Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ለአክሱም ጽዮን ያልተዘረጉ እጆች ለማን ይዘረጋሉ?

በመጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ

በተወላጁም ሆነ በባዕዱ፣ በሐበሻውም ሆነ በፈረንጅኛው ቋንቋ ስለ አክሱም ጽዮን የተጻፉትን የታሪክ መጻሕፍት ስናገለባብጣቸው ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ለሀገራችን ለኢትዮጵያ የእምነቷና የሥልጣኔዋ መሠረት፣ የታሪካውያን ቅርሶች ግምጃ ቤት፣ በጥቅሉ የመንፈሳዊውና የዓለማዊው ጉዳይ ሁሉ መገኛ መሆንዋን በስፋትና በጥልቀት እንገነዘባለን፡፡

በቤተ መንግሥቱም ሆነ በቤተክህነቱ እየተሠራበት ያለው ሥርዓትና ወግማዕረግ፣ ሌላውም ስሪት ሁሉ ከርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው፡፡

የሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና የአገልጋዮች ካህናት የመዐርግ ስሞች የንዋያተ ቅድሳቱ ሁሉ ስሞች ጭምር ሥርዓተ ቅዳሴውና ሥርዓተ ማኅሌቱም የተገኘው ከርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ነው፡፡

ሌላው ቀርቶ በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መሥዋዕተ ሐዲስ የሚሠዋባቸው ታቦታት ሁሉ መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋባት ከነበረችውና ዛሬም መሥዋዕተ ሐዲስ እየተሠዋባት ያለችው በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን የምትገኘው የታቦተ ጽዮን ቅጅና ብዜቶች ናቸው፡፡ ይህም ከሆነ ዘንድ የመላ ኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ለታቦተ ጽዮን ጽዮን ዐሥራት ማውጣት ግዴታቸው ነው፡፡

መልካም የሆነው የሕዝቡ መንፈሳዊ ባሕልና ትውፊትም ሁሉ የተገኘው ከርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ነው፡፡ የታሪካውያን ቅርሶች አጠባበቅ፣ አያያዝና እንክብካቤ ትምህርት የተገኘውና ከአባቶች የተረከቡትን አደራ በታማኝነት ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍንም የምንማረው ከርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ነው፡፡ በሁሉም ነገር ከአክሱም ያልተገኘ ትምህርት ከአክሱም ያልተገኘ ታሪክ ከአክሱም ያልተገኘ ነገርና መልካም ምሳሌነት የለም፡፡

ስለዚህ በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ መዘክር እስከ አሁን ድረስ በቀደሙት አባቶቻችን በጥንቃቄ ተይዘውና ተጠብቀው የቆዩት የተለያዩ ቅርሶች ካለፈው በበለጠ ሁኔታ በዘመናዊ አያያዝ ተጠብቀው ለትውልድ ይተላለፉ ዘንድ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተለየ ጥረትና አመራር ሰጭነት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን በከፍተኛ ወጭ ዘመናዊ መዝየም በማስገንባት ላይ ትገኛለች፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በልባችን የልማት ሐውልት ልንተክል ይገባል፡፡

ተስፋዬ ውብሸት

ከቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት

ዋና ሥራ አስኪያጅ

ይህ ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን የወንጌልን ብርሃን ለጨለማው ዓለም የመግለጥና ነባራዊ እውነታዎችን ባገናዘበ መልኩ የማከናወን ኃላፊነቷ በእጅጉ የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፡፡ ወደ እውነት መድረስ የሚሻውን ትውልድ በመምህሮቿ በኩል የምታግዝበት ዘመን ነው፡፡ ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያትና አበው የሠሩትን ሥራ ዛሬም በዚህ ዘመን ሊሠራ የሚገባው የቤት ሥራ እንጂ የተቋጨ የተጠናቀቀ ጉዳይ አለመሆኑን መረዳት ይገባል፡፡

ለእኔ ይህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን የሩጫ ዘመን መሆን እንደሚገባው ይሰማኛል፡፡ የሩጫው መነሻ ደግሞ የመምህሮቿ ትምህርት ነው፡፡

