Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የትውልድ ቅብብሎሽ

በቀሲስ ቃለጽድቅ አሰፋ

"ትውልድ ይመጽ ወትውልድ የሐልፍ" ይላል መጽሐፍ እግዚአብሔር ዓለምን ከመሠረተ የሰውን ልጅ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሉላትን ስናስተውል እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን እንመለከታለን ግን ሞት ባይኖር ምን ይሆን ነበር ብለን ብንጠይቅ ቅዱሳት መጻሕፍት ከሚያስረዱን ውጪ አንዳች ማወቅ አንችልም፡፡ ምናልባትም መሬት ትሞላና ትጠባለች የሚል ተራ ወሬ ከማውራት በቀር የመወለድና የመሞት ህግ ግን አስገራሚ ነው፡፡

የትውልድ ቅብብሎሽም በዚሁ መልኩ በመወለድና በመሞት ሥርዓት የሚኖር ነው፡፡ ይህም ሥርዓት በሞት መጉደልን ሲያመጣ በልደት ይሞላል በዚህም ሒደት ውስጥ ሰጭና ተቀባይ አለ ማለት ነው፡፡ አባት ለልጁ ሲሰጥ የዛሬው ልጅ የነገ አባት ነውና ለቀጣዩ ያስተላልፋል፡፡ ይህ ቅብብሎሽ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሌላው ትውልድ እያለ ይቀጥላል ሁኔታው ላይቋረጥ ቢችልም ግን የሚሰጠው የሚወረሰው ሊለያይ ይችላል ቅብብሎሽ ግን መለኮታዊ ስሪት /እጅ/ ያለበት ስለሆነ እርሱ በቃ ሲል ብቻ ይቆማል፡፡

በዚህ ቅብብሎሽ ውስጥ ሰጭና ተቀባይ እንመለከታለን ሰጪ የሚቀድም ሲሆን ተቀባይ ደግሞ ተከታይ ነው፡፡ በዚህም ሥር ስርዓት መሠረት ተቀባይ ያለውን እሴት ሁሉ የአባቶቼ በማለት ይናገራል፡፡ የአባቶቼ ባሕል የአባቶቼ ሃይማኖት የአባቶቼ ሀገር፣ የአባቶቼ ሀብት በማለት ይገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሰጭና ተቀባይ መኖሩን ነው፡፡ በሰጭና በተቀባይ መካከል ግን መደማመጥ ካልመጣ እሴቶቹ ለአደጋ ይጋለጣሉ፣ ሃይማኖቱ፣ ባሕሉ፣ ሀገሩ፣ ሀብቱ ሁሉ እንከን ይገጥመዋል፡፡

በመሠረቱ የወደፊት ነገሮችን በትክክል ለመናገር የሚቻለው ዛሬ ላይ ያለወን ወጣት በትክክለኛ መስመርና አቅጣጫ መምራት ሲቻል ነው፡፡ ወጣት ማለት የትናንትናውን ከነገው ትውልድ ጋር ማገናኘት የሚችል ድልድይ ነው፡፡ ወጣትን ማእከል ያላደረገ ለዛሬ ብቻ ይተገበር ይሆናል፡፡ እንጂ ለነገ ማስቀጠል ግን አይታሰብም፡፡

 • ወጣት የሌላት ቤተ ክርስቲያን ነገን ማየት አትችልም

 • ወጣት ቤተ ክርስቲያን ቀጣይነቷን የምታረጋግጥበት አዲስ ደም ነው

 • ወጣት በሌለበት ቤተ ክርሰቲያን የተሰጣትን መለኮታዊ ሐላፊነት ለመወጣት አስቸጋሪ ነው፡፡ Youths are a bridge to connect old generation and new generation. ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ክፍል መቈጣጠር መምራት መንከባከብ ይጠበቅባታል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ትናንትናው ሁሉ ዛሬም ሰዎችን ለመንግሥተ እግዚአብሔር ከማዘጋጀት ጎን ለጎን ለሀገር ልማት፣ ለዕውቀት መዳበር ለታሪክና ለቅርሳቅርስ ጥበቃ መትጋት አለባት ይህ የቤተ ክርስቲያኒቱ የተለመደ ስራዋ ስለሆነ፡፡

 • ይህ ተግባር የተልእኮዋ አንዱ ተግባር ለመሆኑ ቀደምት ገዳማት አድባራት ሊቃውንትና መምህራን ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡ በዚህ ተግባር ውስጥ ወጣቶች ለሃይማኖት መሥፋፋት፣ ለሥራ ባሕል መሻሻል፣ ለሀገር እድገት ያላቸው ሚና ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ ትናንት ዛሬ አይደለም ባለንበት ዘመን በየደቂቃዎች ልዩነት እንኳን የሚለወጡ አያሌ ነገሮች አሉ፡፡ ትናንትና ግን ለዛሬ መሠረት ነው፡፡ ዛሬ የምንለው ትናንት ስላለ ነው፡፡ ስለዚህ ከትናንት የተቀበልናቸውን መልካም እሴቶች ለነገ ለማድረስ ዛሬ ላይ በጥንቃቄ መያዝ አለብን፡፡ የዛሬው ወጣት የነገይቱን ኢትዮጵያ የነገይቱን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የሚያስቀጥል በመሆኑ እንክብካቤ ምሪትና ጥንቃቄ ያሸዋል ጌታም "........ ጠቦቶቼን ጠብቅ ...." ዮሐ. 21፡17 በማለት የአደራ መልእክት አስተላልፏል፡፡

