Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

‹‹እመቦ ዘአሕሰመ ቃለ ላዕለ አቡሁ ወእሙ ሞተ ለይሙት፤
አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል›› (ዘጸ. 21፤17፣ ማቴ. 15፡3-4)

እስክንድር ገብረ ክርስቶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት የባህልና የታሪክ መገኛ በመሆኗ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንተ ሥልጣኔ መሠረት ነች ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በመፈቃቀድ፣ በመከባበርና በመቻቻል በአብሮነት ይኖር ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በግብረገብ ትምህርት በማነጽ በልዩነት ውስጥ ላለን አንድነት መጠንከር ታላቅ አስተዋኦን አበርክታለች ፡፡
ከአሠርቱ ትእዛዛት አንዱና ‹‹እናትና አባትህን አክብር›› የሚለውን የልዑል እግዚአብሔርን ትእዛዝ መሠረት በማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑ በመከባበር፣ በመደማመጥና በመፈቃቀር ይኖር ዘንድ ለዘመናት አስተምራለች፤ በማስተማርም ላይ ትገኛለች፤ ይህ ትምህርቷም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ በመሆኑ በቤተሰብ ደረጃ ሳይቀር ታናሽ ታላቁን እያከበረና በታላቁ እየታዘዘ፣ ታላላቆችም ለወላጆቻቸው እየታዘዙ በመከባበር የሚኖሩበት ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ማሥረፅ ችላለች ፡፡
ይህ የመከባበርና የመደማመጥ ሥርዓት በቤተ ክርስቲያናችን ደረጃ የጠነከረና የሚያስቀና ሥርዓት ሆኖ ይገኛል ፡፡ ዲያቆናት ካህናትን፣ ካህናት ኤጲስ ቆጶሳትና ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ፓትርያርኩን በማክበር፣ በማድመጥና በመታዘዝ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት ባለቤት መሆኗን በተግባር ለሕዝበ ክርስቲያኑ ስታስተምር ኖራለች፤ አሁንም እያስተማረች ትገኛለች ፡፡
በለተይም የሐዋርያት ምሳሌ የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በከፍተኛ ደረጃ ክብር ሊሰጣቸው የሚገቡ አባቶች በመሆናቸው ካህናትና ምእመናን ጉልበታቸውንና መስቀላቸውን ስመው ተገቢውን የሃይማኖት አባትነት ክብር ሰጥተው በሚገባ ያከብሯቸዋል ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰጧቸውን ትእዛዝና መመሪያዎችም ያለማንገራገር ተግባራዊ ያደርጋሉ ፡፡


ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ሕዝቡን ያስተምራሉ፣ ይባርካሉ ፡፡ ይህ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ከጥንት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን ሲወርድ ሲዋረድ እዚህ ደርሷል፡፡ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እንደነበረው ሕዝበ ክርስቲያኑ ለቅዱሳን ፓትርያርኮችና ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ካለው ፍቅርና አክብሮት በመነሣት ቅዱስ ፓትርያርክ ወይም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሄዱበትን መንገድ፣ የተቀመጡበትን ወንበር በመሳለም የተጓዙበትን መንገድና መቀመጫውን በመዳሰስና ሰውነቱን በማሻሸት ከአባቶቹ በረከትን ለማግኘት ይጋፋ እንደነበርና በዚህም ለአባቶቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት ይገልጽ እንደነበር እናውቃለን ፡፡
ዛሬም ይህን የመሰለ አክብሮት በሕዝቡ ዘንድ እንዳለ ነው፤ ለምሳሌ ለመጥቀስ ካስፈለገ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በክልል ትግራይና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሐዋርያዊ አገልግሎት በተንቀሳቀሱበት ወቅት በዚያ አካባቢ ያሉ ምእመናን ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚጓዙበትን መኪናና የተቀመጡበትን ወንበር በመሳለም በጥንቱ ዘመን ወላጆቻቸው ለአባቶቻቸው ይሰጡት የነበረውን ፍቅርና አክብሮት በመስጠት ቅዱስነታቸውን ተከትሎ ከአዲስ አበባ የተጓዘውን ልኡክ አስደምመዋል፡፡
ይህ የመከባበር፣ የመደማመጥና የመታዘዝ ሃይማኖታዊ ሥርዓታችን ታዲያ ዛሬ ዛሬ እየተሸረሸረና እየተናደ መምጣት ጀምሯል፡፡ ይህ ሃይማኖታዊ ሥርዓታችን እንዲሸረሸርና እንዲናድ የሚያደርጉትም ቤተ ክርስቲያን አቅፋ፣ ተንከባክባ አሳድጋና አስተምራ ትልቅ ደረጃ ባደረሰቻቸው ልጆቿ መሆኑ ደግሞ ሁኔታውን እጅግ የከፋ ያደርገዋል ፡፡ ይህ የአባቶችን ክብር ዝቅ በማድረግ በድፍረት የሚፈጸመው ስድብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሆነም ማንም የሚያውቀው ነው ፡፡
የአባቶች መሰደብና መዋረድ የግለሰብ አባቶች መሰደብና መዋረድ የመሰላቸው የዋሆች ታዲያ በአባቶች ላይ የተጻፈውን መጽሐፍ በመግዛትና በማንበብ ለተሳዳቢዎቹ እውቅና በመስጠት ሲሳለቁ ታይተዋል ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ መዋረዷንና መሰደቧን የአባቶች ስም መጥፋት የቤተ ክርስቲያኒቱ ስም መጥፋት መሆኑን የተገነዘቡ ወገኖች ደግሞ በተጻፈው ጽሑፍ ሲያዝኑ ሲያለቅሱና ሲጸልዩ ታይተዋል ፡፡
ይህ ለጊዜው ቀላል የሚመስል፤ ነገር ግን ቀስ በቀስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚቀንስ፣ የምእመናንን አንገት የሚያስደፋና የሚያስለቅስ ተግባር በአባቶች ላይ ሲፈጸም ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በዝምታ ማለፉ የሚያሰቆጭ ሲሆን ሁኔታውን የግለሰብ ጉዳይ አድርጎ መመልከቱና ውሳኔ አለመስጠቱ ዛሬ በርካታ ጸሐፍት ነን ባዮች የሚፈልጉትን በፈለጉት አባት ላይ በዓለማዊ የፖለቲካ ሰዎች ዘንድ እንደሚሰጠው ትችት አንዳንዴም ከዚያ በሚከብድ መልኩ እንዲጽፉ ፈቃድ ያገኙ አስመስሏቸዋል ፡፡