የወንጌል ትምህርት ደግሞ የልማት አንዱ ምሰሶ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን በከተማና በሃገረ ስብከቶች ብዙ መምህራኖች /ሰባክያን/ አሏት፡፡ እነዚህም ሰባኪያን በሕዝቡ ውስጥ የማይነጥፍ የልማት ሐውልት ሊተክሉ የሚችሉ መሆናቸው ሲታሰብ ቤተ ክርስቲያናችን ኃይል እንዳላት መገመት ይቻላል፡፡ የወንጌል ስብከት ትልቁ የልማት ማህደር ቢሆንም ዛሬ የልማት ሐውልት በልባችን ልንተክል እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያናችን ሊሰበክ ይገባል፡፡ የጥንት አባቶች እንደ ላሊበላና አክሱም ያሉትን ታላላቅ ቅርሶች ለትውልድ በማቆየታቸው ሀገራችን በዓለም ታሪክ መዝገብ ስሟ እንዲመዘገብና እንዲወሳ እየተደረገ መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በዚህም ሀገራችን ትልቁን ጥቅም እያገኘችበት መሆኑና የሀገሪቷ ቁልፍ የገቢ ምንጭ በመፍጠር የቱሪስት ፍሰት እንደ አባይ ተፋሰስ ሳያቋርጥ ወደ ሀገራችን እንዲገባ መንገድ ፈጥሯል፤ ይህ ዘመን የማይሽረው ክስተት የተፈጠረው በቀደምት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባታዊ መልእክት

"በመስቀሉ ሁሉን አስታረቀ"

መለያየት የኃጢአት ውጤት እንደሆነ ሁሉ አንድነት ደግሞ የሰላም፣ የፍቅርና የስምምነት ውጤት ነው፡፡ የሰው ልጅ በተከተለው የተሳሳተ አማራጭ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ንብረት ወይም ግንኙነት ሲያጣ ከሌሎች ፍጥረታት ጋር የነበረውን አንድነትም በተመሳሳይ ሁኔታ አጥቶአል፡፡ ይልቁንም የእርስ በርስ መግባባት በመጥፋቱ የሰው ዘር በተለያየ ጎራ እየተሰለፈ በጥላቻ መተያየቱ የዘወትር ክስተት ሆነ፡፡

የተከሰተው መለያየት በሥጋዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ከመምጣቱ በፊት ዓለማችን በመንፈሳዊ ሕይወቷ በኩል በሁለት ጎራ ተከፍላ ትኖር ነበር፣ በአምልኮተ እግዚአብሔርና በአምልኮተ ጣዖት፡፡

እግዚአብሔርን ያመልኩ የነበሩ ሕዝበ እሥራኤል የእግዚአብሔር ሕዝብ ተብለው ሲታወቁ፣ ጣዖትን ያመልኩ የነበሩ ደግሞ አረሚ፤ አረማውያን ወይም አሕዛብ ይባሉ ነበር፡፡ ሁለቱ ወገኖች የማይግባቡና በክፉ ጥላቻ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ናቸው፤ ቢሆንም ጥላቻው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውምና ይህንን የሚያስወግድ የእግዚአብሔር ጥበብ በዓለም እንዲገለጥ የእግዚአብሔር አምላካዊ መሻት ነበረ፣ ይህም መሻት በጌታችን በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጻሚ ሆነ፡፡ የሰው ልጅ ጠላቶች ኃጢአትና እሱን ተከትሎ የመጣው መለያየት ናቸው፤ የእግዚአብሔር ጥበባዊ አሠራርም ያነጣጠረው በኃጢአትና በውጤቶቹ ላይ ነው፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጠ አባታዊ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፤

 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤

 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤

 • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤

 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ

  ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት

       


ሰማይንና ምድርን፣ በውስጣቸው የሚገኙ ፍጥረታትን የሚታዩትንና የማይታዩትን የፈጠረ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ሉቃስ 2ዐዐ3 ወደ ዘመነ ዮሐንስ 2ዐዐ4 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ ፡፡

<<ዘይሔድሳ ለምድር በበረከቱ>>

‹እግዚአብሔር አምላክ ምድርን በበረከቱ ያድሳታል› /ድጓ/

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እኛም እንደምንገነዘበው እግዚአብሔር አምላክ በፍጡራን አእምሮ ሊመጠን በማይችል በረከቱ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ በማያቋርጥ ሒደት እያደሰ ይኖራል ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታት እየታደሱ እንዲተካኩ በማድረጉ የቀደመው ሲያልፍ አዲሱ ሲተካ የሕይወት ጉዞ የማያቋርጥ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎአል ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ቁጭት በቤተ ክህነት

