Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ በዓለ ሲመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የመላ አዲስ አበባ ካህናትና ምዕመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ፡፡

የበዓሉ መርሐ ግብር በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎተ ቡራኬ ከተከፈተ በኋላ በተረኛ ደብር በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ካህናት ጸሎተ ወንጌል ደርሶአል፡፡ ጸሎተ ወንጌሉ ተከትሎ በዚሁ ገዳም ሊቃውንት ለዕለቱ የተዘጋጀ ያሬዳዊ ዜማ የቀረበ ሲሆን እነርሱን በመከተል የሰንበት ትምሀርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማዕከላውያን መዘምራን ለዕለቱ የተዘጋጀ ጣዕመ ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ተራውን በመጠበቅ የአጫብር ዜማም እጅግ ማራኪ በሆነ መልኩ በሊቃውንት ቀርቦ በዓሉ ደማቅ እንዲሆን አስችሎአል፡፡

ከዚህ በመቀጠል ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የበዓለ ሲመቱ አከባበር በሚመለከት መልእክት በሰፊው ካስተላለፉ በኋላ ዕለቱን አስመልክተው መጋቤ ምስጢር ወ/ሩፋኤል ፈታሒ ግሩም የሆነ ቅኔ በማቅረብና ቅኔውን በማብራራት ጭምር በዓሉን እጅግ ደማቅ እንዲሆን አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተው የዓውደ ምሕረቱ መርሐ ግብር ካበቃ በኋላ በዓሉ በሥርዓተ ቅዳሴ ፍጻሜ አግኝቷል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን የቅዱስ ፓትርያርኩን በዓለ ሲመት የሚያሳይ ምስልና ድምጽ እንዲሁም ብፁዕ ዋሥራ አስኪያጅ ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ ቀጥለን እናቀርባለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ትኩረት ለመንፈሳዊ ትምህርት ቤት

ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል
ሥራ አስኪያጅ

ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላቅነትዋን፣ ገናንነትዋንና ማንነትዋን ከሚመሰክሩ ታላላቅ እሴቶች መካከል ዋነኛው፣ መሠረታዊውና የረጅም ዘመን ዕድሜ ያለው መንፈሳዊ ትምህርት ቤታችን ነው፡፡ ይህ ትምህርት ቤት በቀደምት አበው ተጀምሮ እየተስፋፋና እየተጠናከረ ከመምጣቱ በቀር ከሌላ አገር በውርስ እንደተገኘ የሚጠቁም ነገር እስካሁን አልተገኘም፡፡ ትምህርት ቤቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የተመሠረተና ወጥ የሆነ የራሱን ስልት ይዞ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ሃይማኖታዊ ትምህርትን በከፍተኛ ሁኔታ እያስፋፋ፣ እያጠናከረና እየጠበቀ የመጣ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ሕዝባችን ዛሬ ድረስ ለሚጠቀምባቸው ባህላዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ምግባራዊ እሴቶች ምንጫቸው ይህ ትምህርት ቤት እንደሆነ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

መንፈሳዊ ትምህርት ቤታችን በምርምር፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብ፣ በቋንቋ፣ በትርጓሜ፣ በቅኔ፣ በዜማ፣ በሐሳበ ዘመን አቆጣጠር፣ በሥርዓተ ሃይማኖትና በሥርዓተ መንግስት አፈጻጸም ሁሉ ከፍተኛ ሥራ የሠራና ለኢትዮጵያ ሃይማኖትና ማኅበረሰብ ውበትን የሰጠ፣ ግርማ ሞገስን ያላበሰ፣ አኲሪና አስደናቂ ሥርዓትና ባህል ያወረሰ ትምህርት ቤት ነው፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ መንፈሳዊ ትበቤት፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

መልእክት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት በእንተ በዓለ ጾም ዓቢይ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በሙሉ፡-

እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስድስት ዓመተ ምሕረት የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹‹ወእመሰ በምግባረ መንፈስ ቀተልክምዎ ለምግባረ ነፍስትክሙ ተሐይዉ ለዓለም፤ በመንፈሳዊ ሥራ ሥጋዊ ሥራችሁን ብትገድሉ ለዘላለሙ ትድናላችሁ›› (ሮሜ.8÷13)፡፡

ጾም ከጥንት ጀምሮ በዘመነ ብሉይም ሆነ በዘመነ ሐዲስ የተወደደ፣ የፈቃደ ሥጋ መቆጣጠሪያ፣ የፈቃደ ነፍስ ማበልጸጊያ መሣሪያ ነው፤

እነ ሙሴ፣ እኔ ኤልያስና እነ ዳንኤል ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ ይገናኙ የነበረ ራሳቸውን በጾም ለእግዚአብሔር በማስገዛት ነው፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ርእሰ አንቀጽ ዘዜና ቤተ ክርስቲያን

ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይቅደም

የአንድ ሀገር መንግሥት የሚመራውና ሕዝቡን የሚያስተዳድረው በቅድሚያ ሁሉን አቀፍ የሆነ ሕገ መንግሥት ካወጣ በኋላ ነው፡፡ ዋና ዓላማውና ጥረቱም የሚመራበትን ሕገ መንግሥት አክብሮ ማስከበር ነው፡፡የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥትም ያደረገው ይህንኑ ነው፡፡ ሆኖም መንግሥት ራሱ ፈቅዶ ባደራጃቸው ተቀናቃኞቹም በሌላውም ኅብርተሰብእ ዘንደ ቅራኔ የሚፈጠርበትና ለትችት የሚጋለጠው ሕገ መንግሥቱን ሌላው እንዲያከብረው ሌት ተቀን ሥራዬ ብሎ እየወተወተ ራሱ ከሕገ መንግሥቱ ውጭ ሲተገብር በተገኘ ጊዜ ነው፡፡ ወይም ሕገ መንግሥቱ የዜጎችን መብት ያልጠበቀ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡

በዚህ አንጻር ጥንታዊቷ፣ ታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የፓትርያርክነቱን ሥልጣን ከጨበጠችበት ዘመን ወዲህ ለግማሽ ምዕት ዓመታት በሰላም ስትመራበት የኖረችውን በመጀመሪያው ፓትርያርክ ዘመነ ክህነት የወጣውን ሕገ ቤተ ክርስቲያን በመለወጥ በአምስተኛው ፓትርያርክ ዘመነ ክህነት ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የወጣውና ለሃያ ዓመታት ያህል ከሞላ ጐደል ሲሠራበት የቆየው ሕገ ቤተ ክርስቲያን የቀድሞው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ከሚፈቅደው ውጭ ለሙስና ምንጭ የሚሆን ችግር ያለበትና ብፁዓን አባቶችን ለከፍተኛ ትችት የዳረገ ከመሆኑም ባሻገር የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የአገልጋዮች ካህናትን የትምህርት ደረጃና መብት ያልጠበቀ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሠራተኞች በቂ ዋስትና የማይሰጥና ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ጉዳዮችም ያላካተተ ሆኖ በመገኘቱ የተጠቀሱትን ጉደለቶች ሁሉ አሟልቶና ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ተገናዝቦ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲሻሻል ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በእንተ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣

 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፣

 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤

 • በሕመም ምክንያት በየሆስቲታሉ ያላችሁ፣

 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፣

ወልድ ተብሎ ውሉድ እንድንባል ላበቃን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!!

