Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፎች

"ወጣት እና ቤተክርስቲያን"

መግቢያ:

ወጣትነት ከሕፃንነት ወደ ዐዋቂነት በሚደረገው ሽግግር ወቅት አንድን ሰው ለዐዋቂነት የሚያሸጋግሩ ስነልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊና አዕምሮአዊ ለውጦች የሚከናዎኑበት ጊዜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመን ከውስጣዊ ፈተና በተጨማሪ ውጫዊ ፈተና የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሻለ የዐዋቂነት ሕይወት ለመምራት አንድ ወጣት እነዚህን ፈተናዎች በአሸናፊነት መወጣት አለበት፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ ወሳኝ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራት እሙን ነው፡፡ በዚህ መልኩ ልጆቿን ኮትኩታ ባሉበት ፈታኝ ዘመን ፈተናውን ተቋቁመው ማለፍ እንዲችሉ ማገዝ ከቻለች ለመንፈሳዊ ክብር ልታበቃቸው ትችላለች፡፡ በምላሹም ከወጣቶች የሚጠበቀውን መጠነ-ሰፊ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡

ወጣትነት

"ወጣት ማለት በሰው ልጅ ሥነ ሕይወታዊ ምዕራፍ አንድን የእድሜ ክልል የሚወክል እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ ማሕበራዊ አቋምና ደረጃ ያለው ነው፡፡ " ማኅበረሰቦች /ሀገራት/ የየራሳቸው ከሆኑ ማኅበራዊ፣ ባሕላዊና ሌሎችም እሴቶች ጋር በተያያዘ ወጣት የሚለውን የዕድሜ ክልል ለያይተውት እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡ የዓለምጤናድርጅት "Adolescent" ማለትከ10-19 ዓመት ዕድሜ ውስጥ የሚገኘውን የሕብረተሰብ ክፍል የሚወክል ሲሆን "Young peo¬ple" ማለትደግሞከ15-24 ዓመት ድረስ ያለውን ይወክላል በማለት አስቀምጧል (Hand book of pediatrics AIDS , 187)፡፡ ወጣቶችን በተመለከተ የተዘጋጁ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ጽሁፎች በኢትዮጵያም ቢሆን ቃሉ የሆነ የዕድሜ ክልልን የሚወክል አድርገው ቢያቀርቡም ቁርጥ ያለ ነገር ለማግኘት ግን አዳጋችነው፡፡ ለምሳሌ፡- ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊስ (National Youth Policy) ወጣትነትን ከ15- 19 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ሲገድበው ከ2ዐዐ6 -2ዐ15 ድረስ እንዲያገለግል ተደርጎ የተዘጋጀው የወጣቶች የሥነ-ተዋልዶ ትግበራዊ ስልት ዶኩሜንት (Ado-lecent & Youth Reproductive Health Strategy) የዕድሜ ክልሉን ሰፋ 1ዐ- 24 ዓመት እንደ ሚያጠቃልል ይጠቁማል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች መተዳዳሪያ ደንብ ላይ እንደተተረጎመው ወጣት ማለት ዕድሜያቸው ከ7 እስከ 30ያሉ ወንዶች እና ሴቶች መሆናቸውን ይጠቅሳል፡ ፡ እንደ 1999 የሕ/ቤ/ቆ መረጃ በኢትዮጵያ ከ10-35 የሚሆነው ወጣት ቁጥር ወደ 35ሚሊዮን አካባቢ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ወደ 16 ሚሊዮን የሚሆኑት የኦርቶዶከስ ተዋህዶ ተከታይ እነደሆኑ ይገመታል፡፡

የወጣትነት መገለጫዎች

ወጣትነት የሚከተሉት አምስት ዓይነት ለውጦች በከፍተኛ ሁኔታ የሚከሰቱበት ጊዜ ነው፡፡ አካላዊ /Physical/፣ ስሜታዊ /Emotional/ ፣ አዕምሮአዊ /Cogni¬tive/ ማለትምእውቀት/Knowledge/ እናጥበብ /Skill/ እንዲሁም መስተጋብራዊ /Relationship/:: ከላይ ከተገለጹት ጋር በተያያዘ ወጣትነት፣ ራስን ለማወቅ የሚደረገው ጥረት ከፍየሚልበት ለችግር ተጋላጭነት የሚጨምርበት አንድን ነገር በማድረግ በሌሎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይት ለማትረፍ የሚሮጥበት እንጂ በሚደረገው ነገር የሚፈጠረው መጥፎ ነገር በውል የማይጤንበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ከፍተኛ ጾታዊ ፍላጎት የሚቀሰቀስበት እና የወጣቶች አዕምሮ የሚባክንበት፤ ለልዩልዩ ሱሶች የሚጋለጡበት በተለይም በአፍላነት ጊዜ ከወላጆች ይልቅ ሌሎችን ማድመጥ ዝንባሌ እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚባልበት ወዘተ...ጊዜነው፡፡ ወጣትነት፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በሌሎች የቤተክርስቲያን ድርሳናት ተዘግቦ እንደምናገኘው በእግዚአብሔር ቤት ውሰጥ ጉልህ ድረሻ ወይም በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲፈጽሙ የነበሩ ወጣቶች ነበሩ፡፡

