Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ በዓለ ሢመት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሁለተኛው በዓለ-ሢመት የካቲት 24 ቀን 2007 ዓ/ም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፤ አምባሳደሮች፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፤ የድርጅት ኃላፊዎች፤ የኮሌጅ ኃላፊዎች፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ሠራተኞች፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፤ ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ።

Picture 003 Picture 005 Picture 013 Picture 025 Picture 026 Picture 032 Picture 037 Picture 040 Picture 042 Picture 044 Picture 046 Picture 047 Picture 049 Picture 050 Picture 057 Picture 061 Picture 063 Picture 064 Picture 072 Picture 074 Picture 088 Picture 100 Picture 101 Picture 106 Picture 111 Picture 112 Picture 116 Picture 118 Picture 119 Picture 126 Picture 129 Picture 132 Picture 134 Picture 138 Picture 142

በዓለ-ሢመቱ ቤተ ክርስቲያናችን የራሷን የፕትርክና ሥልጣን የያዘችበት ጊዜ ጀምሮ ሲከበር ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ስድስት ፓትርያርኮች ተፈራርቀውበታል። ስድስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ ይኽ ለሁለተኛ ጊዜ የሚከበረው በዓለ ሢመት ነው። በዓለ ሢመቱ ካለፈው ዓመት በብዙ ገጽታው ልዩ መሆኑ ተስተውሏል። የክብር እንግዶችና የታዳሚዎቹ ብዛት አንዱ የበዓሉ ልዩ ገጽታው ሲሆን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከየሀገረ ስብከታቸው በመምጣት እጅግ በብዛት የተገኙበት ታላቅ በዓል ነው። የበዓሉ ታዳሚዎችና የክብር እንግዶች ቁጥር ቀድሞ ከሚታወቀው በላይ መሆኑ በዓሉን ልዩ አድርጎታል።

ክፍል 1

ክፍል 2

 

የበዓሉ ታዳሚዎችና የክብር እንግዶች ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተገኝተው የክብር ቦታቸውን የያዙ ሲሆን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ቅዱስነታቸው በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታጅበው ከመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ሲደርሱ ታላቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የካቴድራሉ የደወል ድምፅም አስተጋብቷል። የበዓሉ መርሐ-ግብርም በቅዱስነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ተከፍቶ ቀጥሏል።

የበዓሉ መርሐ-ግብር በቅርፁና በይዘቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው የተዋጣለት ነው አስብሏል። ከበዓሉ መርሐ-ግብር አንዱ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲሆን በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሊቃውንት ያሬዳዊ መዝሙር ተሰምቷል። በመቀጠልም፤ በሰንበት ት/ቤት መዘምራን ጣዕመ ዝማሬ የተሰማ ሲሆን የአጫብር ጣዕመ ዝማሬም በአጫብር ሊቃውንት ቀርቧል። ወቅቱ ዐቢይ ጾም በመሆኑ በዝማሜና በሽብሸባ የቀረበውና እጅግ ውበትን የተሞላው ያሬዳዊ ስብሐተ እግዚአብሔር ለበዓሉ ታላቅ ድምቀት ሰጥቶታል።

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልእክት አስተላልፈዋል። ለቅዱስነታቸውም መልካም እድሜንና መልካም የሥራ ዘመንን ተመኝተዋል።

ሌላው የበዓሉ ታሪካዊ አመጣጥ የተንፀባረቀበትና ጥልቅ ምሥጢር የተገለጸበት የቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ሀብት የሆነው ቅኔ ነው። በመርሐ-ግብሩ ላይ ቅኔ ለማቅረብ ተዘጋጅተው የነበሩት ሦስት ሊቃውንት ሲሆኑ በጊዜው እጥረት ምክንያት ቅኔው በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከት ወንጌል መምሪያ የበላይ ጠባቂና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብቻ ተጠናቋል። ብፁዕነታቸው በቅዱስ ፓትርያሪኩ ትምህርት እንዲሰጡ የተጋበዙ ሲሆን ቅኔውንና ትምህርቱን አዋህደውና አዋዝተው ሰማዕያኑን እጅግ በአስደነቀ መልኩ አቅርበውታል።

ብፁዕነታቸው በቅኔ ምሥጢርና በትርጓሜ መጻሕፍት እጅግ የታወቁ ሊቅ ሲሆኑ በበዓለ ሢመት ላይ ያቀረቡት ቅኔ፤ ማብራሪያና ትምህርት የተካተተበት በመሆኑ የበዓሉን ታላቅነት በእጅጉ ያመሠጠረ ነበረ። ብፁዕነታቸው ሢመተ-በዓሉ ተራው የሚደርሳቸው ፓትርያሪኮች ይጠሩበት እንጂ በዓሉ ብሔራዊ በዓል ነው ብልዋል። ይኽውም ቀደም ሲል የነበሩት አባቶቻችን ነገሥታትን ጨምሮ ኢትዮጵያን ባለ መንበረ ፓትርያሪክ ለማድረግ ብዙ መሥዋዕት ከፍለዋል። የማዕድናት ውጤቶችን፤ የብርቅዬ እንስሳትን እጅ መንሻ በወቅቱ የፕትርክናውን ሥልጣን ለያዙት (ግብፃውያን) አቅርበዋል። በመሆኑም ይኽ የፕትርክናው በዓለ-ሢመት የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድና አባቶቻችን የከፈሉት መሥዋዕት ውጤት እንደሆነ ብፁዕነታቸው ይበል በአሰኘው ቅኔያቸው አብራርተዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል። በዓለ-ሢመቱን አስመልክቶ መልእክትም አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ወቅታዊና የቤተ ክርስቲያንዋ ቀዳሚ ተደራሽ የሆነውን ትምህርተ-ኖሎት (መንጋውን የመጠበቅ ኃላፊነትን) አካተዋል። በዋናነት የመልእክታቸው ርዕስ አድርገው የተነሱበት በአንደኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ አምስት ቁጥር ሁለት ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን "ረዐዩ ዘሀለዉ ኃቤክሙ መርዔቶ ለእግዚአብሔር" በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ የሚለው ኃይለ ቃል ነው። አያይዘውም ቅዱስነታቸው የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ጥያቄ የመንጋው መጠበቅ እንደሆነ በስፋትና በጽንዖት ገልጸዋል።

የፎንት ልክ መቀየሪያ