 • ወጣቶች ባሕላቸውን የሚያከብሩ፣ ሃይማኖታቸውን የሚወዱ፣ ፈጣሪያቸውን የሚፈሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል ምክንያቱም ወጣትነት ሁሉን ለመያዝ ለመጨበጥ ምቹ ጊዜ ነው አንዲት ሀገር ማንነቷን የሚያውቅ ታሪኳ የሚዘክር ተተኪ ከሌላት ማንቷን ከባዕድ እጅ መፈለጓ አይቀሬ ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ስለማንነታችን እኛ ከምናውቀው ይልቅ የባዕዳን ምስክርነትን ተስፋ የምናደርግበት በመሆኑ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ የአንድን ሀገር ባሕል ወግና ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለማጥፋት ምቹው መንገድ ወጣትነት ነው፡፡ እነዚህም ነገሮች በዘመናችን የሚታዩ ናቸው፡፡ ዛሬ በወጣቱ አካባቢ ቸልተኝነት፣ የባሕል ለውጥ፣ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀናኢ አለመሆን፣ ዳተኝነት፣ ስሜታዊነት የሚንጸባረቅበት ምክንያቱ ወጣቱ የለውጥ ኃይል ስለሆነ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሌኒን የተባለው መሪ "የአንድ ዘመንን ትውልድ ስጡኝና ዓለምን ልለውጥ" ያለው፡፡

 • ወጣቶቻችን የትናንትናውን በመያዝ አዲስ ነገR የሚፈጥሩ መሆን አለባቸው ሰው መፍጠር የሚችለው ግብር እምግብር በመሆኑ አውሮፕላን ለመሥራት አሞራ ማየት የግድ ነበር የአውሮፕላን ሥሪት መነሻ አለው ሁሉም ይኸው ነው፡፡ ወጣቶች ጠንካራ መንፈስ የዳበረ የሥራ ልምድ በጎ ህሊና እንዲኖራቸው አዋዋላቸውን ማስተካከል ይገባቸዋል፡፡ ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዝሙሩ እንዲህ ብሎታል፡፡

ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችን ካልተማሩ ምርመራ ራቅ /ጢሞ. 2፡22፡፡

በማለት ያስጠነቀቀው ስለዚህ ወጣቶች ከማንጋር መዋል እንደሚገባቸው መርምረው ሊረዱ ሊገነዘቡ ይገባቸዋል፡፡ በተለይም ስንፍና እና ያልተማሩ ሰዎች ምርመራ ትውልድን የሚያጠፋ አስከፊ ነቀርሳ ነው፡፡ ይህ ነገር ሕይወት የሚገኝበትን መንገድ ያጠፋል፡፡ የሕይወት እውቀት ግን አንድ ነው፡፡ እርሱም "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘለዓለም ሕይወትናት" ዮሐ. 17፡3 በማለት ጌታ በቅዱስ ወንጌል ተናግሯል ወጣት ሕይወት ለሚገኝበት እውቀት መትጋት ስንፍናን ማስወገድ ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ለማግኘት ውሎው ይወስነዋል፡፡ "ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ" እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ ለዚህም ዋናው መሳሪያ ቤተ ክርስቲያን የወጣቱን ፍላጎት ከቀኖናዋ ከአስተምህሮዋ አኳያ መቃኘትና ማግባባት ይጠበቅባታል፡፡

በተለይም በሃይማኖትና በባሕል ላጌጠችው ሀገራችን ይህ ጌጧ እንዳይጠፋ ማንነቷ እንዳይረሳ ወጣቱን የመቆጣጠር የመምከር የመገሠጽና የመንከባከብ ኃላፊነቷ የላቀ ነው፡፡