ለምሳሌ፡-

 • አቤል፡ ወጣቱ አቤል ሕግ ባልተሠራበት ዘመን ‹‹ እግዚአብሔር ንጽሐ ባሕርይ ሰለሆነ ንጹሕ ነገር ይገባዋል›› በማለት ከሚጠብቃቸው በጎች ጠጉሩ ያላረረውን፣ ቀንዱ ያልከረከረውን፣ ጥፈረሩ ያልዘረረዘረውን ንጹሕ በግ በማቅረብ እግዚአብሔር መስዋዕቱን የወደደለት ወጣት ነው፡፡ ይህ የአቤል ሕይወት ዛሬም ወጣቶች ንጽሐ ልቦና ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያስተምር ነው፡፡ (ዘፍ 4)
 • ይስሐቅ፡- ለአባቱ እስከ ሞት ድረስ ታዛዥ የነበረ እና አባቱ እግዚአብሔርን ያገለግል በነበረበት ጊዜ ሁሉ ሙሉ ጉልበቱን እና ሕይወቱን ለዚህ አገልግሎት አሳልፎ የሰጠ ወጣት ነበር፡፡ ይሰሐቅ የወጣትነት ዕድሜው ሳያሳሳው አባቱ ለእግዚአብሔር መስዋዕትነት ሊያርደው ቢለዋ ሲያነሳ ዘመናትን በሚሻገር አስገራሚ ታዛዥነት ራሱን አቅርቧል፡፡(ዘፍ 21)
 • ዮሴፍ፡ የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ግፍን በአኮቴት በመቀበል እና የሥጋ ፍላጎትን በማሸነፍ በቅዱስ መጽሐፍ ከሚታወሱ ወጣቶች አንዱ ነው፡ ፡ በወጣትነቱ በጌታው ግብፃዊው ጴጥፋራ ቤት ሳለ ከጴጥፋራ ሚስት የቀረበለትን የዝሙት ጥያቄ የወጣትነቱ የፍትወት ፍላጎት ሳያሸንፈው ‹‹ሰው ባያይ እግዚአብሔር ያያል›› በማለት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን ከመሥራት የሸሸ፤ ከዚህም የተነሳ የእዚአብሔር ጥሪ እስከሚደርሰው ድረስ መከራን የተቀበለ፤ ዛሬ ድረስ ወጣቶችን ኃጢአትን እንቢ ማለትን ያስተማረ ወጣት ነው፡፡(ዘፍ 39)

ሳሙኤል፡ሕፃኑ በኋላም ነቢዩ ሳሙኤል በደብተራ ኦሪትከ ካህኑ ዔሊ እግር ስር ሆኖ እየተማረ እና እግዚአብሔርን እያገለገለ በተቀደሰ ወጣትነት አድጎ ለነቢይነት የበቃነ በር፡፡ አፍኒንና ፊንሃስ የተባሉት የዔሊ ልጆች ያልተገቡ እና አስነዋሪ ነገሮችን በእግዚአብሔር ቤት እና በእግዚአብሔር ስም እየፈፀሙ ፤እግዚአብሔርንም ሆነ ሕዝበ እስራኤልን ሲያሳዝኑ ብላቴናው ሳሙኤል የአባቱን የዔሊን የአምላኩን የእግዚአብሔርቃል በመስማት ሌሊት ቀን ሳይል ቤተ መቅደስን ሲያገለግል የተገኘ፤ ለነቢዩ ለዔሊ የተሰወረው የእግዚአብሔር ምሥጢር የተገለጸለት ብላቴና ነው፡፡ (ሳሙ 3)

 • ጢሞቴዎስ፡- በክርስትና ጅማሮ ዘመን ከታላላቅ መንፈሳውያን አባቶች ጋር ቤተክርስቲያንን ለማገልገል የወጣትነት ማንነታቸውን ለሐዲስ ኪዳን ዓላማ ካስገዙ ውድ የቤተክርስቲያን ልጆች መካከል ሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተጠቃሽ ነው፡፡በፍጹም እምነትና በቆራጥነት ክርስቶስን ማገልግል ከጀመረ በኋላ ወደ ጥልቅ እውቀት ከመድረሱ በፊት ከአባቱ ከቅዱስ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ትምርህታዊ መልአክቶችን ይቀበል ነበር፡፡ ምንም እንኳን በወጣትነት ዘመን ራስን ለክርስቶስ አሳልፎ መስጠት ታላቅ ክብር ቢሆንም የታላላቅ አባቶች ቡራኬ፣ ምክርና ተግሳጽ አስፈላጊ ስለሆነ ከቅ/ጳውሎስ የሚላክለትን መልዕክት ከልብ በመቀበል ሕይወቱን እና አገልግሎቱን አጎልብቶባቸዋል፡፡
 • ቅዱስ ጊዮርጊስ፡- በዘመነ ሰማዕታ ትጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በጥብዓት እና በጽናት የተጋደለ ሦስት ጊዜ ሞቶ እየተነሣ ያገለገለ እና በሃያዎቹ ውስጥ ለስማዕትነት ተጠርቶ በሃያዎቹ ውስጥ ምድርን በታላቅ መንፈሳዊ ክብር የተሰናበተ ወጣት የክርስቶስ አርበኛ ነው፡፡ቅዱስ ጊዮርጊስበሀብት፣በስልጣን፣በዝሙት በዝና እና በሌሎችም ከባድ ፈተናዎችን ያለፈ ታላቅ የክርስቲያናዊ ወጣትነት ሕይወት ምስክር ነው፡፡

