Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

“የበገና ታሪክና መንፈሳዊ አገልግሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን”

                   በመምህር ሙሴ ኃይሉ

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዋና የፕሮቶኮል ኃላፊ

“በገና”፡- እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደ መሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡

እነርሱም፡-

1.     ሰዋስዋዊ ትርጉምና

2.    ሥነ ቃላዊ ትርጉም………….. ይባላሉ፡፡

1. የበገና ሰዋስዋዊ ትርጉም

v“በገና” የሚለው ስምና “በገነ” የሚለው ግሥ በተለያዩ መዝገበ ቃላትና የቋንቋ ሊቃውንት ተተርጉሞ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡-

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ”በሚል መጽሐፋቸው በሁለት መልኩ ማለት “ሲጠቅብና ሲላላ” ብለው በማመሳጠር እንዲህ ብለው ተርጉመውታል፡፡

 በገና፡-  በዕብራይስጥ ናጌን ይባላል ካሉ በኋላ ሲተረጉሙት

              ፡- ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ ማለት ነው፡፡

ሲጠብቅ ግን ፡- ነደደ፣ ተቆጣ… ያሰኛል ብሏል፡፡

በገና፡- በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ፡ መጽሐፈ ስዋስው ወግስ                                                                                                                            ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)

  ·        አባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የትግርኛ መዝገበ ቃላት በተባለ መጽሐፋቸው፡-

 - በገናን በቁሙ በገና ብለው ተርጉመውታል፡፡ (አባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፣ ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት፣ 1948፣ አሥመራ)  

 ·        ከሳቴ ብርሃን ተሰማ “የአማርኛ መዝገበ ቃላት” በተሰኘ መጽሐፋቸው እንዲህ ዓይነት ትርጉም ሰጥተውታል፡፡

  - በገና፡- በአሥር አዉታር ጅማት በገናን ሠራ፣ ቃኘ፣ ደረደረ፣ ድምጽን እያጣራ፣ እያጣቀሰ፣ እየነዘረ…                  በገናን በገነ… ካሉ በኋላ

- በገነኛ፡- የሚለው ደግሞ በገናን የሚመታ፣ በገናን የሚያውቅ ደርዳሪ… ማለት ነው ብለው    ተርጉመውታል፡፡ (ከሳቴ ብርሃን ተሰማ፣ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ 1951 ዓ.ም፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ አዲስ አበባ)

2. የበገና ሥነ ቃላዊ ትርጉም፡-  

·        በገነ፡- አደረቀ፣ አቃጠለ፣ አነደደ… ማለት ነው፡፡ በገናም ከዚህ የሚወጣ ስም ነው፡፡  የዚህ ትርጉም ማግኘት ዋና ምክንያትም ሁሉም ነገር (የበገና ሁለገብ ሰውነት) በደረቅ ነገሮች ማለትም በደረቅ እንጨትና በደረቅ ቆዳ እንዲሁም     በደረቅ ጅማት የሚሠራ ወይም የሚዘጋጅ ስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጐማል፡፡

·        በገና፡- “በ” እና “ገና” በመነጣጠል የሚያስገኘው ትርጉም በመጠቀም…  በ … ገና…. በገና በዓል ወይ በገና ወቅት የሚደረደር የምስጋና መሣርያ ስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጎማል፡፡

·        በገና፡- በገነ ማለት ደረደረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር… ማለት ነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በማድረግ ይተረጎማል፡፡ ለምሳሌ፡-

o   “አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግናለሁ” መዝ.42/43፡4

o   “ለእግዚኣብሔር በገና ደርድሩለት” መዝ.48፡5

o   “እግዚኣብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት” መዝ.32/33፡2

የዚህ አጭር ጥናታዊ ጽሑፍ ኣቅራቢ ግን ከሁለቱም ወገን በሚወሰዱ የትርጉም መመሳሰል በመነሳት በምስጢር ከበገና መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ጋር የተሻለ ቀረቤታ ያለውን ትርጉም ቢሆን ይመርጣል፡፡