"ወናሁ ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ ወትሰም¥ዮ ስሞ ኢየሱስ ዘውእቱ ያድኅኖሙ ለሕዝቡ እምኃጢአቶሙ፤እነሆ ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፣ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና፣ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ" (ሉቃ 1.31፤ማቴ 1.21)፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው፤ዘላለማዊና ቀዳማዊ የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሰው ሆኖ እንዲወለድ ምክንያት የሆነው፣የሰው ኃጢአት ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

"ሕገ እግዚአብሔር ይጠበቅ"

ከአባ ገሪማ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊና
የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቀረበ ትምህርታዊ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 • ክቡራን ሊቃውንት፤
 • ክቡራንና ክቡራት በዚህ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ

ሁላችንንም በዚህ ቦታ ሰብስቦ ስሙን በመጥራት ቃሉን ለመስማት ላበቃን አምላክ ክብርና ምስጋና ይግባው፡፡

መነሻ አድርጌ የምናገረው ሕገ እግዚአብሔር ይጠበቅ በሚል ርእስ ይሆናል፡፡ ሕገ እግዚአብሔር ይጠበቅ በሚል ርእስ ብዙ ተጽፏል፣ ብዙም ተነግሯል፣ ከዚህም ጋር ጆሮ ያለው ሰምቶ በሥራ ያላሳየ በመሆኑ ትውልዱ ሁሉ ሲለቀስለት ይታያል፣ ሌላውም በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ዕለተ ሞቱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

ሰለዚህ ሕገ እግዚአብሔር ይጠበቅ በሚል መነሻ ንግግሬን እጀምራለሁ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

"32ኛው አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ እንደታዘብነው"

በመጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ
የዜና ቤተ ክርስቲያን ዋና አዘጋጅ

በዜናው ላይ እንደተገለጸው 32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ከጥቅምት አራት እስከ ጥቅምት አሥራ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ የስብሰባው ቀን ከመቼውም ጊዜ የረዘመ ቢሆንም የየአህጉረ ስብከቱ የሪፖርት አቀራረብ ከሌላው ጊዜ የተቀላጠፈ እንደነበረ አይካድም፣ በጉባኤው ፍጻሜ ወቅት በሥራ ብልጫ ላሳዩ አህገረ ስብከት የተሰጠውም ሽልማት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚረዳ በመሆኑ ምስጋና ሊቸረው የሚገባ ነበረ፡፡ ይሁን እንጂ አህጉረ ስብከት እንደቀድሞው በስምሪት ስለማይገመገሙ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንዲሉ በየራሳቸው የሚያቀርቡት ሪፖርት ግን በምልዓተ ጉባኤው ዘንድ የነበረው ተአማኒነት ይህን ያህል አልነበረም፡፡ ያም ሆነ ይህ ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ የወጣው የአቋም መግለጫ በቃለ ጉባኤ መልክ የተረቀቀ እንጂ እንደአቋም መግለጫነቱ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቀረበውን ማእከላዊ ሪፖርት ከአህጉረ ስብከት፣ ከውጭ አብያተ ክርስቲያናት ከመምሪያዎችና ከድርጅቶች የቀረቡትን ሪፖርቶች አንድ በአንድ በመዳሰስ ችግሮችንና መፍትሔዎቻቸውን እያነጻጸረ ማስቀመጥ ሲገባው ያላስቀመጠ ስድ ንባብ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ ምሁራን ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረበውን ገንቢና ጠቃሚ ሐሳብ ያካተተ አልነበረም፡፡ በዚያውም ላይ በጊዜ እጥረት ተመካኝቶ ውይይት ሳይደረግበት በጭብጨባ ብቻ በግርድፉ በማለፉ ምልዓተ ጉባኤው አሁንም የበለጠ ቅሬታ ነበረው፡፡

ይህ እሰከመቼ ይቀጥላል በየዓመቱ እንዲህ እንዲህ እየተባለ የሚታለፍ ከሆነ የቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ ችግር እስከምንጊዜውስ እንዴት ሊፈታ ይችላል? ችግሩ በደንብ እንዲታወቅና እየአንዳንዱ ሀገረ ስብከት በቅጡ እንዲገመገም የተቋረጠው ስምሪት በተሻለ መልኩ ለምን አይቀጥልም ዓመታዊ ጉባኤውስ የሪፖርት ማንበቢያ ብቻ ሳይሆን ለምን የውይይት ጊዜ አይሆንም ስድስቱን ቀን በሙሉ በሪፖርት ንባብ ብቻ ከማሳለፍ ሦስቱ ቀን ለውይይት ቢመደብ ችግሩ ፍርጥርጥ ብሎ ይወጣ አልነበረም? ወይ መፍትሔውስ ይገኝለት አልነበረምን? ቤተ ክርስቲያን ተዘጋ ተቃጠለ ማተብ ማሰር ተከለከለ እየተባለ ችግሩን ወደ ጎን በመተው አባ እገሌ ከዚህ ቀደሱ አባ እገሌም ከዚያ ቡራኬ ሰጡ ለአባ እገሌ ደግሞ ጥሩ አቀባበል ተደረገላቸው በማለት ገብስ ገብሱን ብቻ እያነበቡ መሸላለሙን እግዚአብሔር ይቀበለዋልን? ችግሩን የሚያውቁት ምእመናን አይታዘቡም ወይ?

