Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በጾመ ፍልሰታ ከመደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ ጸሎተ ምሕላም እንዲደረግ መመሪያ አስተላለፉ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክ ሃይማኖት "ጾመ ማርያምን" ምክንያት በማድረግ ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ኃላፊዎች በተገኙበት አባታዊ የሥራ መመሪያ ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም አስተላለፉ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስነታቸው ጾም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሃይማኖታዊ፣ መንፈሳዊ፣ ቀኖናዊ እና ነባር የክርስቲያኖች ምግባር ትሩፋት መሆኑን ገልጸው ጸጋ እግዚአብሔር በአማኞች ላይ እጅግ የሚበዛበት ምክንያተ ድኅነት መሆኑን ከኦሪት የሙሴ የጾም ሕይወትና ያገኘው በረከት ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለውን የጾም ሃይማኖታዊ ጠቀሜታ በሰፊው አትተው ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ጥንታዊ ሥርዓተ ጾምና ጸሎቷን በአግባቡ ጠብቃ እያገለገለችና ምእመኗን እየጠበቀች የምትገኝ ተቋም መሆኗን በስፋት አስረድተዋል፡፡

በሌላ ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች እምነቱና ትምህርቱ በሚገባ ያላቸው ቢሆንም እንደ ሀገራችን የመሰለ ጥንታዊ ሥርዓቱ ተጠብቆ እየተከናወነ አለመሆኑን በንጽጽር ከገለጹ በኋላ ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን የመሰለ የሱባኤ አፈጻጸም ትውፊት ገንዘብ አድርጋ ዘመናት የተሻገረችው በእግዚአብሔር አጋዥነትና በወላጆቻችን ጽኑ እምነት መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘገብ በማድረግ ትውልዱ እንዲማር ማድረግ ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል፡፡

እኛ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጾማችንና ጸሎታችን በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በመጀመሪያ ውስጣችንን አጽድተን፣ ብልሹ አሠራርን አስተካክለን፣ ሙስናን ተጸይፈን፣ ለምእመናኖቻችን በቅድስናና በንጽሕና ምሳሌ ሆነን መገኘት ይገባል ብለው በሰፊው ከመከሩ በኋላ በመስከረም ወር ወደ ሀገራችን የሚመጡትን የግብፅ ፓትርያርክ አቀባበልና የመስቀል ደመራ በዓል በበለጠ ደምቆ መከበር እንደሚገባው ቅዱስነታቸው ሰፋ አድርገው ቃለ በረከት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዚህ በጾመ ማርያም ሱባኤያችን ከተለመደው የጸሎት ሥርዓታችን በተጨማሪ እግዚአብሔር ለሀገራችን ዝናመ ምሕረቱን፣ ጠለ በረከቱን እንዲሰጥልንና ወርሐ ክረምቱን የተባረከ እንዲያደርግልን በሁሉም አህጉረ ስብከት፣ በሁሉም አድባራትና ገዳማት ዘንድ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ መመሪያ በማስተላፍ ጉባኤውን በጸሎት ዘግተዋል ፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