Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ቅርስ ምንድን ነው

በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ማኀበራዊና መንፈሳዊ ዕድገቱ የተገነባው የኢትዮጵያዊነት ክብርና መለዮ በሆነው "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" በሚለው መሠረት ላይ ነው፡፡ (መዝ 67፡37)
ታሪክ መስታወት ነው፡፡ የረቀቀውን አጉልቶ የተረሳውን መዝግቦ ያሳያል እንደሚባለው የአንድ አገር ሕዝብ ታሪኩ፣ ጀግንነቱ፣ ታላቅነቱ፣ ባህሉና አኗኗሩ በሚገባ ሊታወቅ የሚችለው በሥነ-ጽሑፍና በሥዕል ወይም በቅርጻ ቅርፅ ተስሎና ተቀርጾ ለትውልድ የሚተላለፈው ሥዕላዊ መግለጫ እንደሆነ ማንም ሰው የሚረዳው ነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ቅደመ ልደተ ክርስቶስ በሕገ ኦሪት፣ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ በሕገ ወንጌል ያመነች ጥንታዊት ሀገር ከመሆኗም በላይ በዚያዉ ዘመን ርዝመት መጠንም በሥነ-ጽሑፍ የታወቀችና የሕዝቧ ሥልጣኔ፣ ጥንታዊነት፣ ጀግንነት፣ እምነቱና ባህሉ ሌላውም ሁሉ እንዴት እንደሆነ ሊታወቅ የቻለው መጀመሪያ በሐውልቶች፣ በጠፍጣፋ ድንጋዮችና በሸክላ ዕቃዎች ላይ በኋላም በብራና ተጽፈውና ተሥለዉ ለትውልደ ትውልድ እየተላለፉ በመጡት የቅርጻ ቅርጽ፣ የጽሑፍና የሥዕል ቅርሶች ነው፡፡

ከታሪክ እንደምንረዳው በሀገራችን ሥነ ጽሑፍ የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት አንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ለመሆኑ ብዙ መረጃዎች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌም ያህል በአክሱም ሐዉልቶች ላይ በሳባውያን፣ በግሪክና በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ ጽሑፎች የዓይን እማኞች (ምስክሮች) ናቸው፡፡ ሆኖም የሥነ ጽሑፍ መሠረት የሆነው ፊደልና የሥነ-ጽሑፉ ስልት በደንብ የታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት በኢትዮጵያ ከተጀመረበት ዘመን አንስቶ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ዓለም ገና በጨለማ ውስጥ በነበረበት የዕውቀት ብልጭታም ባልፈነጠቀበት ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከበግ፣ ከፍየልና ከልዩ ልዩ እንስሳት ቆዳ ብራና ፍቀው ልዩ ልዩ ቀለማ-ቀለማትን ቀምመው የሸምበቆ ብዕር ቀርጸው በጉሉሕ ወይም በረቂቅ ለመጻፍ በሚያስችል ሁኔታ እያዘጋጀ ከፊደል በኋላ ከዘመናዊው የአሠራር (የአጠራረዝ) ስልት በማያንስ ሁኔታ እየጠረዙና እየደጎሱ ለተጠቃሚው ሕዝብ በማቅረብ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ ያደረገችው አስተዋጽኦ እጀግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

በመልክዓ ምድር አቀማመጧ ውብና ድንቅ የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ የሰው ልጅ የኖረባት ለመሆኗ አያሌ ማስረጃዎች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የብዙ የተመራማሪዎች ጥናት የሚካሄድባት የውጪ አገር ጎብኚዎችንም ትኩረት የምትስብ ሆናለች ከ3.6 ሚልየን ዓመታት በለይ ያስቆጠረው የሰው ልጅ አፅም ተሟልቶ የተገኘባት ኢትዮጵያ በአስቸጋሪውና በቆላማው የአገራችን ክፍል አርኪዮሎጂስቶች ለረጅም ጊዜያት ተሰማርተው አመርቂ የምርምር ሥራዎችን ለዓለም በማቅረብ ላይ የሚገኙባት አገር ነች፡፡ ከዚህም አልፎ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ በተመራማሪዎች ዘንድ ብዙ ትኩረት ሲስብ የቆየው ጥንታዊ ሥልጣኔ ብዙ ጥናቶች የተደረጉበትና የምርምር ፅሁፎችም የቀረቡለት ነው፡፡ ካለው በርካታ የታሪክ ቅርስ አኳያ ሲታይ ግን ዕፁብና ድንቅ የሆኑትን የታሪክ አሻራዎች መቼ፣ እንዴትና ለምን እንደተሠሩ ለመግለጽ የሚያስችሉ ማጠቃለያዎች ተሟልተው ገና አልቀረቡም፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ መልሶችን ለመስጠት ከመሞከር ይቅል ታሪካችንንን በሚመለከቱ ጥያቄዎችን በማንሳት መገረምና ማሰላሰል የበለጠ ቀላል ነው፡፡