እነዚህ ወጣቶች ከላይ የዘረዘርናቸው እና በወጣትነት የማይቀሩ ተፈጥሮአዊ ለውጦች በእነርሱ ዘንድ ስላልነበሩ ሳይሆን በፈቃደ እግዚአብሔር፣ በራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ጥረት ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው ማስገዛት በመቻላቸው ነበር፡፡

ወጣቶች በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የወጣቶች ተሳትፎ ከጥንት ጀምሮ የታወቀና የተከበረ ነው፡፡ በአብነት ት/ቤቶች ወጣቱን ፊደል ከማስቆጠር ጀምራ ጥልቅ እውቀትን በማስጨበጥ አብዛኛውን ለዲቁና እና ከዕድሜ ብስለት ጋርም ለከፍተኛ መዓረገ- ክህነት በማብቃት አገልግሎት እንዲፈፅሙ ስታደረግ ኑራለች፡፡ እያደረገችም ነው፡፡ ከመካከላቸውም ራሳቸውን ከጣዕመ ዓለም በመለየት በድንግልና ሕይወት እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ የኖሩ እና እያገለገሉ ያሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ካሳለፍነው ክ/ዘመን አጋማሽ ጀምሮም የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋትን ተከትሎ የሰንበትት/ ቤቶች እየተጠናከሩ በመምጣታቸው፤ ቤተክርስቲያን የወጣቶችን አገልግሎት ተቋማዊ ይሆን ዘንድ በቃለ አዋዲ በማካተት እና አስተባባሪ መምሪያ በማቋቋም የሰንበትት/ቤቶችን አገልግሎት ሥርዓት በማስያዝ ወጣቶች ሰፊ አገልግሎት እንዲያበረክቱ ለማድረግ እየጣረች ነው፡፡በተጨማሪም በራሳቸው ፈቃድ በማኅበር ተደራጅተው ቤተክርስቲያንን እናገለገግለላለን የሚሉትን በሙሉ በሆደ ሰፊነት እና በአርቆ አሳቢነት እየተቀበለች እያስተናገደች ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሥነ መለኮት ትምህርትን በዘመናዊ መልክ ለማስተማር መንፈሳዊ ኮሌጅችን በመክፈት የወጣቶች አገልግሎት ስፋት እንዲኖረው እያደረገች ነው፡፡

በወጣቶች አገልግሎት ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶች

ከላይ የተዘረዘሩት የወጣቶችና የቤተክርስቲያን ግንኙነትን የሚያጎሉ ልዩልዩ የአገልግሎት መስኮች በአብዛኛው መሬት የያዙ እንደሆነ ቢታመንም ግንኙነቶቹ በሙሉ ያለ አንዳች ችግር የሚጓዙ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡በዚህ በወጣቶች የቤተክርስቲያን አገልግሎት ዙሪያ ከሚታዩት ችግሮች መካከል

 • የአብነትት/ቤቶቻችን የዘመኑን ወጣት ሁኔታ ባገናዘበ ሁኔታ ባለመደራጀታቸው የተነሳ ወጣቱን ወደ እነርሱ መሳብ ካለመቻላቸው የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጉባኤው እየተፈታ፤ ትምህርቱን የጀመሩትም ያለበቂ እውቀት ወደ ከተማ እየፈለሱ ከሚጠበቅባቸው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ውጭ በሆነ ሕይወት ውስጥ መውደቃቸው፤ የቀሩትም ደግሞ ካለባቸው የኑሮ እና የክትትል ችግር የተነሳ ለመናፍቃኑ ሴራ የተጋለጡ መሆናቸው፤
 • በሰንበትት/ቤቶችም ወጣቶችን በዕድሜ እና በዕውቀት መጠን ከፋፍሎ በአግባቡ በትምህርተ ሃይማኖት፣ በክርስቲያናዊ ሕይወት እና በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ተኮትክተው እንዲያድጉ የሚያስችላቸው ሥርዓተ ትምህርት የሌላቸው መሆኑ፤ ከላይኛው የቤተክርስቲያኗ አካል እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ በተለያዩ የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ደረጃ ላይ ያሉ የቤክርስቲያን አገልግሎት የሰንበት ት/ቤቶችን አገልግሎት እና አስፈላጊነት በአግባቡ አለመገንዘብ፤ እንዲሁም ሰንበት ት/ቤቶችን እንዲያስተባብር የተሰየመው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በቂ የሆነ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል እና በጀት የሌለው መሆኑ፤
 • በፈቃዳቸው በተለያዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ለመሰማራት በማኅበራት የሚሰባሰበውን ወጣት በአግባቡ የሚመራ እና ፈቃዳቸውን እና መሰባሰባቸውን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት በሚመች መልኩ የሚያስተባብር አካል ባለመኖሩ አብዛኛዎቸው የወጣቶች ስብስብ ለመናፍቃን መሳሪያነት ሲውሉ፣ የቀሩት ከወጣትነት በሚመነጭ ስሜታዊነት የተነሳ ወደ ግጭት እና መለያየት በድረስ መበታተናቸው፤ ሌሎቹም ሊሠሩት የሚገባቸውን በትክክልለይቶካለማወቅ እና ባልተሰጣቸውውክልናምውስጥ መግባት፤
 • በመንፈሳዊ ኮሌጆች በመግባት በሥነ መለኮት ትምህርት ተሳታፊ እየሆኑ ያሉት ወጣቶችም ቀዳሚ ትኩረታቸው ትምህርቱን በጥልቀት ተረድቶ ወቅቱ የሚፈልገውን አስተምህሮ በቤተክርስቲያኒቷ ከማስፈን ይልቅ የዕለት ኑሮን ከማደላደል ላይ በማተኮሩ ላልተገቡ ልዩ ልዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸው፤ የመንፈሳዊ ኮሌጆቹም ቢሆኑ በበቂ ሁኔታ ተደራጅተው የተማሪዉን ሥነ-ልቦና አቅንተው ማውጣት አለመቻላቸው፤

