Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ከብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

abun klimatosብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የከምባታና ሐዲያ ስልጤ ጉራጌ አኅጉረ ስብከትና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙ አባት ናቸው፡፡ ሁሉንም አኅጉረ ስብከታቸው ለማጠናከርና የተሰጣቸውን ሐዋርያዊ ተልዕኮ ለመወጣት እስከ ገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በእግርም ጭምር እየተንቀሳቀሱ የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎት እንዲቃና እያደረጉ የሚገኙ አባት ናቸው፡፡ አኅጉረ ስብከቶቹ የተራራቁ ከመሆናቸው የተነሳ አንድም ቀን ዕረፍት ሳያደርጉ ሐዋርያዊ ጉዞ የሚያደርጉበት ጊዜ እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡
ይህንን ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ደግሞ የሕጻናትና ወጣቶች ሁለንተናዊ ዕድገትና አገልግሎት የሰመረ እንዲሆን ለማድረግ በመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በሚገኝ ጽ/ቤታቸው እየተገኙ በአገልግሎት የሚተጉ አባት ናቸው፡፡
ብፁዕ አባታችን ከሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አንዱ ክፍል የሆነው የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ማብራርያ እንዲሰጡን የዝግጅት ክፍላችን ሲጠይቃቸው ፈቃደኛ በመሆናቸው በሁሉ አንባቢዎቻችን ስም ከፍተኛ የሆነ ምስጋና እያቀረብን ብፁዕ አባታችን የሰጡት ማብራርያ እነሆ እንላለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

የወጣቱና የኖላዊ ግንኙነት

በብፁዕ አቡነ ዳንኤልለሰ/ትቤቶች የሥራ ሃላፊዎች 1999 ዓ.ም የወጣትና የኖላዊ ግንኙነት ከሚል የሥልጠና ጽሑፍ የተወሰደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምን ይመስላል የሚል ሲሆን፡-

ይህንን ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል& ምሳሌውም የአብርሃም እና የካህኑ የመልከ ጼዴቅ የመጀመሪያው ግንኙነትን የሚመስልና የነዚህን ፈለግ መከተል ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲታወቅ በዘፍ. 14፡18 ያለውን ቃል መጥቀስ እንችላለን፡፡ መልከ ጼዴቅም አብርሃምን ሲገናኘው እንጀራን እና የወይን ጠጅን ይዞ ተቀበለው እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ ስለዚህም አብርሃምን ባርከውም አለውም አብርሃም ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው ጠላቶችህንም በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው ብሎ ባረከውና ተገናኘው፡፡ ስለዚህ ካህኑ ወጣቱን ሰላም ሲለውና ሲገናኘው ፊቱን በማጥቆርና በማስደንገጥ መልክ ሳይሆን ፈገግ ባለና መቅረብ በሚቻልበት መልክ መሆን አለበት እንላለን፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የሁለቱ አበው ግንኙነት ለካህኑና ለወጣቱ መልካም ምሳሌና አርአያ ሲሆን ይገባል ስትል ቤተ ክርስቲያን ስታስተምር ኖራለች፣ አሁንም በማስተማር ላይ ናት ማለት ነው፡፡ ካህኑ እንደ መልከ ጼዴቅ የሰላም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆኑ የአባቶች አለቃ የሆነውን አብርሃምን የባረከ አሥራት በŸCራት የተቀበለ ሰው ነውና ምሳሌ ቢያስፈልግ እብራውያን ምዕ. 7. ቁ. 1-3 ያለውን ማንበብ ይቻላል፡፡ ካህን ከሰዎች ሁሉ ይመረጣል (መሀል) እሱም የሚመረጠው መስዋዕት ለማቅረብና ኃጢአትን ለማስተስረይ ነው እና ለራሱም ለሌላውም ያስተሰርያል ማለት ነው፡፡