ምክንያቱም ወጣት ተቀባይ ተተኪ ተረካቢ ማለት ነው፡፡ የዛሬዎቹ ወጣቶች በሥነ ምግባር በሃይማኖት ካልጎለመሱ ለተረከቡት ክብር አይኖራቸው አባካኝነትና ግዴለሽነት ያጠቃቸዋል ሽማግሌው ሲያረጅ በልጁ ይታደሳል፡፡ በሥነ ፍጥረት ሥርዓት ውስጥ አንዱ ያለውን ለሌላው በመሥጠት የዓለምን የቅብብሎሽ ሒደት ቀጣይ ያደርጋል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍም እንዴት መዘገበው ታላቁ የእምነት አባት አብርሐም የቃል ኪዳን ልጁ ይስሐቅ ለአቅመ አዳም ከደረሰ በኋላ ለይስሐቅ ማስተላለፉን ሲገልጽ "አብርሐምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ስጠው" ዘፍ. 25፡5 በማለት ተጽፏል፡፡ ይስሐቅ ከአብርሐም የተቀበለውን ሁሉ የመጠበቅ የመንከባከብ ግዴታ አለበት ያ ካልሆነ ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ዘለዓለማዊ ተስፋ እንዴት ይፈጸማል ስለዚህ ይስሐቅ ለዚህም የበረከት ሕይወት የተዘጋጀና የታደለ ነበር፡፡ በይስሐቅ ኑሮ ውስጥ የአብርሃምን ሕይወት እንመለከታለን ለምን ከአብርሃም ሁሉን ተቀብሏልና ነው፡፡ ይስሐቅ በግብር በሃይማኖት አብርሃምን መስሎ የተወለደ ልጅ ነው፡፡ ልጅ አባቱን ሲመስል በጣም ደስ ይላል፡፡ ግን ልጅ የአባቱን አልቀበል ቢልስ፣ አልታዘዝም ቢልስ፣ በሃይማኖቱ ግዴለሽ የሆነ ፈጣሪውን የማይፈራ፣ የራሱን እንደድካም የሌላውን እንደ ጥንካሬ የራሱን ድንቁርና የሌላውን እውቀት አድርጎ የሚቆጥር ባሕሉን የሚጸየፍ ትውልድ ቢከሰት ተጠያቂው ማነው ፍቅርን በጥላቻ የሚለውጥ አንድነትን በመለያየት እውነትን በውሸት ተግባርን በወሬ የሚለውጥ ትውልድ እንዳይከሰት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

ወርቅ እየረገጠ ዳቦ በመሻት ልቡን ወደ ባሕር ማዶ ያስከበለለ ትውልድ በመምጣቱ ለወገኑ የማይበጅ አባቱን የማያከብር በጨሌዎች አፍ የሚደለል ከዕውቀት የራቀ ለወገኔ ይጠቅማል ከሚል በጎ አመለካከት ያፈነገጠ ትውልድ ቢፈጠር በቅብብሎሹ ሒደት ያለውን ክፍተት ያሳያል፡፡

ለዚህም የአቤል ሕይወት በቂ ማስረጃ ነው አቤል ከአባቱ የተመለከተውን ሁሉ ተግብሯልና፡፡ የአቤልን መስዋዕት እግዚአብሔር የተቀበለለት አቤል እግዚአብሔር የሚፈልገው መስዋዕት ምን ዓይነት እንደሆነ በመረዳቱና ያንን በማቅረቡ ነበር፡፡

"አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መስዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ" ዕብ. 11፡4 በማለት ተጽፏልና፡፡ አቤል ይህንን እውቀት ከየትም አላመጣውም ከአባቱ ከአዳም የተቀበለውና የተማረው ነው፡፡ ስለዚህ አቤል ንጽሐ ባሕርይ ላለው እግዚአብሔር ንጹሕ መስዋዕት አቀረበ ስንል ለእግዚአብሔር የሚሆነውን ከመምረጡ ባሻገር፤

 • ቀንዱ ያልከረከረ

 • ጥፍሩ ያልዘረዘረ

 • ጸጉሩ ያላረረ መልካም የሆነ ጠቦት ከማቅረቡ ጋራ ራሱንም በጎ መስዋዕት አድርጎ ማቅረቡ ነበር፡፡ ይህ የተቀደሰ ሕይወት በቅንነቱ፣ በየዋህነቱ ውስጥ ተገልጧል፡፡ የአቤል ቅንነት፣ የዋህነት በታዛዥነቱ ታይቷል፡፡ "ቃየል ወንድሙን አቤልን ወደ ሜዳ እንሒድ አለው" ዘፍ. 4፡8 ይላልና፡፡ በአቤል ሕይወት የታየው ታዛዥነት ለሞት ቢያበቃው እንኳ እግዚአብሔር ከሰማይ ደሙን ተመልክቷል ደሙ ወደ እግዚአብሔር አመልክቷልና አቤል የወጣቶች አርአያ ነው፡፡ ታዛዥነትን፣ ቅንነትን ደግነትን፣ የዋህነትን ገንዘብ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከብራችንና ከወርቃችን ይልቅ እኛን ይሻልና፡፡ እግዚአብሔር በሺ አውራ በጎች አይደሰትም፣ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ አይለውም ሚክ. 6፡6-8፣ እርሱ ግን ከእኛ የሚሻው አለው፡፡ ይቆየን....

እግዚአብሔር ሲፈቅድ እንገናኛለን
ክብርና ምስጋና ለልዑል እግዚአብሔር

የፎንት ልክ መቀየሪያ