Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ

የጠቅላይቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የኢሉባቡርና የጋምቤላ አኅጉረ ስብከቶች ሊቀጳጳስ መልእክት

"እከውኖሙ አምላኮሙ ለሕዝብ፡ ለሕዝቡ አምላክ እሆናቸዋለሁ" ኤር 31.33

abune_filiposበልዑለ ባሕርይነቱ ሁሉን ያዥ፣ሁሉን ገዥ የሆነው እግዚአብሔር አምላክ ከሰው የበለጠ የሚወደውና የሚያከብረው ፍጥረት በጭራሽ የለውም፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡን እንዲህ ከመውደዱ የተነሣ በሐዲስ ተፈጥሮ በሁለት ወገን ድንግል በሆነች እመቤታችን ንጽሕት ማርያም አማካይነት ሰው ሆኖ ከፅንስ እስከ ዕርገት በመስቀል በከፈለው ካሳ በግድ ከሰው ቀርቦ የነበረ ዲያብሎስን ፈጽሞ በማራቅ ሕዝቡን ወደራሱ መልሶ አቀረበው፡፡

በመሆኑም እግዚአብሔር ላላመነበት ፈጣሪ ብቻ ቢሆንም ለአመነበት ሕዝብ ሁል ጊዜ ከፈጣሪነቱ ጋር የፍቅርና የሃይማኖት አባት ነው፡፡ ''ወእሙንቱኒ፣ ይከውኑኒ ሕዝብየ, እነርሱም የፍቅርና የሃይማኖት ልጆቼ ይሆኑኛል፡፡''በማለት በአባታዊ ፍቅሩ ሕዝቡን አክብሮ አቅርቧቸዋል፡፡

ይህ የአምላከ ዓለም እግዚአብሔርና የሕዝብ ግንኙነት ወደር የማይገኝለት ታላቅ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ሕዝብ ማለት በዘይቤም ሆነ በምስጢር ሲፈታ ''ወገን ፣ ነገድ፣የተሰበሰበ ጉባኤ በአንድ ሀገር፣ በአንድ ሕግና ሥርዐት የሚኖር ማኀበር'' ሆኖ ይገኛል፡፡ ቃሉ ውስጠ ብዙኀ ስለ ሆነም ደግሞ ለአንድም ለብዙም፣ለወንድም ለሴትም በቂ ሆኖ ይነገራል፡፡ በዚህ አንጻር ''ሰበካ ጉባኤ'' ማለት የማይናወጽ መሠረቱ ሕዝበ አግዚአብሔር እንደሆነ ለማወቅ ብሩህ ልቡና፣ትሑት ሰብእና ላለው ሁሉ የሚከብድ አይደለም፡፡ የተመሠረተውም በሕያው ስሙ መጠሪያና መቀደሻ ፣ ቤተ እግዚአብሔር ነው፡፡ የቅ/ቤተ ክርስቲያን አምላክ ለሕዝቡ፣ ማለትም ለሰበካ ጉባኤ የሰጠው ቦታ ከሁሉ በሚበልጥ ደረጃ የፍቅርና የሃይማኖት ልጅነት ስለሆነ ክብሩ የላቀ ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይሆንም፡፡

ቸሩ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ወዶ፣ፊቅዶ በቤቱ ያከበረውን ሕዝብ ከማናቸውም የሰበካ ጉባኤ ልማታዊ ተሳትፎ ማግለል ግን ራሱ ቃለ ዐዋዲው ከዓመት ወደ ዓመት ፈጽሞ በሥራ ላይ እንዳይውል መሸራረፍ ነው፡፡ ቃለ ዐዋዲውም ''ወከመዝ ይእቲ ሥርዐት እንተ እሠርዕ ,የምሠራት ሥርዐት እንዲህ ናት፡፡'' በኤር 3.33 በማለት ከቀድሞ ጀምሮ ለቤቱ ማገልገያ መርሕ ትሆን ዘንድ በምሳሌ የዐወጀው ሕግ ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት

የሰበካ ጉባኤ አደረጃጀት የቤተ ክርስቲያናችን ቁልፍ ጥበብ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያናችንን መንፈሳዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ አጣምሮ ለመምራት የሚያስችል በመሆኑ አደረጃጀቱ ቁልፍ ጥበብ ነው፡፡

ato_tesfayeየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና ምግባረ ሰናይ አጣጥማ የምትሄድ ስትሆን ዋንኛዋ ተልእኮዋ ምዕመናንን በኦርቶዶክ ተዋሕዶ እምነታቸው ጸንተው ምግባረ ሃይማኖት ፍሬን አፍርተው በምድራዊ ሕይወታቸው ለሀገር፣ ለወገን ብሎም ለራሳቸው የሚጠቅም ሥራን ሠርተው በምግባራቸው በጸና እምነታቸው የማይታለፍ ዘላለማዊት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሱ ዘንድ ለዚህ የሚያበቃ ትምህርተ ወንጌል መስጠት መቻልዋ ነው፡፡

ይህም በመሆኑ ዛሬ በዚህ በ 31ኛው የመንበረ ፓትርያርክ መደበኛ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የተገኘን የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች ሁላችን ባለፈው የ2ዐዐ4 ዓ.ም. በመዋቅራችን ሀይል ያፈራውን መለስ ብለን ለማየትና በነበረን እንቅስቃሴ ያጋጠሙንን ችግሮች የምናይበትና ጠንካራ ጐናችንን አጠናክረን የምንቀጥልበት ሁላችንም ተጋግዘን ቤተ ክርስቲያናችንን በሁሉም ዘርፍ ለማሳደግ ጥረታችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ ከዚህ አንጻር ወቅቱ የሚፈልገውን ለመሥራትና ለማከናወን የምንችለው ዛሬ ነው፡፡ ነገ እንሠራለን እንዳንል ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለው ነገ የእኛ አይደለምና፡፡ ስለዚህ የዛሬዋ ቀን የእኛ ስለሆነች ዛሬውኑ ተግተን መንቀሳቀስ ግድ ሊለን ይገባል፡፡ ስለሆነም በእንቅስቃሴያችን ሁሉ ሰበካ ጉባኤ የማጠናከሩ ተግባር ቤተ ክርስቲያናችን ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያናችን ምሰሶ የሆነው ሰበካ ጉባኤ ማጠናከር ማለት ቤተ ክርስቲያናችን በመንፈሳዊና በማህበራዊ ተልእኮ በሀገራችን ሊኖራት የሚችለውን ሚና ትልቅ ስፍራ ሊያስጥ የሚያስችል ነው፡፡ ይሁንና ሰበካ ጉባኤን ለማጠናከር የማጠናከሪያ ምሰሶዎች ያስፈልጉታል፡፡ እነዚህም ምሰሶዎች ስብከተ ወንጌል፣የአብነት ት/ቤቶች ቅርሶቻቸን እንዲሁም በፍጹም አንድነትና በፍቅር ስንሠራ ሰበካ ጉባኤን አጠናከርን ብለን ለመናገር ያስችላል፡፡ ይህም በመሆኑ አጋዥ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኗ ተጓዳኝ መዋቅሮቻችን ማጠናከሩ ሌላኛው አብይ ጉዳይ ተደርጎ መታየት ይኖርበታል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምርያ ኃላፊ መልእክት

"ሠላሣ አንድ ዓመታት በስኬት ጐዳና"