ከዚህ በመቀጠል ዘሌዋውያን 9፡17-16 ያለውን ብንመለከት ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአትህን መሥዋዕት ሠዋ ለራስህና ለሕዝብህም አስተሰርይ እግዚአብሔርም እንዳዘዘህ የሕዝቡን ቁርባን አቅርብ አስተሰርይላቸውም አለው ካህኑ ይሄንን ያህል ከፍ ያለና የላቀ ሥልጣን ከእግዚአብሔር የተሰጠው ስለሆነ ከዚህ የበለጠ ሥልጣንና ኃላፊነት ምን ይኖራልና ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ወጣቱና ክርስቲያናዊ ባህል በኢትዮጵያ

ከመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን
የሊቃውንት ጉባኤ አባል

ቤተ ክርስቲያን ማለት በትርጓሜ ቤት ዘይቤ የምእመናን ስብስብ ማለት ሲሆን ምእመናን አምልኮተ እግዚአብሔርን ለመፈጸም የሚሰበሰቡበት ቤተ ጸሎትም ቤተ ክርስቲያን ይባላል፡፡ የምእመናን ስብስብ በእድሜ፣ በጾታ፣ በማዕረግ የተለያየ የኅብረተሰብ ክፍል የሚገኝበት መድበለ ማኅበር ሲሆን ይህም መድበለ ማኅበር፤

 • ካህናት ወመኃይምናን /ካህናትና መኃይምናን/
 • ዕድ ወአንስት /ወንዶችና ሴቶች/
 • አዕሩግ ወደቂቅ /ሽማግሌዎችና ልጆች/
 • ዐቢይ ወንዑስ /ትልቅና ትንሽ የመዓረግ/

በሚል ክፍል ይከፈላል፡፡

ከዚህ መድበለ ማኅበር ዝርዝር ውስጥ "ደቂቅ" ወይም "ልጆች" የሚለው ክፍል ከሕፃናት ጀምሮ ወጣቱን ትውልድ ይመለከታል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም እንደ ቤተ ክርስቲያንነቷ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተሟልቶ የሚገኝባት ተቋም ስለሆነች እንኳን ወጣቶችን ሕፃናትን ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማለት ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተሳትፎ አታገልም፤ ወጣት ሽማግሌ ሳትል ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል እንደ አንድ ቤተሰብ ትንከባከባለች፡፡

1. የወጣቶች አስተዳደግና አያያዝ በቤተ ክርስቲያን፤

"ጠቦቶቼን ጠብቅ" ዮሐ. 21፡16

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃንና የዓለም ጨው ሁነው የሰውን ልጅ እንዲያገለግሉ ካዘጋጃቸው ደቀ መዛሙርት መካከል ለአንዱ ለቅዱስ ጴጥሮስ ከተናገረው የአደራ ቃል አንዱ "ጠቦቶቼን ጠብቅ" የሚል ነው፡፡ ጠቦቶቼ የሌባ ሰለባ እንዳይሆኑ ሌት ተቀን ነቅቶና ተግቶ ይጠብቃል፡፡ ሕፃናትና ወጣቶችም ከሕፃንነታቸውና ከወጣትነታቸው አንጻር ለማይፈለግ ምኞትና ተግባር የወደፊት ሕይወትን ሊጎዳ ለሚችል ሕገ ወጥነት፣ በጀብደኝነት ለሚመጣ ድቀት ወዘተ የተጋለጡ እንዳይሆኑ በመንፈሳዊ ምግብና ቤተ ክርስቲያን ለልጆችና ወጣቶች የምታደርገው ጥንቃቄ ከሌላው የላቀ መሆን ይኖርበታል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች በአዲስ መልክ ተደራጀ፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በየደረጃው በፈጠረው አደረጃጀት መሠረት ሁሉም አኅጉረ ስብከት ወረዳና ሀገረ ስበከት አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት ጠቅላላ ጉባኤዎች ማደራጀቱን ተከትሎ ለሀገር አቀፍና ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አቀፍ ከፍተኛ አገልግሎት የሚያበረክቱትን የአዲስ አበባ ገዳማትና ድባራት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለማደራጀት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲሱ አወቃቀር ለመከተል ሲባል ለተወሰነ መዘግየቱንና አሁንግን በአዲሱ የሀገረ ስብከቱ አዋቀር መሠረት በሰባት ክፍለ ከተማና በአንድ ሀገረ ስብከት አደረጃጀቱ መጠናቀቁ ማደራጃ መምሪያው ይፋ አድርጎአል፡፡
በዚህ መሠረት አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንድ ሀገረ ስብከት አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤና ሰባት የየክፍለ ከተሞት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ እንደተዋቀረ ለማው ተችሎአል፡፡
የሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያደራጅና የሁሉም አደረጃጀቶች አመራር አካላት ዝርዝርም ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቆአል፡፡