የአያሌ ጥንታዊና አስገራሚ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት የሆነችው አገራችን በየዘመኑ ታሪኳ ከውጭና ከውስጥ ይነሱ በነበሩት ጦርነቶች ምክንያት የጀመረችውን የሥልጣኔና የእድገት ፈለግ ከመቋረጡም በላይ የነበረውም ቢሆን ተበታትኖና ተበላሽቶ በአብዛኛው ለጥፋት ተዳርጓል፡፡ ለጥቂት ጊዜ ብቻ ሲያባሩ የነበሩት አለመረጋጋቶች ያካበትናቸውን አያሌ የድንጋይና የብራና ፅሁፎች ተሰብስበው የታሪክ ሰነድ አሟልተን በመያዝ ታሪካችንን በሚገባ ለመግለጽ ሳያስችሉን ቆይተዋል፡፡ የዚህ አኩሪ ቅርስ ባለቤት የሆነው ሕዝብም ታሪኩን በፅሁፍ ሳይሆን በቃል ብቻ በመግለፅ ከሚገደድበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

እስካሁን ምርምርና ጥናት የተካሄደበት የአገራችን ታሪክ በአብዛኛው በውጭ ምሁራን የተካሄደ በመሆኑ በራሳችን ቋንቋ በሚገባ ተተርጉሞና ተዘጋጅቶ ሕዝቡ በስፋት እንዲያውቀው ለማድረግ አልተቻለም በዚህም ምክንያት ለማንበብ ወይም ተዘዋዉሮ አገሩን ለማወቅ አቅም ያለው ኢትዮጵያዊ ሳይቀር ታሪኩንና አኩሪ ያባቶቹን ቅርስ በጥልቀት ለማወቅ አላስቻለውም፡፡

ስለ ጥንታዊ ታሪካችን ጉዳይ ሲነሳ የኢትዮጵያ ጥንታዊትና ታሪካዊት አገር ለመሆንዋ በብዙዎች ዓለም አቀፍና በታሪክ ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን በቤተክርስቲያን ታሪክ ያለው እውቀት ግን አነስተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ አክሱምን ከአንድ ሐውልትና አንድ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ሌላ ምንም የሌላት የሚመስላቸው ሰዎች ብዙዎች ናቸው፡፡ ላሊበላን ከውቅር ቤተ ክርስቲያን በቀር ሌለ ምንም የሌላት አስመስለው የሚናገሩም አሉ፡፡

በኢትዮጵያ ድንቅ የተባሉ እነዚህ አብያተ መንግሥት፣ ሐውልቶች፣ መቃብሮች፣ ጥርብ የደንጋይ ቅርጾች ሌሎች ከምድር በላይና በታች የሚገኙ የታሪክ ስፍራዎች ናቸው፡፡