ሊስተዋሉ እና አፋጣኝ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው በወጣቱ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡

ወጣትነትና ፈተናዎቹ

ወጣቱ ከላይ የጠቃቀስናቸው ከዕድሜ ጋር የተያያዙ / developmetally inevitable/ አንደኛደረጃ /Primary/ ውስጣዊ ጠባያት እንዳሉት ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ጠባያት ግን በራሳቸ ውፈተናዎች አይደሉም ወይም የፈተናዎች መገለጫዎች አይደሉም፤ እንዲያውም በአግባቡ ከተስተናገዱ ትርጉም ያለው ሥራ ለመሥራት የሚያስችሉ የፈጣሪ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ወጣቱን ስናስብም ሆነ ስለ ወጣቱ ስንናገር እነዚህን ሳይፈልጋቸው ሊከሰቱ የሚችሉ ጠባያቱን ልንረዳለት ያስፈልጋል፡፡ እርግጥ ነው እነዚህ ውስጣዊ ጠባያት ተገቢውን ትኩረት አግኝተው ፣በአግባቡ ተገርተው ለጥቅም ካልዋሉ ከዚህ በታች ከምንዘረዝራቸውና ፈተናዎች ብለን ከምንጠራቸው ማኅበራዊ እና ሉላዊ ክስተቶች ጋር ተዳምረው ራሱን ወጣቱን፣ ያስገኘውን ማኅበረሰብ እንዲሁም ቤተክርስቲያንን እና ሀገርን ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ፈተናዎች ምንድን ናቸው?

የኢኮኖሚ ችግር /ECONOMICAL PROBLEM/

አብዛኞቹ ምሁራን ዋነኛው የዘመናችንም ሆነ የነገው ወጣቶች ችግር ሥራ አጥነት እንደሆነ /እንደሚሆን ያስረዳሉ፡፡ በሀገራችን ብዙው ወጣት ገና በትምህርት ላይ አለዚያም በቤተሰቦቹ ኃላፊነትሥር ያለ ነው፡፡ይሁን እንጂ የሥራ አጡ መብዛት እና መንገላታት በራሱ ላይ ከሚፈጠረው ችግር በተጨማሪ እርሱን እንደ ምሳሌ አድርጎ ለሚያየውና ገና በትምህርት ላይ ለሚገኘው ወጣት የሥነ ልቡና ችግር እንደሚፈጠርበት እሙን ነው፡፡ ሥራ አጥነት በከተማ ብቻ የሚወሰን አይደለም ፤ገጠሬውንም ይመለከታል፡፡ ስራ አጥነት ለከፋ ድሕነትይዳርጋል፡፡ተስፋ መቁረጥንያስከትላል፡፡ተስፋ የቆረጠት ውልድ ለአንዲት ቤተክርስቲያን ሕልውና አደጋ ነው፤ተስፋ መቁረጥ ሚዛናዊነትን እና ስብዕናን ያሳጣል፡፡ ቀዬንና ሀገርን ትቶ ያሰድዳል፡፡ ራስን ለክፋየሥነ ምግባር ግድፈት አሳልፎ እንዲሰጥ ያስገድዳል፡፡ ብዙዎች ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ብቻ ሲጋራ የሚያጨሱ፣ ጫት የሚቅሙና እንደ ሄሮይን የመሳሰሉ አደንዛዥ ዕፆችን የሚጠቀሙ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በሰፊው እየተገነረ ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተደረገ አንድ ጥናትበአዲስ አበባ ውስጥ ካሉ ወጣቶች ወደ 2ዐ% ያህሉ እንደ ሚያጨሱ ያሳያል፡፡ በፆታ ደረጃ ስንመለከትም በአሁኑ ሰዓት የሴት ሥራ አጦች ቁጥር የወንዶችን ሦስት እጥፍ ሊያክል አንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የአብዛኞቹ የሴት ሥራ አጦች የተሻለ አማራጭ ሆኖ የሚወሰደው የወሲብ ንግድ /Sex trading/ እና ሴተኛ አዳሪነት ናቸው፡፡ይህም ደግሞ በራሱ እንደ HIV/AIDS ላሉ የአባለዘር በሽታዎች ከማጋለጡም በተጨማሪ የአንድን ማኅበረሰብ ሞራላዊ ክብርን የሚያኮስስ ተግባር ይሆናል፡፡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ለኢኮኖሚ ችግር እንደ መንስዔ ከሚቆጥሯቸው ነገሮች መካከል ወጣቶች አግባብ ያለው ትምህርት እና ስልጠና ያለማግኘት፣ የሥራ ባሕል በወጣቱ ባሕላዊና ስነ ልቦናዊ ይዘት አለመዳበር እና የመሳሰሉት እንደሚገኙበት ይጠቁማሉ፡፡በእንደዚህ አስከፊ የሆነ የኢኮኖሚ ቸግር ውስጥ የሚያልፉ ወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወታቸው በአግባቡ ለመምራት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገባሉ፡፡

