Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ

ሥልጣን ያላቸውን ይሳደባሉ

ይሁዳ. ቁ. 8

ሰዎች የሚድኑበት የሕይወት መልዕክት ወደሰዎች መድረስ ከጀመረ ሁለት ሺህ ዘመን በላይ ተቆጥሯል፡፡ በዚህም የሕይወት ራስ ከሆነው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኋላ አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ሰባ ሁለቱ አርድዕት ሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በረሃብና በጥም በጾምና በጸሎት እየደከሙ ጀርባቸውን ለግርፋት ገጻቸውን ለጽፍአት በመስጠት በዘመናቸው ወንጌልን ሰብከዋል፡፡

እግዚአብሔርም ለዚህ ልዩ የመዳን ወንጌል ከሐዋርያት በኋላ አርድዕትን በኋላም ሊቃውንትን፣ መምህራንን፣ ሰማዕታትን በየጊዜው እያስነሳ አስተምሯል ዛሬም ህዝቡን ያጽናናሉ፣ ይመክራሉ፡፡ የዚህ የተቀደሰ ዓላማ ፈጻሚዋ ደግሞ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስትሆን ለሰው ልጅ ድኅነት መፈጸም ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን ፈጻሚ ካህናት አሉዋት፡፡ የክህነት ተዋረዱም ዲቁና፣ ቅስና፣ ኤጲስ ቆጶስነት /ጵጵስና/ ናቸው፡፡ በተለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ክርስትናን በጃንደረባው ባኮስ አማካኝነት ተቀብላ በታላቁ አባት አባ ሠላማ ከሳቴ ብርሃን ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፣ የወንጌል አገልግሎት በስፋት እንደተጀመረ ይታወቃል፡፡ ዛሬም ቢሆን ክርስቲያኖች ባሉበት ሥፍራ ሁሉ በአርባና በሰማኒያ ቀን ልጅነት ሰጥታ በሰንበት ት/ቤት ሰብስባ ታስተምራለች፡፡ ዋነኛ ተልዕኮዋ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡

ዛሬ በደረስንባቸው ግዜያት ደግሞ ቴክኖሎጂ አንዱ መልካሙን ነገር የምንማርበት እና የምናስተምርበት ወንጌልን ማስፋፍያ፣ ነፍሳትን የመማረኪያ መንገድ ድረ ገጽ (Website) ነው፡፡ ይህንን በአግባቡ ያለመጠቀም ደግሞ ምን ያህል ጎጂ እንደሆነ ከአንባቢያን የተሰወረ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ስልጣኔ ተጠቅመን ምዕመናንን ማስተማር፣ መምከር፣ ማጽናናት ስንችል "ሐራ ዘተዋሕዶ፣ አባ ሠላማ፣ አንድ አድርገን፣ ደጀ ሰላም" ወዘተ በሚል ስያሜ የተከፈቱ የጡመራ መድረኮች ብዙ የሀሰት መልዕክቶችን እየተመለከትን ሲሆን እውነተኛ አማኞች ነገሮችን እንዲለዩ መልዕክት ማስተላለፍ ግዴታችን በመሆኑ ጥቂት ልንል ወደድን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
 • በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

ሞትንና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሣው፣ የሕይወት ራስና የሁሉ ፈጣሪ የሆነው፣ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !!

‹‹ዓይቴ እንከ ቀኖትከ ሞት፤ ወዓይቴ እንከ መዊዖትከ ሲኦል፤ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?
ሲኦል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ?›› /1ቆሮ. 15፡55/፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ሞትና መቃብር የኃጢአትና የበደል ውጤቶች እንጂ የተፈጥሮ ዕድል ፈንታ ሆነው ለሰው የተሰጡ አይደሉም ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከሥተ፡፡

ይህንን ጽሑፍ ለመጽሐፍ ያስገደደኝ ሰሙነሕማማት እና ወርኃ በዓላት በመጡ ቁጥር በየአከባቢው የሚነሳው የምዕመናን ጥያቄ እና የቤተ ክርስቲያን ካህናትና ሰባኪያን መልስ እርስ በራሱ ልዩነት እየፈጠረ ስለመጣ ነው፡፡
በባሕረ ሐሳብ ኢየዓርግ እና ኢይወርድ ሕግ መሠረት ከሚከበሩ በዓላት መካከል ዐቢይ ጾም ነው፤በመጨረሻው ሣምንት የምናገኘው ደግሞ የሰሙነ ሕማማት ሣምንት ነው፡፡ በየዘመኑ ከባሕረ ሐሳብ ዑደትጋር ከሚገናኙ በዓላት መካከል ፣
1 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምወርኃ በዓል ሚያዝያ21ቀን