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

fanatahun_mucheሰበካ ጉባኤ ተመስርቶ ዓመታዊ በዓሉን ማክበር ከጀመረ እነሆ ሰላሳ አንድ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ሁልጊዜ እንደምንለው በሰው ሰውኛ ሲታሰብ ከዛሬ ሰላሳ አንድ ዓመት በፊት የነበሩ አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያኒቱን መጻኢ ሁኔታ ተገንዝበው ሰበካ ጉባኤን ባያቋቁሙ ኖሮ እንኳንስ ይህንን ያህል ልናድግ ቀርቶ መኖራችንም ባጠራጠረ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ቤተ ክርስቲያንን በማይናወጽ ዓለት ላይ የመሠረተ አምላክ በአባቶቻችን ላይ አድሮ የካህናት፣ የምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተስፋ የሆነውን ሰበካ ጉባኤ መሠረተ፡፡ ሰበካ ጉባኤም የቤተ ክርስቲያን ሕይወት መሆኑን በተግባር አስመሰከረ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ያሏት ንብረቶች በሙሉ ያለአዋጅ ተነጥቀው ሊቃውንት እና ካህናት ጦም ማደር ሲጀምሩ፣ አንዳንዶች አብያተ ክርስቲናትም ጧፍ እጣን ዘቢብ ፍሬ ግብር እና ለቅዳሴ አገልግሎት የሚውሉ ንዋዬ ቅድሳት መግዛት አቅቷቸው ሲቸገሩ ካህናትና ምዕመናን፣ በሰበካ ጉባኤ ተደራጅተው አለንልሽ አሏት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከምዕመናን የሚሰበሰበው ገንዘብ ለካህናት ደመወዝ፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚውሉ ንዋዬ ቅድሳት መግዣ፣ ከመሆን አልፎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህኀት የሚላከው 35% ፐርሰንትም በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ ነው፡፡ በርካታ አህጉረ ስብከት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚላክላቸውን በጀት ሸፍነው ትርፍ በመላክ ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ሳይጨምር ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማደጉ የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ካህናት የሙዳዬ ምጽዋትና የሰበካ ጉባኤ አስተዋጽኦ ብቻ እየጠበቁ እንዳይኖሩ ጥቂት የማይባሉ አህጉረ ስብከት ልማት በማልማት ላይ ናቸው፡፡ በልማት ባቡር ሃዲድ ውስጥ ገብተዋል ልማታቸውን እያሳደጉ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን እንደሚያጠናክሩ ጥርጥር የለንም፡፡ የልማትን መንገድ መምረጡ ሁለት ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ቀዳሚው የካህናትን ኑሮ ሁኔታ ያሻሽላል፣ የካህናት ልጆች በጥሩ ት/ቤት እንዲማሩ፣ ቤተሰቦቻቸውም በመልካም ሁኔታ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡ ሌላው ካህናት ከመንፈሳዊው አገልግሎት ጐን ለጐን ራሳቸውን በሥራ ጠምደው በሚያገኙት ገቢ ከራሳቸው አልፈው ሌላውን ይረዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ የቀደሙት አባቶቻችን መንገድ ነበር፡፡ በቀጣዮቹ አሰርት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከሙዳዬ ምጽዋትና ከሰበካ ጉባኤ አስተዋጽኦ ከምታገኘው ገቢ ይልቅ ከልዩ ልዩ የልማት ተቋማት የምታገኘው ሊልቅ እንደሚችል አሁን እየሄድንበት ያለው መንገድ አመላካች ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊ መልእክት

የሰበካ ጉባኤ ዕድገትና የአባቶች አሰተዋጽኦ፣

megabe_hadis_hawaz

የቀደሙት አባቶቻችን በየዘመናቸው በእግዚአብሔር ኃይል እየተመሩ እና እየተረዱ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታላላቅ ሥራዎችን ሠርተው አልፈዋል፡፡ ስማቸውም በመልካም ሥራቸው ሁል ጊዜ ሲወሳ ይኖራል፡፡

‹‹አንትሙሰ አኅዊነ ተዘከሩ ቃለ ዘነገርክሙ ቀዲሙ ሐዋርያቲሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ›› ‹‹ወንድሞቻችን ሆይ እናንተስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት መጀመሪያ ያስተማሯችሁን ቃል አስቡ›› በማለት በያዕቆብ ወንድም በይሁዳ መልዕክት ቁጥር 17 ላይ የተነገረውን መሠረት በማድረግ እኛም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አስዋጽኦ ያደረጉትን ማሰብና ማስታወስ ተገቢ ይሆናል፡፡

ሰበካ ጉባኤ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ደርሶ ካህናትና መእመናን ተባብረው በአንድ አቋም ቤተ ክርስቲያን በሀብት እንድትበለፅግ፣ አገልጋይ ካህናት ከነበረው ልመና እና የሰው እጅ ከማየት ውቅያኖስ ወጥተው የተሸላ ኑሮ እንዲኖሩ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሰፋ፣ ምእመናን የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ቅሬታቸውንም በአግባቡ እንዲገልጡ፣ በቃለ ዓዋዲው አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 11 ላይ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላላ አስተዳደር ለትምህርትና ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ፣እንዲሁም በየሰበካው ለሚከናወኑት የልማት ሥራዎች የሚስፈልገው ገንዘብ በሕግና በሥርዓት እየተመዘገበ የቤተ ከርስቲያኒቱ ህልውና ማስጠበቂያ እንዲሆን ራዕይ ከነበራቸው አባቶች አንዱና ቀዳሚው ሁለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ መሆናቸውን ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያው በይሁዳ መልዕክት በተቀመጠው ኃይለ ቃል መሠረት ስታስባቸው ትኖራለች፡፡ ከባዶ ተነስተው በዚያ የጨለማ ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከዚህ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንድትደርስ በሀገር ውስጥ ከመንግሥት ይደርስባቸው የነበረውን ጫና ተቋቁመው፣ በግብጽ ቤተ ከርስቲያን ይፈጸም የነበረውን ሴራ ተጋፍጠው፣ ቤተ ክርስቲያናችን የራሷ ፓትርያርክ እንዲኖራት ከማድረግ ጀምሮ በደርግ መንግሥት በሰማዕትነት እስከ መሰዋት የደረሱላት ቤተ ከርስቲን በዓለም ትልቅነቷ ጎልቶ እንዲታይ ያደረጉ አባት መሆናቸው፡- መቼም መቼ አይረሳም፡፡ ሁልጊዜም ያልተዛባ አእምሮ ባላቸው ሰዎች ሲዘከር ይኖራል