ሉላዊነት /GLOBALIZATION/

ሉላዊነት ማለት ባንድ የዓለም ክፍል የተከናወኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አካባቢያዊና ባሕላዊ ክስቶች በሌላው የዓለም ክፍል አፋጣኝ የሆነ ተጽዕኖ ማሳደር በሚችሉበት መልኩ መስተጋብራዊ ስልጠትን በማምጣት የአንድ ሉላዊማ ኅበረሰብ መፍጠር ማለት ነው፡፡ ሉላዊነት የመገናኛ፣ የመጓጓዣ ዘዴዎች እና የመረጃ ልውውጥ መንገዶች እጅግ እየተሻሻሉ የመምጣታቸው ውጤት ነው፡፡ የአንድ ሀገር ዜጋ መሆን ሁሌም የማይቀር ቢሆንም በዚሁ አገር የሚኖሩ ሰዎች በዘመነ ሉላዊነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በሌሎች ሀገሮች ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የሚጋሯቸው ባሕላዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ-ልቦናዊ እሴቶች ይኖራሉ፡፡ በሉላዊነት በጎም ሆነ ክፉ ተግባራት በፍጥነት ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ይዛመታሉ፡፡ በሉላዊነ ትድርጊቶች ብቻ ሳይሆኑ አስተሳሰቦች እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ድንበርን ይሻገራሉ፡፡ ዛሬ እጅግ ብዙና የተለያዩ ጽሁፎችን ከኢንተርኔት እንደልብ ማግኘት ይቻላል፡፡ሌላው ቀርቶ ትላልቅ መጽሐፎችንም በነጻም ሆነ በገንዘብ ከኢንተርኔት ማግኘት ይቻላል፡፡ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመዲናችን አዲስአበባ እንዳሸን ፈልተው የምናያቸው ከሌሎች ቋንቋዎች የተተረጎሙ መጽሕፍት የተገኙት ከኢንተርኔት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ በራሳቸው በወጣቱ ሃይማኖታዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር እንደ ድርጊቶች እና አስተሳሰቦች ሁሉ ሃይማኖታዊ አስተምህሮም የሉላዊነት ተጽዕኖ ያርፍበታል፡፡ ሉላዊነት በሃይማኖት ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ምሁራን በሦሰት መንገድ ይከፍሉታል፡፡ የሉላዊነትተጽዕኖ እየገፋ ሲመጣ፡-

 • እያንዳንዱ ሃይማኖት የራሱ የሆነድርጅታዊ ለውጥ እንዲያደርግ ውስጣዊ ግፊት ይኖርበታል፡፡
 • የዶክትሪኖች፣ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ወዘተ ለውጦች የመኖራቸው ዕድል በጣም ይሰፋል፡፡
 • በተከታዮች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጦች እጨመሩ ይመጣሉ፡፡

እነዚህ ሃይማኖታዊ ክስተቶች አሁን በጉልህ ባይታዩም ለወደፊቱ ግን አይቀሬዎች እንደሆኑ ይነገራል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ የነገው ወጣት ፈልጎም ሆነ ሳይፈልግ ከእነዚህ ለውጦች ጋር መጋፈጡ የግድ ይሆናል፡፡

