Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከሥተ፡፡

ይህንን ጽሑፍ ለመጽሐፍ ያስገደደኝ ሰሙነሕማማት እና ወርኃ በዓላት በመጡ ቁጥር በየአከባቢው የሚነሳው የምዕመናን ጥያቄ እና የቤተ ክርስቲያን ካህናትና ሰባኪያን መልስ እርስ በራሱ ልዩነት እየፈጠረ ስለመጣ ነው፡፡
በባሕረ ሐሳብ ኢየዓርግ እና ኢይወርድ ሕግ መሠረት ከሚከበሩ በዓላት መካከል ዐቢይ ጾም ነው፤በመጨረሻው ሣምንት የምናገኘው ደግሞ የሰሙነ ሕማማት ሣምንት ነው፡፡ በየዘመኑ ከባሕረ ሐሳብ ዑደትጋር ከሚገናኙ በዓላት መካከል ፣
1 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምወርኃ በዓል ሚያዝያ21ቀን

2 የቅዱስ ሚካኤል ወርኃ በዓል ሚያዝያ12ቀን፡፡

3 በዓለ እግዚአብሔር ወይምበዓለ ትስብእት መጋቢት 29 ቀን ጌታ የተፀነሰበት ፣የተነሣበት ፤ጥንተ ትንሳኤ፤

4 የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት መጋቢት 27 ቀን የጊዮርጊስ ክብረ በዓል ሚያዝያ 23 ቀን እንደ ባሕረ ሐሳብ ኢየኣርግ እና ኢይወርድ ሰሙነ ሕማማትና በዓለ ፋሲካ የሚያገኛቸው ክብረ በዓላትና የወርኅ በዓላት ናቸው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በቁመት ጊዜ ቃለ እግዚአብሔራቸው አይባልም፤ ክብረ በዓላቸውም ከሰሙነ ሕማማትና ከበዓለ ፋሲካ /ሰሙነ ማዕዶት / ከዳግም ትንሣኤ ውጭ ባሉት ቀናት ነው፡፡

በሰሙን ሕማማት ወርኃዊ በዓልም ሆነ ዓምታዊ ክብረ በዓል የጌታ በዓል ተደርቦ ቢውል ቁመት አይቆምም ቅዳሴ አይቀድስም ፣ክርስትና ማንሳተ ክልክል ነው፣ ክህነት መስጠት ፣ለሙታን መጸለይ አይገባም ፡፡(ፍትሓ ነገስት አንቀጽ15 ቁጥር 600 )

ተፈጣሚ የሚሆነው የሰሙነ ሕማማተረ ሥርዓት ነው፡፡

በተለይም ከቅርብ ዘመናት ወዲህ በዓለ ስቅለት እና የሚያዝያ በዓለ ማርያም አብሮ በሚውሉበት ጊዜ ይሰገዳል ወይስ አየሰገድም በማለት በየ ቤተክርስቲያኑ ክርክር እና መለያየት አየ ተፈጠረ ይታያል ፡፡ ይህ ሊሆን አይገባም ምክንያቱም ሰሙነ ሕማማትን የምናከብረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ተሰቀለበት ነውና ፡፡

ረስጣ 27ወኢይትገበሩ በሰሙነ ሕማማት ›ወኢበዘይመጽእ እምድኅሬሁ፡፡ ዘውእቱ በዓል አሀዱ በእንተ ዘተሰቅለ እግዚእነ ፤ ወካልኡሂ በእንተ ዘተንሥአ ቦቱ እሙታን ፡፡

ረስጣ 27 መሰሙነ ሕማማት እና ከእርሱ ቀጥሎ በሚመጣው በዓል (የማዕዶት ሳምንት) ሥራ አትስሩ ይህውም አንዱ በዓል ( ሳምንት ) ጌታችን ስለተሰቀለበት ፤ ሁለተኛውም ጌታችን ስለተነሣበት ነው ፡፡

(ፍትፈ ነገስት አንቀጽ19 ቁጥር 740 ተመልከት)

በሌላ እቀጽ ወካዕበ እስመ እሙንቱ በዓላት እለ አዘዘዙነ ከመ ኢንጹም ወኢንስግድ ቦቶን ከመ እሁድ ወሰንበት ወበዓላተ እግዚእ ኢዘከረ ዘንተ ሱባዔ) ዳግመኛም እንዳንጾምባቸው እንዳንሰግድባቸው የታዘዝንባቸው ቀኖች እንደ እሁድ ፣እነ3ደ ሰንበት( ቅዳሜ) እንደ ጌታ በዓላት (ልደት ፣ጥምቀት፣በዓለ ትስብእት ) ጣለ ቀናት አሉና፡፡ከእነርሱ ጋር ይህን ሳምንት (ሰሙነ ህማማት) አልተናገረውም (ወይም) ከማጥጾሙት እና ከማይሰገድባቸው ቀናት ጋር አላካተተውም ፡፡