ይህም በመሆኑ በቅርቡ በተለያዩ ጸሐፊ ነን ባዮች በኩል በርካታ ጽሑፎች በጋዜጣና በመጻሕፍት መልክ እየተዘጋጁ የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ክብር በሚያሳጣ ሁኔታ ለንባብ በቅተዋል ፡፡ በእነዚህ መጻሕፍትና መጻሕፍቱን ጽፈው ባሳተሙ ጸሐፍት ላይ ቤተ ክርስቲያን ርምጃ መውሰድ ባለመቻሏ ምእመናን እንዲሰናከሉ ሌሎች የሃማኖት ድርጅቶችም የተጻፉትን መጻሕፍት ዋቢ በማድረግ ምእመናንን የማስኮብለል ሥራ እንዲሠሩበት እድል ሰጥቷል ፡፡
በመሠረቱ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ መስተካከልና መታረም የሚገባው ካልሆነም ለቤተ ክርስቲያኒቱ አደጋ ላይ መውደቅ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ጉዳይ የግለሰባዊ አመለካከት ጉዳይ ነው ፡፡ በፓትርያርኩም ላይ ሆነ በአንድ ጳጳስ ላይ የሚጻፍ ማንኛውም ጽሑፍ በግል የጳጳሱ ወይም የፓትርያርኩ ተደርጎ መታየት የለበትም ፡፡ በሌላ አገላለጽ በፓትርያርኩ ላይም ሆነ በሊቃነ ጳጳሳት ደረጃ የተጻፉ ትችቶችን አንብቦ ‹‹አበጀ ልካቸውን ነገራቸው እውነት ነው›› በማለትም ዕውቅና መስጠት በቤተክርስቲያን ላይ ከማሴር ተለይቶ መታየት አይገባውም ፡፡
መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ‹‹የዳንኤል እይታዎች›› በሚል ድረ ገጽ ላይ ኋላም ሰንደቅ በተባለ የግል ጋዜጣ ‹‹ፓትርያርኩ ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት›› በሚል ርእስ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈና የተለቀቀው ጽሑፍም ከእነዚህ ከላይ ከተመለከትናቸው ጉዳዮች ተለይቶ የሚታይ አይደለም፤ በመሆኑም ጸሐፊው በድረ ገጹ ከቀናት በኋላም በጋዜጣ የለቀቀው ይኸው ጽሑፍ የከተማው መነጋገሪያ ሆኖ በመሰንበቱ ጽሑፉን ለመመልከት ተገደድኩ ፡፡ ጸሐፊው ቀደም ሲል ‹‹ስማችሁ በሰማይ የለም›› የሚል መጽሐፍ ማሳተሙና ማሰራጨቱ ይታወቃል ፡፡
ጸሐፊው በድረ ገጽ የጻፉትን ጽሑፍ ካነበብኩት በኋላም የሕዝቡን አስተያየት ለማዳመጥ ሞከርኩ፤ አብዛኛው ሕዝብም ዳንኤል በጻፈው በዚህ ጽሑፍ ክፉኛ ማዘኑንና ለዳንኤል ይሰጥ የነበረውን ክብርና ፍቅር ጥያቄ ውስጥ እንዲከት ያስገደደው መሆኑን በመግለጽ ጸሐፊውን ሲወቅስ ሰንብቷል ፡፡ በድረ ገጹ ላይ አስተያየት የሰጡ አንዳንድ ወገኖችም ኢትዮጵዊያንነታችንን፣ ሃይማኖትና ባህላችንን ባልጠበቀ መልኩ የሰጡት አስተያየት በእጅጉ አሳዝኖኛል ፡፡ ሥልጣኔ መስሎን አባቶችን ለማዋረድ ምንሰጠው አስተያየትም መጨረሻችን የማያምር መሆኑንም አመላክቶኛል ፡፡
በእኔ እይታ የዳንኤል የዘንድሮ ጽሑፍ የተዛባ እይታን መሠረት አድርጎ የተጻፈ እንደሆነ አመላክቶኛል ፡፡ የጽሑፉ መዛባት ምክንያትም ጽሑፉን ለመጻፍ ያስገደደው ጽንሰ ሐሳብ መሆኑንም ለመረዳት አልተቸገርኩም ፡፡ ጸሐፊው ይህን ጽሑፍ ፍጹም ስሜታዊ ሆነው የጻፉት የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርዕይን መዘጋት መነሻ አድርገው እንደሆነም ከጽሑፉ ይዘት መረዳት ይቻላል ፡፡
