Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የወጣቱ ሕብረትና አንድነት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሳካት ጉልህ ሚና አለው፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል የመምሪያ ኃላፊ

አሁን ባለንበት የዘመን ቀመር እንኳንስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለሥጋዊ ዕድገትና ብልጽግናም ቢሆን በኅብረትና በስምምነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ መንቀሳቀስ ውጤታማ ለመሆን የሚያበቃ ሁነኛ ዘዴ መሆኑ ዓለም አወድሶታል፡፡ ለአንድ ተልዕኮ መሳካት ሕብረት መሠረታዊ ነገር እንደሆነ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ "ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህ የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ አንድ አድርጋቸው" (ዮሐ.17፡11-12) እያለ አገልግሎታቸው የሰመረ ተልዕኮአቸው የተሳካ እንዲሆን ሕብረትና ስምምነት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ከመለኮት ሕብረት ጋር በማነጻጸር ሲያስተምራቸው እንመለከታለን፡፡
በመቀጠልም በዋለበት እየዋሉ ባደረበት እያደሩ ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብለው ትምህርተ ሃይማኖቱን ይማሩና ይመራመሩ ለነበሩት አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት የሕብረትና የአንድነት ጥቅም ከገለጸ በኋላ ሕብረቱና አንድነቱ አምላካዊ ወይም ሰማያዊ ተዋረዱን መጠበቅ እንዳለበት፤ አምላካዊ ተዋረዱን ካልጠበቀ ግን ሕይወት ሊኖረውና የተባረከ አገልግሎት ሊያበረክት እንደማይችል ራሱን በግንድ እነርሱን በቅርንጫፍ መስሎ በመተርጎም አስተምሮአቸዋል፡፡

 • "እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው፡፡ ...ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም፡፡ ...እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተ ቅርንጫፎች ናችሁ" ዮሐ.15፡1-5

በእርግጥ የአንድ ዛፍ ውበት ቅርንጫፎቹ ናቸው፡፡ የቅርንጫፎቹ በሕይወት መኖር ምክንያት የሚሆነው ደግሞ ግንዱ ነው፡፡ ቢያምርበትም ባያምርበትም ግንድ ያለ ቅርንጫፍ መኖር ይችላል፡፡ ቅርንጫፍ ግን በምንም መልኩ ያለ ግንድ ሕይወት ዘርቶ በጤና መኖር አይችልም፡፡ ግንድ የሌለው ቅርንጫፍ መጀመርያ ይደርቃል፤ ፍጻሜውም የእሳት ማገዶ ይሆናል፡፡ ከግንዱ ጋር በአግባቡ የኖረ ቅርንጫፍ ግን ልምላሜ፣ ጽጌና ፍሬ በአጠቃላይ ሕይወት ኖሮት ከራሱም አልፎ ለሌሎች በመትረፍ ምግብ፣ መድኃኒት ወዘተ በመሆን ያገለግላል፡፡

በአጠቃላይ ለመግለጽ የተፈለገው አንድ ዛፍ ውበት የሚኖረው ልምላሜ፣ ጽጌና ፍሬ ገንዘብ ባደረጉ ቅርንጫፎቹ ምክንያት ሲሆን ቅርንጫፎቹ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችል ደግሞ ከግንዱ ጋር በአግባቡ ሲዛመዱ ብቻ መሆኑ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን በዓለመ ነፍስና በዓለመ ሥጋ የሚገኙ ምዕመናን እንዲሁም የቅዱሳን መላእክት ሕብረትና አንድነት ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ራስ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ኤፌ.5፡23)፡፡ የነቢያት ትንቢት ሰምተን፣ የሐዋርያት ስብከት ተረድተን እነርሱን መስለን አምነን የተጠመቅን ለእኛ ለክርስቲያኖች ደግሞ የሕይወት ግንዳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ለጊዜው ቅርንጫፎች ናችሁ የተባሉት ለሐዋርያት ቢሆንም ፍጻሜው ግን በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት ለታነጽነው (ኤፌ.2፡20) ለእኛ ለክርስቲያኖች መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እውነተኛ ዘለአለማዊ የባሕርይ ሕይወት ኢሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለሆነም የቅርንጫፎቹ የእኛ ሕይወት እውን የሚሆነው ከአማናዊ የሕይወት ግንድ ጋር በአግባቡ ተዛምዶ መኖር ሲችል ብቻ ነው፡፡
ወጣቶች የመጠቀና የጠለቀ ዕምቅ ኃይልና ችሎታ ያላቸው፣ ከሌላው የተሻለ ሀገራቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን ይበልጥ አብዝተው ማገልገል የሚችሉ የጀርባ አጥንቶችና የደም ሥሮች እንደሆኑ አጥብቃ ታምናለች፡፡ የዚህ እምነት ውጤትም ወጣቶችን የሚያገለግል በመምሪያ ደረጃ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ጽ/ቤት በማቋቋም ወጣቶች በሕብረትና በአንድነት ይበልጥ ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ትገኛለች፡፡
ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ "ወንድሞች በሕብረት ቢኖሩ መልካም ነው" (መዝ.133፡1) እንዳለ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያም ወጣቶች ከመንበረ ፓትርርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ቃለዓዋዲውን በሚፈቅደው መልኩ ይበልጥ ሕብረት ፈጥረው፣ የቤተ ክርስቲያኒቷን ሐዋርያዊ ተዋረድ አጽንተው፣ ትምህርተ ሃይማኖቷን አጥንተውና ጠብቀው፣ ትውፊትዋንና ቀኖናዋን አክብረው ከላይ እስከ ታች፣ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ድረስ አንድነታዊ ትስስር ፈጥረው ቤተ ክርስቲያናቸውን ማገልገል ዘመኑ የፈቀደው ለነገ የማይባል የመንፈሳዊነት ግዴታ መሆኑ መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡


የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ወጣቶች ሕብረት ፈጥረው የጋራ አገር አቀፋዊ መሪ እቅድ አንግበው የሚያበረክቱት መንፈሳዊ አገልግሎት በእቅድ እንዲመራ ለማድረግ ከየሰንበት ትምህርት ቤቶች በተገኙ ምሁራን ዘመናዊ ጥናት አስጠንቶ በማስገምገም በአገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ አጸድቆ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
ይህንን መሪ እቅድ ከማደራጃ መምሪያው ጎን በመሆን ሊመሩና ሊያስተባብሩ የሚችሉ ኮሚቴዎችም በጠቅላላ ጉባኤ አስመርጦ "ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት" የሚል ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ተጠሪነቱ ለማደራጃ መምሪያው ሆኖ ተቋቁሟል፡፡
ይህንን የአንድነት አደረጃጀት በመጠቀም የወጣቱ አገልግሎት በሕብረትና በአንድነት ተደራጅቶ የሚፈጸም ከሆነ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎትና ሁለንተናዊ ዕድገት ከነበረው ይልቅ የሚኖረው ጉልህ ሚና አጠያያቂ አይሆንም፡፡
ስለሆነም ሁሉም ወጣቶች አሁን በተፈጠረው ምቹ የአገልግሎት ሁኔታ በመጠቀም ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ድረስ ያላቸው ትስስርና ተሳትፎ የበለጠ በማጠናከር አሁንም እንደተለመደው ያለምንም ክፍያ በነጻ የሚያበረክቱት መንፈሳዊ የፍቅር አገልግሎታቸውን እንዲያጎለብቱ አደራ ስል መልካም የነቢያት ጾም እንዲሆንልንም ጭምር በመመኘት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የፎንት ልክ መቀየሪያ