Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ያልተጠመቁ አጥማቂያን

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት መንፈሳዊ ሀብታት መካከል አንዱ ቅዱስ ጠበል ነው፡፡ በዚህም ሀብቷ ብዙ ምዕመናንን ከደዌ ፈውሳቸዋለች የታመሙትን ምራለች የታወሩትን አብርታለች የተሸቡትን /ሽባ የሆኑትን/ ተርትራለች ከዓለም ጥበብ በላይ በሆነ መዳንም እባብ የወጣላቸው፡ እንቁራሪት የወጣላቸው አሞራ የወጣላቸው ... ወዘተ ብዙ ተአምራት እና የመዳን ውለታ የተዋለላቸው ወገኖቻችን እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ ይህን ምክንያት በማድረግ ብዙ ሕገወጥ ለራሳቸው ያልተጠመቁ አጥማቂያን በየጊዜው እየተነሱ ሕዝቡን ግራ የሚያጋቡ የፀጉር ባሕታዊያን በዝተዋል፡፡ ስለዚህም በእነዚህ ሰዎች ሳያውቁ የሚጐዱ ወገኖቻችንም እየበዙ ስለመጡ ሁኔታውን ጥቂት እንዲረዱ አንድ እንበላቸዉ፡፡

አጥማቂዎቹ ከየት ወገን ናቸው? 

በዚህ በሰለጠነ ዘመን የሥጋ ወገኑን በዘረኝነት መንፈስ ሆኖ የሚጠይቅ ሰው ችግር ያለበት ሰው እንደሆነ ይታወቃል አልያም የመንፈሳዊ ዕውቀቱ ያነሰ ነው ማለት ነው፡፡ ይሁንና ግን እዚህ ጽሑፍ ላይ ወገን በማለት የተጠቀምኩት ውሎንና ኃላፊነትን ለመግለጽ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አጥማቂዎች ከጥቂቶች በስተቀር በብዛት ቀድሰው የማያቆርቡ፤ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው የማያስቀድሱ የቤተ ክርስትያኒቷን ፍልቅ ፀበል የማይጠቀሙ እንዲሁም አጋንንትን በዱላ በጧፍና በአለንጋ ደብድቦ ለማስለቀቅ የሙከራ ሥራ ላይ የተሠማሩ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው እንግዲህ ያልተጠመቁ አጥማቂናያን በማለት የጀመርኩት፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የተጠመቀ አንድ አማኝ ቢያንስ የአጋንንት መንፈስ የሚለቀው በጾምና በጸሎት እንጂ በድብደባና በግርፍያ እንደማይለቅ ያውቃል፡፡እነዚህ አጥማቁያን ግን ለመጾምና ለመጸለይ አቅሙና ህይወቱ ስለሌላቸዉ ያደጉበትን የሥራ ልምዳቸውን ይዘው በቀጥታ አጥማቂ በመሆን አስቀድሞ ዘራፊ እና ማጅራት መቺ የነበሩት አሁን ግን መንፈሳዊያንን ምዕመናን በመደብደብና በመግረፍ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡

የአጋንንትን ምስክርነት የሚቀበሉ አጥማቂያን ቤተ ክርስትያንን ሊወክሉ አይችሉም፡፡

በሽተኞች ለመዳን ፣ አስታማሚዎች ወገናችን ይድንልናል በማለት ተስፋ አድርገው ሲመጡ አጥማቂው ደግሞ አጋንንትን ተናገር በማለት ማን ላከህ ሲለው ጐረቤቷ ነው ጐረቤቱ ነው እያለ ይናገራል ይህ እንደ እውነት ይወሰድና ግለሰቡን በጤና ያሰቃየው ጋኔን እንደገና የጐረቤትን ሰላም የሕዝብን ትስስር ያውካል፡፡አጥማቂ ነኝ ባዩም እውነት ነው በማለት ከጠንቋዮች ባልተናነሰ ሁኔታ ያሰናብታል፡፡ በሽተኛውም ከመጀመሪያው በሽታ ሳይፈወስ በማህበራዊ ሕይወት ሰላም ማጣት በሽታ ተመትቶ ይሄዳል፡፡አጋንንት የሃሰት አባት እንጂ የእዉነት አባት ሊሆን እንደማይችል መጽሐፍ ይናገራል፡፡

