሔር ይስጥ፣ ይኽም ሁለት ዓላማ አለው አንደኛው ባለን ነገር እግዚአብሔርን ማክበር፣ ማመስገን፣ ማምለክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ካለን ወይም ካተረፍነው ነገር አንድ ዐሥረኛውን ቀንሰን በመስጠት ዘጠና በመቶውን ለማስባረክና ለምንፈልገው ነገር ለማዋል ነው፡፡ ስለዚህ የትርጉሙ ማጠቃለያ ዐሥራት በኩራትም ሆነ ወደ ቤተ እግዚአብሔር የምናቀርባቸው ስጦታዎች በሙሉ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ አምልኮቶች ወይም የአምልኮት መገለጫዎች ሲሆኑ ለአቅራቢው ደግሞ የአምልኮቱን ዋጋ ቡራኬ (በረከት) ጸጋ፣ ሐብት የሚያሰጡ ሥራዓቶች ናቸው፡፡

ሁለተኛው ጉዳይ ዓላማው ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በመስፍኑ በኢያሱ አማካኝነት ርስትን ለሕዝቡ ለእስራኤል ሲያከፋፍል በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉት ለሌዋውያን የመሬት ርስት አልሰጣቸውም፡፡ ለሌዌ ርስትህ እኔ ነኝ ነው ያለው፡፡ ይኽ ማለት ሌዋውያን አይቆፍሩም፣ አያርሱም፣ አይነግዱም፣ ውትድርና አይሔዱም፣ ሥራቸው በክህነት እግዚአብሔርን ማገልገል ነው፡፡ ሕዝቡ የሚከፍለው ለሌዋውያን የክህነት ዋጋ ነው፡፡ እዚህ ላይ በጥንቃቄ የምናየው ጉዳይ ካህናት የሕዝቡን የአምልኮት ሥራ በቤተ መቅደስ ይሠራሉ ንስሐውን ይቀበላሉ፣ ለበደሉ ይጸልያሉ፣ ሲታመም ይፈውሳሉ፣ ምግባሩን ይጠብቃሉ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተረጉማሉ፣ ሀገርን ከጠላት ንብረቱን ሁሉ ከመቅሰፍት በጸሎትና በመስዋዕት ይጠብቃሉ፣ ሌሎቹንም የቤተ መቅድስ አገልግሎቶች ሁሉ ይፈጽማሉ፡፡ ይኽን ሁሉ ሲያደርጎ ለመብል ለመጠጥ፣ ለሌላም የሚሆናቸውን የሚከፍለው ሌላው ዐሥራ አንዱ ነገድ ነው፡፡ ሕዝቡ ዐሥራቱን ካላወጣ ካህናት ሥራቸውን በአግባቡ አይሠሩም ምክንያቱም ለእለት ጉርስ ለዓመት ልብስ ለማለት ለልጆቻቸው ትምህረት እነርሱም ሰዋች ናቸውና የደካማ ሥጋ ግዳጅን ለመወጣት ደፋ ቀና ሲሉ የቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይዳከማል፡፡ ትምህርት ይጎድላል፣ አገልግሎት ይቀንሳል የእግዚአብሔር አልምኮት ይዳከማል በዚህ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር አላመለክነውም፣ አላከበርነውም፣ አላመሰገንነውምና በረከቱን ያነሳል፣ ምድር ለእኛ እንድትሆን የታዘዘችው ከርሱ ነውና አልታዘዝም ትላለች የእግዚአብሔርን ወስደናልና እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠንን ይወስዳል፡፡

እግዚአብሔርን ሰርቃችኋል!

ሰው እግዚአብሔርን እንዴት ይሰርቃል፡፡ እንዴት (ሚልክ 3፡8-10) ይኽ ጥያቄ ያለው በትንቢተ ሚልክያስ ነው፡፡ መልሱ አዎ ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃል፡፡ የሚሰርቀውም ዐሥራትና በኩራት ባለመክፈል ነው፡፡ ይላል ራሱ መጽሐፉ፡፡ የሰው ልጅ በራሱ ፈቃድ ወዶ የሚሰጠው ብጽዐት ወይም መባዕና በቃል ኪዳን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ በሚከፍለው ስዕለት ለምን አልተሳልክም ተብሎ አይጠየቅም ዐሥራት በኩራ ግን ሕግና ቀኖና ነው፡፡ ዐሥራት በኩታር የአምልኮት ሥርዓት ነው፡፡ የቤተ መቅደሱ አምልኮት የሚከናወንበት መሣሪያ ነው፡፡ ለምሳሌ በቀደመው የአነጋገር ሥርዓት አስቀዳሽ ማለት ለአንድ ቅዳሴ የሚያፈልገውን ዕጣን፣ ጧፍ፣ ዘይት፣ ስንዴና ወይን፣ የሚያሟላ ሰው ነው፡፡ ቀዳስያን ደግሞ ካህናት ሲሆኑ፣ ሌላው ተሳታፊ ነው፡፡ ዐሥራት በኩራት ካልወጣ ካህናት አራሽ ገበሬ፣ ነጋዴ፣ ዘበኛ፣ ተላላኪ ይሆናሉ ከዚያ የቤተ መቅደሱ አገልግሎት የትርፍ ጊዜ ሥራ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔርን ማገልገል የትርፍ ጊዜ ሥራ ሲሆን ያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሰረቅን ይባላል፡፡