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት በሀዲያ ዞን ቤተክርስቲያን በመሥራት ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያላትን መንፈሳዊ የምስጢር ጥልቀትና ምጥቀት በአግባቡ ጠብቃ ለማቆየት አልፎም ለትውልድ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ካቋቋመቻቸው ተቋማት አንዱ ሰንበት ት/ቤት ነው፡፡ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና የወጣቶች መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወት የሚታነጽበት፣ መንፈሳዊ ዕውቀት የሚፈስበትና የሚገበይበት፣ የበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚከወንበት፣ በሃይማኖት የሚጸኑበት፣ በምግባር በትሩፋት ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉበት ተቋም ነው፡፡ ሰንበት ት/ቤቶች ይህንን በሕግ በቃለ ዓዋዲ የተሰጣቸውን የአገልግሎት ተልዕኮ በመላ ሀገሪቱ ወጥ በሆነ ሥርዓት ለመፈጸም ይቻል ዘንድም መሪ ዕቅድ አዘጋጅተው ከሀገር አቀፍ እስከ ወረዳ አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች የአንድነት አደረጃጀትን ዘርግተው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ ሆኖ እያለ ሰ/ት/ቤቶች በደብራቸው ከሚያበረክቱት አገልግሎትና በአካባቢያቸው ከሚያከናውኑት የበጎ አድራጎት ምግባረ ሠናይ በተጨማሪ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰ/ት/ቤት ከአዲስ አበባ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ወዳለችው እና በአጽራረ ቤተክርስቲያን ወደ ተዳከመችው ገጠር ቤተ ክርስቲያን ተጉዘው የፈጸሙት ተምሳሌታዊ ተልዕኮ ለሁሉም ምሳሌ ይሆን ዘንድ በአጭሩ ለማቅረብ ተገደድን፡፡

በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን በጊቤ ወረዳ አሞጨራ ቀበሌ ወደ ሚገኘው የአጀጊዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአካባቢው ታሪክ በሚያውቅ አንድ ወጣት አሳሳቢነት የሰ/ት/ቤቱ ወጣቶች የጉዞ መርሐ ግብር አዘጋጅተው ሲሄዱ ቤተ ክርስቲያኑ

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በሁሉም አኅጉረ ስብከት ዘንድ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለመመስረት ለሚሰማሩ ምሁራን ስልጠና ሰጠ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በመላ ሀገሪቱ በሁሉም አኅጉረ ስብከት ዘንድ ሀገረ ስብከት አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት /ሕብረት/ ለማቋቋምና ከዚህም አንድነት ውክልና የተሰጣቸው ወጣቶች በሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ ዘንድ ተገኝተው በመሪ ዕቅዱ ለመጨረሻ ጊዜ ተወያይተው በማጽደቅ በከፍተኛ የወጣት ንቅናቄ ወደ ሥራ ለመግባት እንዲያስችለው ይህንን መርሐ ግብር በአግባቡ ለሚመሩ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ ከአራቱም የአዲስ አበባ አኅጉረ ስብከትና ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሰ/ት/ቤቶች የተውጣጡ ወጣቶች ከመሪ ዕቅድ ጀምሮ እስከ አፈጻጸሙ ድረስ እንዲሁም በየአኅጉረ ስብከቱ የሚቋቋሙ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በሚመለከት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ትናንት ሚያዝያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም አካሄደ፡፡

በስልጠናው ወጣቶቹ ሰፊ ውይይትና ምክክር ያደረጉ ሲሆን በሁሉም አኅጉረ ስበከት ለማደራጀት ከማደራጃ መምሪያው ዘንድ ሲላኩ በምን ዓይነት ዘይቤ ሥራውን የተሳካ ማድረግ እንደሚገባቸውም የጋራ ስምምነትና መረዳት ደርሷል፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዓመታዊ የወጣቶች መደበኛ ጉባኤ ለማካሄድ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ሲሆን ይህም አንዱ የጉባኤ አካል መሆኑ በዕለቱ ተገኝተው ስልጠናውንና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሩን የመሩ የመምሪያው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

