Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የወጣቱ ተሳትፎ ከመዝሙር አገልግሎት ባሻገር መሆን አለበት

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ኅብረትና አንድነት አስፈላጊነት በማመን ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ ጠንቅቀው እነዲማሩና ለአስተማረቻቸው ቤተ ክርስቲያንም መልካም መዓዛ ያለው አገልግሎት በፍቅር እንዲያገለግሉ ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሯ ሕያው የሆነ እውነታ ነው፡፡ ይህንን ዕድል ተጠቅመው ሁሉን ማድረግ የሚያስችል እውቀትና ትኩስ ጉልበት እንዲሁም እምቅ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች በኅብረት ተሰባስበው የቤተክርስቲያናቸውን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓትና ቀኖና ተምረውና አጥንተው በአባቶቻቸው ፍኖተ ሃይማኖት ተከትለው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በፍቅር በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በተለይ በመዝሙር አገልግሎት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከአገልግሎታቸው ሁሉ ሚዛን የሚደፋ እሴት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ በተለይም በዓመታዊና በወርሐዊ በዓላት ላይ ቀድመው እየተገኙ የአባቶቻቸውን ፈለግ ተከትለው፣ ጥንግድርብና የደንብ ልብሳቸውን በየደረጃቸው ለብሰው፣ በቤተክርስቲያኒቷ የአቋቋምና የአዘማመር ስልት አደግድገው፣ በያሬዳዊ ዜማ ተቃኝተው፣ ታቦታትን አጅበው ዝማሬውን ዘምረው ካበቁ በኋላ ሊቃውንቱን ተከትለው በመወረብ... ወዘተ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን በዓላትን በመንፈሳዊ የዝማሬ አገልግሎት እጅግ በጣም በማድመቅና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በማክበረ የጐላ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡ ፡

ይህ እንዳለ ሆኖ በዓመት አንድ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናችን በማዕከላዊነት ከምታከብራቸው በዓላት ውስጥ በቅርቡ ያከበርነው የመስቀል ደመራ በዓል አንዱ ነው፡፡ በዚህ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓልም ወጣቶች በየክፍለ ከተማቸው ተሰባስበው፣ በሕብረት ሰልጥነው... ባቀረቧቸው የተለያዩ ዓይነት ይዘት ያላቸው አስተማሪ ትርዒቶች እንኳንስ እኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ኢትዮጵያውያን በቦታው ላይ ይህንን ጥንታዊ ሥርዓት ለመከታተል የመጡትን የውጭ ሀገር ጎብኝዎችና አምባሳደሮችንም ጭምር ሳይቀር በጣም ከማስደሰቱም በላይ ቀልባቸውን የሳበ እጅግ በጣም ማራኪና የተዋጣለት ሥራ ለመሥራት የቻሉ የቤተክርስቲያ የብርሃን ልጆች /አገልጋዮች/ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሰንበት ትበቤቶች ወጣቶች በየአብያተ ክርስቲያናቱ የተማሩትን ትምህርት ላልደረሰው ለማዳረስ ጉባኤያትን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተላየዩ መርሐ ግብሮችን በመዘርጋ አቅማቸው በሚፈቅደው መልኩ የማስተማርያ ሥርዓተ ትምህርት ቀርፀው የተለያዩ ይዘት ያላቸው የቤተ ክርስቲያናችንን አስተተምህሮዎች በሦስት ወር፣ በስድስት ወር ወዘተ.. ተከታታይ ትምህርት /ኮርስ/ በመስጠት ወጣቶችን እያስተማሩ፣ እያሰለጠኑ... በሰርተፊኬት በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ ቁምነገር አለ፡፡ይኸውም ወጣቶች ቤተ ክርስቲያናቸውን በመዝሙርና በትምህርት በኩል ሰፊ አገልግሎት በመስጠት በተለይ ህጻናትና ወጣቶች ከአላስፈላጊ የስሕተት ትምህርትና የሥነ ምግባር ሕጸጽ ተቆጥበው የቤተ ክርስቲያናቸውን ትምህርት አውቀው፣ በትህትናና በፍቅር እንዲያገለግሉ በማድረግ እንዲሁም በተለይ በዓበይት በዓላት ነዳያንን በመመገብ የተለያዩ አልባሳትን በማደል.. ወዘተ የማይናቅ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ነው፡፡ ነገር ግን በብዙዎቻችን አእምሮ የተቀረጸው የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የሚያስፈልጉት በእነዚህ የበዓላት ቀናት ለመዝሙር አገልግሎት ማለትም ከላይ ለገለጽነው አገልግሎት ብቻ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ እውነታው ግን ወጣቶች ዘመኑን መዋጀት የሚችሉ፣ ዘርፈ ብዙ የዘመኑ እውቀት ያካበቱ፣ በሙያ የጎለበቱ በዘመናዊ ጥበብ የመነጠቁ ወዘተ.. ናቸወ ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡ ስለሆነም በቤተክርስቲያን ውስጥ ከመዝሙር ባሻገር በሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም እንዲሳተፉና ከአባቶች ጋር ተናብበው አመርቂ ሥራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሁኔታ ማመቻቸት ለነገ የማይባል አንገብጋቢ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያቀደቻቸውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልዕኮዎች ጊዜአቸውን ጠብቀው፣ ዘመኑን ዋጅተው.. በተሳካ መልኩ ከግብ መድረስ የሚችሉት በወጣቶቻችን ሁለገብ ተሳትፎና ያላሰለሰ ጥረት መሆኑ ሁሉም ሊያምንበተ የሚገባው እውነት ነው፡፡

በመሆኑም በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያናችን ሁለተንተናዊ አገልግሎት መቃናትና እድገት የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝበን ከመዝሙርና ከላይ ከገለጽናቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ በሌሎችም ተልዕኮዎች በመሳተፍ የተሻለ አመርቂ ውጤት ስለሚያስመዘግቡ በሁሉም ዘርፎች እንዲሳተፉና ኃላፊነት ወስደው እንዲያገለግሉ ማበረታታት ዘመኑ የሚጠይቀው እውነታ መሆኑን አውቀን በቤተክርስቲያን መዋቅራዊ አገልግሎት የተቀመጥን ሁላችንን ወጣቶች ልናቀርባቸው ልናበረታታቸውና ኃላፊነት ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ ወጣቶችም ከመንፈሳዊ አገልግሎቱ በተጨማሪ በቤተክርስቲያናችን አጠቃላይ ተልዕኮ በንቃት የመሳተፍና ከግብ የማድረስ የፍቅር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባቸዋል እላለሁ፡፡

መልካም የአገልግሎት ዘመን!!

የፎንት ልክ መቀየሪያ