ጸሐፊው የዐውደ ርዕዩ መዘጋት ምንኛ እንዳበሳጫቸው የገለጹት በዚህ መልኩ ነበር፡፡
‹‹ዐውደ ርእዩ እንዲዘጋ ያዘዘውስ የትኛው መንግሥት ነው? አንዱ የሚፈቅድ ሌላኛው የሚዘጋ ስንት መንግሥት ነው ያለው? ወይስ ደብዳቤ መጻፉ አላዋጣምና ዝጋልኝ$ ተብሎ እጅ የተሰነዘረለት አካል ያደረገው ነው? መጽሐፉ እንደሚለው ‹‹የማይገለጥ የተሰወረ አይኖርምና ዐውቀነዋልም እናውቀዋለንም›› በማለት ለማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርዕይ መዘጋት ቅዱስ ፓትርያርኩን ተጠያቂ ሊያደርግ ሞክሯል፡፡
እዚህ ላይ ጸሐፊውና ማኅበሩ ልዩነት አላቸው ማኅበረ ቅዱሳን የዐውደ ርዕዩን መዘጋት ምክንያት በማድረግ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ግልጽ ውይይት በማድረግ መረዳዳትና መተማመን ላይ በመድረሱ በሁለቱም ወገን በመገናኛ ብዙሃን የዐውደ ርዕዩ መሠረዝ ምክንያት ተገልጿል፡፡ ይህን ዐውደ ርዕይ በማስቀረት ደረጃም የማንም ጣልቃ ገብነት እንደሌለ ማኅበሩ ማረጋገጡን ገልጿል፡፡ ጸሐፊው ግን ለዚህ ተጠያቂ የሚያደርጉት ቅዱስ ፓትርያርኩን ነው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ቅዱስ ፓትርያርኩ በማኅበሩ ዙሪያ በሚያራምዱት ጠንካራ አቋም ምክንያት እንደሆነ ይታወቃል፡
በእርግጥም በዐውደ ርዕዩ መከልከል ምክንያት በማኅበረ ቅዱሳንና በሚመለከተው የመንግሥት አካል መካከል በተደረገው ውይይት ከተደረሰበት ስምምነት ውጭ የማንም እጅ እንደሌለበት ማኅበሩ ሳይቀር ያረጋገጠው ሀቅ ሆኖ ሳለ ጸሐፊው ቅዱስ ፓትርያርኩን ለመተቸት መሞከራቸው በዐውደ ርዕዩ መቅረት መበሳጨታቸውንና ለተራ ወቀሳ መነሳታቸውን ያሳያል፡፡
በቤተ ክህነት አካባቢም አንዳንድ እንወደድ ባዮች ዐውደ ርዕዩን እነርሱ እንዳዘጉት በማስመሰል የሚፎክሩት ፉከራም ለጸሐፊው የተዛባ እይታ መያዝ በምክንያትነት የሚጠቀስ ስለሆነ በቤተ ክህነት አካባቢ ያልሠሩትን እንደሠሩ በማስወራት ከበሬታና ዝናን ለማግኘት የሚሞክሩ ወገኖችም ከ‹‹ላም ባልዋለበት ....›› አሠራር የሚርቁበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ፡፡
እኒሁ ጸሐፊ ቅዱስ ፓትርያርኩን በተቹበት በዚህ ጽሑፋቸው ርዕስ ላይ #ቅዱስ ፓትርያርኩ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ሥጋት$ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ በጽሑፋቸው ላይ የምንመለከተው መሠረታዊ ሐቅ ጸሐፊው ሕዝቡን ለዐመጽ ያነሳሳ ጽሑፍ በመጻፍ የሀገሪቱ የደኅንነት ሁኔታ አስጊ እንዲሆን እንደሚመኙ አሳይተውናል ፡፡ በዚህም የሀገሪቱ የደኅንነት ሥጋት የሆኑት እርሳቸው እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ፡፡ ሕዝቡን ለአመጽ ለማዘጋጀት የሞከሩትም በዚህ መልኩ ነበር፡፡ #ዐውደ ርዕዩ የማይደረግበት በቂ ምክንያት ከነበረ ቢያንስ ከሳምንት በፊት መግለጥ ይቻል ነበር፤ ዓላማው ግን ማበሳጨት፣ ዐመጽ ማስነሳት፣ ተስፋ ማስቆረጥና ምዕመናንን ወደማይፈልጉት መስመር መውሰድ ነው፡፡$ በማለት ሕዝቡ የዐውደ ርእዩን መከልከል ተከትሎ ለአመጽ እንዲነሳ ጋብዘዋል፡፡

