Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት ሐዋርያዊ አገልግሎት

የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት በሕዳር ወር በ1962 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ አባላት ከነበራቸው ከፍተኛ እንቅስቃሴ አንፃር ብሥራተ ወንጌል ሬድዮ ጣቢያ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ይሳተፉ ነበር፡፡ ሰንበት ት/ቤቱ በአዲስ አበባ ከሚገኙት ሰንበት ት/ቤቶች መካከል ተመርጦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት እና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ከውጭ ሀገር በሚመጡበት ጊዜ ቦሌ ኤርፖርት በመገኘት መዝሙር በመዘመር አቀባበል ያደረጉ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ አባላት ያስታውሱታል፡፡ በወቅቱ የነበሩ አባላት በዲቁና ማዕረግ ቤተ ክርስቲያንን በቅዳሴ ያገለግሉ ነበር፡፡ ከእነሱም መካከል ቀሲስ ትዕግስቱ (አሁን በእስራኤል ሀገር የሚገኙ) መልአከ ፀሐይ መኰንን ፍስሐ (የደብረ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ) ይገኙበታል፡፡ ሰንበት ት/ቤትችን የተለያየ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማዋቀር ለእያንዳንዱ አባል ፋይል በማዘጋጀት የሰንበት ት/ቤት ቅርጽ ይዞ እንዲጓዝ የተደረገው በ1971 ዓ.ም የተቋቋመና በወጣት መልአኩ ጌታነህ (አሁን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል) ሊቀ መንበርነት ያገለግል የነበረው ኮሚቴ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የነበሩ አገልጋዮች ከተለያዩ አድባራትና ገዳማት ሰንበት ት/ቤቶች ጋር በበዓለ ንግሥ በጋራ በማክበር የጠነከረ ግንኙነት እንደነበራቸው በሰንበት ት/ቤት የሚገኙ ፋይሎች ያስረዳሉ፡፡

በ1974 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ሥራ ሲጀመር ሰንበት ት/ቤቱ የአዳራሽ ችግር የገጠመው ሲሆን አባላቱ በመጠለያ እየተቀመጡ እንዲማሩ አስገድዷቸዋል፡፡  ከዚህ በመቀጠል ሰንበት ት/ቤታችን ትልቅ ፈተና የገጠመው መጋቢት 28 ቀን 1992 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሸችንና በደብሩ ዕቃ ግምጃ ቤት የደረሰ ቃጠሎ ነው፡፡ በዚህ አደጋ ሰንበት ት/ቤታችን የነበረውን ንብረት ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን በወቅቱ የነበረው የሰንበት ጽ/ቤታችን የሥራ አመራርና አባላቱ ባሳዩት ጥንካሬ በጐ አድራጊዎችን በማስተባበር አሁን ያለው አዳራሽ እንዲሠራ የነበሩት ንብረቶች እንዲተኩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሲሆን አዳራሹ እስከሚሠራ ድረስ አባላቱ ይሰበሰቡበት የነበረው በደጀ ሰላም ሲሆን ቦታው ለመማሪያ የማይመች ዝናቡ የሚያስገቡ ስለነበረ ይህንን ተቋቁመው አብዛኛው አባላት አገልግሎታቸውን ሊቀጥሉ ጥቂት አባላት ግን ከአገልግዘት እርቀዋል፡፡ አዳራሹ ከተሠራ በኋላ በ1994 ዓ.ም የተመረጠ የሥራ አመራር ኮሚቴ አሁን ላለው አገልግሎት የሰንበት ት/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ በመቅረጽ የአገልግሎት ክፍሎች የዓመት እቅዶችቻውን እንዲያቅዱና በጠቅላላ ጉባኤው እንዲያጸድቁ በማድረግ ሰንበት ት/ቤታችን ያሬዳዊ መዝሙራትን ሳንሱር እያደረጉ እንዲዘምሩ በማድረግ መሠረት ጥሏላ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሰንበት ት/ቤቱ ከፍተኛ ትኩረት በመሥጠት የሚንቀሳቀስባቸው፡-

1. ያሬዳዊ ዜማን ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ በሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን አባቶች ያሬዳዊ ዜማ በማጥናት ለሌሎችም ሰንበት ት/ቤቶችአርአያ መሆን

2. ለወጣቱና ለሕጻናት የአብነት ትምህርት በማስተማር ለወደፊቱ በቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ ዲያቆናትን ማፍራት እስካሁን ሰባት ወጣቶች ማዕረገ ዲቁና እንዲቀበሉ አድርጓል

3. ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ለ1ኛ ለ2ኛ ለ3ኛ ዓመት ተማሪዎች ተከታታይ ትምህርቶች መስጠት

4. የግቢ ጉባኤያትና የሠራተኛ ጉባኤ በተጠናከረ መልኪ እንዲቀጥል ማድረግ

5. ከደብሩ አገልጋይ ካህናትና መዘምራን እንዲሀም የስብከተ ወንጌል ጋር በጋራ ማገልገል (በስብከተ ወንጌል ልዩ መርሐ ግብር በማዘጋጀትና በማኀሌት በመገኘት ከሊቃውንት አባቶች ጋር ማገልገል) በወር በአውደ ምሕሐረት ልዩ ጉባኤ ያዘጋጃል

6. ከሰንበት ት/ቤቱ አባላት መካከል አቅማቸው ፈቅዶ የትምህርት መረጃ መሳሪይዎች ማሟላት የሚችሉትን የሰንበት ት/ቤቱ አባላት አስተዋጽኦ በማደረግአስፈላጊውን የትምህርት መርጃ መሳሪያ በየዓመቱ የሚያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

7. በበጎ አድራጎት ክፍልበአጥቢያችን የሚገኙትን ነዳያንን በመመዝገብ የንስሐ አባት እንዲኖራቸውና እራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ እንዲሁም ሥራ ያጢትንና ከፍልው ለመማር አቅም የሌላቸውን አባላት ስፖንሰር በማፈላለግ ነፃ የትምህርት እድል እንዲያገኙና እራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን እስካሁን የተለያዩ ኮሌጆች በሰጡን እደል ትምህርታቸውን ፈጽመው የተመረቁ እና በመማር ላይ የሚገኙ አሉ፡፡በያዝነው ዓመትም ለመሥራት ካቀድናቸው መካከል የሰንበት ት/ቤቱን ቋሚ ጽ/ቤትና አዳራሽ ማሠራት እንዲሀም የቅዱስ ያሬድን የዜማ ምልክቶች የጠበቀ የመዝሙር ካሴት አዘጋጅቶ ማሳተምና የቅዱስ ያሬድን ታሪክ በመጽሐፍ ማዘጋጀት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ይህንንም አምላክ ቅዱስ ያሬድ እንደሚያስፈጽመን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መረጃና መዛግብት ክፍል

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