Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ

ሥልጣን ያላቸውን ይሳደባሉ

ይሁዳ. ቁ. 8

ሰዎች የሚድኑበት የሕይወት መልዕክት ወደሰዎች መድረስ ከጀመረ ሁለት ሺህ ዘመን በላይ ተቆጥሯል፡፡ በዚህም የሕይወት ራስ ከሆነው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኋላ አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ሰባ ሁለቱ አርድዕት ሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በረሃብና በጥም በጾምና በጸሎት እየደከሙ ጀርባቸውን ለግርፋት ገጻቸውን ለጽፍአት በመስጠት በዘመናቸው ወንጌልን ሰብከዋል፡፡

እግዚአብሔርም ለዚህ ልዩ የመዳን ወንጌል ከሐዋርያት በኋላ አርድዕትን በኋላም ሊቃውንትን፣ መምህራንን፣ ሰማዕታትን በየጊዜው እያስነሳ አስተምሯል ዛሬም ህዝቡን ያጽናናሉ፣ ይመክራሉ፡፡ የዚህ የተቀደሰ ዓላማ ፈጻሚዋ ደግሞ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስትሆን ለሰው ልጅ ድኅነት መፈጸም ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን ፈጻሚ ካህናት አሉዋት፡፡ የክህነት ተዋረዱም ዲቁና፣ ቅስና፣ ኤጲስ ቆጶስነት /ጵጵስና/ ናቸው፡፡ በተለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ክርስትናን በጃንደረባው ባኮስ አማካኝነት ተቀብላ በታላቁ አባት አባ ሠላማ ከሳቴ ብርሃን ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፣ የወንጌል አገልግሎት በስፋት እንደተጀመረ ይታወቃል፡፡ ዛሬም ቢሆን ክርስቲያኖች ባሉበት ሥፍራ ሁሉ በአርባና በሰማኒያ ቀን ልጅነት ሰጥታ በሰንበት ት/ቤት ሰብስባ ታስተምራለች፡፡ ዋነኛ ተልዕኮዋ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡

ዛሬ በደረስንባቸው ግዜያት ደግሞ ቴክኖሎጂ አንዱ መልካሙን ነገር የምንማርበት እና የምናስተምርበት ወንጌልን ማስፋፍያ፣ ነፍሳትን የመማረኪያ መንገድ ድረ ገጽ (Website) ነው፡፡ ይህንን በአግባቡ ያለመጠቀም ደግሞ ምን ያህል ጎጂ እንደሆነ ከአንባቢያን የተሰወረ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ስልጣኔ ተጠቅመን ምዕመናንን ማስተማር፣ መምከር፣ ማጽናናት ስንችል "ሐራ ዘተዋሕዶ፣ አባ ሠላማ፣ አንድ አድርገን፣ ደጀ ሰላም" ወዘተ በሚል ስያሜ የተከፈቱ የጡመራ መድረኮች ብዙ የሀሰት መልዕክቶችን እየተመለከትን ሲሆን እውነተኛ አማኞች ነገሮችን እንዲለዩ መልዕክት ማስተላለፍ ግዴታችን በመሆኑ ጥቂት ልንል ወደድን፡፡

በተለይ በአሁን ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለስሜ ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እህቶችን ወይም አባትን ወይም እህትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፣ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል" ማቴ. 19፡29፣ ማቴ. 19፣12 ባለው ቃል መሰረት ከዚያም በሐዋርያት ይህ የተቀደሰ ሕይወት ጌታን ደስ ለማሰኘት፣ የጌታን ነገር ለማሰብ የሚጠቅም ለወንጌል አገልግሎት ትጋትን እንደሚሰጥ በተደጋጋሚ ተሰብከዋል፡፡ 1ቆሮ. 7፡32 ክብር ይግባቸውና ብዙ ቅዱሳን አበው ወአእማት በዚህ ሕይወት አትርፈውበት የሕይወት አክሊል ተቀብለውበታል፣ አሁንም እየተቀበሉበት ይገኛሉ፡፡

ታዲያ ዛሬ ላይ ይህንን ሕይወት መኖር ያቃታቸው ያለ አንዳች ፍርሐት መንፈስ ቅዱስ ለቤተክርስትያን የሾማቸው አባቶችን መስደብና መንቀፍ ብሎም በስም እየጠቀሱ ማዋረድ አጸያፊ ከመሆኑም በላይ ምንኩስናን የሚጠላ የዲያብሎስ መመሪያ ተቀባይ መሆንም ጭምር ነው፡፡

