Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የእግዚአብሔር ፈቃድ አንዱ ስንኳ እንዳይጠፋ ነው፡፡

በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ
የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ ስትመሠረት ሰማያዊና ዘለዓለማዊ የሆነ መንፈሳዊ ተልዕኮ አላት፣ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረውን የሰው ልጅ በሁለመናው የተሻለ ሕይወት እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን ለክብር እንጂ ለኃሣር አልፈጠረምና ሰዎች በሥጋና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የተሟላ ስብእናና ጥበቃ እንዲኖራቸው፣ በዚህ ዓለም ሲኖሩም እርስ በርስ ተስማምተው፣ ተዋደውና ተረዳድተው በሰላም፣ በፍቅርና በስምምነት እንዲኖሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች ለሥጋዊ ሕይወታቸው የሚጠቅማቸውን ከመፈጸም ባሻገር ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው የሚበጀውን ሁሉ እንዲከተሉ የእግዚአብሔር ቀዋሚና ዘላቂ ፈቃዱ ነው፡፡

 

የእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ወንጌል እንደተገለጸው አንድ ሰውስ ስንኳ እንዳይጠፉ ማድረግ ነው፡፡ ከክርስቶስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዘመናችን ያሉ የሃይማኖት መምህራንና መሪዎች ይህን የእግዚአብሔር ፈቃድ

በመፈጸም ሰውን ለማዳን ብዙ ደክመዋል፤ በድካማቸውም ቤተክርስቲያንን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረች ከዘመናችን ደርሳለች፡፡የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጸምበት የቅዱስ ወንጌል ትምህርት የቀደሙት መምህራን ከሀገር ሀገር እየተዘዋወሩ በረኃብ፣ በድካም፣ በከፍተኛ እንግልትና እስከሞት ድረስ መሥዋዕት በመሆን መተኪያ የማይገኝለትን አገልግሎት ለቤተክርስቲያን አበርክተዋል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰውና ዛሬ ዓለም በቴክኖሎጂ ጥበብ ወደ አንድ መንደር የተጠቃለለችበት ሁኔታ በመፈጠሩ የአሁኑ ትውልድ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማትም ሆነ ለማሰማት እንደቀድሞ ዘመን ችግር የሚያጋጥመው አይደለም፡፡

ዘመናችን ቅዱሳት መጻሕፍትን በየቋንቋው ተተርጉመው በብዛት ለዓለም የተሰራጩበት ዘመን ነው፡፡ ከዚህም ጋር በልዩ ልዩ ሚድያ የእግዚአብሔርን ቃል ለዓለም ማሠራጨት የሚቻልበት ዘመን ነው፡፡

በተለይም ዘመኑ ባፈራው የድኅረ ገጽ መሣሪያ ተጠቅሞ የእግዚአብሔርን ቃል ለሁሉም ማዳረስ የጊዜያችን ልዩ ጸጋ ሆኖ ይገኛል፡፡

መቼም ቢሆን የእግዚአብሔር ቃል ሁሉንም ያሸንፋል እንጂ እርሱ በምንም በምን አይሸነፍምና ‹ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል›(ማቴ.24፡14)በማለት የተናገረው ቃሉ አሸናፊ ሆኖ ይወጣ ዘንድ ለሥጋዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ተግባም ጭምር ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጠው የድኅረ ገጽ መሣርያ እርሱ ራሱ በፈቀደላቸው ፍጡራን አማካይነት ጥቅም ላይ እንዲውል አድርጐአል፡፡

ቤተክርስቲያን እነዚህ መሣሪያዎች ለቃሉ ማሰራጫ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገኙ መሆናቸውን ተገንዝባ በአግባቡ በመጠቀም ቅዱስ ወንጌልን ለሁሉም ለማዳረስ መንቀሳቀስ አለባት፡፡

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማከናወን የሚያስችለው የድኅረ ገጽ መሣርያ ጥቅም ላይ ለማዋል ያደረገው ጥረት ሊበረታታ የሚገባው ነው፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ይህን የመሰለ ዕድል ለወጣቶች ሲያመቻች ወጣቶችም በዕድሉ ተጠቅመው በአግባቡ ሊገለገሉበት፣ ሊጽፉበት ሊማማሩበትና ሃይማኖታዊ አገልግሎታቸውን ለማስፋት ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

ሊቃውንትና መምህራንም ይህን መሣሪያ ተጠቅመው ለወጣቱ ትውልድና በአጠቃላይ ለህዝበ ክርስቲያኑ የቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፤ ሥርዓትና ትውፊት በአግባቡ በጥራት ሊያስተላልፍ ይገባል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሁሉም በየፊናው ኃላፊነቱን ለመወጣት የተባበረ እንደሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጠበቅብንን ለመፈጸም እንችላለን፡፡

 

መልካም የሥራ ዘመን

ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ

የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