ጸሐፊው በዐውደ ርዕዩ መዘጋት ምክንያት ሕዝቡ የተሳሳተ ግምት እንዲጨብጥ በዚህ መልኩ ቀስቅሰውት ነበር፡፡ #የዚህች ሀገር ሰላም አይፈልግም? ምእመናን ሀገር እንደሌላቸውና መብት እንደሌላቸው ራሳቸውን እንዲቆጥሩ ይፈልጋል? #ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል$ እንዲል ሀገሪቱ ያለባት ችግር አይበቃምን? ተጨማሪ ችግር ማምጣት ይፈለጋል? በማለት በሀገሪቱ ላይ ሽብርና ሕውከት ሊነሣ የሚችልበትን አቅጣጫ ለማመላከት ሞክረዋል ፡፡
ይህን ሃሣባቸውን የበለጠ በማጠናከርም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሀገሪቱን በሚመራው መንግሥትና ሥርዓት ላይ ማነሳሳት እንደሚቻል በመግለጽ መንግሥትን ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅም የሚከተለውን ጽፈዋአል፡፡ #ከቤተ መቅደስ የተነሳ ችግር መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው አይታወቅምና እንዲህ ያሉ ነገሮች የምዕመናንን የአስተሳሰብ ቅርጽ ይቀይራሉ፡፡ የሐበሻን ስነ ልቦና የሚረዳ ደግሞ ሲረገጥ እንደሚጠነክር ጭቃ ያጠነክረዋል፡፡ ሲሞረድ እንደሚሾል ቢላዋ፣ ሊቀረጽ እንደሚሾል እርሳስ ያደርገዋል፡፡ በማለት ሕዝበ ክርስቲያኑ በእልህና በወኔ ወዳልተፈለገ ሕውከት ራሱን እንዲከት በማነሳሳት በተግባር የሀገሪቱ የደኅንነት ሥጋት ጸሐፊው እንጂ ቅዱስ ፓትርያርኩ አለመሆናቸውን በማረጋገገጥ ከጽሑፉ ርዕስ ጋር ተጋጭቷል፡፡$
¾ዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ አይደለም ከዲያቆን ከክርስትና እምነት ተከታይ ምዕመን በማይጠበቅ ደረጃ ቅዱስ ፓትርያርኩን ለመተቸት የተጠቀሙባቸው ቃላት በሙሉ የስሜታዊነትና የትምክህት ሰለባ መሆናቸውን ያመለከተ በመሆኑ ብዙም አያስደንቅም፡፡ ለመሆኑ ምሁሩና አዋቂው ጸሐፊያችን አባት ማክበርን እንዴት ሳይማሩ ምሁር እንደሆኑ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ አባትን በመናቅና በመሳደብ አባትን በማዋረድና በማሳጣት ቤተ ክርስቲያንን ማክበር እንደማይቻል እንዴት እንዳልተማሩ አልገባኝም፡፡ የሃይማኖት አባታቸውን ሳያከብሩ ሕዝበ ክርስቲያኑን አልያም ልጆቻቸውን ስለወላጆችና ስለ ታላላቆች ክብር ምን ብለው እንደሚያስተምሩአቸው አይገባኝም፡፡
ሌላው ጸሐፊውን ትችት ላይ የሚጥላቸው ዐቢይ ጉዳይ በምዕራብ አርሲና በደቡብ አፍሪካ ተነስቶ ለነበረው ችግር ቅዱስ ፓትርያርኩን ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው የጻፉት ጉዳይ ነው፡፡ ጸሐፊው መረጃ ስለሌላቸው እንጂ በሁለቱም ቦታዎች ያለው ችግር መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ሲኖዶስ መክሮ ልዑካን ልኰ ውጤቱ ቀርቦ በሲኖዶስ ውሣኔ እያገኘ ያለና ቅዱስ ፓትርያርኩም በቅርበት የሚከታተሉትን ጉዳይ ለትችት ማዳበሪያነት መጠቀማቸው ያለባቸውን የመረጃ እጥረትና ስሜታዊነታቸውን የሚያሳይ በመሆኑ የጸሐፊውን አንገት የሚያስደፋ መሠረተ ቢስ ውንጀላ ነው፡፡