ልዑልሰገድ ግርማ

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

ቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም የግንቦት 20፣ 20ኛ ዓመት የድል በዓል ማጠቃለያ በሚሌኒየም አዳራሽ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል፤ በዚሁ መድረክ ላይ የተላለፈ አንድ መልእክት ደግሞ እጅግ አስደምሞኛል፡፡ የዘንድሮው የግንቦት 20 በዓልን ያጀበውን የታላቁን የህዳሴ (የዓባይ ግድብን) የተመለከተ ነበር መልእክቱ፡፡ ‹‹ድሮ ድሮ የዓባይ ገባሮች በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሆነዋል፡፡ ሕፃን፣ ወጣት፣ ዐዋቂ ሳይል ሁሉም ለግድቡ የሚችለውን በማዋጣትና ቦንድ በመግዛት ገባርነቱን እየገለጸ ይገኛል፡፡ የድሮዎቹ ገባሮች የኢትዮጵያን ለም ዐፈር እየጠራረጉ ለባእዳንና ለሜዲትራኒያን ባሕር እየገፉ ወስደዋል፡፡ ያሁኖቹ ገባሮች ግን ተመሳሳይ ተግባርን የሚያበረታቱ ሳይሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት የሚገባ ውጤትን የሚያመጡ ናቸው›› የሚል ነበር መልእክቱ፡፡ እኔ ድንቅ መልእክት ብየዋለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ከሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ባላት መዋቅር ለተመሳሳይ ጉዳይ የራሷን ድርሻ እየተወጣች ትገኛለች፡፡ ይኸውም በቦንድ ግዢና በመዋጮ ይገለጻል፡፡ ይህም ተገቢና ወቅታዊ አስተዋጽኦ ነው፡፡

የደርግ መንግሥት ግብዓተ መሬት ከተፈጸመ ዕለት ጀምሮ በሀገራችን በርካታ ለውጦችን እያየን ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተገቢውንና ትክክለኛውን ዕውቅና የሚሰጥና በዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖች ውስጥ የተካተቱ ሰብዓዊና ዴሞክራሰያዊ መብቶችን ሊያስከብር የሚችል ሕገ-መንግሥት ጸድቋል፣ ታላላቅ የልማት አውታሮች ተገንብተዋል፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሰሚነት ጨምሯል፣ ዴሞክራሲያዊነትን የተላበሱ አገር አቀፋዊና አካባቢያዊ ምርጫዎች ተካኺደዋል፣ በርካታ የሆኑ ተቃዋሚ (ተፎካካሪ)ፓርቲዎች በአገሪቱ ጉዳይ ድምፃቸውን አሰምተዋል፣ በርካታ የመንግሥትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገንብተዋል፤ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተስፋፍተዋል፣ የሴቶች እኩልነት ተከብሯል፣ ድህነትና ረሃብን ለማጥፋት ጥረት ተደርጓል፣ ወዘተ. አሁን ደግሞ ኢትዮጵያን ወደሌላ ደረጃ ለማሸጋገር የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ታቅዶና ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ተመክሮበት ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ በቤተክህነታችንስ?

በተጨማሪ ያንብቡ…

ይህን ያውቃሉ?

 • "ቅድስት ቤተክርስቲያን አንዲት ማኅበር ብቻ እንደሆነች ያውቃሉ?"
 • በአዲስ አበባ የሚገኙ ማኅበራት የየራሳቸው ቢሮ እንዳላቸው፤ ሠራተኛ ቀጥረው እንደሚያሠሩ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ገቢ እንደሚሰበስቡ፤ የቤተክርስቲያኒቷን ደረሰኝ ግን እንደማይጠቀሙ፤ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ፈቃድ እንደሌላቸው፤ የባንክ አካውንት እንዳላቸው፤ ባንክ ሂሳባቸውንም ቤተክርስቲያን እንደማታውቅ፤ ታዲያ ገንዘቦን እና ጉልበትዎን ለማኅበር ሲሰጡ ለብልጣብልጥ ሰዎች እየሰጡ እንደሆነ ያውቃሉ? ግን ለምን?
 • ብዙ የተማሩ ሰዎች ሥራቸውን እየለቀቁ ለማኅበራት ቅጥረኛ መሆናቸውንስ ያውቃሉ? ለምን ይመስሎታል? የተሻለ ደመወዝ ስላገኙ፤ ኦዲት ስለማይደረጉ እንደፈለጉ ገንዘብ ለማግበስበስ፣ ግምገማ ስለሌለባቸው፤ በሃይማኖት ስም ማታለል ስለሚያረካቸው፤ ለመንግሥት ግብር ስለማይከፍሉ፤ ቫት ስለሌለባቸው፤ ወይ መማር!
 • አንዳንዶች ማኅበራት በየወሩ የገንዘብ መቀበያ ካርድ አሳትመው እንደሚያሰራጩ ያውቃሉ? ምዕመናን ከደሞዛቸው በየወሩ ማኅበራቱ ወደ ከፈቱት ቢሮ በመሄድ እንደሚከፈሉስ? ይህንንም ጉዳይ ቤተክርስቲያኒቱ እንደማታውቀው ያውቃሉ? የዚህ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በምዕመናን ገንዘብ እንደሚነግዱስ? ደርጅታቸውስ በርስዎ ገንዘብ እንደሚንቀሳቀስ ያውቃሉ? ካወቁስ ምን መፍትሔ ወሰዱ? አይ ወንጀል!