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከአቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ የተሰጠ አባታዊ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤

 • የሀገርን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤

 • በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዛችሁ በየሆስፒታሉ የምትገኙ፤

 • የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ፤

 • በተለያየ ምክንያት ከሀገራችሁ ከኢትዮጵያ ወጥታችሁ በዓለሙ ሁሉ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤

የዘመናት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2004 ዓ.ም ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2005 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ፤ ለሚቀጥለውም ዘመን በቸርነቱ ጠብቆ በሰላምና በጤና እንዲያደርሳችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ዘወትር ያለማቋረጥ ጸሎቷን ወደፈጣሪ ታቀርባለች፡፡

"ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ስብሐተ ሐዲሰ" "እግዚአብሔርን በአዲስ ምስጋና አመስግኑት" ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት (መዝ. 149 ቁ.1)

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ባለፈው ዓመት ስለተደረገልን መልካም ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ በአዲሱ ዓመትም በአዲስ መንፈስ አዲስ ሥራን ለመሥራት እንዲረዳን የልመና ጸሎት ማቅረብ ይገባናል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

“ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ወይጸግቡ ጠላት ገዳም ወይረውዩ አድባረ በድው”

“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል የምድረ በዳውም ተራሮች ይረካሉ” 

መዝ.64፡11-12

በመምህር ሙሴ ኃይሉ /B.TH, MA in Philo/

የዘመን አጀማመርን ወይም አፈጣጠርን በተመለከተ እጅግ የረቀቁ የሥነ መለኮት ሙሁራንም ቢሆን አንድ የሆነ እሳቤ ላይ አልደረሱም፡፡ በዚህ ዙርያ ሊቃውንቱ ከሚያትቱት የዘመን ምስጢራዊ ትምህርት ንድፈ ሐሳብ ጥቂቶቹን ለግንዛቤ ያህል ከዚህ ቀጥለን እንመልከት፡፡ መሠረተ ዘመንን አስመልክቶ በሥነ መለኮቱ አስተምህሮ ውስጥ በስፋት የሚተነተኑ ሦስት ዋና ዋና ንድፈ ሐሳቦች አሉ፡፡ ቀዳሚው “ይህ ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ ጊዜ /ዘመን/ ነበረ” የሚል ንድፈ ሐሳብ /theory/ ነው፡፡ ተከታዩ “ፍጥረታትን ወደ መኖር ከማምጣቱ ወይም ከመፍጠሩ በፊት አስቀድሞ ፍጥረታትን ለመፍጠር እንዲያመች ጊዜ ተፈጠረ” የሚል ንድፈ ሐሳብ ሲሆን ሦስተኛው “ዘመን /ጊዜ/ የተፈጠረው ከተፈጠሩት ፍጥረታት አብሮ እንጂ በፊትም በኋላም አይደለም” የሚል ነው፡፡

ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አመንኩ በዘነበብኩ ብላ ተቀብላ የምታምነውም ሆነ ለተከታዮቿ ምዕመናን የምታስተምረው ትምህርተ ዘመን በሦስተኛ ደረጃ የቀረበውን ትምህርት ነው፡፡