ዘረኝነት/ጎሰኝነት/ ዘውጌነት /ETHNOCENTERISM/

በመሠረቱ የዘረኝነትን ምንነት በትክክል መናገር የሚቻል እንዳልሆነ ምሁራን ይስማማሉ፡፡ በአማርኛ ዘር፣ ጎሳ የሚባሉትን ቃላት ለመለየት አስቸጋሪ የመሆኑን ያክል ብዙ ሰዎች እየቀላቀሉ ሲጠቀሙባቸው ይታያል፡፡ጎሳ የሚለው ቃል/Ethnicity/ የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ይወክል ይሆናል፡፡ የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁራን የሆኑት እንደ ፍሬድሪክ ባርዝ እና ኤሪክ ወልፍ የጎሳ ጉዳይ ዓለምዓቀፋዊ እንዳልሆነ ያስተምራሉ፡፡ጎሳ ዘላለማዊ ወይም ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ውሱን የሆኑ ማኅበራዊ መስተጋብሮች በሂደት የፈጠሩት ክስተ ትነው፡፡ጎሳ /ዘር/ እና ቋንቋም እንዲሁ ዘላለማዊ ውሕድና የላቸውም፡፡ቋንቋ የሚለምዱት ካልተጠቀሙበት ደግሞ የሚረሱት ነው፡፡ ስለዚህ ቋንቋ የጎሳ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ በጥቅሉ ከሁሉም በላይ ሰው መሆን ይበልጣል፡፡ በሃይማኖት ትምህርትም ቢሆንም ሰው ሲፈጠር ጎሳ አልነበረውም፣ ምናባልትም የአንድ ቋንቋ ብቻ ባለቤት ነበር፡፡ ሰውን የፈጠረ እና ያዳነ እግዚአብሔር ቅድሚያ የሚሰጠው ቋንቋም ሆነ ጎሳ የለም፡፡ቤተክርስቲያንም እንዲሁ፡ ፡ሃይማኖት ከጎሳም፣ ከቋንቋም በፊት የነበረ ነውና፡፡

እውነታው ታዲያ እንዲህ ሆኖ እያለ በእኛው በራሳችን፣ በክርስቲያኖች ውስጥ ከሃይማኖት አንድነት ይልቅ ለጎሳ አንድነት ብልጫ መስጠት እየገነነ መጥቷል፡፡ የነገው ኢትዮጵያዊ ወጣት ጎሰኛነት የበለጠ ያሰጋዋል፡፡ምክንያቱም ጎሰኛነት ከውጫዊ መገለጫነቱ ይልቅ የውስጣዊ ማንነት ማዕከል እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል፡፡ ጎሰኛነት ፀረ-ፍቅር ነው፤ ምክንያቱም ፍቅር ስፉህ እና ወሰን የለሽ ነው፡፡ ቋንቋ ከመግባቢያነት የዘለለ መንፈሳዊ ወይም መለኮታዊ ዋጋ የለውም፡፡ ጎሰኛነት ከነገሠ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳቸው በተቀደሰው ቦታ ርኩሰትን ሊፈጽሙ ይችላሉ፣በጎሳ ልዩነት በተነሳ ጥል በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከመፈነካከት የበለጠ በደል የታለና! የነገው ወጣት እንዲህ ባለና ስር በሰደደ ጎሰኝነት መፈተኑ አይቀርም፡፡

ከዚህ በላይ በመጠኑም ቢሆን የዳሰስናቸው በዛሬውም ሆነ በነገው ወጣትፊት የተጋረጡ ዋና ዋና ፈተናዎች ናቸው፡፡ ለነዚህ ፈተናዎች ከዚህ የዳሰሳ ጥናት ከፍ ባለ ሁኔታ ጥናት አድርጎ ምላሽ መስጠት የቤተክርስቲያን ለሆነ ሁሉ የቤት ሥራው ነው፡፡

ፈተናዎችን መቋቋሚያ መንገዶች

መቋቋሚያ ያልነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ መከላከያ እንዳንል ፈተናዎቹ አሁንም እየታዩ እና ለወደፊቱም በሚያሰጋ መልኩ መቀጠላቸው ፈጽሞ አይቀሬ በመሆኑ ነው፡፡ስለዚህ የማይቀሩ ከሆነ በአግባቡ መጋፈጥ እና የሚያስከትሉትን ጉዳት መቀነስ /Minimiz¬ing the Damage/ ላይ ማተኮር ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት /Stakeholders/ በጋራም ይሁን በተናጠል ሊያከናውኗቸው የሚገቡ ተግባራት ይኖራሉ፡፡ ዋና ዋናዎቹ ባለ ድርሻ አካላት የምንላቸው አገራዊ ተቋማት ሲሆኑ እንደ አስፈላጊነቱ ድንበር ዘለል የሆኑ የተራ ድኦድርጅቶችን እገዛሊ ጠይቁ ይችላሉ፡፡ እነዚህ አገራዊ ተቋማት የምንላቸው ቤተሰብ፣ማኅበረሰብ፣መንግሥት እና ዋናዋ ባለ ጉዳይ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡

ቤተሰብ /FAMILY/

የአንድ ልጅ የመጀመሪያ ት/ቤት የሚያድግበት ቤቱ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ አስተማሪዎችም ወላጆቹ /አሳዳጊዎቹ/ ናቸው፡፡ ወላጆቹ መጭውን ጊዜና ገፀበረከቱን እንዲሁም መርገሙን በሚገባ ተገንዝበው ልጆቻቸውን በአዕምሮም ሆነ በመንፈስ በልጽገው