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመስቀል በዓልን አስመልክተው ያስተላለፉት ቃለ በረከት፤

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣

 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፣

 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣

 • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣

 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፣

በቅዱስ ደሙ ፈሳሽነት ከኃጢአት፣ ከሞተ ነፍስና ከሲኦል ግዞት ነጻ አድርጎ ያዳነን ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!

‹‹መስቀል ዓለም የዳነበት የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ነው››፤ (1ቆሮ.1÷18-24)

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በመላ ኢትዮጵያና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ፡-
እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን፣ መስቀልን በታላቅ ድምቀት የምናከብርበት ዋናው ምክንያት፤ መስቀል ሰዎችን ለድኅነት፣ ዲያብሎስን ለሽንፈት ያበቃ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ በመሆኑ ነው፤

ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን፣ ከሰው ልጅ ውድቀት ጀምሮ እስከ ስቅለተ ክርስቶስ ድረስ በነበረው ዘመን፣ በኃጢአት ምክንያት ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ በሰው ላይ የሰለጠኑበት፣ ዲያብሎስ ኃጢአትን መሣርያ አድርጎ፣ በሞት አቀባይነት፣ ሰውን በሲኦል ውስጥ አጉሮ ያሰቃየበት ዘመን ነበረ፤

DSC_0227 Picture 006 Picture 010 Picture 047 Picture 087 Picture 113 Picture 119 Picture 141 Picture 1610 (72) Picture 166 Picture 170 Picture 175

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የመምርያው የዓውደ ዓመት (የዘመን መለወጫ) መልእክት

ዘመንና የሰው ልጅ

በእግዚአብሔር ጥበቃና ቸርነት 2005 ዓመተ ምሕረትን ጨርሰን ወደ 2006 ዓ.ም ተሸጋግረናል፡፡ እንኳን ከዘመነ ዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሠላም፣ በፍቅር አደረሰን፣ አደረሳችሁ፡፡ ለዚህም ያበቃን አምላካችን ክብርና ምስጋና ይድረሰው፡፡ በእርሱ እንደተገለጸው ዘመን ለሰው ልጅ የሕይወት መለኪያ ነው፡፡ አንድን ትውልድ አሳልፎ ሌላውን ትውልድ ሲተካ የሚኖር መታደስና ማርጀት የሌለበት ሁል ጊዜ ለውጥና መታደስ በሚሻ በሰው ልጅ ሕይወት እየተወከለ አሮጌ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ሲባል መኖሩ የተለመደ ቢሆን ም ዘመን ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የመመለስ ባሕርይ ስለሌለው ዘመን አልፎ ሌላ ዘመን ሲተካ ሁል ጊዜ እንደተናፈቀ ይኖል፡፡ የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔርም በዘመናት መካከል የቸርነቱ ሥራ ስለሚፈጽም ለዘመንም እንደ ሰው ልጅ ጠባይ የተለያየ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

