Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

"ለወንበዴው ጣሊያን የተገዛ እንደ አርዮስ የተረገመ ይሁን
እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ"
ብፁዕ አቡነ ሚካኤል

 • ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ማናቸው ?

አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ በሚሰውበት ወቅት ኢሉባቦር ጎሬ ከተማ ላይ የተሰው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጳጳስ ናቸው ፡፡

 • ታዲያ ለምን ተሰው?

ለሀገር ጉዳይ ብለው

 • እርሳቸው ጳጳስ አይደሉም እንዴ ? ታዲያ ምን አገባቸው ?

ወይ አለመማር ! ፡፡ ታዲያ ጳጳሱ ፣ ሼኪው ፣ፓስተሩ ፣ ወዘተ በአገር ጉዳይ ካላገባው ማንን ነው የሚያገባው ?

 • እስቲ በቅጡ አጫውተኝ ሀገር ምን ሆና ነው አቡነ ሚካኤል የተሰውት ?

ጉዳይ እንዲህ ነው ?

ኢትዮጵያ ራሷን ችላ ጳጳስ መሾም በማትችልበት እና በግብጾች ሠንሠለት ተጠፍራ በነበረችበት ወቅት ከብዙ ክርክር በኋላ ይምጡና ይሾሙ ተብሎ ለአራት ሰዎች ጵጵስና ተፈቀደ ፡፡ ከአራቱ ሰዎች አንዱ የበፊቱ መምህር ሐዲስ የአሁኑ አቡነ ሚካኤል ናቸው፡፡ ታዲያ በቀጥታ ወደ ግብጽ ሄደው ጵጵስና ተቀብለው መጡ ፡፡ ከዚያ በኋላ እንደመጡ በቀጥታ ወደ ኢሉባቦር ሀገር ጎሬ የምትባል ከተማ ሆነው ሕዝብ እንዲመሩ ታዘው ጎሬ መኖር ጀመሩ ፡፡

ኢሉባቡር ደግሞ የት ነው ?

ወይ ጉድ ! ኢሉባቦርን አታውቅም ?
ኧረ አላውቀውም ! በጣም ሰፊ ደን ያለበት ያ እንኳ ነጭ ፣ ቢጫ፣ ጥቁር ማር የሚጫንበት ቦታ እሽ እሱን ተው ከኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የከሰል ድንጋይ የተገኘባት ሀገር ? ለመሄድ ከፈለክ ከአዲስ አበባ ተነስተህ ጅማ አድረህ ጠዋት ኢሉባቦር ትገባለህ የሚያምር ሀገር ነው ፡፡ ልዩ ነው ፡፡

እሺ ወዳጄ ከዚያ ?

ከዚያማ ጎሬ እያሉ በ1928 ዓ/ም ጣሊያን ሀገራችንን ወረረ ፡፡ በዚያ ሰዓት አቡነ ሚካኤል ከኢሉባቡር 3ዐዐዐዐ ሠራዊት መልምለው ባርከው ወደ ኦጋዴን ልከው እርሳቸው ከቀረው ሕዝብ ጋር የሠራዊቱን ቤተሰብ መጠበቅ ጀመሩ ፡፡ ታዲያ ጣሊያን አዲስ አበባ ገባ እዚያ ጓደኛቸውን አቡነ ጴጥሮስን አግኝቶ በል አሁን ሕዝቡ ለታላቋ ጣሊያን እንደገዛ አውጅ ሲል አቡነ ጰጥሮስ እንኳን ሕዝቡ ምድሪቷም አትገዛም በማለት ሲመልሱ በአደባባይ ረሸናቸው ፡፡ አቡነ ሚካኤል ይህን ሲሰሙ በጓደኛቸው ቆራጥ እምነት ደስ አላቸው ፡፡

ከዚያስ ?

ጣሊያን ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በኮሎኔል ማልታ እየተመራ በ1929 ዓ/ም ኢሉባቦር ጎሬ ከተማ ገባ ፡፡ ያኔ በመንግሥት በኩል ሀገርን ያስተዳድሩ የነበሩት እነ ቢትወደድ ወልደ ጻዲቅ እና ሌሎች ሹማምንቶች ሁሉ ቄየአቸውን ጥለው ሕዝቡን ለጠላት በትነው ወደ ከፋ ተሰደዱ፡፡ አቡነ ሚካኤል ግን በዘር ሳይከፋፍሉ በሃይማኖት ሳይለዩ ሕዝቡን በአንድ ሰብስበው ለአውሬ ጥዬ አልሄድም ብለው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ ፡፡

እና ተያዙ ?