2 የቅዱስ ሚካኤል ወርኃ በዓል ሚያዝያ12ቀን፡፡

3 በዓለ እግዚአብሔር ወይምበዓለ ትስብእት መጋቢት 29 ቀን ጌታ የተፀነሰበት ፣የተነሣበት ፤ጥንተ ትንሳኤ፤

4 የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት መጋቢት 27 ቀን የጊዮርጊስ ክብረ በዓል ሚያዝያ 23 ቀን እንደ ባሕረ ሐሳብ ኢየኣርግ እና ኢይወርድ ሰሙነ ሕማማትና በዓለ ፋሲካ የሚያገኛቸው ክብረ በዓላትና የወርኅ በዓላት ናቸው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በቁመት ጊዜ ቃለ እግዚአብሔራቸው አይባልም፤ ክብረ በዓላቸውም ከሰሙነ ሕማማትና ከበዓለ ፋሲካ /ሰሙነ ማዕዶት / ከዳግም ትንሣኤ ውጭ ባሉት ቀናት ነው፡፡

በሰሙን ሕማማት ወርኃዊ በዓልም ሆነ ዓምታዊ ክብረ በዓል የጌታ በዓል ተደርቦ ቢውል ቁመት አይቆምም ቅዳሴ አይቀድስም ፣ክርስትና ማንሳተ ክልክል ነው፣ ክህነት መስጠት ፣ለሙታን መጸለይ አይገባም ፡፡(ፍትሓ ነገስት አንቀጽ15 ቁጥር 600 )

ተፈጣሚ የሚሆነው የሰሙነ ሕማማተረ ሥርዓት ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

‹‹እመቦ ዘአሕሰመ ቃለ ላዕለ አቡሁ ወእሙ ሞተ ለይሙት፤
አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል›› (ዘጸ. 21፤17፣ ማቴ. 15፡3-4)

እስክንድር ገብረ ክርስቶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት የባህልና የታሪክ መገኛ በመሆኗ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንተ ሥልጣኔ መሠረት ነች ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በመፈቃቀድ፣ በመከባበርና በመቻቻል በአብሮነት ይኖር ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በግብረገብ ትምህርት በማነጽ በልዩነት ውስጥ ላለን አንድነት መጠንከር ታላቅ አስተዋኦን አበርክታለች ፡፡
ከአሠርቱ ትእዛዛት አንዱና ‹‹እናትና አባትህን አክብር›› የሚለውን የልዑል እግዚአብሔርን ትእዛዝ መሠረት በማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑ በመከባበር፣ በመደማመጥና በመፈቃቀር ይኖር ዘንድ ለዘመናት አስተምራለች፤ በማስተማርም ላይ ትገኛለች፤ ይህ ትምህርቷም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ በመሆኑ በቤተሰብ ደረጃ ሳይቀር ታናሽ ታላቁን እያከበረና በታላቁ እየታዘዘ፣ ታላላቆችም ለወላጆቻቸው እየታዘዙ በመከባበር የሚኖሩበት ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ማሥረፅ ችላለች ፡፡
ይህ የመከባበርና የመደማመጥ ሥርዓት በቤተ ክርስቲያናችን ደረጃ የጠነከረና የሚያስቀና ሥርዓት ሆኖ ይገኛል ፡፡ ዲያቆናት ካህናትን፣ ካህናት ኤጲስ ቆጶሳትና ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ፓትርያርኩን በማክበር፣ በማድመጥና በመታዘዝ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት ባለቤት መሆኗን በተግባር ለሕዝበ ክርስቲያኑ ስታስተምር ኖራለች፤ አሁንም እያስተማረች ትገኛለች ፡፡
በለተይም የሐዋርያት ምሳሌ የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በከፍተኛ ደረጃ ክብር ሊሰጣቸው የሚገቡ አባቶች በመሆናቸው ካህናትና ምእመናን ጉልበታቸውንና መስቀላቸውን ስመው ተገቢውን የሃይማኖት አባትነት ክብር ሰጥተው በሚገባ ያከብሯቸዋል ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰጧቸውን ትእዛዝና መመሪያዎችም ያለማንገራገር ተግባራዊ ያደርጋሉ ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን

በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በተለያዩ ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፤
ምሕረቱ የበዛ መዓቱ የራቀ ቸርና ሰው ወዳጅ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም ዓቢይ በሰላም አደረሳችሁ !!
‹‹ወአንሰ መጻእኩ ከመ ይርከቡ ሕይወተ ወፈድፋደ ይርከቡ፣ እኔ የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲያገኙ መጣሁ›› (ዮሐ10፡10)
ይህ ቃል የሕይወት አስገኚና ሰጪ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ዘላቂና ዘላለማዊ ሕይወት ሊሰጥ ሰው ሆኖ ወደሰዎች እንደመጣ ሲያመለክት የተናገረው ቃለ አድኅኖ ነው ፡፡
ለፍጡራን ሁሉ ትልቁና የመጀመሪያው ጸጋ ሕይወት ነው፤ ሰውም ሆነ ሌሎች ፍጥረታት በዚህ ዓለም ሲወጡና ሲወርዱ የሚገኙት ሕይወትን ለመንከባከብ፣ ለመጠበቅና ለማስቀጠል ነው፤
ምክንያቱም ሕይወት ካለ በሕይወት መሣሪያነት ሁሉም ይገኛል፤ ሕይወት ከሌለ ግን ሁሉም የለምና ነው ፡፡
በመሆኑም ሕይወት በፍጡራን ዘንድ ተወዳዳሪና መተኪያ የሌላት ሀብት ናትና ሙሉ ጥበቃና እንክብካቤ ሊደረግላት ይገባል ፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንንና ነፍሳችንን በመዋሐድ ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ በዓለም ላይ የተገለጠው ሕይወታችንን ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለማዳን ነው ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ተገልጦ ይመላለስ በነበረበት ጊዜ ሕይወትን አጥተው በጉስቁልና የነበሩ የተለያዩ ሕሙማን ሕይወተ ሥጋን እንዲያገኙ አድርጎአል፤
ሕይወተ ነፍስን አጥተው የነበሩትም በሕያው ትምህርቱ ተስፋ ሕይወትን እንዲላበሱ አድርጎአል፤ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ሙታን ሕይወታቸውን ተጎናጽፈው ከመቃብር እንዲነሡ አድርጎአል፤ በእነዚህ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ራስ መሆኑን ከመግለጽ ጋር ለሰው ልጆች ሁሉ ሕይወትን ለመስጠት እንደመጣ በትምህርትም በተግባርም አሳይቶአል ፡፡
ከዚህ አንጻር ሕይወት በፈጣሪም ሆነ በፍጡራን ምን ያህል ታላቅ ዋጋ እንዳላት ማስተዋሉ አይከብድም፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን ባሳየችው እመርታ የጥምቀትንና የመስቀልን የመሳሰሉትን በዓላት የምታከብረው ያሬዲዊ ዝግጅት በማቅረብና የቃል ትምህርት በመስጠት ብቻ ሳይሆን በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጽሔቶችንና በራሪ ጽሐፎችንም ጭምር ለሕዝበ ክርስቲያኑ በማሠራጨት ነው። በዘንድሮውም የጥምቀት በዓል አከባበር ከፍ ብሎ በተገለጸው መሠረት የበዓለ ጥምቀትን ምንነት በስፋትና በጥልቀት ለማስረዳት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ርእሶችን ያካተተና ጠቃሚ ትምህርቶችን የያዘ ሌዩ ዕትም መጽሔት በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች አዘጋጅታለች።

በዚህም መሠረት፦

 • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ስለ በዓለ ጥምቀት ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት፤

