Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ መክ.12፡1

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ወጣትነት የጉብዝና ወራት እንደመሆኑ መጠን ወጣቶች ወጣትነታቸውን በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲመሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ወጣትነት በአብዛኛው አካልን የሚያሳምርና ብቃት የሚሰጥ ሲሆን በጥንቃቄ ካልተያዘ ግን አእምሮን የሚያበላሽ ወቅትና ጊዜ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልካም የሠሩ እና በረከትን ያገኙ ወጣቶች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ራሳቸው ስተው ሕዝብን ያሳቱ ከእግዚአብሔርም ርቀው በላያቸው ላይ ቁጣ ያመጡትን ወጣቶች እናያለን::

ለምሳሌ ዮሴፍ በወጣትነት ወይም በጉብዝናው ወራት የእግዚአብሔርን ሕግ ያከብር የነበረ እና በሚሄድበት ቦታ ሁሉ አምላኩን የማይረሳ ወጣት እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ዘፍ.39፡1፡፡ስለዚህም እግዚአብሔር ስራውን ያከናውንለት ነበር፡፡ ዛሬም በወጣትነት ወራት ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ እውቀትና ስልጣኔ ከምናስበው በላይ ሊገዛን ይችል ይሆናል፣ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዓላማ ውጪ እንዳያደርጉን ሕይወታችንን በመንፈሳዊው ጐዳና ልንመራ ያስፈልገናል፡፡ እነዚህ ከላይ የገለጽናቸው ሁሉ ሥጋዊ እርካታን እንጂ ሕሊናዊ እርካታን ሊሰጡን ፈጽሞ አይችሉም፡፡

ሁል ጊዜ ሰዎች የሕሊና እረፍት ማግኘት የሚችሉት ከእግዚአብሔር ጐዳና ብቻ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ በምድር ላይ አንቱ የተባሉ ባለፀጎች ራሳቸውን በመርዝ፣ በስቅላት እና በተለያዩ መሣሪያዎች ባላጠፉ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለበት ገንዘብና ንብረት እንዲሁም ዕውቀት ሁሉ የሚያገለግለው ለጥፋት ብቻ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እህልን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ስለሚራቡ፡- “እነሆ በምድር ላይ ራብን የምሰደድበት ዘመን ይመጣል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠጣት አይደለም” (አሞ.8፡11) ምድራዊውን ምግብ እየተመገቡ ነገር ግን እርካታን አያገኙም፡፡ ሀብትና ንብረትን እያሰባሰቡ ነገር ግን ጣዕሙን አያውቁትም፡፡ እግዚአብሔርን የማወቅ ጉድለት በልቡናቸው ያለባቸው ሰዎች ሁሉ በእውነት ከንቱ ናቸው… ሥራውን እያዩ ሠሪውን አላወቁትምና መ.ጥበብ 13፡1 በመጽሐፈ መክብብ ላይ እንደምናየው በወጣትነትህ ሰዓት ልብህ የፈቀደውን ሁሉ አድርግ ነገር ግን ለምትሠራ ሁሉ በመጨረሻው ሰዓት እግዚአብሔርን ለፍርድ እንደሚያቆምህ እወቅ በማለት ይናገራል፡፡ ይህ የሚያመለክተው በወጣትነታችን ሰዓት የእግዚአብሔርን ዓላማ የምንፈጽምበት ወቅት እንጂ ባህሪያችንን በእንስሳ ባሕርይ ለውጠን በስሜት ብቻ የምንነዳበት ጊዜ አለመሆኑን ነው፡፡

“ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ እንደሚጠፋ እንስሶች ራሱን መሰለ” ወጣትነት በመንፈሳዊ ሕይወት ሲታሽ መልካሙን ጸባይ ይላበሳል በተቃራኒው ደግሞ በሥልጣኔ ሰበብ አልባሌ ቦታ የሚውሉ ከሆነ የሴይጣን መናኸሪያ ሆነው ለቅድስና የሚሆነውን ሰውነታቸውን ለእርኩሰት፣ ለምርት ይውል የነበረውን ሀይላቸውን ለጥፋት እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ለወጣቶች መሠረታዊ የሆነ የሥነ ምግባር ማስተማሪያ ቦታ ስለሆነች ሁሉም ወጣቶች ያለምንም ዋጋ በነፃ ከማይነጥፈው ዕውቀቷ እየቀዱ እንዲጠጡ ወደ እኔ ኑ ትላለች፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