ለአጋንንት ጉቦ መስጠት የጠንቋዮች ድርሻ እንጂ የካህናት አይደለም፡፡

በቅድስት ቤተ ክርስትያናችን አጋንንትን በጌታ ቃል ብቻ ቀጥቅጠው አዝዘው የሚያባርሩ ንጹሐን አባቶች እንዳሉ ሁሉ ለመውጣት ምን ትፈልጋለህ እያሉ የሚጠይቁ አጥማቂያን ብቅ እያሉ ነው፡፡ የዘመኑ አጥማቂያን ከሚያደርጉት አጸያፊ ተግባራት አንዱ አጋንንትን ምን ላምጣልህ ብሎ መጠየቅ ነው፡፡ አጋንንቱም አመድ አምጣልኝ አተላ አምጣልኝ አፈር ወዘተ አምጣልኝ እያለ ያዘዋል፡፡ለእግዚአብሔር ሕዝብ ሳይሆን ለሆዱ እና ያልለፋበትን ገንዘብ ለማግበስበስ የቆመው አጥማቂ ያለ ምንም ርህራሄ አተላ አመጥቶ ወይም አመድ አምጥቶ በሽተኞቹን ይግታቸዋል፡፡ እጅግ በጣም አሳዛኝ ጉዳይ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ የተወለዱ ልጆች አተላ ምን እንደሆነ ስለማያውቁ አንብበው ቢጠይቋችሁ ወላጆች እንድታስረዷቸው በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና እነዚህ አጥማቅያን የኛን የቤተ ክርስትያን ልጆች ሲታመሙ ያለ አንዳች ርህራሄ እንዲህ ዓይነቱን ቆሻሻ ነገር ሲያስግቷቸው በመጀመሪያ ደረጃ ለሌላ በሽታ ያስረክቧቸዋል በመቀጠልም ለሞራል በሽታ አሸጋገሯቸው ማለት ነው፡፡ የሚያሳዝነው ነገር ሰዎቹ አመድ ሲልሱና አተላ ሲጋቱ በቪዲዮ እየተቀረፁ ለአጥማቂው የዘላለም እንጀራ እነርሱ ደግሞ ለዘላለም የሕሊና በሽታ ተሸላልመው መሄዳቸው ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስትያናችን ግን በነጻ የተቀበላችሁትን በነፃ ስጡ ያለውን አምላካዊ ቃልመሠረት በማድረግ ያለ ምንም ዋጋ ለሕሙማን በመጸለይ ከአጋንንት አሥራት ነፃ ታወጣለች፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ከአጭበርባሪ አጥማቂያን ሊጠበቁ ይገባል፡፡ሲታመሙም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደዉ ሊጠመቁ ይገባል፡፡

የጠንቋዮች ጨሌ ወይስ የጸሎት መቁጠሪያ

ይህኛው ጉዳይ እጅግ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በቤተ ክርስትያን አባቶች ዘንድ መቁጠሪያ የሚጠቅመው ለጸሎት እንጂ ጓዳ ውስጥ ሰቅሎ አጋንንትን ያባርራል ብሎ እንደ ጣዖት ለማምለክ አይደለም፡፡ አሁን ያሉት አጥማቂዮች ደግሞ መቁጠሪያ ነው በማለት በኩንታል ሞልተው በገጠሪቷ ኢትየጵያ በመሄድ ይህን በቤታችሁ በጓዳችሁ ውስጥ ከሰቀላችሁ ሰይጣን አይገባም እያሉ በማሞኘት በ3 ብር የሚገዙትን በ50 እና በ70 ብር እየሸጡ ሕዝብን በማታለል እያስጨነቁ ያተራምሳሉ፡፡ ስለ ሃይማኖቱ በጥልቀት የማያውቀውና ያልተረዳው ሰው በየጓዳው በፊት የጠንቋይ ጨሌ ጥሎ የተገላገለው በርሱ ፈንታ መቁጠሪያ በጓዳው ሰቅሎ ከቤተሰቡ አንዱ ሲታመም በታዘዘው መልኩ መቁጠሪያውን ከተሰቀለበት አውርዶ ይገርፍበታል፡፡ ይህ ነው የዘመኑ አጥማቂ ነን ባዮች ሥራ፡፡

እነዚህ አጥማቂዎች የቤተክርስቲያኒቱን ጸበል የማይጠቀሙት ጸበሉ ሲነካቸዉ ራሳቸዉ ስለሚጮሁ ነዉ፡፡ስለዚህ በጀሪካን እያስመጡ በበርሜል በማስሞላት ካልሆነ በቀር ፈጽሞ የቤተክርስቲያኒቱን ጸበል አይጠቀሙም፡፡

  ....... ይቀጥላል

የፎንት ልክ መቀየሪያ