ጥናታዊ ጽሑፎች

ፈተናዎችን መቋቋሚያ መንገዶች

መቋቋሚያ ያልነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ መከላከያ እንዳንል ፈተናዎቹ አሁንም እየታዩ እና ለወደፊቱም በሚያሰጋ መልኩ መቀጠላቸው ፈጽሞ አይቀሬ በመሆኑ ነው፡፡ስለዚህ የማይቀሩ ከሆነ በአግባቡ መጋፈጥ እና የሚያስከትሉትን ጉዳት መቀነስ /Minimiz¬ing the Damage/ ላይ ማተኮር ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት /Stakeholders/ በጋራም ይሁን በተናጠል ሊያከናውኗቸው የሚገቡ ተግባራት ይኖራሉ፡፡ ዋና ዋናዎቹ ባለ ድርሻ አካላት የምንላቸው አገራዊ ተቋማት ሲሆኑ እንደ አስፈላጊነቱ ድንበር ዘለል የሆኑ የተራ ድኦድርጅቶችን እገዛሊ ጠይቁ ይችላሉ፡፡ እነዚህ አገራዊ ተቋማት የምንላቸው ቤተሰብ፣ማኅበረሰብ፣መንግሥት እና ዋናዋ ባለ ጉዳይ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡

ቤተሰብ /FAMILY/

የአንድ ልጅ የመጀመሪያ ት/ቤት የሚያድግበት ቤቱ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ አስተማሪዎችም ወላጆቹ /አሳዳጊዎቹ/ ናቸው፡፡ ወላጆቹ መጭውን ጊዜና ገፀበረከቱን እንዲሁም መርገሙን በሚገባ ተገንዝበው ልጆቻቸውን በአዕምሮም ሆነ በመንፈስ በልጽገው ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው ፣ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ሆነው እንዲያድጉ መሰረታዊ ሥራ መሥራት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን እንደ ሚወዷቸው ሁሉ ትዕግስታቸው ሰፊ ሆኖ ማናቸውንም ነገር በድፍረት እና በግልፅ ለመወያየት የሚያስችል ከባቢ እና ሀገርን ወዳድ ሆነው እንዲያድጉ ማገዝ አለባቸው፡፡

ማኅበረሰብ /COMMUNITY/

የብዙ ቤተሰቦች ድምር ማኅበረሰብ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ወላጅ የራሱን ልጅ ከማንኛውም ነገር አብልጦ የሚወድ ቢሆንም ልጁ ብቻውን ሊኖር እንደማይችል በማወቅ ለራሱ ልጅ ሲል እንኳን ለሌላ ውል ጅማ ሰብይገባዋል፡፡ ሲሆን እንደ ክርስቲያን የሌላው ሕመም የኔነው በሚል መንፈሳዊ አስተሳሰብ የአንድን ማኅበረሰብ ልጆች በእግዚአብሔርና በሰው ፊት በጥበብ እና በሞገስ ማደግ እንዲችሉ በጋራ መምከር ያስፈልጋል፡፡ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ሥራ አጥ ወጣቶች በወጣት አጥፊነት ወይም ወንጀለኝነት ሲሰማሩ እየታየ ማኅበረሰቡ ችላ ማለት የለበትም፡፡

መንግስት/GOVERNMENT/

የነገው ወጣት በበጎ ሥነ-ምግባርና በሀገር ወዳድነት ማደግ እንዲችል በሥራ ላይም ሲሰማራ በሙሉ ኃይሉ፣ በኃላፊነት፣በተቆርቋሪነትና በቅንነት መሥራት እንዲችል መንግሥት በአግባቡ መሥራት ይኖርበታል፡ ፡የመንግሥት ፖሊሲዎች እና ፖሊሲዎቹን የሚያስፈጽምበት መንገድ ለሁለንተናዊ ጥቅም ይሆን ዘንድ መታሰብ አለበት፡፡

ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያን ምናልባት ከሁሉ የበለጠ ኃላፊነት ይኖርባታል፡፡ከላይ የዘረዘርናቸው አካላት ሁሉ የየራሳቸው ኃላፊነትና ድርሻ ቢኖራቸውም እንደዋንኛ የጉዳዩ ባለቤት እነዚህን አካላት በማስተባበር እና በመምራት ደረጃ ከፍተኛው ድርሻ የሚጠበቀው ከቤተክርስቲያን ነው፡፡ ለመሆኑ ቤተክርስቲያን ለነገው ለወጣቱ ምን ልታደረግ ይገባታል?

በትምህርት ማነፅ

ትምህርት የሰው ልጅ ለመኖር ሲታገል በሂደት የፈጠረው ኑሮን ማቃለያ መንገድ ነው/Incarta 2007/፡፡ትምህርት የሰውን ልጅ የእውቀት፣ የክህሎት እና የአመለካከት ለውጥ የሚያገኝበት መንገድ ነው፡፡ ይህ እድገት በአዕምሮም ሆነ በመንፈስ ተስተካክሎ ያድግ ዘንድ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ኃላፊነት አለባት፡፡ ቤተክርስቲያን ወጣቶችን በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ ሆነው ለቤተ ክህነትም ሆነ ለቤተ መንግሥት አገልግሎት ብቁ የሆኑ ዜጎች ለማድረግ ልትሠራ ይገባታል፡ ፡ ከዚህ አንጻር ቤተክርስቲያን ለሰ/ት/ቤቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ይጠበቅባታል፡፡ሰ/ት/ቤቶች እንደ ሕፃናት መዋያዎች እና እንደ ሥራ ፈቶች መሰባሰቢያ መቆጠር የለባቸውም፡፡ነገረ ሃይማኖትን፣ ምግባርን እና ሥርዓትን ያዋሀደ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆላቸው ትምህርት ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ ማመቻቸት አለባት፡፡ወጣቱ ሉላዊነት በፈጠረው ፈጣን መረጃ ልውውጥ የተነሳ በቀን ለ24 ሰዓታት፣ በሳምንት ለሰባት ቀናት ያለማቋረጥ የሚዘራበትን የዓለማዊነት ጥፋት መቋቋም የሚችልበት መንፈሳዊ ብስለት ላይ የሚያደርሰውን ትምህርት ከቤተክርስቲያን ሊያገኝ ይገባል፡፡