በመሆኑም፡-

በገነ፡- ደረደረ፣ መታ፣ አነዘረ…. ወዘተ ማለት ነው በሚለው መልካም ትርጉም       ይስማማል፡፡   ምክንያቱም ከነባራዊ የበገና ማኅበራዊም ሆነ መንፈሳዊ እሴት ማለትም ከድርጊቱ ወይም     ከአቀራረቡ (ከአገልግሎቱ) ጋር አብሮ ይሄዳልና         ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት፡-

በገና፡-ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር… ወዘተ ማለት ነው፡፡ በገነኛው ቅዱስ ዳዊት      በመዝሙሩ     በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ ምስጋና… በማለት ሲገልጽ እናገኘዋለንና፡፡

$1·       የበገና ታሪካዊ አጀማመር፡-

በገና፡- በትክክል መቼና እንዴት ተጀመረ የሚለው ጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆንም ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ዓለምም ቢሆን በስፋት በግልጽ በአደባባይ እያወደሰው እንዳለ የሁሉም ጥበባት ማለትም ሥጋዊ ጥበብንም ጨምሮ መገኛቸው ወይም ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በመሆኑም nበመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገልጾ የምናገኘው የምስጋና ወይም የዜማ መሣሪያ በገና ብቻ ነው፡፡

·        እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነታ የመረመርነው እንደ ሆነ፡-

በገና ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅ የዩባል /ኢዮቤል/ ልጆች ነበሩ (ዘፍ.4፡19-24)፡፡ ይኸውም ዓይነ ስውር (ማየት የተሳነው) የነበረ ላሜህ አያታቸው በበረሃ እየሄደ እያለ ቃኤል ተቅበዝባዥ ነበርና ለብቻው በዱር ተሰውሮ ሲንኮሻኮሽ ሰምቶ መንገድ ይመራው ለነበረው ረድእ (መንገድ መሪ) “እጄ ይሞቅብኛል፣ ቅጠሎች ሲንኮሻኮሹም እሰማለሁ አራዊት መጥቶብናል መሰለኝና ድንጋይ አቀብለኝ” ካለው በኋላ  ድንጋዩን ተቀብሎ በተሰማው አቅጣጫ ቢወረውር ግንባሩን መትቶ ገደለው፡፡ ቀርበው ሲመለከቱት ቃየን ሆኖ ሲያገኘው እጅግ መሪር የሆነ ለቅሶ አለቀሰ፡፡

ላሜሕ ወደ ቤቱ ተመልሶም ዓዳና ሴላ ለሚባሉት ሚስቶቹ “ስምዓኒ ዓዳ ወሴላ አንስትያየ አነ ቀተልክዎ ለቃየን አቡየ፡- ዓዳና ሴላ ሚስቶቼ ሆይ ስሙኝ፤ እኔ ዛሬ አባቴ ቃየንን ገድየዋለሁና…” በማለት ነገራቸው፡፡ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ታሪካዊ ተዋረዱን ጠብቀው የታሪክ እውነታውን ለልጆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም የላሜህ የልጅ ልጆች (የዩባል ልጆች) በቃየን ሞት ብቻ ሳይሆን በወላጆቻቸው የአሟሟት ሁኔታ እጅግ አዘኑ፡፡

ይኸውም አቤል በቅንዓት ምክንያት በገዛ ወንድሙ በቃኤል መገደሉ፤ ቃየንም “ተባርዮን የማያስቀር አምላክ ነውና” በገደለው ዓይነት የአገዳደል ዘይቤ (“ሰይፍ ሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና” ማቴ.26፡52፤ እንዲል) በድንጋይ በአምስተኛ ልጁ በላሜሕ መሞቱ… እያወጡ እያወረዱ እጅግ ከማዘናቸው የተነሳ በገና ለመጀመርያ ጊዜ ከደረቁ ቁሳቁሶች አበጅተው በመሥራት በበገና እያንጎራጎሩ ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