 • ዘመነ መርዓዊ በሚሌ ርእስ የዘመነ አስተርእዮን ትምህርትና ምሥጢር በስፋትና በጥልቀት የሚተነትን፥

በመጋቤ ብርሃናት አባ ተክለ ያሬደ ጎርጎርዮስ

 • በአንዲት ጥምቀት እናምናለን በሚል ርእስ የጌታችን፥ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀትን ምሥጢርና ትርጕም የሚያብራራ፥

በሊቀ ማእምራን ፈንታሁን ሙጪ

 • የአማላጅነት መሠረት በአዲስ ኪዲን በሚል ርእስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት የማማለዷን ምሥጢር የሚያስረዳ፥

በመ/ር አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሣሙኤል

 • በዓለ ጥምቀትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠለ ይገባዋል በሚል ርእስ ቤተ ክርስቲያናችንና መንግሥት የጥምቀትን በዓል በዩኔስኮ በቅርስነት ለማስመዘገብ እያደረጉ ያለውንና ወደፊትም ሊደረግ የሚገባውን ጥረት የሚገልጽ፥

በእስክንድር ገ/ክርስቶስ

 • መንፈሳውያት በዓላት ያላቸው በጐ ጎንና ለሕዝቡ አንድነት ያበረከቱት አስተዋጽኦ በሚል ርእስ በልዩ ልዩ ምሑራነ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀውንና ትምህርታዊ ጽሑፎች የተካተቱበትን ይህን መጽሔት በማንበብ መንፈሳዊ ዕውቀታችንን በማጎልበት የጥምቀትን በዓል ልናከብር ይገባናል።

በመምህር ካህሣይ ገ/እግዚአብሔር

እነዚህንና ሌሎች ትምህርታዊ ጽሑፎች የተካተቱበትን ይህን መጽሔት PDF በዚህ ድረ ገጽ እንደታነቡ ጋብዘናል፡፡ መልካም ንባብ ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
 •  የተከበሩ ....
 • ክቡራን አምባሳደኖችና ኮር ዲፕሎማቶች
 • የተከበራችሁ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
 • የተወደዳችሁ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች
 • በአጠቃላይ በዚህ ዓቢይ በዓል የተገኛችሁና በየአካባቢው ሆናችሁ በዓሉን በማክበር ላይ የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ

በማየ ጥምቀት አማካኝነት ሀብተ ጽድቅንና ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ያደለን እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ጥምቀተ ክርስቶስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹‹ወይደልወነ ከመ ንፈጽም ኵሎ ጽድቀ፤ እንግዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናል›› (ማቴ.3፡15)

ከሁሉ በፊት በዓለ ጥምቀቱን ስናከብር ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ዕለት በቃልም ሆነ በድርጊት የፈጸማቸውንና ያስተማራቸውን ነገራተ ጽድቅ ሁሉ በልዩ ተመስጦና አንክሮ በማስታወስ ልናከብር ይገባል፡፡

ጌታችን በዚህ ቀን ከተናገራቸው ዓበይት ነገሮች አንዱ ‹‹ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› የሚለው ቃል ነው፤ ይህ መለኮታዊ ቃል ሰዎች በጥምቀት ሱታፌነት የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያገኙበት ከመሆኑ አንጻር የማይታለፍ ጉዳይ እንደሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዮሐንስ አስረግጦ የተናገረው ኃይለ ቃል በመሆኑ የበዓሉ ዓቢይ ርእሰ - ትምህርት ነው፡፡

Picture 069 Picture 070 Picture 071 Picture 072 Picture 073 Picture 076 Picture 077 Picture 078 Picture 083 Picture 087 Picture 091 Picture 100 Picture 102 Picture 108 Picture 110 Picture 113 Picture 114 Picture 116 Picture 118 Picture 124 Picture 137 Picture 154 Picture 211 Picture 217 Picture 419 Picture 432 Picture 434 Picture 446 Picture 483 Picture 4o8

በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው ምግባረ ጽድቅ በሰማያውያኑም ሆነ በምድራውኑ ፍጡራን እንዲሁም በሥራዎቻቸው ሁሉ እጅግ አስፈላጊ ናት፤ ነገሮች ፈራቸውን ለቀው ወደመተረማመስ፣ ወደ ዓመፅ፣ ወደ ግጭት፣ ወደ ክፋት፣ ወደጭካኔ፣ ወደ ፍርድና ቅጣት እንዲያመሩ የሚገደዱበት ዋና ምክንያት ጽድቅ ስትዘነጋ ነው ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
 • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

የርስተ መንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ በጌታችን በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ የወለደን እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንተኛው የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ !!