"የሰንበት ትምህርት ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ፣ የአዲስ አበባና የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤት አንድነት አመራሮች ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ትውውቅና ቡራኬ ተቀበሉ"

ከሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ድረስ የሚገኙ የሰንበት ት/ቤት አመራሮች በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አስተባባሪነት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቅዳሜ ሚያዝያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተገኝተው ትውውቅ፣ ሰፊ የሥራ ምክክር እና አባታዊ መመሪያና ቡራኬ ተቀበሉ፡፡

መርሐ ግብሩ ከመጀመሩ አስቀድሞ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑት መምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ የወጣቶቹን ሁለገብ የፍቅር አገልግሎትና የማደራጃ መምሪያው ድጋፍ ሰፊ ገለጻ ካደረጉ በኋላ "አሁንም እንደ ትላንቱ ይህንን ወጣት የቤተ ክርስቲያኑ ድምጽ በመስማት እየታዘዘና ከልቡ እያገለገለ የሚገኝ ታማኝ አገልጋይ ነው" በማለት ስለወጣቶች አገልግሎት አብራርተዋል፡፡ በመቀጠልም ይህንን የፍቅር አገልግሎት ለማደናቀፍ የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈታተኑት መሆኑን አብራርተው ወጣቱ ግን ይህንን ሁሉ ችሎ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ ታማኝ ሆኖ በጽናት በማገልገል፣ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንም በመከላከል ላይ የሚገኝ የቤተ ክርስቲያን አለኝታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራሮች ዲያቆን በላይ ገ/ሕይወት ንግግር ያደረገ ሲሆን ንግግሩ ያተኮረውም በሰንበት ት/ቤቶች አደረጃጀትና የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድን በሚመለከት ነበረ፡፡ ሰንበት ት/ቤቶች ከማዕከል እስከ አጥቢያ ድረስ መዋቅራዊ ትስስር እና ከወረዳ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ሀገር አቀፍ ድረስ ሕብረትና አንድነት ፈጥረው የተሻለ አገልግሎት እንዲያበረክቱና ሁሉም አንድ ዓይነት ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ አገልግሎት ... እንዲኖራቸው ለማድረግ ሁሉንም ቅድመ ሁኔታዎች አልቀው ወደተግባር እየተገባ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከአዲስ አበባ አንድነትም የአንድነቱ ሰብሳቢ ዲ/ን ሄኖክ አስራት የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት መልክና ቅርጽ ይዞ ወጥ የሆነና የተሳካ ሁለገብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከማደራጃ መምሪያው ጀምሮ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንና ቅዱስነታቸውን ትኩረት ለወጣቱ በመስጠት አባታዊ ቡራኬያቸው ሁሌም እንዳይለየው አደራ ጭምር አብራርቷል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩም የሁሉንም ንግግር ካዳመጡ በኋላ የወጣቱ ኃይል የቤተ ክርስቲያን የደም ሥር ስለሆነ ልዩ ትኩረትና እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ከዚህ የበለጠ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ አይኖርም፣ እንደአብነት ት/ቤቱ ሁሉ ለሰ/ት/ቤትም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ያለው ተጠናክሮ የሚቀጥልበት መጨመር ያለበትን ዳግም ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ በማቅረብ አስፈላጊ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግ አብረን እየተወያየን እየተመካከርን አገልግሎቱ የተሳካ ማድረግ ይኖርብናል በማለት ሰፊ አባታዊ ምክራቸውንና መመሪያቸውን ከሰጡ በኋላ ቡራኬ ሰጥተው በጸሎት መርሐ ግብሩን ዘግተውታል፡፡

ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መደበኛ ጉበኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አስታወቀ