በዚህም በገና ከፍጥረተ ዓለም ብዙም ባልራቀ ሁኔታ (ከአዳም ዘጠነኛ የትውልድ ሐረግ በሆኑ አበው) የተገኘ የመጀመርያ የሐዘን፣ የእንጉርጉሮ፣ የንስሐ፣ የልመናና የምስጋና መሣሪያ ነው እንላለን፡፡ ተዋረዱም፤

·           አዳም፡- ቃኤልን ይወልዳል

·           ቃኤል፡- ሄኖሕ ይወልዳል

·           ሄኖሕ፡- ጋይዳድ ይወልዳል

·           ጋይዳድ፡- ሜኤል ይወልዳል

·           ሜኤል፡- ሙቱሣኤል ይወልዳል

·           ማቱሣኤል፡- ላሜሕ

·           ላሜሕ፡- በገና የሚደረድሩትን አባት ይወልዳል (ስማቸው  በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አልተገለጸም)፡፡

በመሆኑም ከአዳም ዘጠነኛ ትውልድ የሆኑ የላሜሕ የልጅ ልጆች በሆኑት በእነዚህ አበው ምክንያት በገናን ተዘጋጅቶ መደርደር ተጀመረ፡፡

·        ቃለ በገና፡- ቃለ ማኅዘኒ

                   ፡- ድምፀ ማኅዘኒ … ነው፡፡

ምክንያቱም በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አራቅቀው እንደሚተረጉሙት ይህ ምድራዊ ማኅዘኒ ዜማ የመጣው በዮባል ልጆች ኃዘንና እንጉርጉሮ ምክንያት እንደሆነ ይኸው ከላይ የተጠቀሰው ታሪክ ጠቅሰው ያትታሉ፣ ያመሰጥራሉ፡፡

ይኸውም ከላይ እንደተገለጸው፡-

o  ቃየል ወንድሙ አቤልን መግደሉ፤

o   ቃየል ደግሞ በልጁ በላሜህ መገደሉን፤ እያስታወሱ የዩባል ልጆች የደረቀ እንጨት ጠርበውና  አለዝበው፣ ቆዳ ወጥረው፣ ፍቀው፣ አድርቀውና ዳምጠው፣ ጅማት አክርረውና አበግነው… በቃለ ማኅዘኒ፣ በድምፀ ማኅዘኒ… ያንጐራጉሩ ነበር በማለት ሊቃውንቶቻችን ያትታሉ፡፡

በዚህ ታሪካዊ እውነታ ምክንያት ነው “በገና” ቃለ ማኅዘኒ፣ ድምጸ ማኅዘኒ ሆኖ የሐዘን ማለትም የንስሐ፣ የልመናና የምስጋና ማቅረቢያ የዜማ መሣሪያ በመሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው፡፡

§  የበገና የአጀማመሩ ታሪክ በዩባል ልጆች ቢሆንም ዘመናት አልፎ ከትውልድ ትውልድ ሲተካ ይዘቱም ሆነ ዓይነቱ እየተሸሻለ መጥቶ የበገና አጠቃላይ ማኅበራዊ ሚናውም ሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ይበልጥ ጎልቶ የታወቀው ግን በመዝሙረኛው (በበገነኛው) በቅዱስ ዳዊት ምክንያት ነው፡፡

·        የበገና አገልግሎት

በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊ ትሩፋት ማለትም ለምስጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ተመርጦ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ብቻ ይውላል፡፡

ለምሳሌ፡-

o   “አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ” መዝ.42/43/4

o   “አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት” መዝ.32/33/2

o   “ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት” መዝ.4.8/5/… ወዘተ ከተመዘገቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እንደአስፈላጊነቱ ለማኅበራዊ እሴት፣ ለሃገር ክብር፣ ለሉዓላዊነት… በገና ይደረደራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማስረጃችን በአፄ ቴዎድሮስ ጊዜ የተደረደረውና እስከ አሁን ድረስ የበገና መማርያ የሆነው የበገና አገልግሎት ነው፡፡     