ፍተሐ ነገስት ቁጥር 582 ላይ ተመልከት፡፡

ማጠቃለያ

1ኛ ሲጀመር በዚህ ሰሙነ ሕማማት እና ሰሙነ ማዕዶት የመላእክት የቅዱሳን የሰማዕታት የእመቤታችቭ በዓላት አይከበሩም የቁመት አገልግሎትም አይነገርባቸውም ተደርበው ነዳይከበሩም ተከልክለዋል፡፡

2ኛ. ከጸሎት እንኳን ከነገረ መስቀሉ እና ነገረ ሕማሙ የሚያነሱ ካልሆኑ በቀር ሌላጸሎት ድርሳናትመልክዓ መልክዕ አይፈቀድም ክልክል ነው፡፡

3ኛ. ሰሙነ ሕማመት የሚከበረው በጸሎት እና በስግደት ነው ካልተሰገደ ሰሙነ ሕማማት መባሉ ከምኑ ላይ ነው ፡፡

4ኛ. በግዝት በዓል ስግደት መሰገድ የለበትም ብለው ግራ የሚያጋቡ ስግደትን እነደ ዓለማዊ ሥራ ስለተመለከቱት ነው ይህም ስግደትን እንደ ቅጣት እንደ ዓለማዊ ሥራ ማየት በራሱ ስህተት ነው ፡፡ ስግደት የመንፈሳዊነት መገለጫ እንጂ ዓለማዊ ሥራ አይደለምና፡፡

ስለዚህ ሕዝበ ክርስቲያኑ በያለበት ዓለም ሆኖ በተረጋጋ መንፈስ ለእግዚአብሔር አምላኩ መስገድ ይገባዋል ፡፡

እግዚአብሔር ኃጢአትን መስራት ከለከለ እንጂ ለስሙ መስገድን አልከለከለም ፡፡

ትንሣኤ ክርስቶስ

ስለ ክርስቶስ መነሣት አስቀድሞ ትንቢት ተነግሯል፡፡ ይህም ዳዊት "ይትነሣዕ እግዚአብሔር ወይዘረው ጸሩ ወይጒየዩ ጸላዕቱ እምቅድመ ገፁ" እግዚአብሔር ይነሣል፣ ጠላቶቹም ይበተኑ፣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሸሹ፡፡ /መዝ. 67፥1 / "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመዘንቃህ እምንዋም፣ ወከመ ኃይል፣ ወኀዳገ ወይን፣ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ" "እግዚአብሔርም ከፍንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደኃያል ሰው ጠላቶቹንም በኋላቸው" መታ መዝ. 77፥65

በደቂቀ ነቢያት፡- "በሠኑይ ዕለት ይቀስፈነ፤ ወበሠሉስ መዋዕል ይሠርየነ፤ ወየሐይወነ፤ አመሣልስት ዕለት ይትነሣእ ወንቀውም ምስሌሁ"፡፡ በኦሪት "አንበሳ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ዕርግ እምንዝኀትከ" እየተባለ በብሉይ፣ በሐዲስ በብዙ ዓይነት ተነግሯል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ ማለት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ዝም ብሎ ድንጋዩ እንደ ተገጠመ ተነሥቶ ሄደ፡፡ ከዚያ በማርቆስ ወንጌል እንደተጻፈው ሴቶች ወደ መቃብሩ ሂደው "መኑ ይከሥትለነ" "ድንጋዩን የሚገለብጥልን ማነው" ሲሉ መላእክት አነሱላቸው፡፡ (ማር. 16፥ 1-8፣ ማቴ. 28 ፥ 1-8 ሉቃ. 24 ፥ 1-10 ዮሐ. 20፥1)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክታቡ "ክርስቶስ ላንቃላፉት በኲር ሆኖ ተነሥቷል፡፡" ይላል ይህም ማለት መጀመሪያም ትንሣኤ ዘጉባኤ የተነሣ እሱ ነው፡፡ ሌላ ገና አፈር ሆኖ ለመነሣት ዕለተ ምጽአትን ይጠብቃል "ተነሥአ እግዚእነ ከመይምሐረነ በተንሥኦቱ እንከሰ ዳግመ ኢይመውት" ከእንግዲህ ወዲህ ሁለተኛ አይሞትም" እነ አልአዛር ቢነሡ ተመልሰው ሞተዋል፣ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃሉ፡፡

ጌታችንና እመቤታችን ግን ተመልሰው አይሞቱም እንዲህ ያለው ትንሣኤ ዘጉባኤ ይባላል፡፡ "ቀደመ ተንሥአ እምኲሎሙ ሙታን" "ከሙታን አስቀድሞ ተነሣ" የተባለው ስለዚህ ነው፡፡ እስከ አሁን ሁለቱ ብቻ ናቸው ትንሣኤ ዘጉባኤ የተነሡት፡፡

