Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

መንፈሳዊያን ወጣቶች እና የጉርምስናቸው ወቅት

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ጉርምስና በቤተ ክርስቲያናችን ቋንቋ ውርዝውና ወይም በአማርኛው ወጣትነት በመባል ሊወስድ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ አምድ ጽሑፍ ውስጥ ሁሉም በቀላሉ ሊረዳው እንዲችል በማለትና እንዲሁም ሰዎች ለጉርምስና ያላቸውን አመለካከት ለመግለጽ ስለሆነ ጉርምስና በሚለው ቋንቋ ጽሑፌን አስተላልፋለሁ፡፡ መንፈሳዊያን ወጣቶች ማለትም ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጡ የሚያድጉትን ልጆች ለማለት ተፈልጎ ነው፡፡

ጉርምስና ወቅቱን ጠብቆ የሚመጣ ጤናማ እና አስደሳች ወቅት ነው፡፡ ይህ ወቅት በእያንዳንዱ ሰው ላይ የሚያሳየው ትርኢት እጅግ በጣም የተለያየ እና የራሱ ውበት ያለው ነው፡፡

 ይሁን እንጂ በብዙ ሰዎች ዘንድ “ይህ ልጅ ጐርምሷል”ወይም“ጐርምሳለች” ማለት እንደ ስድብ በመወሰዱ ከጥፋትም ጋር በመያያዙ እጅግ በሚገርም ሁኔታ የተለየ ትርጉም እና አመለካከት ተሰጥቶታል፡፡
ስለዚህ ብዙ ወጣቶች ይህንን ወቅት እግዚአብሔር እንደሰጣቸው ልዩ ስጦታ ሳይሆን በራሳቸው እንዳመጡት ተጽዕኖ ስለሚቆጥሩት ደስተኞች አይሆኑም፡፡ ይህ ደግሞ የተሳሳተ ግንዛቤ በመሆኑ መምህራኖቻቸው ሊያስተምሯቸው ይገባል፡፡ 

 ጉርምስና የእግዚአብሔር ስጦታ ነው?

በዚህ ዓለም የምናገኘው ሁሉ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድም ምንም ሊሆን እንደማይችል መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም የዮሐ.1፡3፡፡ ስለዚህ እኛነታችን እንኳ የተሰጠን ከእግዚአብሔር ነው፡፡

በመሆኑም ከእናት ማህፀን ጀምሮ ቀስ በቀስ እያሳደገ የሚያኖር እርሱ ስለሆነ በእያንዳንዱ እድገታችን ውስጥ የእግዚአብሔር ስጦታ ይታያል፡፡

ጉርምስና የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ በምን ይታወቃል?

በመጀመሪያ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ዕድሜያቸው በእግዚአበሔር ዘንድ እንደሚታወቅና የሰውንም ዕድሜ መጨመርና መቅጨት የራሱ የእግዚአብሔር ድርሻ መሆኑ ይታወቃል ይታመናልም መ.ነገ.ካልእ 20፡1፡፡ 

በመሆኑም የጉርምስና የዕድሜ ክልል እንድንገባ ዕድሜን የሚሰጠን እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡

አንድ ህፃን እያደገ ሲመጣ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ የሃይማኖትን ትምህርት መማር ይጀምራል፡፡  

በመሆኑም ለራሱ ጥሩ ግምት መስጠትን ያዳብራል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ዲያቆን፣ ዘማሪ፣ ወንጌላዊ፣ እንዲሁም በተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ራሱን በማስቀመጥ በአእምሮ ይስላል፡፡

ይህ ጤናማ የሆነ አካሄድ ከጉርምስና በፊት በጣም ቀላልና ትልቁ ምርጫ ሆኖ ይሰማዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታ በወንጌል እንደተናገረው “እንደ ህፃናት ካልሆናችሁ የእግዚአብሔን መንግሥት አትወርሱም”ማቴ.19፡13 የሚለው የጌታ አባባል ለህፃናት ከፍተኛ ምስክር ነውና በዚህ ጊዜ ለህጻናቱ ልዩ የመንፈሳዊ ሕይወት ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ወቅት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚሄዱ ህፃናት መሠረታቸው ጽኑ ስለሚሆን በጣም ጥቂት ልጆች ካልሆኑ በስተቀር ብዙዎቹ መጨረሻቸው ከማማርም በላይ የሀገር ተረካቢ እንደሚሆኑ ምንም አያጠራጥርም፡፡