የወጣቱን የኢኮኖሚ አቅም ለማጠንከር መሥራት

ወጣቱን ዋልጌ፣ ሥራ-ፈት፣ ቦዘኔ፣ እያሉ ፈታኝ እና ልብ አድሚ የሆኑ ቃላትን እየወረወሩ ሥነ-ልቦናውን ከመጉዳት ይልቅ ከማስተማሩ ጎን ለጎን የኢኮኖሚ ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ለመቀየስ ካሁኑ መጣር የተሻለ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሀገራዊ ጠቀሜታ ባላቸው የኢንቨስትመንት መስኮች መሳተፍ ትችላለች፡፡ የእነዚህ መስኮች መስፋፋት የሥራ እድሎችን ይከፍታል፡፡ ያላትን በልዩ ልዩ ሙያ የሰለጠነ የተማረ ኃይሏን በመጠቀም ልዩ ልዩ ኘሮችጀክቶችን መንደፍ ትችላለች፡፡ ጃንጥላ ዘቅዝቆ ለምኖ ቤተክርስቲያን ከመሥራት ይልቅ እንደምንም ብሎ አንድመለስተኛ ኢንዱስትሪ ማቋቋም ቢቻል የቤተክርስቲያንንም ሆነ የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ችግር መቅረፍ ይቻላል፡፡ ለዛሬውም ሆነ ለነገውወጣት ሁኔታዎችን ብናዘጋጀለት ውጤታማ እንሆናለን፡፡

ፖሊሲ መቅረጽ

የወጣቶችን አጠቃላይ አያያዝ በተመለከተ ቅድስት ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ ፖሊሲ እና እስትራቴጂ ያስፈልጋታል፡፡ ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው ፣ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ሆነው እንዲያድጉ መሰረታዊ ሥራ መሥራት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን እንደ ሚወዷቸው ሁሉ ትዕግስታቸው ሰፊ ሆኖ ማናቸውንም ነገር በድፍረት እና በግልፅ ለመወያየት የሚያስችል ከባቢ እና ሀገርን ወዳድ ሆነው እንዲያድጉ ማገዝ አለባቸው፡፡

ማኅበረሰብ /COMMUNITY/

የብዙ ቤተሰቦች ድምር ማኅበረሰብ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ወላጅ የራሱን ልጅ ከማንኛውም ነገር አብልጦ የሚወድ ቢሆንም ልጁ ብቻውን ሊኖር እንደማይችል በማወቅ ለራሱ ልጅ ሲል እንኳን ለሌላ ውል ጅማ ሰብይገባዋል፡፡ ሲሆን እንደ ክርስቲያን የሌላው ሕመም የኔነው በሚል መንፈሳዊ አስተሳሰብ የአንድን ማኅበረሰብ ልጆች በእግዚአብሔርና በሰው ፊት በጥበብ እና በሞገስ ማደግ እንዲችሉ በጋራ መምከር ያስፈልጋል፡፡ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ሥራ አጥ ወጣቶች በወጣት አጥፊነት ወይም ወንጀለኝነት ሲሰማሩ እየታየ ማኅበረሰቡ ችላ ማለት የለበትም፡፡

መንግስት/GOVERNMENT/

የነገው ወጣት በበጎ ሥነ-ምግባርና በሀገር ወዳድነት ማደግ እንዲችል በሥራ ላይም ሲሰማራ በሙሉ ኃይሉ፣ በኃላፊነት፣በተቆርቋሪነትና በቅንነት መሥራት እንዲችል መንግሥት በአግባቡ መሥራት ይኖርበታል፡፡የመንግሥት ፖሊሲዎች እና ፖሊሲዎቹን የሚያስፈጽምበት መንገድ ለሁለንተናዊ ጥቅም ይሆን ዘንድ መታሰብ አለበት፡፡

ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያን ምናልባት ከሁሉ የበለጠ ኃላፊነት ይኖርባታል፡፡ከላይ የዘረዘርናቸው አካላት ሁሉ የየራሳቸው ኃላፊነትና ድርሻ ቢኖራቸውም እንደዋንኛ የጉዳዩ ባለቤት እነዚህን አካላት በማስተባበር እና በመምራት ደረጃ ከፍተኛው ድርሻ የሚጠበቀው ከቤተክርስቲያን ነው፡፡ ለመሆኑ ቤተክርስቲያን ለነገው ለወጣቱ ምን ልታደረግ ይገባታል?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