ዐሥራት በኩራት የኦሪት ሥርዓት አይደለም፡፡ ዐሥራት በኩራት በሕገ ልቡና ነበር ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ የቤቴል የቃል ኪዳን ሐውልት አቁሞ ስዕለትን ሲሳል ከሰጠኽኝ ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን (ዐሥራት) እስጣለሁ ብሎ ነበር፡፡ ይኽ ሕግ ለሙሴ ከመሰጠቱ በፊት ነበር፡፡ ከዚያም በኦሪት ዘመን በዘኁል 18፡21-30፣ በዘሌ 27፡ 31፤ በዘዳግም 26፡ 13 ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ በዘመነ ነቢያትም አንዲሆ ሰፊ ትምህርት ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም አባቶቻችን በቀኖና ከሠሯቸው ሥርዓቶችና ደንቦች ዋናው በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 18 የተቀመጠው የዐሥራት በኩራት ጉዳይ ነው፡፡ ይኽ ትልቅ የምእመናን ግዴታ ነው፡፡ ምእመናን የእግዚአብሔር ቤት ሥርዓት ተዳከመ፣ ካህናት ቤተ ክርስቲያንን አላገለገሉም ብለው መክሰስና መተቸት የሚችሉት የእነርሱ ግዴታ ከሆኑት ውስጥ እንድ ዐሥራት በኩራት ያሉትን ሲያሟ ነው፡፡ ካህናትን የትርፍ ጊዜ ሠራተኞች አድርገው ቤተ ክርስቲያን ተዳከመች ማለት አይቻልም፡፡ ምእመናን የእግዚአብሔርን ዐሥራት በኩራት ሰርቀው ካህናትን ሰረቁ ማለት አይችሉም፡፡ ካህናት አገልግሎታቸውና ሥራዓታቸው እንደመላእክት አንዳንዴም ከመላእክት በላይ ቢሆንም አኗኗራቸው እንደ ሰው ነው፡፡ ልጆች አሏቸው ይበላሉ ይጠጣሉ፣ ይለብሳሉ ለዚህ ሁሉ ተገቢ የሆነ ከማንም ያላነሰ ገቢ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የካህናት አኗኗር ተጎሳቆለ ማለት የእግዚአብሔር አገልግሎት ተጎሳቆለ መለት ነው፡፡ እኛ ሥራውን ደሙን ለመቀበል ታጥበን ንጽሕ ልብስ ለብሰን፣ አምሮብን ስንመጣ ሥጋውን ደሙን የሚያቀብሉት ካህናት ከእኛ የበለጠ እንደሚያፈልጋቸው ማሰብ አለብን፡፡ ያ የሚሟላው በዐሥራት በኩራት ነው፡፡ ዐሥራት በኩራት ባለመስጠት የገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል፣ መመህራን ተሰደዋል፣ የቅርስና የንዋየ ቅድሳት ጠባቂዎች ብቻቸውን ቀርተው ለሌባ ተጋልጠዋል፡፡

እንግዲህ ሥለ ዐሥራት በኩራት ይን ያህል ካልን የዐሥራት በኩራት ሥርዓትን በተለመለከተ በአጭሩ ለመናገር ያህል ዐሥራት ሰው ሠርቶ ከሚያገኘው ወረቱን ሳይነካ ከዐሥሩ አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር ይሰጣል፡፡ ነጋዴ ከትርፉ ገበሬ ከምርቱ፣ አርቢ ከእርባው፣ ሠራተኛ ከደመወዙ፣ በኩራት የምርት የመጀመሪያ፣ የትርፍ መጀመሪያ፣ የርቢ መጀመሪያ፣ የደመወዝ መጀመሪያ ማለት ነው፡፡ በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፡፡ ሚልክ 3፡ 10 ብሎ እንደተናገረው እነዚህ እግዚአብሔር አገልጋዮች መብል ናቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር አብሮ የሚከናወነው ተግባር በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ሁሉ ሙሉ ከሆነ ነዳያን አይራቡም፣ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተሳካ ሁኔታ ይከናወናል፡፡ ፍትሐቱ፣ ክርስትናው፣ ቅዳሴው፣ ለደሐ ለሐብታም ሳይል ይከናወናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ቅጽር፣ ሕንጻው እና በውስጡ ያለው ቅርስ ሁሉ በሚገባ ይጠበቃል፡፡ ምስጢራት በሚገባ ይፈጸማሉ፣ ስብሐተ እግዚአብሔር በሰዓቱና በጊዜው ሳይጓል ይከናወናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ምእመናን በፈለጓቸው ጊዜ ሁሉ ያገኘዋቿል፡፡ ካህናት ሌሊት በአገልግሎት አድረው ቀን የመንግሥትና የሀብታም ቅጥር ለመጠበቅ መሣሪያ ይዘው ዘበኛ አይሆኑም፣ የቀን ሥራ ፍለጋ ከተማ ለከተማ አይንከራተቱም፣ የእግዚአብሔር ክብር አወዳሾች ጥምጣም ለብሰው፣ ጥላ ዘቅዝቀው ሥዕል ዘርግተው አይለምኑም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር ክብር አይጋለጥም፡፡

ዐሥራት በኩራትን በአግባቡ መክፈል የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመወስድ በንስሓ አባት ምስክርነት ለዚህ ተብለው ለተሾሙ አገልጋዮች በመስጠት ደረሰኝ በመቀበል መክፈል ይቻላል፡፡ ደረሰኝ መቀበል የቤተ ክርስቲያንን አገልጋዮች አለማመን ማለት አይደለም፡፡ ተገቢ የሆነ ሥርዓት ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያለው አሠራር እና ለውስጥ ቁጥጥር አስፈላጊ ስለሆነ መስጋት አያፈልግም፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