ከዚህ በመቀጠል ያለው ጊዜ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ ጊዜ ይሆንባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከላይ የተገለጸው የጉርምስና ወቅት ከተደበቀበት ጓዳ እራሱን አደራጅቶ ኃይል አሰባስቦ ብቅ የሚልበት ጊዜ ስለሆነ:: ብዙዎቻችን በመንፈሳዊ ሕይወት ስናድግ የሚሰማንን አዲስ ስሜት ከሰይጣን ጋር ስለምናያይዘው ለራሳችን የምንሰጠው ግምት በጉርምስና ወቅት የማይገባ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን እጅግ አድርገን እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ጊዜ እንደሆነ ሊነግረን የሚችል መንፈሳዊ መምህር ያስፈልገናል፡፡

ስለጉርምስናችን እግዚአብሔርን ማመስገን ያስፈልጋል?

እግዚአብሔርን ማመስገን በዚህ ጊዜ የሚባል አይደለም ሁሉም ጊዜ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ስለሆነ፡፡ ይሁን እንጂ በጉርምስና ወቅት እግዚአብሔርን የምናመሰግነው የባውሎጂ /የሥነ አካል/ዕድገታችንን በተስተካከለ መልኩ ጠብቆ ጤናማ ሰው ሊሰማው የሚገባውን ስሜት ለእኛም እንዲሰማን በማድረጉ ልናመሰግነው ይገባል፡፡

ይህ ወቅት ሙሉ ሰው የምንሆንበት ስለራሳችን መናገር የምንችልበት ስለራሳችንም መልካም ገጽታ መሠረት የምንጥልበት ወቅት ነው፡፡ ጌታ በወንጌል ያዳነው የእውሩ ቤተሰቦች “እርሱ ሙሉ ሰው ነውና እርሱን ጠይቁት” በማለት መልስ የሰጡበትን ምዕራፍ እናገኛለን ዮሐ.9፡21፡፡

ይህ መሉ ሰውነት በደረጃ የምንደርስበት ነው ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በጣም ከፍተኛ የሆነ ኃጢአት ወይም ሰይጣናዊ ፍላጎት የሚመስል ነገር ግን ያልሆነ ስሜት ይሰማናል፡፡ ምን ይሆን? የተቃራኒ ጾታ ፍላጎት፡፡

በጉርምስና ወቅት የተቃራ ጾታ ፍላጎት መሰማት ሰይጣናዊ ነውን?

የተቃራኒ ጾታ ፍላጐት ሰው ሲፈልግ የሚያገኘው ካልፈለገ ደግሞ የሚያርቀው የግሉ ንብረት ሳይሆን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሚሰጠው የተቀደሰ መንፈሳዊ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስሜት የማይሰማቸው ብዙ የውስጥና የውጭ ደዌ ያለባቸው አያሌ ሰዎች አሉ፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች ቢመኙም ሊያገኙ አይችሉም ፤ ሰው ካልነገራቸው በስተቀር ሁኔታውንም ሊያውቁት አይችሉም፡፡

የተቃራኒ ጾታ ፍላጐት የሚያያዘው ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ዘፍ.2፡18ከሚለው ከእግዚአበሔር አምላክ አባባል ጋር ነው፡፡ ይህ አባባል ተራ ሰው የተናገረው ሳይሆን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ራሱ የተናገረው ስለሆነ ሁሉንም የሰው ልጆችን የስሜት ዑደት በዚህ መልኩ ውብ አድርጐ የለገሰን እርሱ ራሱ ነው፡፡