ከዚህ ሁሉ የከፋ ፈተና የሆነው ምን እንደሆነ ያውቃሉ?

ከዚህ ሁሉ ለቤተክርስቲያን የከፋ ፈተና የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ለምን መሰልዎት? በአንድ ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ሁለተኛው ጠቅላይ ቤተክህነት ሆኗል፡፡ እንዴት ቢሉ ከፈለገ ማኅበሩ በራሱ ሥልጣን የሃይማኖት ሕፀፅ አለብዎት ብሎ ያወግዞታል፤ 17 መምሪያ እንደ ጠቅላይ ቤተክህነት በሥሩ አለው፡፡ ሌላ ማኅበር እንዳይኖር ይታገላል፤ ይህንን የሚያደርገው ለቤተክርስቲያን በማሰብ ሳይሆን አባላቱ ሌላ ማኅበር ቢመሠረት እንዳይከፈሉበት በመሥጋት ነው፤ በርካታ የንግድ ተቋማት በመላ ሀገሪቱ አለው፤ በነዚህ የንግድ ተቋማት የሚንሸራሸረው የሀብት መጠን ቤተክርስቲያን አታውቀውም፡፡ ከውጭ የሚያስገባቸውን ማንኛውንም ዕቃ ያለቀረጥ ያስገባል፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱ እንድታውቅ አይፈቅድላትም፤ ተጠሪነቱ ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ቢሆንም ከመምሪያው ጋር እንደማይሠራ በተደጋጋሚ ገልጿል፡፡ ለመሆኑ እርስዎ የቤተክርስቲያን አባል ኖዎት? ወይስ የማኅበረ ቅዱሳን?

የጉዞ ማኅበራትስ ጥሩ የንግድ ሥራ እንደሆኑ ያውቃሉ? ስለ ጻድቁ ዕገሌ እጃችሁን ዘርጉ ሲሏችሁ ደስ ብሏችሁ ያውቃል? እርስዎ ስለመልካም ስራዎ ደስ ይልዎታል፤ ኮሚቴው ደግሞ እርሶን ስላታለለ እና እንደ ጅል ስለቆጠሩዎት ደስ ይለዋል፤ ኮሚቴዎቹ በቤተክርስቲያኒቱ ስም መተዳደሪያቸውን በጥሩ ሁኔታ አውቀውበታል፡፡ እርሶ ፊት የሚናገሩት ካህናትን አትመኑ ቤተክህነትን ተውት ከኛ ጋር ሥሩ የሚል ነው፤ የእነርሱስ ቦታ የት ይሆን? በዚህ ምክንያት እርሶም አይከሱ እነርሱም ለእርሶ ራሱን የቻለ ጠቅላይ ቤተክህነት ሆነው አሥራቶትን ይቀበላሉ፡፡ ስእለቶትን ይረከብዎታል እየሸጡ ይኖሩበታል፤ እርሶ በደስታ እየሳቁ እነርሱም በሕሊና እየተሳቀቁ አብራችሁ ሳትተዋወቁ ትኖራላችሁ፡፡ ይሁና! ግን እስከ መቼ?

በስሟ የሚተገበረውን ይህንን እኲይ ተግባር ሁሉ ቤተክርስቲያኒቷ አታውቀውም ሲባል እውቀቱ የላትም ማለት ሳይሆን ይህን የሚያደርጉ አካላት ሕገ ወጦችና በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ሥር አይደሉም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያንን በማኅበራት በኩል ለመርዳት ከሚሞክሩ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን በኩል ይርዱ፡፡ ምክንያቱም የእያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ወጪና ገቢዋ ይታወቃል፡፡ የማኅበራቱ ግን እንደማይታወቅ አስቀድመን ነግረንዎታል፡፡