ወበዝንቱ ተዐውቀ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር ላዕሌነ እስመ ለወልዱ ዋሕድ ፈነዎ ውስተ ዓለም ከመ ንሕየው በእንቲአሁ፤ የእግዚአብሔር ፍቅሩ በዚህ በእኛ ላይ ታወቀ፤ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደዓለም ልኮታልና፤ (1ዮሐ.4፡9)፡፡

የእግዚአብሔር ባሕርይ ፍቅር እንጂ ጥላቻ አይስማማውም፤ ጽድቅ እንጂ ሐሰት አይዋሐደውም፤ ብርሃን እንጂ ጨለማ አይቀርበውም፤ ሕይወት እንጂ ሞት በእርሱ ዘንድ የለምና በፍጹም ፍቅሩ እኛን ለመፈለግ ሥጋችንን ለብሶ በመካከላችን ስለተገኘ ለእርሱ የሚገባ የአምልኮ ምስጋና እናቀርባለን ፡፡Picture 004

እግዚአብሔር ፍጹም በሆነ ፍቅሩ ሰማያትንና ምድርን እንደዚሁም በውስጣቸው የሚገኙትን፣ የሚታዩና የማይታዩትን ፍጥረታት ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶአል፤ ወይም አስገኝቶአል፣

ፈጣሬ ፍጥረታት የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን በየዓይነቱ የፈጠራቸው ፍጥረታት በእርሱ ዘንድ ከሚታወቁ በስተቀር በፍጡራን ዓቅም ተቆጥረው የሚዘለቁ ባይሆኑም በጥቅሉ የሚታዩና የማይታዩ፣ ሕይወት ያላቸውና የሌላቸው ተብለው ሊመደቡ ይችላሉ ፡፡
ከፍጡራን መካከል ሕይወት ያለውና በግዙፋኑ በኩል ሊታይ የማይችለው የቀደመ ስሙ ሳጥናኤል የኋላ ስሙ ሰይጣን፣ ወይም ዲያብሎስ የተባለ ረቂቅ መልአክ፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ነጻ ፈቃድ ለክፉ ነገር በመጠቀም በፈጸመው ትልቅ በደል ለፍርድና ለቅጣት ተዳርጎአል (ኢሳ. 14፡12-15፤ ይሁ1፡6) ፡፡

ይህ ስሑት ፍጥረት በራሱ ስሕተት ሳያበቃ ሕያው ሆኖ በግዘፍ የሚታየውን ሰው በማሳሳት እንደእርሱ ለፍርድና ለቅጣት እንዲጋለጥ አደረገ (ዘፍ 3፡1-24፤ ራእ፣ 12፡7-9)

በዚህም ምክንያት ሰው ሕይወቱን አጣ፤ ሕይወት ማጣት ማለት እግዚአብሔርን ማጣት ወይም ከእግዚአብሔርና ከመልካም ስጦታው መለየት፣ መራቅ፣ መወገድ ማለት ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በግብፅ የእስክንድርያ ፖፕና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመስቀል በዐልን ለማክበር በተደረገላቸው ይፋዊ ጥሪ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

 

በመላው ኢትዮጵያ የመስቀል ደመራ በዐል በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን የሚከበር ሲሆን በዐሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመናን፣ ካህናትና አባቶች ሁሉ በአንድነት ሁነው በሚገኙበት በወጥነትና በደመቀ ሁኔታ መከበር ከጀመረ በርካታ ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ከበዐሉ ድምቀትና ታሪካዊነት አንፃር በየዓመቱ በዐሉን ለማክበር ጎብኚዎችና አጥኚዎች ከመላው ዓለም ወደ ሀገራችን ይመጣሉ፡፡ በሰፊው እንደሚታየው የበዐሉን ሃይማኖታዊ ትውፊት መሠረት በማድረግም በርካታ ማኅበራዊ፣ ሥነ ጥበባዊና ኪነ ጥበባዊ ዕሴቶች በሀገራችን ሕዝቦች ዘንድ ዳብረውና ሠርጸው ይገኛሉ፡፡ ከሃይማኖታዊ ዕሴቱ በተጨማሪ በዐሉ ለሀገራችን ሰላም፣ ለሕዝባችን ፍቅር፣ አንድነትና የባህል ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ የበዐሉን ጥንታዊነት፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ዕሴት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ለትምህርታዊ ዕውቀት ሽግግር ያለውን ጠቀሜታ በመለየት የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን በኢትዮጵያ ካሉ የማይዳሰሱ ባህላውያን ቅርሶች ተመርጦ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲኖረው አድርጓል፡፡

