Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት በሀዲያ ዞን ቤተክርስቲያን በመሥራት ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያላትን መንፈሳዊ የምስጢር ጥልቀትና ምጥቀት በአግባቡ ጠብቃ ለማቆየት አልፎም ለትውልድ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ካቋቋመቻቸው ተቋማት አንዱ ሰንበት ት/ቤት ነው፡፡ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና የወጣቶች መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወት የሚታነጽበት፣ መንፈሳዊ ዕውቀት የሚፈስበትና የሚገበይበት፣ የበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚከወንበት፣ በሃይማኖት የሚጸኑበት፣ በምግባር በትሩፋት ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉበት ተቋም ነው፡፡ ሰንበት ት/ቤቶች ይህንን በሕግ በቃለ ዓዋዲ የተሰጣቸውን የአገልግሎት ተልዕኮ በመላ ሀገሪቱ ወጥ በሆነ ሥርዓት ለመፈጸም ይቻል ዘንድም መሪ ዕቅድ አዘጋጅተው ከሀገር አቀፍ እስከ ወረዳ አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች የአንድነት አደረጃጀትን ዘርግተው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ ሆኖ እያለ ሰ/ት/ቤቶች በደብራቸው ከሚያበረክቱት አገልግሎትና በአካባቢያቸው ከሚያከናውኑት የበጎ አድራጎት ምግባረ ሠናይ በተጨማሪ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰ/ት/ቤት ከአዲስ አበባ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ወዳለችው እና በአጽራረ ቤተክርስቲያን ወደ ተዳከመችው ገጠር ቤተ ክርስቲያን ተጉዘው የፈጸሙት ተምሳሌታዊ ተልዕኮ ለሁሉም ምሳሌ ይሆን ዘንድ በአጭሩ ለማቅረብ ተገደድን፡፡

በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን በጊቤ ወረዳ አሞጨራ ቀበሌ ወደ ሚገኘው የአጀጊዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአካባቢው ታሪክ በሚያውቅ አንድ ወጣት አሳሳቢነት የሰ/ት/ቤቱ ወጣቶች የጉዞ መርሐ ግብር አዘጋጅተው ሲሄዱ ቤተ ክርስቲያኑ

የፈራረሰ ከመሆኑም በላይ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ርቀት አዳራሽና ማታሊያ በመስጠት ምዕመናን በመንጠቅ አማኝ ያሳጡት ቤተክርስቲያን ሆኖ በአይናቸው አይተው ካረጋገጡ በኋላ ያላቸው ይዘውና ደጋግ ምዕመናንን አስተባብረው ቤተክርስቲያኑ በፎቶው በምታዩት መልኩ ሠርተው አጠናቅቀዋል፡፡
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰ/ት/ቤት ከዚህ ጎን ለጎንም በመናፍቃን ተወረው በቁጥር ሃያ ብቻ ቀርተው የሚገኙ የአጥቢያው ምዕመናን ለማጠናከር የተታለሉትን ለመመለስ ሰፊ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብሮች ከማካሄዳቸው በላይ የሕፃናትና የወጣቶች ሕይወት በመንፈሳዊ ትምህርት የሚታነጽበትን ሰንበት ት/ቤትን አቋቁመው ሕፃናትና ወጣቶች አገልግሎት እንዲጀምሩ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ይህ የሰንበት ት/ቤቱ መልካም አገልግሎት ማለትም ቤተክርስቲያኑን ጨርሶ ቅዳሴ ቤቱ ለማክበር በሚደረጉት ጥረት በአቅም እጥረት ምክንያት መዘግየቱንና ይህንን የምናነብና በአይናችንም /በፎቶ/ የምናይ ምዕመናን እንድናግዛቸውም አደራ ጭምር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