Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ”

በቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሃላፊ

በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ ከሁሉ አስቀድሜ የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና ጠብቆ ለ2003ዓ.ም የምሕረትና የቸርነት ዓመት የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትና በዐለ ጥምቀት እንድናከበር ስላደረሰን ለአምልኮቱ የሚገባው ምስጋና ክብርና ምስጋና ይግባው፣ በያላችሁት ሰላምና ጤና ፍቅርና አንድነት ይብዛላችሁ፡፡

  

ይህ የማነቃቂያና የማስጠንቀቂያ ቃል የተናገረው ብርሃኑ የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ብርሃነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን አምኖና ተከትሎ ባሳየው የወንጌል አገልግሎት ብቃት “የዓለም ብርሃን”መርሐ ዕውራን የዕውራን መሪ የሚል ቅጽል የተሰጠው ሐዋርያዊው ቅዱስ ጳውሎስ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በነበረው ጽኑ የኦሪት እምነት በአምላኩ እጅግ ቀናኢ ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን የተከናወነውን ምሥጢር ገና ሳይገባው እውነተኞች የክርስቶስ አማኞችንና ተከታዮችን ለማሳደድና ለማሰቃየት ሙሉ ፈቃድ ከባለሥልጣናት ተረክቦ ሲጓዝ የእምነቱን ጽናት ተመልክቶ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደማስቆ ሜዳ ላይ ከጠራው ሰዓት ጀምሮ ወደኋላ ሳይል የኦሪትን ሕግና ሥርዓት ጠንቅቀን እናውቃለን ከሚሉ የሥጋ ወገኖቹ እሥራኤላውያን “ቢጽ ሐሳውያን” ብዙ ፈተና የተቀበለ ስለ ቤተ ክርስቲያን “ምእመን” ዕለት ዕለት ይቆረቁሩና ይጨነቅ የነበረ. ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌላ የግሌ የሚለው ዓላማ ጥቅም ያልነበረው ወደር ያልተገኘለት ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡ የሐዋ. 2፡1 ፣ የሐዋ. 20፡31 ይህ ታላቅ ሐዋርያ ያለንበትን ዘመን መሠረት ያደረጉ በርካታ መልእክቶችን አስተላልፏል፡፡ የሐዋ. 20.28-31፣ ሮሜ. 1፡20-23 ፣2ኛ ጢሞ 3.1 - 8

ከእነዚህም መካከል “ቀኖቹ ክፍዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” ሲል በኤፌሶን መልእክት ያስተላለፈው ኃይለ ቃል አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ በዚህ ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዘመኑን የዋጀ ሥራን መሥራት ተገቢና አምላካዊ መመሪያ ስልሆነ በተለይ ያለንበት ዘመን ወይም በዘመኑ እየተከናወነ ያለው ሁሉ በርካታ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በመንፈስ ቅዱስ መነጸርነት አሻግረው ይመለከቱት የነበረ ዘመን እንደሆነ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡

እንዲሁም አስቀድሞ ነቢያትን የጠራና በነቢያት የተናገረው እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት በሚያስተምርበት ወቅት ስለዚህ ዘመን ምንነትና በዚህ ዘመን ስለሚከናወኑ ክንውኖች በሚገባ፤ አስተምሮአል ማቴ 23.3፡፡

ዘመናችን፡-እንደዘመኑ አጠራር የኢንፎርሜሽንና የቴክኖሎጂ ዘመን ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በዚህም ምክንያት ዓለማችን ወደ አንዲት መንደር ራስዋን እየቀየረች የምትገኝበት ወቅት መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

ዘመናችን፡- የዓለም አቀፋዊነት Globalization መዝሙር የሚዘመርባት ወይም የአንድ መንግሥት ምሥረታ one world government or new world order ነጋሪት የሚጐሰምበት ዘመን እየሆነች መጥታለች፡፡

ዘመናችን፡- በትንቢተ ዳንኤል ምዕ. 12፡4

ዳንኤል ሆይ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ መጽሐፉንም አትም ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ እውቀትም ይበዛል”እንዳለውና እንዲሁም "ዳንኤል ሆይ ቃሉ! እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያጡሩማል ይነጥሩማል ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፡፡ ክፉዎችም ሁሉ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ"እንደተባለው ዘመናችን የምርምር የፍልስፍና የምጥቀትና የርቀት ዘመን እንደሆነ ሁላችን የምንገነዘበው ሐቅ ነው የዘመናችን ሰውም ከምድር አልፎ በጨረቃና በፀሐይ ብሎም በሌሎች ፕላኔቶች ላይ ከፍተኛ ምርምር እያካሄደ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ከምድር በታችና በታላላቅ ውቅያኖሶች ውስጥ ከዚህም በታች ሰርጎ በመግባት ምርምሩን እያካሄደ የሚገኝበት ዘመን ላይ እንደሆነ ለሁላችን ግልጽ ነው፡፡ ይህ ዘመን ለነቢዩ ዳንኤል እንደተነገረው ጥበበኞች ዘመኑን በመዋጀት “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔን መፍራት ነው” ምሳሌ. 1፡7 የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ የጥበብ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በሰጠው ጥበብ ለሰው ልጅ ጠቀሜታ ያላቸውን ሥራዎች በጥበብ ሲያከናውኑ አምላክነቱንና ጥበቡን የዘነጉ ሰዎች ደግሞ በክፋ ጎዳና ተሰማርተው ጥበበኞች ሲመስላቸው የታወሩ በእጅጉ እየበረከቱ የሚገኙበት ዘመን እንደሆነ በሚገባ የምንገነዘብበትእውነት ነው፡፡ ሮሜ. 1፡22-25 በሌላ በኩል በነቢዩ ዳንኤል የተዘጋው የትንቢት ቃለ መጽሐፍ በዘመናችን እንደተከፈተና የተነገረው የዘመኑ ትንቢትም እየተከናወነ የሚገኝበት ዘመን እንደሆነ በግልጽ እንረዳለን፡፡ማቴ. 24፡3-15፣ 2ጴጥ. 2፣1-22፣ 1ዮሐ. 2፡18 ራእይ 5.1-6 ፣ 1-7፣ 9፣1-13፣ 13፣1-18