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ወጣቶችን ከሀገር አቀፍ ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እሰከ አጥቢያ ድረስ ልዩ ትስስር ፈጥረው የራሳቸው የሆነ አንድነትና ሕብረት መስርተው አንድ ሀገር አቀፍ ራዕይና ተልዕኮ ገንዘብ አድርገው የተሳለጠ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲመሩ ለማስቻል በቀድሞ ቅዱስ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር አማካኝነት በዓለ ጰራቅሊጦስን የሰንበት ት/ቤቶች ቀን በሚል በተሰየመው መሠረት ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ ሀገር አቀፍ መደበኛ ጉባኤ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

ማደራጃ መምሪያው የዚህ የመጀመሪያ የሆነ የጉባኤም "የምስረታ መደበኛ ጉባኤ" ተብሎ ባለፈው ዓመት ተካሂዶ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ተወካዮች በተገኙበት ሀገር አቀፍ መሪ ዕቅድ ረቂቁ ቀርቦ ከፍተኛ ውይይትና ምክክር ተካሂዶበት ከጉባኤተኞቹም እንደግብአት የሚያገለግሉ ተጨማሪ ሐሳቦች ቀርበውለት ለዘንድሮ ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲውል ያለፈው ዓመት ቀጠሮ መያዙን አስታውሶ የዘንድሮ ዓመት መደበኛ ጉባኤ ግን ለየት ያለ ከመሆኑም በላይ ለሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች ተልዕኮ መሠረት የሚጥል መሪ ዕቅድ ጸድቆ መመሪያ ለሁሉም አኅጉረ ስብከት ተላልፎ ሥራ የሚያስጀምር ጉባኤ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህንን መደበኛ ጉባኤ ሰኔ 15 እና 16 ቀን 2005ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ጉባኤው የተሳካ እንዲሆንም አስፈላጊ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ሥራ መጀመራቸውን አስታውቋል፡፡

የወጣቱ ሕብረትና አንድነት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሳካት ጉልህ ሚና አለው፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል የመምሪያ ኃላፊ

አሁን ባለንበት የዘመን ቀመር እንኳንስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለሥጋዊ ዕድገትና ብልጽግናም ቢሆን በኅብረትና በስምምነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ መንቀሳቀስ ውጤታማ ለመሆን የሚያበቃ ሁነኛ ዘዴ መሆኑ ዓለም አወድሶታል፡፡ ለአንድ ተልዕኮ መሳካት ሕብረት መሠረታዊ ነገር እንደሆነ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ "ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህ የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ አንድ አድርጋቸው" (ዮሐ.17፡11-12) እያለ አገልግሎታቸው የሰመረ ተልዕኮአቸው የተሳካ እንዲሆን ሕብረትና ስምምነት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ከመለኮት ሕብረት ጋር በማነጻጸር ሲያስተምራቸው እንመለከታለን፡፡
በመቀጠልም በዋለበት እየዋሉ ባደረበት እያደሩ ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብለው ትምህርተ ሃይማኖቱን ይማሩና ይመራመሩ ለነበሩት አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት የሕብረትና የአንድነት ጥቅም ከገለጸ በኋላ ሕብረቱና አንድነቱ አምላካዊ ወይም ሰማያዊ ተዋረዱን መጠበቅ እንዳለበት፤ አምላካዊ ተዋረዱን ካልጠበቀ ግን ሕይወት ሊኖረውና የተባረከ አገልግሎት ሊያበረክት እንደማይችል ራሱን በግንድ እነርሱን በቅርንጫፍ መስሎ በመተርጎም አስተምሮአቸዋል፡፡

 • "እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው፡፡ ...ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም፡፡ ...እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተ ቅርንጫፎች ናችሁ" ዮሐ.15፡1-5

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰ/ት/ቤት ወጣቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሐሳባቸውን አቀረቡ

የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በአጠቃላይ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሐሳባቸውንና የአገልግሎታቸውን አቅጣጫ የሚያሳይ ሐሳብ በቃልና በጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቀረቡ፡፡ ወጣቶቹ መግለጫውን በአካል ተገኝተው ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ካቀረቡ በኋላ ይህንን ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ የተገደዱት በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ስም የማይመለከታቸው አካላት የወጣቶቹ ሐሳብና አቋም ያልሆነውን አካሄድ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በመግለጻቸው እውነተኛ የወጣቶቹ ወቅታዊ ሐሳብ በአካል ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርበን ለማስረዳት ነው በማለት ገልጸውላቸዋል፡፡ የወጣቶቹ ጽሑፍ የተቀበሉት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በወቅታዊ የቤተክርስቲያናችሁ ሁኔታ የልጅነት ድርሻችሁን ለመወጣት እንዲህ ዓይነት ሐሳብ ለቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረባችሁ የሚያስመሰግን ነው በማለት ጽሑፉንም ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚቀርብ ገልጸውላቸዋል፡፡የተከበራችሁ አንባቢዎች ከዚህ ቀጥሎ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረቡትን ጽሑፍ እነሆ እንላለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ለሁሉም አኅጉረ ስብከት የሰንበት ትምሀርት ቤት ክፍል ኃላፊዎች መሪ እቅዱን ይፋ አደረገ፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በምሁራን የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች አስጠንቶ ያዘጋጀውን የአምስት ዓመት መሪ ስትራተጂክ እቅድ በሰንበት ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ ዓመታዊ የበዓለ ሐምሳ አገር አቀፍ ጉባኤ የሁሉንም አኅጉረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ኃላፊዎችና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ለውይይት አቅርቦ አስፈላጊ ግብአቶችና ማሻሻያ እንዲደረግበትና ለሁሉም አኅጉረ ስብከቶች እንዲተላላፍ በተወሰነው መሠረት መምሪያው በጉባኤተኞች የተሰጡትን የማሻሻያ ሐሳቦችና ግብአቶችን አጠናቅቆ እቅዱ ላይ በማካተት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የበላይ ኃላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የበላይ ኃላፊ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያና የስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ዋና ኃላፊዎች፣ የየአኅጉረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ኃላፊዎ፣ የየአኅጉረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች በተገኙበት የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅዱ ይፋ አድርጎአል፡፡

እቅዱ ከሸኚ ደብዳቤ ጋር ለሁሉም አኅጉረ ስብከቶች የተላከ ሲሆን የዚህ እቅድ አፈጻጸም ለመከታተልም ማደራጃ መምሪው እስከታች ድረስ እየወረደ የማጠናከርና የማደራጀት ሥራ እንደሚሠራ የማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ መምህር እንቈባሕርይ ተከስተ ለጉባኤው ገልጸዋል፡፡ የየአኅጉረ ስብከቶቹ ኃላፊዎችም እቅዱን ተግባራዊ ለማድርግ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻም ሁለቱም ብፁዓን አባቶች በየተራ በሰጡት ቡራኬንና መመሪያ መሠረት ስብከተ ወንጌልና ሰንበት ትምህርት በሀተት የማይነጣጠሉ ሁለት ግን አንድ ዓይነት ተልዕኮ ያላቸው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለማሳካት የደም ሥር ስለሆኑ በሕብረት እንዲንቀሳቀሱ አደራቸውን ካስተላለፉ በኋላ ጉባኤው በብፁዓን አባቶች ጸሎት ፍጻሜ አግኝቶአል፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፎች

"ወጣት እና ቤተክርስቲያን"

መግቢያ:

ወጣትነት ከሕፃንነት ወደ ዐዋቂነት በሚደረገው ሽግግር ወቅት አንድን ሰው ለዐዋቂነት የሚያሸጋግሩ ስነልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊና አዕምሮአዊ ለውጦች የሚከናዎኑበት ጊዜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመን ከውስጣዊ ፈተና በተጨማሪ ውጫዊ ፈተና የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሻለ የዐዋቂነት ሕይወት ለመምራት አንድ ወጣት እነዚህን ፈተናዎች በአሸናፊነት መወጣት አለበት፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ ወሳኝ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራት እሙን ነው፡፡ በዚህ መልኩ ልጆቿን ኮትኩታ ባሉበት ፈታኝ ዘመን ፈተናውን ተቋቁመው ማለፍ እንዲችሉ ማገዝ ከቻለች ለመንፈሳዊ ክብር ልታበቃቸው ትችላለች፡፡ በምላሹም ከወጣቶች የሚጠበቀውን መጠነ-ሰፊ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