በአጠቃላይ አሉባልታን መሠረት በማድረግና በዐውደ ርዕዩ መዘጋት ቁጭት ተነሣስቶ ይህን የመሠለ ተራ የውንጀላ ጽሑፍ መጻፍ ሆን ብሎ በተዛባ እይታ ቤተ ክርስቲያንን በመወንጀል የሃይማኖት አባትን ለመዳፈር መሞከር ጸሐፊው እስኪበቃቸው የተጠቀሙባትን፣ ሀብትና ዝናን ያተረፉባትን ቤተ ክርስቲያን እንደመናቅና እንደማዋረድ የሚቆጠር ሲሆን በዚህ የተዛባ እይታቸው ጸሐፊው ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንዳላገኙበት ጥርጥር የለኝም፡፡
ሲጠቃለል የመከባበር፣ የመደማመጥ፣ የመቻቻልና አብሮ የመኖር መሠረት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ እርስዋን የማይወክሉ ሁኔታዎች እየተከሠቱ እንደሆነ ልብ ማለቱ ተገቢ ነው ፡፡ ከፍ ሲል እንደገለጸው የተለያዩ ጸሐፊዎች በአባቶች ዙሪያ የጻፏቸው ለምሳሌ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች፣ የጳጳሱ ቅሌት፣ ስማችሁ በሰማይ የለምና ዛሬ ደግሞ ፓትርያርኩ ለኢትዮጵያ የደኀንነት ለምዕመናን የድኅነት ሥጋት በሚል ርዕስ የተጻፉ ጽሑፎች በሙሉ በግለሠቦች ላይ ያነጣጠሩ ተራ ትችቶች ተደርገው መወሰድ አይገባቸውም፡፡
አባቶች ለዚህች ቤተ ክርስቲያንና ለሀገራችን ኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የከፈሉት መንፈሳዊ መስዋዕትነት እያበረከቱት ያለው ሐዋርያዊ አገልግሎት ሊያስከብራቸው፣ ሊያስወድዳቸውና ሊያስደንቃቸው ሲገባ ማንም እየተነሳ በተራ ስሜት ገፋፊነት ሲሰድብና ሲያዋርዳቸው ሰድቦ ለሰዳቢ ሲሰጣቸው በዝምታ መመልከት አይገባም፡፡ የእያንዳንዱ አባት መዋረድም የቤተ ክርስቲያን መዋረድና መሰደብ መሆኑን በጋራ ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል፡፡ መከባበርን በምታስተምር ቤተ ክርስቲያን አባቶቻቸውን የሚሳደቡ ልጆች ሲገኙም በትክከል እኛ ያሳደግናቸው የእኛ ልጆች ናቸውን? ብሎ መጠየቅ፣ መገሰጽና ማስተማር ይገባል፡፡
ዝምታ መፍትሔ አይሆንም በአባቶች ላይ ለሚወርድ የስድብ ናዳ ዝምታ መልስ ከሆነ እያንዳንዱ አባት እንደ ፖለቲካ መሪ ከማንነቱ ውጭ በተቺው ዕይታና ፍላጐት አልያም በተራ ስሜታዊነት መዘለፋቸው፣ መሰደባቸውና መናቃቸው አይቀርም፤ ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረት መናድ የሚያሳይ ስለሆነ በሲኖዶስ በኩል ሊታሰብበት ይገባል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ያሉ አገልጋዮች ሁሉ እንደየደረጃና ማዕረጋቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የሥራ ድርሻ ብቻ አገልግሎታቸውን እንዲያፋጥኑ በማድረግና በመቆጣጠርም ከልክ በላይ እንዳይዘሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