በ2008 ዓ.ም. የሚደረገውን የበዐሉን አከባበር ልዩ የሚያደርገው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ሀገራችንን እንዲጎበኙ ባቀረቡላቸው ይፋዊ ግብዣ መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የእስክንድርያ ፖፕና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመሆን ከመስከረም 15-19 ቀን 2008 ዓ.ም. ሀገራችንን ሲጎበኙ ታላቁንና ደማቁን የመስቀል ደመራ በዐላችንን ከእኛ ጋር ሁነው የሚያከብሩ መሆናቸው ታውቋል ፡፡

በታሪክ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ከ1600 ዓመታት በላይ የቆየ ግንኙነት ነበር፣ ይህ ግንኙነትም በአብዛኛው በኢትዮጵያ ነገሥታትና በግብፃውያን መሪዎች እንዲሁም በሃይማኖት አባቶች መካከል ሲደረግ የኖረ ሲሆን ግንኙነቱ ሃይማኖትንና መንግሥትን ያማከለ ብቻ ሳይሆን ባህልን፣ ቋንቋን፣ ሥነ ጽሑፍን፣ ንግድንና ማኅበራዊ ጉዳዮችን ሁሉ ያካተተ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዘመናትን ያስቆጠረው ግንኙነት በደርግ ወታደራዊ መንግሥት በነበረው አስከፊ አገዛዝ ተቋርጦ ከቆየ በኋላ እንደገና በቀጠለው ግንኙነት መሠረትም ከጥር 1-7 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመሆን ይፋዊ ጉብኝት በግብፅ አድረገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኩል የቅዱስነታቸው ጉብኝት ካለው ነባርና አኩሪ የእንግዳ ተቀባይነት ባህላችንና ነባር ሃይማኖታዊ ግንኙነት በተጨማሪ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በመገንባትና በሁለቱ ሀገሮች ሕዝቦች መካከል ያለውንም ግንኙነት ከማጠናከር አንፃር በማየት በቂና ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን፣ የእስክንድርያው ፓትርያርክ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ቆይታ ቅዳሜ መስከረም 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሚደረግላቸው ይፋዊ አቀባበል ጀምሮ፣ ከከፍተኛ የሀገራቱ ባለሥልጣናትም ጋር እንደሚገናኙ፣ ታሪካውያን ገዳማትንና ቅርሶችን እንደሚጎበኝ፣ ከሃይማኖት መሪዎች ጋርም ውይይት እንደሚያደርጉና በመስቀል ደመራ በዐል አከባበር ላይም ተገኝተው ንግግር እንደሚያደጉ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ገልፃለች፡፡

ስለዚህ ለደመራ በዐል አከባበር ትኩረትን በመስጠት እሑድ መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በመላ ሀገራችን በሚከበረው የ2008 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዐል ላይ በኅብረት በመገኘት የሰላም አንድነት፣ የፍቅርና የዕድገት ምልክት የሆነውን በዐል በተለመደው ኢትዮጵያዊ ሥርዓትና አኩሪ ባህላችን መሠረት በመከባበርና በመተባበር መንፈስ ሁላችንም በጋራ እንድናከብረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣

 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
 • በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

የዘመናት ፈጣሪ የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር ያለፈውን ዓመት በሰላም አስፈጽሞ እንኳን ለአዲሱ የሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አደረሰችሁ!!

‹‹ወኀሊ ዓመተ ለትውልደ ትውልድ፤ የብዙ ትውልድን ዓመታት አስብ›› (ዘዳ. 32፡7)፡፡

 

በተጨማሪ ያንብቡ

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