ከዚህ ጋር አብሮ ሊታይ የሚገባ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሣ ማርያም መግደላዊት ቀርባ ልትነካው ባሰበች ጊዜ ገና ወደ አባቴ አላረጉምና አትንኪኝ ብሎ እንደነገራት በዮሐንስ ወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ የዚህ ዋና ትርጒሙ ጌታችን ሴት እንዳትነካው /ንቆ/ ሳይሆን ማርያም መግደላዊት የሚያርግ መስሏት ስለነበር ገና 40 ቀን እቈያለሁ ለማለት ነው፡፡

ወንጌላዊው ዮሐንስ በሌላ ምዕራፍ "አኀዛ እገሪሁ ወስገዳ ሎቱ" እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት ይላል፡፡ አሁንም በዚሁ ምዕራፍ 20 ቁጥር 24 "ከአሥራ ሁለት አንዱ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም ምልክት ከእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ማለቱን ያስረዳል፡፡ በእርግጥ ቶማስ ጌታ ከሙታን ተነሥቶ በዝግ ቤት ገብቶ ለደቀ መዛሙርቱ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ሲላቸው አልነበረም በዚህም ምክንያት ተጠራጥሮአል፡፡

ጌታ ደግሞ ለምን ተጠራጠርክ? ካልዳሰስኩህ አላምንም ብለሃል፡፡ በልና የተወጋው ጎኔን እይ፣ የተቸነከረው እጄን ተመልከት፡፡ ብሎ እንዲዳስሰው ፈቀደለት፡፡ ቶማስም ሲዳስስ እሳተ መለኮት ቀኝ እጁን አቃጠለው፡፡

"እግዚእየ ወአምላኪየ" ፈጣርየ አምላኪየ መዳሰሱ ሲያይ፡ እግዚእየ ማቃጠሉን ሲያይ አምላኪየ አለ፡፡ ይኸንን "እግዚእየ ወአምላኪየ" ያለውን ወስዶ በሃይማኖተ አበው "አንተ ቀዳማዊ ወአንተ ዳኀራዊ" አንተ መጀመሪያ አንተም መጨረሻ ነህ ብሎ ተርጒሞታል፡፡

ይህች ገቦ መለኮት የዳሰሰች እጅ ሳትሞት ሕያዊት ሆኖ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ትኖራለች፡፡ ጥር 21 ቀን የአስተርእዮ ዕለት በዓሉ ይከበራል፡፡ ይህ ታሪክ የሚገኘው መጽሐፈ እንድልስ በሚባለው ነው፡፡

ቅዱስ ያሬድም "ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሰይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ኅምዝ" ያለው ትሑታኑ ደቂቀ አዳም ልዑላኑ መላእክት ጌታ አስታረቃቸው ሁሉም ደስ አላቸው ማለቱ ነው ሰማያውያንና ምድራውያን በክርስቶስ አንድ ሆኖአልና፡፡ "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ" "ምድርም በክርስቶስ ደም ተቀድሳ የክርስቶስን ትንሣኤ ታከብራለች"፡፡

አንድም ያመኑ ምዕመናን ሁሉ በክርስቶስ ደም ነጻ ወጥተው በዓለ ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ መጽሐፍ ለግዕዛን ሰጥቶ መናገሩ የተለመደ ነው፡፡

"ትባርኮ ምድር ለእግዚአብሔር" "ምድር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች" ይህ ማኀበረ ምዕመናን እግዚአብሔር ያመሰግኑታል ማለት ነው፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር በመቈየት ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፣ ሞትን ድል ነስቶ ተነሥቶልናል፡፡

27.2፣ሠሉስ መዋዕለ ወሠሉሰ ለያልየ
የሚለው በሰዓት ሲቈጠር አይሞላም ይህ እንዴት ነው? ቢሉ እንግዲህ ጌታ በምሴተ ኀሙስ ሦስት ሰዓት አሳልፎ ነው መከራ መቀበል የጀመረ፡፡ ሥጋወደሙ ለሐዋርያት የሰጣቸው በዕለተ ኃሙስ ነው፡፡

ስለዚህ"መዓልት ይስሕቦ ለሌሊት፣ ወሌሊት ይስሕቦ ለመዓልት" ቀን ሌሊቱን ይስበዋል፣ ማለት መዓልተ ዓርብ ሌሊተ ኀሙስን መዓልተ እሑድ ደግሞ ሌሊተ እሑድን ሲስበው፣ ቅዳሜ መዓልትና ሌሊት ሲቀመር ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት የተባለው ይኸ ነው፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