Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የወጣቱና የኖላዊ ግንኙነት

በብፁዕ አቡነ ዳንኤልለሰ/ትቤቶች የሥራ ሃላፊዎች 1999 ዓ.ም የወጣትና የኖላዊ ግንኙነት ከሚል የሥልጠና ጽሑፍ የተወሰደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምን ይመስላል የሚል ሲሆን፡-

ይህንን ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል& ምሳሌውም የአብርሃም እና የካህኑ የመልከ ጼዴቅ የመጀመሪያው ግንኙነትን የሚመስልና የነዚህን ፈለግ መከተል ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲታወቅ በዘፍ. 14፡18 ያለውን ቃል መጥቀስ እንችላለን፡፡ መልከ ጼዴቅም አብርሃምን ሲገናኘው እንጀራን እና የወይን ጠጅን ይዞ ተቀበለው እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ ስለዚህም አብርሃምን ባርከውም አለውም አብርሃም ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው ጠላቶችህንም በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው ብሎ ባረከውና ተገናኘው፡፡ ስለዚህ ካህኑ ወጣቱን ሰላም ሲለውና ሲገናኘው ፊቱን በማጥቆርና በማስደንገጥ መልክ ሳይሆን ፈገግ ባለና መቅረብ በሚቻልበት መልክ መሆን አለበት እንላለን፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የሁለቱ አበው ግንኙነት ለካህኑና ለወጣቱ መልካም ምሳሌና አርአያ ሲሆን ይገባል ስትል ቤተ ክርስቲያን ስታስተምር ኖራለች፣ አሁንም በማስተማር ላይ ናት ማለት ነው፡፡ ካህኑ እንደ መልከ ጼዴቅ የሰላም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆኑ የአባቶች አለቃ የሆነውን አብርሃምን የባረከ አሥራት በŸCራት የተቀበለ ሰው ነውና ምሳሌ ቢያስፈልግ እብራውያን ምዕ. 7. ቁ. 1-3 ያለውን ማንበብ ይቻላል፡፡ ካህን ከሰዎች ሁሉ ይመረጣል (መሀል) እሱም የሚመረጠው መስዋዕት ለማቅረብና ኃጢአትን ለማስተስረይ ነው እና ለራሱም ለሌላውም ያስተሰርያል ማለት ነው፡፡

ከዚህ በመቀጠል ዘሌዋውያን 9፡17-16 ያለውን ብንመለከት ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአትህን መሥዋዕት ሠዋ ለራስህና ለሕዝብህም አስተሰርይ እግዚአብሔርም እንዳዘዘህ የሕዝቡን ቁርባን አቅርብ አስተሰርይላቸውም አለው ካህኑ ይሄንን ያህል ከፍ ያለና የላቀ ሥልጣን ከእግዚአብሔር የተሰጠው ስለሆነ ከዚህ የበለጠ ሥልጣንና ኃላፊነት ምን ይኖራልና ነው፡፡

ካህኑንና ወጣቱ የሚራራቁበት ምንም ምክንያት የለም እንዲያውም ከጠዋቱ ጀምሮ መቀራረብና መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ከላይ የተጠቀሱት ምላሴዎች በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

ካህን ማለት በመሠረቱ ቢከራከሩ እውነት የሚፈርድ ቢጣሉ የሚያስታርቅ ማለትም እንደ መልከ ጼዴቅ ያለ የዘመናችን ካህን ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያለውም ካህን አሁን ባለንበት ዘመን ለወጣቱ ትውልድ ስለ እርሱ ፃድቅና የሰላም ሰው ነበርና የዚህ ምሳሌ የሆነውንም ካህን ማክበር ያስፈልጋል፡፡