ይህንኑ አስተምህሮ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ሲያስፋፋ ፍጥረት በተወሰነ ቦታና ጊዜ የተዘረጋ አምላካዊ ጥበብና ካለመኖር ወደ መኖር የተለወጠ የአምላክ ክዋኔ ነው፡፡ በመሆኑም ዘመንም /ጊዜም/ ቢሆን በዚህ አምላካዊ ክስተት ውስጥ የሚገለጽ ከፍጡራን ጋራ ፍጡራንን ለማገልገል የተፈጠረ ጸጋ ነው በማለት ይገልጸዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አስተላለፈ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ ቤተ ክርስቲያንን በአግባቡ የሚመራ ቅዱስ አባት እግዚአብሔር በመንበሩ እንዲያስቀምጥና የምርጫውን ሂደት ሐዋርያዊ ትውፊቱን ጠብቆ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትና አድባራት ከጳጉሜ አንድ እስከ መስከረም አስር ቀን በአጠቃላይ አስራ አምስ ቀን የጸሎት ቀናት ጸሎት እንዲደረግ ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም በይፋ ጥሪውን አስተላለፈ፡፡

መጪው ዘመን እግዚአብሔር የተባረከ እንዲያደርግልንና ምርጫው ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው መርሐ ግብር መሠረት በአግባቡና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንድፈጸም እግዚአብሔር እንዲረዳን የሁሉም ገዳማት አባቶች መነኮሳትና መነኮሳይያት፣ በየበረሀው የሚገኙ አባቶቻችን መናንያን፣ አገልጋዮች ካህናት፣ ዲያቆናትና ምዕመናን አብዝተው በጸሎት እንዲተጉ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታን አስመልክተው ያስተላለፉትን ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

felseta2004

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ

 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አኅጉር የምትኖሩ

 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ

 • በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ

 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ያስተላለፉትን መልእክት

"ጎበዞች ሆይ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ" (፩ ዮሐ. ፪፣፲፫)

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ ወጣት ክርስቲያኖች ሆይ፤

ከላይ በርእሱ የተጻፈው ትምህርት ፍቊረ እግዚእ ሐዋርያው ቅ/ዮሐንስ ለወጣቶች ያስተማረው ነው። ሐዋርያው በዚህ ምዕራፍ ላይ ምዕመናን በሦስት የዕድሜ ደረጃ (ማለትም ልጆች፣ ጎበዞች/ወጣቶች፣ አባቶች በማለት) መድቦ ለሁሉም እንደሚስማማው መሠረታዊ የክርስትናን መልእክት አስተላልፏል።

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ያስተላለፉትን መልእክት

አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐ ዱ አምላክ አሜን !

"በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ" መዝ፡45፥16

በየዓመቱ በዓለ ጰራቅሊጦስን የምናከብረው ቤተ ክርስቲያናችን የተመሠረተችበት ቀን ከመሆኑም በላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት አባቶቻችን ወርዶ ጽናትን፣ ኃይልን፣ ብርታትን ያጐናጸፈበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ቀን የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ልደት ስናከብር ተርበው ተጠምተው በእሳት ተቃጥለው ለአናብስት ተጥለው በመንኮራኮር ተፈጨተው በመጋዝ ተሰንጥቀው ጥርሳቸው እየረገፈ አንድም ጊዜ ሳይማረሩ ይልቁንም የእምነት ፍሬ ነው እንካችሁ እያሉ ጽናት ያስተማሩንን ደጋግ ቅዱሳን አባቶቻችንን እና ደጋግ ቅዱሳት አንስትን እያሰብን ነው፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ልደት ስናከብር ዓለም በዓሏን ስታከብር ያለዋጋ እንደምታከብር ሳይሆን የተከበረ በወርቅና በብር የማይለካ የአባቶች የሕይወት ዋጋ እንደተከፈለበት ልናምን እንዲሁም ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል፡፡ለቤተክርስቲያናችን የሕይወታቸውን ዋጋ ከከፈሉት ቅዱሳን መካከል በርካታ ወጣቶች ነበሩ፡፡ በወጣትነታቸዉ ዓለምን ንቀው የዚህን ዓለም ተድላና ደስታ ጥለው ከመጥገብ መራብን ከመርካት መጠማትን ከመልበስ መራቆትን ከመክበር መዋረድን መርጠው ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን አንክድም ብለው ሕይወታቸውን ለዓለም ውርደት በሚመስል ለወንጌል ግን የክብር ክብር በሆነው ጎዳና ሔደው እንደፈጸሙ ገድለ ቅዱሳን ምስክራችን ነው፡፡

Read more...

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