ከዚህ ውጭ በገና ለዓለማዊ ፍላጐት ማስፈጸሚያ ማለትም፡-

üለዳንስና ለዳንኪራ

üለዘፈንና ለጭፈራ

üለዝናና ለጉራ

üለቀልድና ለፉከራ … ወዘተ ፈጽሞ አገልግሎት አይሰጥም፡፡

·       የበገና ጥቅም፡-

ከላይ እንደተገለጸው በገና በዋናነት ለመለኮታዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማስፈጸሚያ ማለትም ለምስጋናና ለልመና የሚያገለግል ሲሆን በተጨማሪም ለማኅበራዊ እሴት መግለጫ የሚውል መንፈሳዊና ጥንታዊ የዜማ መሣሪያ ነው፡፡

ለምሳሌ፡-

·       እግዚአብሔርን ለማመስገን እና እግዚአብሔርን ለመለመን

ስለ በገና በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉ በአብዛኞቹ የሚገልጹት “በገና ለምስጋናና ለልመና ሲቀርብ” ብቻ ነው፡፡

$1·       ትንቢት ለመናገር

ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ መመልከት ወይም ማንበብ በቂ ነው፡፡

ü“ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል” 1ኛ መ. መሳ. 10፡5 እንዲል፡፡

$1·       ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን

$1ü“እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር” (1ኛሳሙ.16፡23) እንዲል፡፡

$1·       የሀገር ሉዓላዊነት ለመግለጽ … ወዘተ ይጠቅማል፡፡

ü“ፈረሱ አባ ታጠቅ ስሙ ቴዎድሮስ….. እኔ መዩ ቱርክን ባይ የምሸሽ ነኝ ወይ….” እንደ ምሳሌ ልንወስደው እንችላለን፡፡

  

$1·       በገና ወደ ሀገራችን እንዴት መጣ?

የበገና ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የአመጣጥ ታሪክ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡

1.     የሀገራችን ኢትዮጵያ የሥልጣኔዋ ውጤትና በሕገ ልቡና የማመንዋ ውጤት ነው፡፡                     /የተጀመረ እዚሁ ሀገራችን ነው የሚል ታሪካዊ አንድምታ ነው፡፡/

2.    በቀዳማዊ ምኒሊክ ጊዜ ከታቦተ ጽዮን ጋራ አብረው ከመጡት የዜማና የሥርዓተ አምልኮ ንዋያተ ቅድሳት፣ መጻሕፍት… ወዘተ እንደ አንድ ሆኖ የመጣ ነው የሚሉ ሲሆን ይህንኑ አመለካከትም ይበልጥ በሀገራችን ጠበብት ሊቃውንት በስፋት ይተረጎማል፣ ይተረካል… ይታመናልም፡፡

$1·       የበገና አሠራር፡-

o   በገና የሚሠራው፡- ከደረቀ እንጨት /ተጠርቦና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ ተውቦ/

o   ከደረቀ ቆዳ፡- /ተፍቆና ተዳምጦ እንዲሁም ዙሪያውን ተሰፍቶ/

o   ከደረቀ ጅማት፡- /በግኖና ከርሮ ከላይ እስከ ታች ተወጥሮ፣ በቁጥር ተቀምሮ                               ይሠራል፡፡/

$1·       የበገና አቀራረብ ዘዴዎች፡-

o   በገና በሁለት መልኩ ሊቀርብ ወይ ሊደረደር ይችላል፡፡

1.    በእጅና፡-

2.    በድሕንጻ፡- (ድሕንጻ፡-  መግረፊያ ሆኖ እጅግ መሳጭና የበለጠ በሚመስጥ መልኩ         በገናውን የሚያስጮኽ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ወይም የበገና ማጫወቻ ነው)

“በድሕንጻ መንፈስ ዝብጢ አውታረ መሰንቆሁ ለልብየ ወአስተንፍሲ ውስተ አፉየ ከመ       እኩን እንዚራሁ ለበኩርኪ……) እንዲል  (መጽሐፈ ሰዓታት፡ እሴብሕ ጸጋኪ ይመልከቱ)