ይኸውም፤

 • ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ዘመን፣ ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኵነኔ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም በአዳም ውድቀት ምክንያት ሰው በሠራው በደል ለ5 ሺህ 5 መቶ ዘመን ሙሉ በሙሉ ተጠያቄ ሁኖ በመገኘቱ፤
 • ከክርስቶስ ልደት ወዲህ ያለው ዘመን ዓመተ ሥጋዌ፣ ዓመተ ምሕረት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ልዑል እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮ ዓለምን በልጁ ደም ሰለዋጀ በዚህ ምክንያት በምሕረትና በአምላካዊ ቸርነት የሚኖርበት የይቅርታ ዘመን በመሆኑ ዓመተ ምሕረት ተብሏል፡፡

ሊቃውንትም የዘመን ታሪክና የሰው ልጅ ሕይወታዊ ጉዞ በመከተል ዘመናትን በመከፋፈል ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኲነኔ፣ ዓመተ ሥጋዌ፣ ዓመተ ምሕረት በማለት ሰይመውታል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ሃይማኖት የሌላቸዉ ሃይማኖተኞች

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ የሰ/ብ/ቅ/ጳ/መ/ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን

የተከበራችሁ የድረ ገጻችን አንባቢያን እንደምን ሰነበታችሁ ድረ ገጻችን ብዙ ቁም ነገሮችን እንደምታስጨብጥ ከሰጣችሁን አስተያየት ልንገነዘብ ችለናል ስለሰጣችሁን አስተያየት እጅግ በጣም እያመሰገንን ለዛሬ ያዘጋጀነዉን ጽሑፍ እነሆ ብለናል፡፡በሃይማኖት ሰበብ የሚተገበሩትን አንዳንድ ነገሮች አይተን በመታዘባችን ሃይማኖት የሌላቸዉ ሃይማኖተኞች በሚል ርዕስ ይህቺን ትንሽ ንባብ ለገስን፡፡

ከአስራ ሁለቱ አንዱ የነበረዉ ሐዋርያ እርሱም ይሁዳ ይባል የነበረዉ ሰዉ ከአምላኩ የተሰጠዉን ሥልጣን፤ኃላፊነት እንዲሁም መንፈሳዊ ጸጋ ያጣዉ ከንቱ የሆነ የገንዘብ ጥማት ስለነበረበት ነዉ፡፡ ታዲያ እርሱ የወለዳቸዉ አንዳንድ የግብር ልጆቹ ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ መኖራቸዉ ለሁላችንም ግልጽ ነዉ፡፡

ያገሬ ሰዉ የተናገረዉን ቀልድ መሳይ ቁም ነገር ልንገራችሁ

አንድ የከተማ ጮሌ የጌታችንን ስዕል ለመሸጥ ሲያዞር የሀገራችንን አርሶ አደር ገበሬ ያገኛል፡፡ ከዚያም ጋሼ ይህን ግዙኝ እያለ ሲያሳያቸዉ በስዕሉ ማማር ልባቸዉ ተነክቶ ዋጋዉ ስንት ነዉ ልጄ? ይሉታል፡፡ እርሱም ለስዕሉ ያላቸዉን ፍቅር በሚገባ ስላወቀ 150 ብር ነዉ ጋሼ ይላቸዋል፡፡ እርሳቸዉም እጃቸዉን በአናታቸዉ ላይ ጭነዉ ኸረግ ያንተ ያለ! ያ ርኩስ እንኳ በሥጋዉ ወራት እያለ በ30 ብር ነዉ የሸጠዉ አንተ ደግሞ ስዕሉን በ150 ብር ትሸጥልኝ ? ሞጭላፋ ሌባ ወግድልኝ ! ከይሁዳ የባስክ ሌባ ብለዉ ተለዩት፡፡ ይባላል፡፡እንግዲህ ይህንን የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስንመለከት ቀልድ ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን እዉነታዉ ይህ ነዉ፡፡ ይሁዳ የሸጠዉ ጌታችንን ብቻ ነዉ፡፡ የዛሬዎቹ ሐይማኖት የሌላቸዉ ሃይማኖተኞች ግን ያልሸጡት ነገር የለም፡፡ እነርሱ ያልሸጡት ነገር ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የሚነፍሰዉን ነፋስ ብቻ ነዉ፡፡ እርሱንም መጨበጥ ስለተሳናቸዉ ነዉ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