በተጨማሪም ይህ ፍላጐት ዘር ከመተካት ጋር እንዲሁም በተገቢው መስመር ፍቅርን መግለጽ የሚጠቁም ስለሆነ በምንም መልኩ የሰይጣን መሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት /ዘፍ.1፡28/ እና ባልና ሚስት አንድ ሥጋ ይሆናሉ /ዘፍ.2፡24/ ያለው እግዚአብሔር እንጂ ሰይጣን አይደለም፡፡ በመሆኑም አንድ ሕፃን አድጐ በጉርምስና ክልል ሲገባ በትክክል መረዳት ያለበት፡-

1. እግዚአብሔር አምላክ በሙሉ ጤንነት እንዳሳደገው
2. እግዚአብሔር ለአዳም ብዙ ተባዙ በማለት የገባውን ቃል ለእርሱም እንደቸረው
3. ሙሉ ሰው መሆኑን
4. ከእርሱ በፊት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ደርሰው ያዩትን ስሜት በውስጡ መታደሉን እና
5. የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ መልካምና ውብ እንደሆነ ሊረዳ ያስፈልጋል፡፡

 የጉርምስና ፍላጐቶቻችንን ሁሉ መከተል ይገባልን?

እንደ ስሜቶቻቸው የሚጓዙ እንስሳት ሲሆኑ ስሜቶቻቸውን በአእምሮ መነጽር የሚመለከቱ ግን ሰዎች ናቸው፡፡ ሰው መሆን ያቃታቸው ብዙ ሰዎች የበዙት ተራ የሆኑ ስሜቶቻቸውን ስለሚከተሉ ነው፡፡
ለዚህም ነው ቅዱስ ዳዊት ልጁ ሰሎሞንን “ልጄ ሆይ ሰው ሁን”(ነገ.ቀዳ.2፡2)በማለት የመከረው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ሥጋ በሥጋ ሕግ እንድሄድ ይጐትተኛል፡፡ መንፈስም በመንፈስ ሕግ እንድሄድ ግድ ይለኛል በማለት ስሜቶቻችን አስቸጋሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ 

ከነዚህ የጉርምስና ፍላጎቶቻችን አስቀድመው መሟላት ያለባቸው የዕውቀት፣ የአካል፣ የኢኮኖሚ እንዲሁም የመንፈሳዊ ደረጃዎች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ጉርምስና ከነዚህ ሁሉ ቀድሞ በከባድ ፍጥነት ስለሚመጣ በጥንቃቄ ካልተያዘ እነዚህ የዘረዘርናቸው ሁሉ ዋጋ እንደሌላቸው በማስመሰል በዜሮ ስለሚያባዛ እና ለስሜቶቻችን ብቻ መልስ እንድንሰጥ ስለሚገፋፉን መንፈሳዊ መምህራን ያስፈልጉናል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጊዜ መንፈሳዊያን ወጣቶች ከሌሎች ጐረምሶች የሚለዩበት ዜዴ ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

ይህን በምሳሌ ለማየት ይረዳን ዘንድ፡- ሁለት ዘመናዊ መኪናዎችን ለሁለት የተለያዩ ሾፌሮች ብንሰጥ መኪኖቹ መቶ ሰማንያ ፍጥነት ቢኖቸውና አንደኛው ሾፌር በጠመዝማዛ፣ በዳገት፣ በቁልቁለት እና በሁሉም ሥፍራ እኩል በ180ፍጥነት ቢነዳ፤ ሁለተኛው ሾፌር ደግሞ በእያንዳንዱ ሥፍራ እንደመኪናው ችሎታ ሳይሆን በአእምሮ እና በጥንቃቄ ቢነዳ መጀመሪያ ሕይወቱን ለራሱ የሚያተርፍ ቀጥሎም ንብረቱን የሚጠብቅ በመጨረሻም ለሀገሩ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ሁለተኛው ሾፌር እንደሆነ መገመት አያስቸግርም፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት ሾፌሮች ተፈልገው ለከፍተኛ ባለሥልጣናት ሾፌርነት ይታጫሉ፡፡ የመጀመሪያው ሰው ዓይነት ሾፌሮች ግን የአደጋና የኪሳራ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ክብር እና ፍቅር እንዲሁም ተፈላጊነት የማይኖራቸው ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ጉርምስና ለመንፈሳዊያን እና መንፈሳዊያን ላልሆኑ ወጣቶች እኩል የተሰጡ ጊዜያት ሲሆኑ ልዩነቱ አነዳዱ ላይ ነው፡፡