በአገራችን ውስጥ ያሉትንና ወደ ሌሎች አገሮች የተሻገሩትን ቅርሶች በተመለከተ በርካታ ፅሑፎች የወጡና በመወጣት ላይ ያሉ ቢሆንም ከጊዜው ርቀትና በመረጃዎች መውደም፣ መጥፋት ወይም ተቆፍረው ያለመወጣት የተነሳ በምርምር በተገለፁትና በአፈ - ታሪክ በሚነገሩት ታሪኮች መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ በቁፋሮዎች የሚገኙ ማስረጃዎች በምርምር ጥናት ለሚደረጉ ትንተናዎች መሠረት ሲሆን በአፈ-ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የቆዩት ታሪኮች ደግሞ ለዘመናት ምርምር አጋዥነት ቢኖራቸውም የማስታወስ ችሎታንና የተናጋሪዎቹን ስሜት ተከትለዉ የሚሄዱ ናቸው፡፡ በአገራችን ውስጥ ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በቀደምት ሊቃውንት የተፃፉ የብራና መፃሕፍትም ለዘመናዊው ታሪክ ምርምር ሥራ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ቀላል ባይሆንም ዓላማቸውና አፃፃፋቸው ሃይማኖታዊ እሴትን ለማዳበርና በፀሐፊዎቹ የማስታወስ ችሎታ ላይ ተመርኩዘው የተፃፉ ናቸው፡፡ ስለዚህ የብራና መፃሕፍቱ በሃይማኖቱ መሪዎችና ተከታዮች ከፍተኛ ከበሬታ አላቸው፡፡

በዘመናዊ የታሪክ ምርምር የተሰማሩት የውጭና የሀገር ዉስጥ ምሁራን የኢትየጵያ ታሪክ የሚያወጧቸው ፅሑፎች ማስረጃዎችና ቀደም ሲል የውጭ አገር ተመራማሪዎች ያሳተሟቸውን መፃሕፍት ዋቢ አድርገው በመጥቀስ ነው፡፡

በአንዳንድ የተለያየ ሁኔታዎችም ጥንታውያኑ የሃገር ውስጥ የብራና መጻሕፍት እንደማነጻጸርያና እንደማሟያ አድርገው ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ስለዚህ ዘመናዊው የታሪክ ምርምር ውጤት ለባለታሪኩ በሚገባ መንገድ ሊቀርብ ባልቻለበት ሁኔታ ውስጥ እየተረሳ ያለውን አፈ-ታሪክ እንደየሁኔታው እየጎደለበትና እየተጨመረበት ለመጠቀም የግድ ይሆናል፡ ይህም የታሪክ ትምህርት በህብረተሰቡ ዘንድ ሊኖረው የሚችል ጥቅም እንዳይጎላ ከማድረጉም በላይ ህዝቡ ታሪካዊ ቅርሶቹን ለመንከባከብና ለመጠበቅ ብቃት እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡ ከዚህም በላይ አገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክና ነጻነት ያላት ጥንታዊት ሃገር መሆኗን አበክሮ ለማወቅ የሚጣጣረው ዜጋዋ ራሱ አይቶና አንብቦ ለመረዳት የሚኖረው ዕድል ጠባብ እንዲሆን ያደርጋል፡

ይህ እንዳለ ሆኖ በቅርብ ጊዜ እየተደረጉ ያሉት ጥናቶችና ምርምሮች የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ጎልቶ እንዲወጣ እያበረከቱት ያሉት አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡ ከአንድ መቶ ዓመታት በፊት የተጀመረው ዘመናዊ የአርኪዮሎጂ ቁፋሮ እስካሁን የተራመደበት የዕድገት ሂደት በጣም አዝጋሚ መሆኑ ባይካድም በቅርብ ዓመታት የተካሄዱት ተከታታይ ጥናቶች ግን አበረታች ናቸው፡

ሌላው ቀርቶ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ምን እንዳለና በቤተ ክርስቲያን ዙርያ ያሉት የታሪክ ቅርሶችን በሚመለከት ያለው እውቀት ለአካባቢው ነዋሪዎቹ ሳይቀር እውቀቱ አነስተኛ ነው፡፡

ለዚህ እውቀትና ግንዛቤ አለመዳበር በርካታ ምክንያቶች ሊቀርቡ የሚችሉ ቢሆንም ዋና የሚባሉት ግን በጽሑፎችና በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ታሪካችንንና ቅርሳችንን ለማስተዋወቅ የተደረገው ጥረት ኢምንት መሆኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስና ታሪክ፣ በውስጧ የያዘቻቸውን ቅርሶችና ሌሎች መስህቦች ኢትዮጵያ በሰው ልጅ ታሪካዊ ዕድገት ሂደት ውስጥ በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ህብረተሰባዊ አደረጃጀት በስነ ጽሑፍ በስዕል የሃይማኖታዊ ትሩፋቶችና ሌሎች የስልጣኔ አሻራዎች ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚገባውን ያህል እንዲታወቅ አልተደረገም፡፡