የመልከ ጼዴቅ ክህነት ለወልደ እግዚአብሔር ክህነት በምሳሌነት ፀንቶ በምሳሌነት ይኖራል፡፡ ጌታ መልከ ጼዴቅን በምን ይመስለዋልና እንዲህ አለ ቢባል መልከ ጼዴቅ በስንዴና በወይን ያስታኩት እንደነበረ እሱም ሥጋውንና ደሙን በስንዴና በወይን ሰጥቶናልና መልከ ጼዴቅ ሹመቱን ከእገሌ ተሾመው አይባልም ከእግዚአብሔር ተሹሞታል እንጂ የካህኑ ሹመት ግን እንደ ሐዋርያት ሥርዓት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ስለሆነ ከሊቀ ጳጳስ ከጳጳስ በቤተ ክርስቲያን እስከ ዕለተ ምፅአት ድረስ ሲሰጥና ሲናኝ ይኖራል፡፡ ለዚህ ምሳሌ የምንጠቅሰው ወጣቱን ሳሙኤል ሽማግሌውን ኤሊን ነው፡፡ ብላቴናውም ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ ጠነከረ በእግዚአብሔር ቤት የታመነ ሆነ 1 ሳሙኤል 2፡21 ብንመለከት ይረዳናል፣ ከመልካም ቤተሰብ የተወለደ ሰው ሁሉ ካህን መሆንም ሆነ ወይም መስፍን ሁለቱንም ደርሶ መያዝ እንደሚችል ይህ ቃል ያስተምረናል፡፡ የሳሙኤልና የኤሊ ግንኙነት ግን እቅዱም ሆነ ፕላኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ዛሬም ሆነ የካህኑና የወጣቱ ግንኙነትም በዚህ ፈለግ ወይም በዚህ መንገድ መሆን ይኖርበታል እንጂ ሌላ አማራጭ መንገድም ከተገኘ አያሻማም ማለትም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚጐዳ መሆን የለበትም ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆን እንዳለበት ሳንጠቁም አናልፍም ኤሊ የሚባለው ታላቁ ካህን በጠዋት ተነስቶ ብላቴናውን ሳሙኤልን ጠራው ልጄ ሳሙኤል ሆይ አለው እርሱም እነሆ አባቴ አለሁ አለው እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው ንገረኝ ከኔ አትሸሽግ ከነገረህ ነገር ሁሉ የሸሸከኝ እንደሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ እንዲህ ይጨምርብህ አለው ስለዚህ ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው አንዳችም አልሸሸገውም፡፡ ስለዚህ የዛሬውም ወጣቶች ለካህኑ በሕይወቱ ያለውን ነገር ሁሉ ለካህኑ ፈጽሞ መናገር አለበት ምክንያቱም በዚህ ግልጽነት የተነሳ ወጣቱና ካህኑ ግንኙነታቸው የጠነከረ ይሆናል 1ሳሙኤል 3፡15 ላይ ያለውን ብንመለከት ፍፁም እምነት ሊሰጠን ይችላል፣ ማለትም ለካህኑም ለወጣቱም በዚህ ዓይነት አመራርና ዕቅድ የሄድን እንደሆነ እራሳችንንም ሌላውንም ማዳን እንችላለን፡፡

ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ሚና

"እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ አብረኸኝ መከራ ተቀበል የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም፡፡ ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል የድሉን አክሊል አያገኝም......." (2ኛ. ጢሞ. 2፡3-5) ማንም ሰው በወጣትነት እድሜው ሃይማኖትና ምግባርን መሠረት በማድረግ ለሃይማኖቱና ለወጣቱ በቅንነት በታማኝነት መታገል እንዳለበት ቅዱሳን መጻሕፍት ያስረዱናል፡፡ እንደ ሳሙኤል ከሕፃንነት እድሜው ጀምሮ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ማደግ እንዳለበት እሙን ነው፡፡

ይኼውም "ሳሙኤል ግን ገና ብላቴና ሳለ የበፍታ ኤፋድ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር" (1ኛ. ሳሙ. 2፡18) ስለዚህም የዛሬ ዘመን ወጣቶች ደግሞ እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና እንደ ነቢየ እግዚአብሔር እንደ ኤርምያስ ከእናት ማኅፀን ጀምሮ ፈጣሪያቸውን እንዳወቁና እንደ አመሰገኑ ሁሉ ወጣቶች አምላካቸው እግዚአብሔርን አውቀው ማምለክ አለባቸው (1፡45) (ኤር. 1፡5 ገላ. 1፡15) ወጣቱ በእናንተ አማካኝነት እነዚህ ሁሉ ማስረጃዎች ሲደርሱት እንደሚጠቀምበት እምነታችን ነው፡፡