የጉርምስና ወቅት ከዚህ ምሳሌ ጋር ይመሳሰላል፡፡ መንፈሳዊያን ወጣቶች ሲጐረምሱ በምን ያህል ፍጥነት በየትኛው ጊዜ እና በየትኛው ቦታ ጉርምስናቸውን እንደሚነዱ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ፣ የኢኮኖሚ ድጋፍ ሳያገኙ፣ በአካልም በአእምሮም ሳይበስሉ ስሜቶቻቸውን ብቻ በመከተል በጭፍን የሚሮጡ ጠመዝማዛ መንገድ ላይ እየሮጡ ስለሆነ ገደል ይገባሉ ካልሆነ ጎማቸው ይተነፍስና ከጥቅም ውጪ ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ የሚከተለው የማዕረግ ስም በሕብረተሰቡ ዘንድ ይሰጣቸዋል፡፡ ዱርዬ ሆነ፣ ጫት ቃሚ፣ አጫሽ፣ ሰካራም፣ ማጅራት መቺ…እና ሌላም የመሳሰሉትን ሆኖቀረ እየተባለ ልዩ ኮድ ይለጠፍላቸዋል፡፡ በዚህ መልኩ አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ሰርቪስ ለማስገባት ዋጋው ቀላል ቢሆንም ልፋቱ ግን እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡

ይህ ስለሆነ መንፈሳዊያን ወጣቶች ስሜቶቻቸውን የሚከተሉ ሳይሆኑ ለስሜቶቻቸው የሚሰጡትን ትክክለኛ መልስ በተገቢው ጊዜ እንዲሆን ዘመኑን ይዋጃሉ፡፡ ስለዚህም መንፈሳዊያን ወጣቶች ተወዳጆች እና ተከባሪ ከመሆናቸውም በላይ አደራ እና ኃላፊነት ተሸካሚ የሚያደርጋቸውን አሜኔታ በሰዎች ውስጥ ይቀርፃሉ፡፡ 

ለሁሉም ጊዜ አለው መ.መክብብ 3፡1

ይህንን ቃለ ስናነበው በተደጋጋሚ የሰማነው ስለሆነ ትርጉሙ እምብዛም ውስጣችንን ላይነካ ይችል ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ በጥልቀት ስናየው ምን ያህል ኃይል እንዳለው ልንረዳ እንችላለን፡፡ ከዚህ ትምህርት ጋር ለማገናኘት ይረዳን ዘንድ አንድ ህፃን ወደ ጉርምስና ከገባ በኋላ በምንም ዓይነት ተመልሶ ሕፃን ሊሆን አይችልም እንደዚሁም ከሸመገለ በኋላ በምንም ዓይነት ተመልሶ ጐረምሳ ሊሆን እይችልም፡፡

ስለዚህ ጠቢቡ የተናገረው ነገር “ነገርን ሁሉ በጊዜ ውብ አድርጎ ሰራው”(መክ.3፡11)የሚል ነው፡፡ ስለሆነም በሁሉም የእድሜ ክልል የማይቀርና አስፈላጊው ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን ሁሉም የአካላችን ለውጥ ግን እጅግ በጣም ውብ ተደርጐ በእግዚአብሔር እቅድ የተሰራ ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነ መንፈሳዊያን ወጣቶች የጉርምስና ሰሜት ሲሰማቸው እጅግ በጣም ደስተኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡ በአንጻሩ ግን የሥነ ጾታ መምህራን እንደሚያስፈልጓቸው እመክራለሁ፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