በአሁን ኢትዮጵያዊ ማንነታችን እርሾ መብቀያ፣ በጥቁር አፍሪካ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን መሠረታችን ናት፡፡

ቱሪዝም ምንድ ነው


ቱሪዝም ለአንድ ሀገር ግንባታ ከሚሰጠው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አንጻር ጢስ አልባው ኢንዱስትሪ በመባል ይታወቃል፡፡ ይኸውም በዘመናችን በነዳጅ ዘይት ገቢ ባልተናነሰ ሁኔታ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ያለው የጎላ አስተዋጽኦ በመሆኑ ነው፡

ሀገራችን ባላት የተፈጥሮ ጸጋ በሌላው አለም የማይገኙ የዱር እንስሳት እና ዕፀዋት፣ ማራኪ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ ፏፏቴዎች፣ ፍልውሃ፣ ሰው ሰራሽ የተለያዩ ቅርሶች እና ታሪኮች እንዲሁም የብሔረሰቦች ባህል ለበርካታ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ጎብኝዎች የዐይን ማረፊያ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቱሪስት መስቦቹ በተለያዩ አካላት ኃላፊነት ሥር ይተዳደራሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ ከፊሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅርሶች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ማዕከል ብቻ ሳትሆን የምጣኔ ሀብታዊ ማህበራዊ ሥነ ጥበባዊ የሥርዓተ መንግስት የውጭ ግንኙነት ባጠቃላይ የታሪክ የሥልጣኔ እና የነገሥታት ገድሎች ዜና መዋዕሎች መረጃ ማዕከል ናት፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ቤተ ክርስቲያኗ ከዚህ የኢንዱስትሪ መስክ ካሏት ሀብት ተጠቃሚ አልሆነችም፡፡ ይልቁንም በአንድ ወቅት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን ከጠቅላላ ገቢው 85 በመቶው የሚሆነው ምንጩ እነኝሁ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶችና መስህቦች ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር የቤተ ክርስቲያኗ የቱሪስት መስህቦች ከቤተ ክርስቲያን አካላት ውጭ በሆነ እና ታሪክን ባልተረዱ ግለሰቦችና ድርጅቶች ለጎብኝዎች መገለጻቸው የታሪኳንና የማንነቷን መረጃ እየተዛባ መጥቷል፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ውስጥ ወደ 60 የሚጠጉ የግል የጉዞና አስጎብኝ ድርጅቶች ተመዝግበው በመሥራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ጥቂቶች ብቻ በሙሉ አቅማቸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡

በቅርስ ባለቤትና የቅርስ ጠባቂዎች ምንም አይነት ጥቅም ሳያገኙ ጥሬ ቆርጥመው ውሃ ተጎንጭተው ድንጋይ ተንተርሰው ለትውልድ ያስረከቡትን ቅርስና ታሪክ ተጠቃሚው ሌላ አካል መሆኑ ያሳዝናል፡፡

ከዚህ አንጻር ነው ቅርሶች በጠባቂያቸው የሚሸጡና የሚዘረፉ ለምን ጥቅም ፍለጋ እነዚህ የቅርስ ጠባቂ በቂ ደሞዝ ካላገኙ እንደአባቶች ፈተናውን በመወጣት የሚጠብቁ አይሆኑም ዘመኑ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ መፍትሔ መፈለግ የቤተ ክርስቲያኗ ይሆናል፡

ቤተ ክርስቲያኗ ከሃብቷ ተጠቃሚ እንድትሆንና ትከክለኛውን መረጃ ለተጠቃሚው በመስጠት የጎላ ሚና መጫወት ይኖርባታል፡፡

ታኅሣሥ 1999 ዓ.ም "በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ" ከሚል ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች ከተዘጋጀ ጽሑፍ የተወሰደ

የፎንት ልክ መቀየሪያ