$1·       ከበገና ምሳሌያዊ ትምህርቶች፡-

o   ላይኛው፡- የፈቃደ እግዚአብሔር

o   ታችኛው፡- የማኅፀነ ድንግል

o   ግራና ቀኙ፡- የሚካኤልና የገብርኤል

o   አሥሩ አውታር፡- የዓሠርቱ ቃላት

o   አውታሩ በእጅ ሲመታ ሁለቱም ማለትም አውታሩንና እጁን ተዋሕደው ድምፁ የሚሰማው ከታችኛው (ከቆዳው) ዘንድ እንደ ሆነ ሁሉ መለኮትና ሥጋ ተዋሕደው ከማኅፀነ ድንግል ዘንድ ለማደራቸው ምሳሌ ነው፡፡

 

አንድም፡-

o   ላይኛውና ታችኛው፡- የሰማይና የምድር

o   ግራና ቀኙ፡- የብሉይና የሐዲስ

o   አሥሩ አውታር፡- የዓሠርቱ ትእዛዛት

o   በብሉይ ኪዳን ፈጣሪና ፍጡርን የሚያገናኙ ዓሠርቱ ትእዛዛት ስለነበሩ በዚሁ ተመስሏል፡፡

$1·        የበገና ቅኝቶ፡-

በገና ሦስት ዓይነት ቅኝት አለው፡፡ እነርሱም፡-

$11.     በበገና ቅኝት ሰላምታ በተለምዶ አምባሰል እንደሚባለው ነው፤

$12.    በበገና ቅኝት እርግብና ዋኔን በተለምዶ ትዝታ እንደሚባለው ነው፤

$13.    በበገና ቅኝት ስለቸርነትህ (መጾሙን ይጾማል) በተለምዶ አንቺ ሆዬ ለኔ እንደሚባለው ነው፤

በተለምዶ ያልኩበት ምክንያት በሌሎች የዜማ መሣርያ (በዘፈን መሣርያዎች) የሚሰጣቸው ስም ሲሆን በገና ደግሞ የራሱ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያበረክትበት የራሱ መዝሙርና የቅኝት ስልት ያለው እድሜ ጠገብ ቅርስ በመሆኑ “በተለምዶና በበገና” ተብለው ቀርበዋል፡፡ ከሁለቱም በአንዱ ግልጽ እንዲሆን ታስቦ ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻ ስለ በገና ለወደፊት ሰፊ ነገር የምለው ነገር ቢኖረኝም ግን ለጊዜው ለማጠቃለል ያህል፡-

$1·       በበገና፡-

o    እግዚአብሔር፡- ይመሰገንበታል፣ ይቀደስበታል፣ ይለመንበታል… ፡፡

o    ቅዱሳን፡- ይከበሩበታል፣ ይታሰቡበታል… ፡፡

o    ሕሙማን፡- ይፍወሱበታል…፡፡

o    ሕዙናን፡- ይጽናኑበታል….፡፡

o    አማኞች፡- ይመከሩበታል…፡፡

o    የሀገረ ክብር፡- ይገለጽበታል፣ ይነገርበታል… እያልኩ ለወደፊት በገና እንዴት እንደሚደረደር ለማሳየትና የድምጹን ሁኔታ ለማስተማር በድምጽ፣ እንዲሁም በድምጽ ወምስል ለማዘጋጀት ሐሳብ አለ፤ ሁሉን የሚፈጽም ግን እግዚአብሔር ስለሆነ የዚህ ታሪካዊና ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጣዕም ለሥርዓተ አምልኮ፣ ለልመናና ለምስጋና ተጠቅመንበት ሕይወታችን በንስሐ መርተን ፍጻሜአችን ያማረ የተስተካከለ እንዲሆንልን አምላከ ዳዊት እግዚአብሔር ይርዳን፤ የወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ጣዕም በአንደበታችን ፍቅርዋንም በልቡናችን ይሣልልን፡፡ አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር

                                               ወርሐ ነሐሴ 2004ዓ.ም

                                          አዲስ አበባ

የፎንት ልክ መቀየሪያ