ዘመናችን በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ፊት ለሚነሣው የአንድ መንግሥት ሥርዓት መሠረትና የመላው ዓለም መሪ ሆኖ የሚነግሠውን መንግሥት ለመቀበል እየተዘጋጁ የሚገኙበት ሲሆን በበጉም ደም ልብሳቸውን ያጠቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እውነተኞች አማኞችም ሰማያዊ አክሊላቸውን ለመቀበል እየተዘጋጁ የሚገኙበት ዘመን እንደሆነ በሚገባ መረዳት አያዳግትም ራዕይ 7፡9-17፣ ራዕይ 13.1- በመሆኑም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው ዘመኑን ዋጁ እንዳለው ዘመኑን በሚገባ በመዋጀት የተሰጠንን አምላካዊ ኃላፊነትና አደራም ለመወጣት ከምን ጊዜም በበለጠ ዕለት ዕለት ቃሉን መሠረት አድርገን መንቀሳቀስ እንዳለብን አምላካዊ ቃል በሚገባ ያስተምረናል፡፡

በመሆኑም ዘመኑን ለመዋጀት ከሚያስችሉን መንገዶችም አንዱ ይህ የድኅረ ገጽ ስርጭት ስለሆነ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የዚህን ድኅረ ገጽ ሥርጭት ለመጀመር ተገዷል፡፡

ስለሆነም ቴክኖሎጂውን ወደ መንፈሳዊ ተልዕኮ በመቀየርና የመንፈሳዊ ተልዕኮ ማስፈጸም ማድረጉ አስፈላጊና ወቅታዊ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ስለሆነም ከእግዚአብሔር ሕገ መንግስት ሊለዩን ከሚችሉት ሁሉ ራሳችንን በማራቅና ለሕብረተሰቡ ጠንቅ የሆኑትን ለይተን በማውጣትም በየጊዜው ምክርና፣ ተግሳጽና የሃይማኖት ትምህርት በዚሁ መረብ ማስተላለፍ አስፈላጊና ወቅታዊ ተግባራችን መሆን አለበት፡፡ በተለይ የዘመኑና የችግሩ ተጋላጭ የሆነው ወጣቱን ትውልድ ለመታደግ ይህ ስርጭት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ማደራጃ መምሪያው በጽኑ ያምናል፡፡

ስለሆነም ማደራጃ መምሪያው ይህ ስርጭት ሲጀምር፡-

1. በመላው ዓለም የሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ ሁሉ ሃይማኖቱን፣ ሥርዓቱን፣ ባህሉንና ትውፊቱን በሚገባ ለማወቅ የሚያስችል እንደሆነ፣

2. ስለ ቤተርስቲያናችንና ስለሃይማኖታችን የተቀላጠፈና ትክክለኛ መረጃ ማግኘት እንደሚያስችል፣

3. ታሪኩን፣ ሥነ ጥበቡንና ኪነጥበቡን በሚገባ ለመረዳት እንደሚያስችለው፣

4. ከቤተክርስቲያኑ የሚፈልገውን ሁሉ ጠይቆ እውነተኛና ትክክለኛ መልስ ጠቃሚ እንደሚሆን፣

5. ስለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብዙ ዕውቀት የሌላቸው ወገኖች የተሟላ እውቀትና ግንዛቤ የሚያስችል፣

6. በኢትዮጵያ የሚገኙትን ጥንታውያን ገዳማት፣ የአብነት ት/ቤቶች፣ የታሪክ ቦታዎችና ልዩ ልዩ ቅርሶችን ወዘተ… የት እንዳሉና እንዴት እንዳሉ የሚረዳ፣ በውስጥና በውጭ ባሉት ጠላቶች በቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ላይ የሚሰነዘረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ እውነተኛ መልስ ለመስጠት እንደሚያስችል ማደራጃ መመሪያው በጽኑ ያምናል፡፡

ስለዚህ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያላችሁት ሁሉ የድኅረ ገጹ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ እየጋበዝን ሁላችሁም የቤተክርስቲያኒቱ ምሁራን ሊቃውንት እውቀታችሁን በመጠቀም ለሕብረተሰቡ በጽሑፍም ሆነ በኦድዮ /በድምጽ/ጠቃሚ ነው የምትሉትን ትምህርትና ምክር እንድታስተላልፉ ጥሪያችንን እያቀረብን ሥርጭቱ በጥራትና በስፋት እንዲሠራጭ መሆን አለበት የምትሉትን ሓሳብም እንድትለግሱንና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