ይኼውም፡- ቅዱስ ጳውሎስ ለወዳጁና ለደቀ መዝሙሩ ለጢሞቴዎስ እንደ ፃፈው "አንተ ግን በተማርክበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር ከማን እንደተማርከው ታውቃለህና ከህፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መፃሕፍትን አውቀሀልና...." (2ኛ ጢሞ. 3፡14-17) እያለ ያስተምራል፡፡በመሆኑም አሁን ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧአል፡፡ ቲቶ 2፡11

ይህም ፀጋ ኃጢአተኝነትና የዓለማዊ ምኞትን ትተን የተባረከውን የተመሰከረለት ተስፋችንን (ተስፋ ትንሣኤን) ስንጠባበቅ መኖር እንዳለብን እንረዳለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች በመጠቀም የበለጠ መትጋትና መሥራት እንዲችሉ ዘመኑም ጊዜውም በእውቀትና በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ካለፈው ከነበረው ዘመን ይልቅ የተሻለና የተሻሻለ ዘመን ላይ መድረሳቸውን አውቀው እንዲሠሩ ማድረግ፡፡

የሰንበት ት/ቤቶች አጠቃላይ ዓላማ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች አጠቃላይ ዓላማ

1. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ታሪክና ባህል ሳይለወጥ ሳይፋለስና ሳይበረዝ በትክክል ተጠብቆ ከአበው ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ሚድረግ፡፡
2. የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ሃይማኖታቸውንና የሃይማኖታቸውን ሥርዓት እየተማሩ በመንፈሳዊ ጥበብ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት እንዲያድጉ ማድረግ፡፡
3. የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች በሰንበት ት/ቤታቸው ተደራጅተው እየተማሩ የሀገርንም ሆነ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በሚገባ አውቀው የነገረ ሃይማኖትን ምሥጢር (ጥበብ) ቀስመው በዕውቀት ብስለት እንዲያገኙና የነገዋን ቤተ ክርስቲያን በኃላፊነት ለመረከብ ብቃት እንዲኖቸው ማደረግ፡፡
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች የቤተ ክርስቲያናቸውን ሕግና ሥርዓት ተምረው እንደ ቀደምት ኢትዮጵያውያን በዛፍ ሥር ሊያገኙት ያልቻሉትን መንፈሳዊ ጥበብ በየሰንበት ት/ቤታቸው ተምረውና አውቀው በሃይማኖትና በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያደርጉ ለሀገርና ለወገን መልካም ዜጎች እንዲሆኑና የቤተ ክርስቲያናቸው አገልጋዮች እንዲሆኑ ማድረግ
5. ወጣቶች በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን የማገልገል ኃለፊነታቸውንና ግዴታቸውን እንዲያውቁ በማድረግ በፈቃደ እግዚአብሔር እየተመሩ ፈጣሪያቸውን እያሰቡ በቅዱሳት መፃሕፍት የታዘዘውን እየፈፀሙ ንፁህን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሆነው እንዲያደጉ ማድረግ፡፡
6. የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ጊዜ ከወለደው ከኑፋቄ ትምህርት ተጠብቀው የመናፍቃንን እርካሽ ተልዕኮ በማክሽፍ መንፈሳዊና ታሪካዊ ብኩርናቸውን ጠብቀውና አክብረው እንዲኖሩ ማድረግ ነው፡፡
7. በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንፀው አድገው በመንፈሳዊ ጥበብ እየተጓዙ ሥጋዊ ድህነትና መጥፎ አመለካከትን ከምድረ ኢትዮጵያ ማስወገድ እንዲችሉ ማድረግ

ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ሊኖራቸው የሚገባቸው ሚና

 • ለወጣቶች በቤተ ክርስቲያን መሰባሰብ መሠረቱ የእግዚአብሔር ጥሪ ነው፡፡
 • የዋህነት እንደ አቤል (ዘፍ. 4፡ 1-15)
 • ቅንነትና ታዛዥነት እንደ ይስሐቅ (ዘፍ. 22፡1-18)
 • ፈራሄ እግዚአብሔር እንደ ዮሴፍ (ዘፍ. 39፡1-23)
 • ከራስ ጥቅም ይልቅ ለወገኑና ለእምነቱ ተቆርቋሪነትን እንደ ሙሴ (ዘዳ. 21፡11-22)
 • ከእምነቱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አለማለትን ከኢያሱ (ኢያሱ 1፡5-9) በመማር ቤተ ክርስቲያንን በፈሪሃ እግዚአብሔር ማገልገል ነው፡፡

ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን መሰባሰብ መሠረት

1. ልጆች ወደ እኔ ኑ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ (መዝ. 33፡11)
2. ሕፃናትን ተውአቸው ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና (ማቴ. 19፡13-14)
3. ማኅበረ እስጢፋኖስ (8 ሺህው ማኅበር እስጢፋኖስ) (የሐ.ሥ. 6፡7) በዚህ ሁኔታ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ከተሰበሰቡ በኋላ ትልቁ የሥራቸው መጀመሪያ መሠረቱ ፍፁም ዕምነት፣ ተስፋ ፍቅር ነው፡፡
ይኸውም በጥበብና በሞገስ እንደ ጌታ ለማደግ በምግባር የሚተጉ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተ ክርስቲያን በማወቅና በመጠበቅ መመላለስና ሕጉንም በእግዚአብሔር ፊት በመፈጸም እንዲፀድቁ በማኅፀን ጀምረው የተጠሩ መሆናቸውን ማስረዳት "በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉ ይፀድቃሉ እንጂ የሚሰሙት ብቻ አይፀድቁም" (ሮሜ. 2፡13፣ ማቴ. 7፡21 ያዕ. 1፡22-25) ስለሚል ወጣቶች በቤተ እግዚአብሔር ሊተጉ እንዴት እንደሚገባቸው መንገሩ ተገቢ ነው፡፡

ሀ. በከCር የሆነችውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን ለጊዜያዊ ጥቅም ብለው ከመተው ይልቅ ሃይማኖታቸውን በሚገባ በመጠበቅ እንዳለባቸው (ዘፍ. 25፡27-34፣ ዕብ. 12፡16-17፡ ሮሜ. 16፡18፣ ፊል. 3፡18፣ 1ኛ ቆሮ. 1፡18)
ለ. ለወጣቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዙሪያ ሊኖራቸው ስለሚገባው የሥራ ድርሻ፡፡
ሐ. ወጣቶች ከካህናት ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባው የአባትነትና የልጅነት ግንኙነት፡፡
መ. ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ሊኖራቸው ስለሚገባቸው ሚና፡፡
ሠ. ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት መንፈሳዊ አገልግሎትን በእግዚአብሔር ፊት መፈጸም እንዳለባቸው ትኩረት ተሰጥቶት ሊገለጥላቸው ይገባል፡፡

ይኼውም፡- "ንፁሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮት ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም ከመከራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ እደፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው፡፡" (ያዕ. 1፡27)
በአጠቃላይ ለወጣቶች እጅግ በጣም ጥንቃቄና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ስለሆነ አንድን ችግር ወይም ተክል ተንከባክቦ ውኃ አጠጥቶ እንደ ማሳደግ ሁሉ ትውልዱንም በመንፈሳዊ ሕይወትና በሥጋዊ ሕይወት ጭምር በተቀናጀ መልኩ አስተምሮ ማሳደግ የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ስለሆነ ከ40 ቀንና ከ80 ቀን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በኃላፊነት ከተረከበቻቸው ጊዜ ጀምሮ ተንከባክባና ጠብቃ የማሳደግ ኃላፊነት እንዳለባት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በዮሐ. 21 ፡ 15 ጀምሮ የተናገረውን ቃል መነሻ በማድረግ ግልገሎቼን ጠብቁ በማለት በታላቁ በነቢዩ በኢሳይያስ አድሮ እንደተናገረንና እንዳስተማረን ጠቦቶቹን በክንድ ሰብስቦ በማያዝና በመንከባከብ የሚያጠቡትንም በቀስታ ያለቀጠና ያለፍርሐት እንዲመሩ ያደርጋል ብሎ የሰጠንን መመሪያ ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት የቤተ ክርስቲያን ስለሆነ እናንተም ይኼንኑ ተልእኮ ትወጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት እንዳይለያችሁ እንለምናለን፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