"የመንገድ ደህንነት የተግባር 10 ዓመት" የትግበራ ዕቅድ ይፋ የሚደረግበት ቀን የሃይማኖት አባቶች በጋራ ያስተላለፉት መልዕክት

በዛሬው ዕለት የሃይማኖት አባቶች በጋራ የተሰበሰብን ለሕዝባችን ለማስተላለፍ የፈለግነው ዋና ጉዳይ ዘወትር የዓለማችን ሕዝብ በሰላም ውሎ በሰላም እንዲያድር ወደ ፈጣሪ አምላካችን ጸሎት በማቅረብ ላይ ብንሆንም በሰዎች ጥንቃቄ ማነስ የሰዎች ሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መድረስ አሁንም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመምጣቱ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል፡፡

በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት በዓለማችን በአሁኑ ወቅት ከ1-3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለሞት እንዲሁም ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ይዳረጋሉ፡፡ ይህም በሀገራችንም 2200 ሰዎች ለሞትና ከ8000 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

ስለዚህ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የዓለማችን ትልቅ ስጋት ሆኖአል፡፡ ሆኖም እኛ የሃይማኖት አባቶች በሰው ልጆች ስሕተት የአንድ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ መደረግ እንደሌለበት እናምናለን፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የ2003ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን ያስተላለፉት

ቃለ ምዕዳን

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

- በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ ያላችሁ፤

- ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤

- የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤

- በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤

- እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቼ ልጆቼ!

 

በአምላክነቱ ኃይል ሞትንና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሣው ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺህ ሦስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

እርቅ ለፍትህ፣ ለሰላምና ለልማት

በልዑልሰገድ ግርማ

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ

ከ199ዐዎቹ ጀምሮ እርቅ በዓለም ላይ ከፍተኛ ትኩረት ከተሠጣቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ 21ኛው ክፍለ ዘመን ‹‹የኢንፎርሜሽን ዘመን›› ነው የሚባለውን ያህል ‹‹የእርቅ ዘመን›› ተብሎ ሊጠራም ይችላል የሚሉ ምሁራን አሉ፡፡ ዓለም አሁን በደረሰችበት የእድገት ደረጃ ሰላምን፣ ልማትንና ማኅበራዊ ፍትህ ጐን ለጐን ማራመድ ለዴሞክራሲያዊና ማኅበራዊ ደህንነትን መስፋፋት የማያወላዳ ቀጥ ያለ መንገድ ሆኗል፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው እርቅና የእርቅ ግንዛቤ ሲስፋፋ ብቻ ነው፡፡ እርቅ እንደ ኢትዮጵያ በግጭት ውስጥ ለቆዩ ሀገሮች ጠቃሚ መሆኑ እየታመነበትና ዘመናዊ አስተሳሰብና አሠራርም እየሆነ መጥቷል፡፡ በእርቅ ውስጥ እውነትና ፍትህ ታምቀው ስለሚገኙ በዳይን ይቅርታ የሚያስጠይቅና ተበዳይም ይቅርታን የሚሰጥበት ሂደት ተፈጥሮአዊና ሕጋዊ ነው፡፡

እርቅ ሰላምን፣ ዴሞክራሲንና ማኅበራዊ ፍትህን ሊያሰፍንና ሊያስፋፋ የሚችል ረቂቅ መሣሪያ ነው፡፡ እርቅ ባለፈው ጊዜ የተፈፀመውን በደልና ከፍተኛ አለመግባባት በመለየትና አጥፊ የሆኑትን አስተሳሰቦችና ድርጊቶችን ወደጠቃሚና ገንቢ ግንኙነት በመቀየርና እንዳይደገሙ ለማድረግ ዘላቂ የሆነ ሰላምንና ልማትን ማምጣት የሚችል ማኅበራዊ ሂደት ነው፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ለውጥና ልማት በቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያናችንን የተሻለችና ጠንካራ ለማድረግ

ልዑል ሠገድ ግርማ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ውጤታማና ዘላቂ የሆኑ ውጤቶችን ማስመዝገብ ከፈለገች የዘመናዊውን ዓለም አካሄድ በመከተል ዓላማዋንና አካሄዷን መልሳ መላልሳ በማየት ማሻሻልና መራመድ መቻል አለባት፡፡ ይህንንም ለማድረግ አዳዲስ ስልቶችን፣ መዋቅሮችንና ሲስተሞችን (ሥርዓቶችን)ማዋሐድ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ስልታዊ ትኩረትና ውጤታማ የሆነ አሠራርን ይፈጥራል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ የሆነ ተፈጥሮና ከሌሎች ተቋማት የምትለይበት ልዩ ባሕርይ ሲጠበቅ ብቻ ነው፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