ውድ አንባብያን ምዕመናንን ከአባቶቹ ለመለየት፣ ተማምነው ተከባብረው የኖሩትን፣ የራቀውን አቅርበው፣ የተጣላ አስታርቀው ያዘነ አጽናንተው፣ የሚኖሩትን አባቶች መንቀፍና ማዋረድ መብቱንም ሆነ ስልጣኑን ማን ሰጣቸው? ብለን ብንጠይቅ መልሱ አጭር ይሆናል፡፡ ዲያብሎስ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳም "እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ስጋቸውን ያረክሳሉ፣ ጌትነትንም ይጥላሉ፣ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ" በማለት ሲናገር ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ላይ ሲገልጥ "ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፡፡ እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደርያውንም በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ" ራዕ. 13፣5 በማለት ስድብ የዲያብሎስና የአባላቱም ሥጋውያን መሆኑን ገለጠልን፡፡

ምንኩስና የተቀደሰ ሕይወት እንጂ የኑሮ ፍልስፍና፣ አልያ ሰው፣ ሰራሽ ዘመን አመጣሽ አለመሆኑን ከላይ የጠቀስን ሲሆን መነኮሳት ደግሞ ሕይወቱን የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች ደግሞ ሊደክሙ፣ ሊስቱ ይችላሉ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ገዳም ውስጥ ምን እንደሚሰሩ ሲጠየቅ "በገዳም ውስጥ እንወድቃለን እንነሳለን ሌላ ምንም አንሰራም" በማለት መለሰ፡፡ ይህ ደግሞ የክርስትና ኑሮ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ "ኃጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም" በማለት ገልጧል 1ዮሐ. 1፡10፡፡ ማንም ደግሞ አንተ ይህንን አደረግክ አንቺ ይህንን አደረግሽ ብሎ ጣትን ማንሳትና መክሰስ በኢየሱስ ፊት ለክስ ያቀረቡዋትን ሴት ከሳሽ ፈሪሳውያንን መስሎና አህሎ መገኘት አይደለምን? የጌታም መልስ "ከእናንተ ኃጢአተ የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው"፡፡ ዮሐ. 8፡7 የዛሬዎቹ ደግሞ የጡመራ ድንጋያቸውን በቤተክርስቲያን አባቶች ላይ ማንሳታቸው ጻፎችንና ፈሪሳውያንን በግብር መድገም ነው፡፡ ውድ አማንያን እንዲህ ያለውን አጸያፊ የዲያብሎስ ተግባር ልናወግዘውና ልንርቀው ተገቢ ነው፡፡

በሌላ መልኩ በቤተክርስቲያናችን የትኛውንም አስተዳደራዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ የመጨረሻ ስልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሆን ውሳኔውም የቤተክርስቲያንና የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መሆኑን እናምናለን፡፡ ሐዋ. 15፡29:: ዛሬ ሁላችንም የምንመራበትን ቀኖና ቤተክርስቲያንን የወሰነ በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ የቅዱስ ሲኖደስ ውሳኔዎች መሆኑን ልብ ልንል ተገቢ ነው፡፡ ትናንትም ዛሬም ነገም ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ትክክል ሲሆን እኛ አማኞቹ ተቀብለን እንመራበታለን፡፡ ምዕመናን የዚህ ሁሉ ትችትና ማጣጣል ከወዴት እንደሆነ ልብ በማለት ለሚሆነው ሁሉ በጸሎት ፈጣሪን እያሳሰብን "ስለቤተክርስቲያን ሰላም ጸልዩ" እንዳለ ቅዳሴ፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ምዕመናንና ካህናት ስለቤተክርስቲያናችን በትጋት እየጸለይን ቢፅ ሃሳውያን ነቅተን በመጠበቅ የሴራቸው አልያ የጥፋታቸው ሰለባ እነዳንሆን ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ሁላችሁም የጡመራ መድረክ አዘጋጆች የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከሆናችሁና ትጋታችሁና ቁጭታችሁ ከቤተክርስቲያን ከሆነ ምዕመናን የሚጽናኑበትና የሚታነጹበት ወንጌል የሚስፋፋበትን መንገድ የምትፈልጉ ከሆነ ከስህተት ጉዞ መለስ በማለት መልካሙን አገልግሎት ትቀጥሉ ዘንድ ማደራጃ መምሪያው ጥሪውን ያቀርባል፡፡ 

"ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን"

ቢፅ ሃሳውያን

የፎንት ልክ መቀየሪያ