ምን መያዝ ብቻ ? ጣሊያን ሕዝቡን ሰብስቦ አቡነ ሚካኤልን በመሐል አስቁሞ " አባታችን ሕዝቡ የእርስዎን ቃል ስለሚሰማ ለታላቋ የኢጣልያ መንግሥት እንዲገዙ ቃል ይግቡ ሕዝቡም እንዲገዛ ቃል አስገቡ አላቸው " እርሳቸውም እንኳን እኔ እና ሕዝቡ ልንገዛ ቀርቶ ምድሪቷም ለወንበዴ አትገዛም አሉና ድምጻቸውን ከፍ አድርገው " ለወንበዴው ጣሊያን የተገዛ እንደ አርዮስ የተረገመ ይሁን እንኳን ሕዝቡ ምድሪቷም እንዳትገዛላቸው አውግዥለሁ " ብለው አወጁ ፡፡ ያን ጊዜ ኮሎኔል ማልታ በጥይት ተደብዳበው እንዲገደሉ አዘዘ ፡፡ ታዛዦቹም በጥይት ደበደቧቸው ፡፡ ሲገደሉም ቀኛዝማች ይነሱ በስተቀኝ ፣ ግራዝማች ተ/ሐይማኖት በስተግራ አቡነ ሚካኤል በመሃል ሆነው ነበር ፡፡

እናስ የት ተቀበሩ ?

ወይ መቀበር ! አንድ የተከበሩ አቶ ወልደ አብ የተባሉ የጐሬ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ሰው በሌሊት ደብቀው ቀበራቸው ፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ሥርዓተ ቀብር ስላልተፈጸመላቸው ጠላት ኃፍረት ተከናንቦ ተዋርዶና ተሸንፎ ከሀገራችን ከወጣ በኋላ በ1936 ዓ/ም ዓጽማቸው ከተቀበረበት ቦታ ተለቅሞ በአሁኑ ሰዓት በጎሬ ደብረ ገነት ቅ/ማርያም ቤ/ክ ሙዚዬም ውስጥ በክብር ተቀምጧል ፡፡

ግን የጉሬ ሕዝብ ምን መታሰቢያ አደረገላቸው ?

በ1934 ዓ/ም ጎሬ ከተማ ውስጥ የተቋቋመ አንድ ት/ት ቤት ነበረ እርሱን ሕዝቡ በስማዠው ሰይሞላቸዋል ፡፡

ሌላስ ሐውልት አላቆመላቸውም ?

በፍጹም ! እስከ አሁን ምንም የለም ፡፡
የጎሬ ሕዝብ ታሪክ አላጠናም እንዴ ? ነው ወይስ ጎሬን ለመምራት መንበሩን እና ሥልጣኑን ከእነ አቡነ ሚካኤል እጅ የተቀበሉት ሰዎች አልገባቸውም፡፡

ለመሆኑ የተሰውት ለሀገር ነው አላልከኝም ?

አዎ ለሀገር ነው የተሰውት !ታዲያ የሀገር ፍቅር ያለው መሪ አሁን በኢሉባቦር እንዴት ጠፋ ? የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ያሠራው እኮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ፡፡ እስላሙም ክርስቲያኑም ፕሮቴስታንቱም በኢትዮጵያ ውስጥ በሠላም የሚኖር ሁሉ ተባብሮ ታሪክ እንዲይጠፋ አደረገ ፡፡ ታዲያ የኢሉባቦር ሰዎች ምን ሆነው ነው ? ነው ወይስ ጣሊያን እስካሁን ኢሉባቦርን አልለቀቀም ?

ታዲያ መጨረሻው ምን ሆነ ?

ወጨረሻውማ አስደሳች እየሆነ ነው ፡፡ በኢሉባቦር የሚኖሩ ሁሉ በአዲስ አበባ ካሉት የኢሉባቦር ተወላጆች ጋር ሆነው አሁን አንድ ታላቅ ጉባኤ አድርገው በጉዳዩ ሊወያዩ ዝግጅቱ ሁሉ ተጠናቅቋል ፡፡ የአቡነ ሚካኤል ሐውልትም እንደ ጓደኛቸው አቡነጴጥሮስ በትልቁ ተሠርቶ ወደ ጎሬ ሊወሰድ ተዘጋጅቷል ፡፡ ያኔ ታዲያ ጎሬ ከተማ ለጀግናው ሰማእት አቡነ ሚካኤል ሲል በሚመጣው የቱሪስት ፍስት መድመቅ ትጀምራለች ፡፡
እንዲህ ከሆነማ አቡነ ሚካኤል በሕይወት እያሉ ኢሉባቦርን ካገለገሉበት አገልግሎት ይልቅ ከተሰው በኋላ የሚያገለግሉበት አድማስ ሰፋ ማለት ነው ፡፡

ይቅርታ ወዳጄ ጨቀጨኩህ ጉባኤው መቼ ነው ?

የካቲት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ነው ፡፡ ሁሉም ክርስቲያን ተጋብዟል በተለይ ደግሞ በዚህ ታሪካዊ ሥፍራ የተወለዱ ሁሉ በዕለቱ ሲገናኙ ሰፊ ታሪኩን ይነግሩሀል እንዳትቀር እኔም አለሁ በሠላም ያገናኘን ፡፡

መ/ር ይቅርባይ እንዳለ /ዘቡሬ/
የቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን

የፎንት ልክ መቀየሪያ